Get Mystery Box with random crypto!

#በተደጋጋሚ #በሆድ #ጥገኛ #ትላትል #እጠቃለሁ #ምን #ይሻላል? #በቅን | Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809

#በተደጋጋሚ #በሆድ #ጥገኛ #ትላትል #እጠቃለሁ #ምን #ይሻላል?

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
#የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የእድሜ ክልል የሚከሰቱ ሲሆኑ በዋናነት ክብ እና ጠፍጣፋ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነት የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫ እና በአፍ በኩል በእንቁላል መልኩ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ ይራባሉ፡፡
#ለሆድ #ጥገኛ #ትላትል #መንስኤዎች
በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ
የተበከለ ዉሃ
በደንብ ያልበሰለ ምግብ መመገብ
በባዶ እግር መሄድ
የግል ንፅህና አለመጠበቅ
የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ
በጥገኛ ትላትሎች ከተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር
#ምልክቶች
የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
የምግብ ፍላጎት መቀነስ/መጨመር
ማቅለሽለሽና ማስመለስ
የሆድ ህመም/ቁርጠት
በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት
የሆድ መነፋት እና ጋዝ መብዛት
በፊንጢጣ ወይም ብልት ዙሪያ ማሳከክ
#የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎችን #መከላከል #መንገዶች
ፍራፍሬዎች ከመመገብ በፊት በደንብ ማጠብ
ከመመገብ በፊት ምግብን በደንብ ማብሰል
ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የተጣራ ዉሃ መጠቀም
ንፅህና መጠበቅ
ከመመገብ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ በኋላ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡
በባዶ እግር አለመሔድ እና ንጽህናዉ በተጠበቀ/በታከመ ገንዳ ዉስጥ መዋኘት
#ህክምና
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መኖራቸዉ በሰገራ ምርመራ ከተረጋጋጠ በኋላ ለተገኘዉ የትላትል አይነት መድሐኒት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በአግባቡ ካልታከመ እና አመጋገብ ካላስተካከልን ከፍተኛ የአንጀት ጉዳት ያስከትላል፡፡