2022-06-15 18:09:55
ተከታታይ ፅሁፍ||ክፍል ⓶
አርዕስት፦ ሰለፊያ
الســلام ؏ـليڪم ورحمــۃاللـہ وبرڪاتـہ
||
ሰለፊያ መባል ለምን አስፈለገ
ይህ ጥያቄ በረካታ አላዋቂው ማህበረሰባችን ውስጥ ያለ ነው ፤ አንዳንዶች ደግሞ የራሳቸውን አላማ ለማስኬድ "እኛ አንድ ነን...#ሙስሊሞች" ነን ይላሉ ። በዚህ የተነሳ እኛ ሰለፊያ፣ ሱኒ ፣ ኢኽዋን፣የመሳሰሉት እያላችሁ አትለያዩን የሚልም አይጠፋም።
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ሙስሊም ብቻ ነን ብለን ካሰብን ፤ ይህም ማለት ቀጥተኛው መንገድ ላይ ነን ማለታችን አደል?! እንደዚህ ለመረዳት ምንን ተመርኩዘን ነው..?
ቁርዓን እና ሀዲስ በዚህ ረገድ ምን ይላል የሚለውን በጥቂቱ እንመልከት፦
{ وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ }
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
አል አንዓም ፡[153]
የአላህ ባሪያዎች ሆይ !
ይህ የቁርዓን አንቀፅ የቀጥተኛው መንገድ አንድ ብቻ እንደሆነ እና ሌሎቹ የጥመት(የተሳሳተ) መንገድ እንደሆነ ያስረዳናል።
ከሐዲስ
~~~
ዓብደላ ብን መስዑድ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፦
“የአላህ መልእክተኛ አንድ መስመር አሰመሩ ከዚያም “ይህ የአላህ መንገድ ነው” በማለት ተናገሩ፡፡ ከዚያም በቀኝና በግራ በኩል መስመሮችን አሰመሩ፡፡ “እነዚህ መንገዶች ናቸው በእያንዳንዱ መንገድ ላይ ወደርሱ የሚጣራ ሰይጣን አለ፡፡” በማለት ተናገሩ፡፡ ከዚያም ከላይ ያሳለፍነውን የቁርዓን አንቀጽ አነበቡ።
||
መልዕክተኛው ሰለዋቱረቢ ወሰላሙ ዓለይሂ ለመጠቆም የፈለጉት ከትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ ያፈነገጡ አንጃዎች መኖራቸውንና ትክክለኛው አስተምህሮን እንድንይዝ አስጠንቅቀውናል።
ከቁርዓን ከሐዲስ እንደ ቅምሻ ካየን ፤ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ ሙስሊም ነን ብለን ካሰብን ከየትኛው ነን..?
የዓሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ ብቸኛ ወዳጆችና ደጋፊ ፤ እንዲሁም የሙስሊሞች ብቸኛ ኢማም እርሱ እና ልጆቹ እንጂ ሌሎቹ ኢማም ሊሆኑ እንደማይችሉ የሚሰብኩ ሺዓህ ሙስሊም ነኝ ከሚሉት ነህ?
ሙታንን፣ደጋግ ሷሊሆችን፣ድረሱልኝ እያለ እንዲሁም መቃብርን የሚዞር ከሆኑ የሱፊ ሙስሊም ነኝ ባዬች ነህ?
የአላህን ስምና ባህሪያት በልቅናው በሚገባው መልኩ የሚፀድቀውን እናመሳስላለን በማለት የሚያራቁቱ ፤ የአላህን ከአርሽ በላይ መሆኑን የሚያረጋግጥን የሚያከፍሩ አህባሽ የተሰኙት ጋር ሙስሊም ነኝ ትላለህ?
በዲን ስም ከሚነግዱ ለስልጣን እና ለገንዘብ ሲሉ ዲኑን ትተው ከፊል ለከፊሉ በተስማማንበት ተስማምተን በተለያየንበት ዑዝር እየተሰጣጠን እንሂድ የሚል መርህ ይዘው ከሚጓዙት አል ኢኽዋን አልሙስሊሙን (አልሙፍሊሲን,አልሙፍሲዲን) ከተሰኙት ሙስሊም ነኝ ባዬች ነህ?
ሸሪዓ ያልደነገገውን ለዳዕዋ ጥሪ ግዜ እየገደቡ ያለምንም እውቀት ፤ ለማህበረሰቡ ጠቃሚ ይዘትን ያልያዘ ፤ በየሀገሩ እየተነሱ ከሚዞሩት ጀማዓተል ተብሊግ ነህ..?
ውድ የቻናላችን ተከታታዬች
እስኪ ይህ ሁሉ አንጃ/ቡድን/ እያለ ሙስሊም ነኝ ማለቱ የሚያስኬድ ነው..?
▼ለዚህም ነው ሰለፊያ/አህሉሱና ወልጀማዓ/ መባል ያስፈለገው!
በርግጥ አዎን ሙስሊም ነን! ነገር ግን በቁርዓን በሀዲስ በደጋግ አበው ቀደምቶች አረዳድ የምንረዳ ከሆንን ነው።
~~
ይህን ካልን ሰለፊያ/አህሉሱና ወልጀማዓ/ መባሉን ልንጠላ አይገባም..!
~
ኢንሻአላህ ....▷ይቀጥላል
Abu Fadyaa
ሀሳብ አስተያየት መስጫ ግሩፕ
https://t.me/Al_Qelb_Selim_Group
================
ጤናማ ልብ||የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Al_Qelb_Selim
958 viewsⒶbu Fewzan iftah, 15:09