Get Mystery Box with random crypto!

#ፕላሴቦ_ኢፌክት_በኮሜዲያን_ክበበው ገዳ ኮሜዲያን ክበበው ገዳ በአለቤ ሾው ላይ አንድ ገጠመኙን | ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ

#ፕላሴቦ_ኢፌክት_በኮሜዲያን_ክበበው ገዳ

ኮሜዲያን ክበበው ገዳ በአለቤ ሾው ላይ አንድ ገጠመኙን ተናግሯል። "አባቱ ይታመሙና ከየካ ሚካኤል ፀበል እንዲያመጣ ጀሪካን አስይዘው፤ የባስ ገንዘብ ሰጥተው ይልኩታል። ክበበው ጀሪካኑን ይዞ ጉዞ እንደጀመረ ኳስ የሚጫወቱ ልጆች ያይና ለትራንስፖርት የተሰጠውን ገንዘብ እያስያዘ ተጫወተ። ቀስበቀስ ሁሉንም ሳንቲም ተበለና ባዶ እጁን ቀረ። ወደ ቤት ምንም ሳይዝ ሊመለስ ሆነ። ግራ ቢገባው ከአጂፕ ነዳጅ ማደያ ውሀ ቀድቶ ወደ ቤት ይመለሳል። ፀበሉን በራፍ ላይ እንዲያስቀምጥ ነግረውት ለምን እንደቆየ ሲጠይቁት ባሱ ውስጥ ሌባ ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ እንደሄዱ ይነግራቸዋል።

በነጋታው ጠዋት አባቱ ወደ ጓሮ ሄደው ከጀሪካኑ በኩባያ እየቀዱ ጠጡ። ከሰአት በኋላ ከበሽታቸው ተሻለኝ አሉ።" ብሏል።

በብዙ ጥናቶች ሰዎች 'ያድነኛል' ብለው አምነው መድሀኒት ሲወስዱ የተሻለ እንደሚያድናቸው ታይቷል። መድሀኒትነት የሌላቸው ኪኒኖች እንኳ አምነው ከወሰዱ እንደህመሙ አይነት ከ15 እስከ 75 ከመቶ ለውጥ እንደሚያሳዩ በተደጋጋሚ ታይቷል።

ብዙ ዐ.ነገሮች የሚካሄዱት አእምሮ ውስጥ ነው።
https://telegram.me/counselingA