Get Mystery Box with random crypto!

ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ

የቴሌግራም ቻናል አርማ counselinga — ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ
የቴሌግራም ቻናል አርማ counselinga — ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ
የሰርጥ አድራሻ: @counselinga
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.26K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ የስነ ልቦና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው የሚቀርቡበት ልዩ ቻናል፡፡

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-13 22:06:49 ባል ሚስቱን ከሌላ ሴት ጋር ማነፃፀር የጀመረ እለት ትዳሩ መሞት ይጀምራል!

በትዳር ውስጥ ወሲባዊ እርካታ እንዲቀንስ ያደርጋል:: ምክንያቱም porn video ላይ ያየነውን ነገር ቤታችን ማግኘት አንችልም:: ለምሳሌ ባል porn አይቶ ከሆነ ወደ ሚስቱ ሚመጣው እዛ porn video ላይ ያያትን ሴት እና ድርጊት በአይምሮው ይዞ ወደ ሚስቱ ይመጣና ሚስቱን እንደዛ እንድትሆን ይጠብቃል:: porn video ላይ ያያትን ሴት ከሚስቱ ጋር ማነፃፀር ይጀምራል:: ባል ሚስቱን ከሌላ ሰው ጋር ማነፃፀር የጀመረ እለት ትዳሩ መሞት ይጀምራል:: ወሲባዊ እርካታ በትዳር ውስጥ ባል እና ሚስት እርስ በእርስ እየተጠናኑ በግዜ ሂደት የሚመጣ እንጂ ከሌላ ቦታ የምንማረው ነገር አይደለም::

ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት porn ሚያዩ ሰዎች በጭንቀት (depression) ይጠቃሉ:: ደስታን እና እውነተኛ እርካታን በማጣት ይሰቃያሉ:: ይሄም በትዳር ውስጥ ሰላም እንዳይኖር ያደርጋል::

Porn በማየት ስሜትን ማርካት ከማመንዘር የሚተናነስ ተግባር አደለም:: የማቴዎስ ወንጌል 5
28፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።

https://telegram.me/counselingA
697 viewsÃsh€ Ġ, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 21:24:42 ትኩረትህን አታባክን!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
አውቀን ቆመናል ወይስ መራመድ እንዳለብን ረስተናል? አቅጣጫ እየፈለግን ወይስ የእርምጃችን ትርጉም ጠፍቶን? መወሰን ከብዶን ወይስ ውሳኔያችን ትርጉም አቶ? የመሃል ሰፋሪነታችን ሚስጥር፣ የማወላወላችን ምክንያት ምን ይሆን?
አዎ! መሃል ሰፋሪነት ሁለት ያሳጣል፤ ግራመጋባት መዳረሻን ያዛባል፤ ለውሳኔ መዘግየት ዋጋ ያስከፍላል። ከማንም አንሰህ ወደኋላ እንዳልቀረህ አስታውስ። ግዴለሽነትህ ግን ዋጋ አስከፍሎሃል፤ የዘገየው ውሳኔህ ኋላ አስቀርቶሃል፤ ያልጠራው መንገድህ እርምጃህን አቀጥቅዞታል፤ ተስፋህን ገድሎታል፤ አቅምህን አሳንሶታል።

አዎ! መጓዝ ካለብህ በጠራው ብረሃናማ መንገድ ተጓዝ፤ ማወቅ፣ መማር ካለብህ በጥልቀት እወቅ፤ መረዳት ከፈለክ በትኩረት አዳምጥ፣ ተከታተል። የከላይ ከላይ ሰራ፣ የይስሙላ ተግባር ይቅርብህ። ማንም ቢያየህ ከማውራት ውጪ ምንም አያደርግም አንተ ግን በጥንቃቄ በማድረግህ ህይወትህ ላይ የሆነ ነገር ትቀይራለህ፤ አንዳች የምታሻሽለው ነገር ይኖራል። ትኩረትህን አታባክን፤ በጥልቅ ሃሳብህ፣ በገዢው አመለካከትህ አትቀልድ። ባልተገራ ሃሳብ፣ ባልተቃኘ መንገድ፣ ባልተጠነ አኳሃን መጓዝህ ዋጋ ሊያስከፍልህ እንደሚችል አስተውል።

አዎ! ትኩረትም እንዲሁ ልማድ ይፈልጋል። በአንድ ጊዜ አንድ ጉዳይ ላይ ማተኮር አለመቻልህ የትኩረት ክፍተትህን ያሳያል። አዕምሮህ ያስለመድከውን ያደርጋል። በተመሳሳይ ሰዓት ብዙ ነገር መስራት ከለመደ አንድ ነገር ለመስራት ብትሞክርም ላይታዘዝልህ ይችላልና በአንዴ አንድ ነገርን ብቻ መስራት ላይ አተኩር። ጥሩ ውጤት ከፈለክ ሁሉን አትነካካ እጅህ ላይ ያለውን አድምተህ ስራ፣ የወደድከውን ነጥለህ በሙላት ፈፅመው፤ በየትኛውም መንገድ አመርኪውን ውጤት ታገኘዋለህ።

https://telegram.me/counselingA
834 viewsÃsh€ Ġ, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 13:40:50 ስለ ኤም ኤስ መልቲፕል ስኮለረሲስ የጤና ችግር መንስኤና መፍትሄ ለማወቅ ይህንን የ YouTube ቻናል subscribe በማድረግ ይመልከቱ። እጅግ ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ።
https://youtube.com/channel/UCT4Q0W2JlZBbh75P2Dfa4GA
738 viewsÃsh€ Ġ, 10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 10:20:41 ምን ያህል አትችልም የሚሉ ቃላትን ተሸክመሀል ?

ይቅርብህ ፣ አይሆንም ፣ አትችለውም ፣ አይሳካልህም ፣ አትመጥኚም፣ አይገባሸም ፣ ላንቺ አይሆንም የሚሉ ቃላቶች ምን ያህል ከመንገድሽ መድረስ ከተመኘሽበት አሽሽተውሻል? ዛሬ አለም ያደነቃቸው ጀግንነታቸው ያስደነገጠን ምን አይነት ጥበብ ነው ብለን የተደመምንባቸው ሰዎች ልክ ሲጀምሩ ሁሉም ተቃውሟቸው እንደነበርስ ምን ያህል ሰምተናል?

ስኬት ማደግ አዲስ መንገድ መሞከር ለብዙዎች እብደት ነው ስለዚህ የማይሆን ነገር እንደሆነ ይነግሩናል ሆነው ስላላዩት ማሳካት ስላልቻሉ ሌላው እንዲያሳካው አይፈቅዱም ! ምክንያቱም ማንም ሰው መበለጥ አይፈልግም ስለዚህ እንዳትበልጣቸው እንደተሸነፍክ ይነግሩሀል ፣ እንዳታሸንፋቸው የተሸነፍክ እንደሆንክ አድርገው ከመንገድህ ያቆሙሃል ።

ወገኔ ብልጥ ሁን እንጂ ንቃ ራስህን እየው ካንተ በላይ አንተን የሚያውቅህ ማነው? ካንተ በላይ ችሎታህን ሊነግርህ የሚችለው ማነው? ለምን ራስህን ማንነትህን አቅምህን አሳልፈህ ትሰጣለህ? ትችላለህ ትችያለሽ!

https://telegram.me/counselingA
791 viewsÃsh€ Ġ, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 07:54:40 ...አቅጣጫ ጠቋሚ ነው!
፨፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨፨
ተሳሳት ግን አትፀፀትበት፤ ተማርበት። ፀፀት ሽክሙ ከባድ ነው፤ ትምህርት ሁነኛው የስህተት ስጦታህ ነው። ለመሳሳት ያለህ ድፍረት ወሳኝና ህይወትህን የሚቀይር እርምጃ ነው፤ ደረጃህንና አቅምህን ልታውቅ የምትችለው ስትሳሳት ነው። ነገር ግን ስህተትህ ለመማር እንጂ ለመፀፀት አይደለም፤ ለማደግ እንጂ ወድቆ ለመቅረት አይደለም፤ ለመለወጥ እንጂ በእራስ ለማዘን፣ ለመከፋት አይደለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ስለተማርክ እውቀትህን ትለካለህ፤ አለማወቅህን ትረዳለህ። ስለወደክ የውድቀት ስሜት ይገባሃል፤ በስህተት ውስጥ ልትደግመው የማትችለው አዲስ የስህተት መንገድ ታውቅበታለህ፣ ሌላ የማይሳካበትን፣ ነገሮች እንዳሰብከው የማይመቻቹበትን መንገድ ትረዳለህ። ስትሔድ እንቅፋት ቢመታህ፣ ስትመለስ ግን እራሱ እንቅፋት ድጋሜ እንዳይመታህ አብዝተህ ትጠነቀቃለህ። አንዴ ብትሳሳት፣ በማይሆን አኳሃን ብትገኝ ዳግም ጥረትህ ከዛ ስህተት ለመታረምና የመንገድህን አቅጣጫ መለመቀየር ነው።

አዎ! ስህተት አቅጣጫ ጠቋሚ ነው፤ ውድቀት ሌላ ታዓምራዊ አቅምን መፈተሻ አቅም ነው። ስለተሳሳትክ ሌላ የተሻለ አማራጭ ትፈልጋለህ፤ ስለወደክ ዳግም እራስህን አጠንክረህ ትነሳለህ፤ ትመለሳለህ። ስህተት የአለም ፍፃሜ፣ ውድቀትህም ያንተ መጨረሻ አይደለም።
ስህተቶችን ብቻ መቁጠር፣ ማጉላት፣ ማግዘፍ አቁም፤ አንዴ ብትሳሳት አምስት ትክክለኛ ነገር አድርገሃልና በእነርሱም መኩራትህን እንዳትረሳ። በሂደትም ብዙ የተሻሉ ተግባራትን ትፈፅማለህ። ውድቀትህ ስሜትህን እንዲጎዳ፣ አቅምህን እንዲያልፈሰፍስ፣ ለስንፍና እንዲያጋልጥህ አትፍቀድ።
ተሳሳት አትፀፀት፤ ውደቅ፤ በርትተህ ድጋሜ ተነስ።
https://telegram.me/counselingA
757 viewsÃsh€ Ġ, 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:14:28 ከንቃትህ በላይ ነህ!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
ሁሌም ንቁ ባትሆን እንኳ ምግባር ያለህ /disciplined/ መሆን እንዳለብህ እንዳትረሳ። ምትነሳው በእርሱ ነው፤ ቀና የማለትህ ሚስጥር የማይቋረጥ ጥረትህ እንዲሁም በምግባር የዳበረው ልማድና ተጋድሎህ ነው። ጥሩ ስሜት ላይ ላትሆን ትችላለህ፣ ላይመችህ ይችላል፣ ሌሎች ጊዜያዊ ደስታን የሚሰጡ ነገሮች ከፊትህ ይኖሩ ይሆናል፣ ተነሳሽነት ጎድሎህ ለእራስህ ሃይል አጥሮህም ይሆናል፤ ነገር ግን ግዴታ ዛሬም እንደ ትናንቱ፣ እንደቀድሞው ልታደርገው የሚገባ፣ ባንተ የሚከወን ብርቱ ነገር አለ። ከንቃትህ በላይ ቆራጥነትህን፣ ታታሪነትህን የሚጠይቅ የቤት ስራ አለብህ፣ ያልጨረስከው ጉዳይ፣ እለት እለት የምትኖረው የእራስህ ህልም አለ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከንቃትህ በላይ ነህ! የማትተኛው በንቃትህ ምክንያት ሳይሆን በማያስተኛው ትልቁ ህልምህ ምክንያት ነው፤ የማታንቀላፋው በተነሳሽነትህ ልክ ሳይሆን በራዕይህ ግዝፈትና ልህቀት ነው፤ ለአፍታም የማትዘናጋው ከመንፈስህ ጋር የተሳሰረ ትልቅ ሃሳብ ስላለህ ነው። ተነሳሽነትህ በሌለ ሰዓት የሚቆም አላማ የለህም፤ ባልነቃህ ጊዜ የሚገታ ህልም የለህም፤ ስሜትህ በተዛባ ወቅት የምታሸጋግረው እቅድ የለህም። ለእራስህ የገባሀውን ቃል አስታውስ፤ ደጋግመህ የምታስበውን የኑሮ ደረጃ ተመልከት። ደስ ባለህና በተመቸህ ሰዓት ብቻ እነሰራህ የምታሳካው አይደለም፤ ፍላጎት ባለህ ጊዜ ብቻ እየሰራህ የሚኖርህ አይነት ህይወት አይደለም።

አዎ! ላሰብከው ህይወት እውንነት መቾትህን መሰዋት፣ ስሜትህን መገደብ አለብህ። ከንቃት በላይ በምግባር ተገዛ። Stay disciplined. ቆራጥና የምግባር ሰው ለመሆን ቅርፅ አታብዛ፤ መስፈርት አትደርድር። አንዴ እስከወሰንክ ድረስ ወደኋላ የምትልበት፣ ግፊት የምትፈልግበት ምክንያት የለህም። ግፊትህ የህልምህ ትልቅነት ነው፤ ብርታትህ ከመንፈስህ የተሳሰረው ውጤታማው ልማድህ ነው። በምንም ሁኔታ ወስጥ ብትሆን ከተነሳኝነተህ በላይ እንደሆንክ አስታውስ፤ ቢበርድህም ቢሞቅህም እኩል መታገልህን ትቀጥላለህ፤ ምቾትና አለመመቸት ጥረትህ ላይ ለውጥ እንደማያመጡም ታስመሰክራለህ።
https://telegram.me/counselingA
675 viewsÃsh€ Ġ, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 20:13:50 #ፕላሴቦ_ኢፌክት_በኮሜዲያን_ክበበው ገዳ

ኮሜዲያን ክበበው ገዳ በአለቤ ሾው ላይ አንድ ገጠመኙን ተናግሯል። "አባቱ ይታመሙና ከየካ ሚካኤል ፀበል እንዲያመጣ ጀሪካን አስይዘው፤ የባስ ገንዘብ ሰጥተው ይልኩታል። ክበበው ጀሪካኑን ይዞ ጉዞ እንደጀመረ ኳስ የሚጫወቱ ልጆች ያይና ለትራንስፖርት የተሰጠውን ገንዘብ እያስያዘ ተጫወተ። ቀስበቀስ ሁሉንም ሳንቲም ተበለና ባዶ እጁን ቀረ። ወደ ቤት ምንም ሳይዝ ሊመለስ ሆነ። ግራ ቢገባው ከአጂፕ ነዳጅ ማደያ ውሀ ቀድቶ ወደ ቤት ይመለሳል። ፀበሉን በራፍ ላይ እንዲያስቀምጥ ነግረውት ለምን እንደቆየ ሲጠይቁት ባሱ ውስጥ ሌባ ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ እንደሄዱ ይነግራቸዋል።

በነጋታው ጠዋት አባቱ ወደ ጓሮ ሄደው ከጀሪካኑ በኩባያ እየቀዱ ጠጡ። ከሰአት በኋላ ከበሽታቸው ተሻለኝ አሉ።" ብሏል።

በብዙ ጥናቶች ሰዎች 'ያድነኛል' ብለው አምነው መድሀኒት ሲወስዱ የተሻለ እንደሚያድናቸው ታይቷል። መድሀኒትነት የሌላቸው ኪኒኖች እንኳ አምነው ከወሰዱ እንደህመሙ አይነት ከ15 እስከ 75 ከመቶ ለውጥ እንደሚያሳዩ በተደጋጋሚ ታይቷል።

ብዙ ዐ.ነገሮች የሚካሄዱት አእምሮ ውስጥ ነው።
https://telegram.me/counselingA
607 viewsÃsh€ Ġ, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 17:02:01 አስተማሪ ጥቅሶች
1."ገንዘብ የማይገዛው ነገር እስከሌለህ ድረስ ባለፀጋ አይደለህም።"

2."የሰው ልጅ ነፃ ነኝ ብሎ የሚያምን የልማድ ባሪያ ነው።"

3."ጉድለትህን ወደ ፍፁምነት የሚቀይረው ፤ ፈጣሪህ እንጂ ሀይማኖትህ አይደለም።"

4."የመገለጥን ብርሃን ትጨብጥ ዘንድ የሥጋን ጨለማ አሸንፍ።"

5.እያንዳንዱ ሰው ልክ እንደጨረቃ ነው፡፡ ለማንም የማያሳየው ግማሽ ጎን አለው ።

6."በፍቅር የተሰራ ኃጢያት፤ ፍቅር ከሌለበት አምልኮ ይበልጣል።"

7."ፈላስፋ በሕይወት ጨዋታ ላይ የተገኘ ተመልካች ነው።"

8."የእኔ ፍላጎት የፈጣሪን ሀሳብ ማወቅ ነው ፤ ሌላው ሁሉ ዝርዝር ጉዳይ ነወ።"

9."የምትኖረባትን ሕይወት በቅጡ ሳታውቅ ስትሞት ሌላ ዓለም መኖሩን እንዴት ታውቃለህ።"

10."ታላላቅ እምነቶች ሁሉ መነሻቸው መናፍቅነት ነው።"

11."ያልተመረመረ ህይወት ሊኖሩት የማይገባ ነው። "

12."የእግዚአብሔር ፍቃድና እውቀት በእኛ አላዋቂነት ሊፈተን አይችልም።"

13."ለማመን እንጂ ላለማመን ምክንያት አያስፈልግም።"

14."የሞት ፍርሃት የሕይወት ማጣፈጫ ቅመም ነው።"

15."መልካምነት የተደረገልህን ሳይሆን ያልተደረገልህን የመክፈል ብቃት ነው።"

16."ከፍቅር ሁሉ የሚበልጠው ምላሽ ሳያገኙ ማፍቀር መቻል ነው።"

17."የሰው ልጅ ሐሳብ እንጂ እውነት አትለዋወጥም።"

18."የሰው የነፍስ አርነት በሥጋ ባርነት የሚገኝ ልምምድ ነው።"

19."እኔ የሚል አእምሮ በጨለማ እንዳልተለኮሰ ሻማ ነው።"

20."አዕምሮ እንደፈሳሽ ወንዝ ነው ፤ መገደብ ባትችልም አዲስ መንገድ አብጅለት።"

ምንጭ- ጥበብ ከጲላጦስ
https://telegram.me/counselingA
630 viewsÃsh€ Ġ, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 14:41:41 የማይቆም ነው!
፨፨፨///////፨፨፨
የማያቆም የእውቀት ጥማት፣ የማያቆም ጥረት፣ የማያባራ ተጋድሎ፣ የማይሸበር ድፍረት፣ የማይረበሽ ፅናት፣ የሚሳሳት የሚታረም፣ የሚወድቅ የሚነሳ ማንነት ሁሌም በመንፈስ የጠነከረ በአካል የጎለበት ማንነት ነው። ትናንት ከትናንት ወዲያ ያወከው፣ የተረዳሀውና የገባህ ነገር መቼ እንደሚጠቅምህ አታውቅም፤ እስከ ዛሬ የተማመንክበት፣ ተስፋም ያደረከው አምላክህ የት እንደሚያደርስህ አታውቅም፤ ባለፈው ጊዜያት የጣርከው ጥረት፣ የለፋሀው ልፋት መቼ እንደሚከፍልህ አታውቅም። ጥረትህ ግን አያቆምም፣ ትግለህ አይገታም፣ ጉልበትህ ሸብረክ አይልም። በአዕምሮህ ትልቅ ነገር ይመላለሳል፤ በፅናትህ ልክ የምትደርስበት፣ በድፍረትህ መጠን የምትጋፈጠው፣ ታግለህለት፣ ወድቀህለት የምታሸንፈው፤ ተፈትነህ የምታልፍለት ድንቅ ሃሳብ አለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! የማይቆም ነው! ለእውቀት ያለህ ፍላጎት፣ ለማወቅ የምታደርገው ጥረት የማይቆም ነው። ብዙ ባወክ ልክ ብዙ እንደምታድግ ገብቶሃል። የማትደራደርበት ፅኑ አቋም አለህ፤ ተስፋ ያለመቁረጥ፣ ያለማቆም ብርቱ አቋም። በሁለቱ ማንነት በስንፍናና በብርታቱ መሃከል ብትዋጥም ቀደሚው ምርጫህ ብርቱው፣ ጥንካሬው፣ ተስፈኛው፣ አላሚው፣ ሞካሪው፣ አድራጊው ነው። ፍላጎትህ እስካልቆመ ጥረትህ የሚቆምበት ምክንያት የለም። ግበዓት /resource / ቢያልቅም፣ የሰው ልጅ ፈጣሪነት /creativity / እንዳያልቅ ተደርጎ፣ መጨረሻ ሳይበጅለት ተሰቶናልና አውጥትህ ተጠቀመው።

አዎ! ክፍያውን አትወቅ፤ ድርሻህ አይታወቅ ጥረትህ ግን አያቆምም። እውነታውን ትቀበላለህ፤ የዛሬ ትግልህ ዛሬ አይከፍልህም፤ የዛሬ ልፋትህ ዛሬ አያሳርፍህም፤ የዛሬው ተጋድሎህ ውጤት ግዜያትን ይወስዳል። በልዩነት ማሰብ ትጀምራለህ፤ እንደ አብዛኛው ሰው በፈጣን ተግባር ፈጣን ውጤት ጠባቂ አይደለህም። ሂደቱ ይማርክሃል፤ በጥበቃ ውስጥ ታድጋለህ፤ በሰነከው ተስፋ በተማመንከው አምላክ፣ በታመንከው በእራስህ፣ ትልቅ ያልከው ቦታ ትደርሳለህ። ፍላጎትህ ጥራት ነው፤ ተግባርህ በየጊዜው እየተሻሻለ፣ እያደገ የሚሔድ ነው። በማያቋርጥ ጥረት አትደራደር፤ ለአፍታም ትግልህን እንዳታቆም፤ ለደቂቃ ከአቋምህ እንዳትመለስ፤ በጀመርከው መንገድ ህልምህን መኖር፣ ለአለማህ መታገልህን ቀጥል።
https://telegram.me/counselingA
644 viewsÃsh€ Ġ, 11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ