Get Mystery Box with random crypto!

ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ

የቴሌግራም ቻናል አርማ counselinga — ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ
የቴሌግራም ቻናል አርማ counselinga — ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ
የሰርጥ አድራሻ: @counselinga
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.26K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ የስነ ልቦና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው የሚቀርቡበት ልዩ ቻናል፡፡

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 16:04:30 #10 Easy ways to Appear a more Powerful person.

1. Be calm
2. Talk less
3. Avoid drama
4. Be less reactive
5. Make eye contact
6. Listen more to others
7. Think outside the box
8. Think before you speak
9. Don't always be available
10. Speak less about yourself


https://t.me/counselingA/603
213 viewsÃsh€ Ġ, 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:12:34 መፍትሔው የችግሩ እውቀት ነው!
፨፨፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨፨
በቅድሚያ ችግሩን አሳደህ አግኘው፣ እወቀው፤ በመቀጠል መፍትሔውን ፈልግ። አስር አይነት መፍትሔ አንድን ያልታወቀ ችግር አይፈታውም። ችግርህን ሳታውቅ ብዙ አማራጭ መፍትሔዎችን ብትፈልግ በፍፁም ልትቀርፈው አትችልም። ያለበትን ችግር ምንንነት ያወቀ አንድ ሰው ከመፍትሔው ለመድረስ ከግማሽ መንገድ በላይ እንደተጓዘ ይቆጠራል። ስለታመምክ የምትወስደው መድሃኒት ሁሉ አያድንህም፤ ለመዳን የህመምህ አይነት መታወቅ ይኖርበታል። ብዙ ስለደከምክ ሃሳብህን አታሳካም፤ የሃሳብህን ምንንነት ማወቅ፣ መረዳት ግድ ይልሃል።

አዎ! መዳረሻ የሌለው ሰው በፈለገው መንገድ መጓዝ ይችላል ምክንያቱም ማረፊያውንና የሚያስኬደውን መንገድ አያውቅምና። እንዲሁ ችግሩን ያላወቀ ሰው ምንም እንኳን ብዙ አማራጭ መፍትሔዎችን ቢሞክርም ትክክለኛውን መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም። ከየትኛውም መፍትሔ በፊት የቸግሩ ምንጭ፣ የችግሩ ምንነት መታወቅ አለበት። ሃገራዊ ችግር ይሁን፣ ግላዊ ችግር ምንም የተፈለገው መፍትሔ ቢሞከር መሰረቱ እስካልታወቀ ከድካም ውጪ ትርፍ አልባ ነው።

አዎ! ለመታረቅ የፀቡ መንስዔ መታወቅ አለበት፣ ለመስማማት ልዩነት ፈጣሪ ሃሳቦች ግልፅ ሊሆኑ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድ የጋራ መግባቢያ ሃሳቦች ይፋ መውጣት አለባቸው። እያንዳንዱ ከባድ ጉዳይ በጥቃቅን ሃሳቦች የተዋቀረ ነው። የመፍትሔ ሰው ነው የሚባል ሰው መፍትሔ በመዘርዘር የሚታወቅ ሰው አይደለም። በምትኩ ችግሮችን በመፈልፈል፣ መንስዔያቸውን በመለየት የሚታወቅ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! መፍትሔው የችግሩ እውቀት ነው። ችግርህን ካላወክ መፍትሔውን እንዳታስበው፤ ችግሩን ከተረዳህ ግን በእርግጥም መፍትሔው በእጅህ ነው። የፍቅር ህይወትህ ዋናው ችግር ምንድነው? መንሰኤውስ? የቤተሰብህ ትልቁ ችግር ምንድነው? መነሻውስ? የእራስህ ችግር ምንድነው? ምክንያቱስ? እነዚህን ጥያቄዎች ከመለስክ መፍትሔው ሊጠፋብህ አይችልም። ችግርህን ለመቅረፍ ችግርህን እወቅ፤ ወደፊት ለመጓዝ መሰናክሎችህን አስቀር፤ ህልምህን ለማሳካት ሰበበኛ ሃሳቦችህን ተሻገር።

https://telegram.me/counselingA
313 viewsÃsh€ Ġ, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 09:51:11 የአዕምሮ ሰላም!
፨፨፨///////፨፨፨
ሕይወቴን ደግሜ የመኖር ዕድል ቢሰጠኝ መድገም የምፈልገው ይህንኑ አኗኗር ነው፡፡ አሁን የሠራኋቸውን ስህተቶች ደግሜ የምሰራ ቢሆንም ስህተቶቼን ለማረም በቂ ጊዜ እንዲኖረኝ ስህተቶቼን አሁን ከሠራሁባቸው ጊዜያት ቀደም እያልኩ ለመሥራት እሞክር ነበር፡፡ በወጣትነት ስህተትን ተቀብሎ ማረም ብዙ ህመም የለውም፡፡ እድሜ ከገፋ በኋላ ሲሆን ግን ስህተቶች የሚመጡት የበዛ ህመም አስከትለው ነው፡፡

ከዚህ የስኬት ፍልስፍና ያገኘኸው ትልቁ ካሳ ምንድነው ብላችሁ ብትጠይቁኝ የምሰጠው ምላሽ የአእምሮ ሰላም የሚል ነው፡፡ ሰዎች በእኔ ዕድሜ ወይም ከእኔ በዕድሜ ያነሱ ሆነውም የአእምሮ ሰላምን የሆነ አካል ወይም ሰው እንዲሰጣቸው በመጠባበቅ ላይ ያሉ አሉ፡፡ ምንም ጥረት ሳያደርጉ የአእምሮ ሰላምን ከሌላ አካል እንዲመጣ ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም እየፈለጉት ያሉት በተሳሳተ ቦታ ላይ በመሆኑ እስካሁን እንዳላገኙት ሁሉ መቼም ሊያገኙት አይችሉም፡፡

የአእምሮ ሰላም እናንተው ለእናንተ ልታገኙለት የሚገባ ነገር ነው፡፡ ሆኖም የአእምሮ ሰላም ለማግኘት ከየት መጀመር እንዳለባችሁ ግራ እንደምትጋቡ እሙን ነው፡፡ እኔ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ የአእምሮ ሰላም በገንዘብ የሚገዛ፣ አልያም በዝናና በሀብት የሚገኝ ሳይሆን ከልባችሁ ዝቅ ብላችሁ በማገልገል ብቻ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡ የአእምሮ ሰላም ለማግኘት ከእናንተ ከሚጠበቀው ተጨማሪ ኪሎሜትሮችን መራመድ ነው፡፡

https://telegram.me/counselingA
180 viewsÃsh€ Ġ, 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:46:23 ወጣቱ የአንድን አርሶ አደር ቆንጆ ልጃገረድ ማግባት ፈልጓል፡፡ እናም ወደ አባቷ ቀርቦ ፍቃዳቸው ይሆን ዘንድ ጥያቄውን አቀረበ፡፡ አባት ልጁን ከእግር ጥፍሩ እስከ እራስ ፀጉሩ እየተመለከቱት አንድ ተግባር ሰጡት፡፡ “ናስኪ ልጄ! ሂድና እዛ እመስኩ መሐል ቁምና እነዚህን ሦስት ኮርማዎች ተራበተራ እለቃቸዋለሁ፡፡ ከሦስቱ ኮርማ ያንደኛውን ኮርማ ጅራት የያዝክ እንደሁ ልጄን እድርልሃለሁ፡፡ ታገባታለህ” አሉት፡፡ ወጣቱ በታዘዘው መሰረት ከግጦሹ ሜዳ ሁኖ መጠባበቅ ጀመረ፡፡ የኮርማዎቹ በረት እንደተከፈተ ትልቅ ኮርማ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቅ ሻኛ የተሸከመ ኮርማ ሲመጣ ተመለከተው፡፡ ወጣቱ “ይሄስ ይለፈኝ የቀጣዩን ኮርማ እይዘዋለሁ” ብሎ ወሰነና አስተላለፈው፡፡ ሁለተኛው ሲመጣ የሚያየውን ማመን አልቻለም፡፡

ከመጀመሪያው በላቀ ግዙፍ ሆነበት፡፡ “የሚቀጥለው ኮርማ (ሦስተኛው ማለቱ ነው፡፡) የፈለገውን ይሁን እሱን እይዘዋለሁ” በማለት ይሄኛውን ወደ ጥግ በመሸሽ አሳለፈው፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ የኮርማዎች በር ሲከፈት ወጣቱ ፈገግ አለ፡፡ ከበረቱ የወጣው ኮርማ ደከም ያለ ነበር፡፡ ወጣቱ የኮርማውን ጅራት ለመያዝ እንዲያመቸው አቋቋሙን አስተካክሎ ጠበቀው፡፡ ኮርማው እሱጋ ሲደርስ ዘሎ ወጣበት ነገር ግን የኮርማውን ጅራት መያዝ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ኮርማው ጅራተ ቆራጣ ስለነበር ሙሉ ጅራት አልነበረውምና፡፡


ሕይወት በመልካም አጋጣሚዎች (Opportunities) የተሞላች ናት፡፡ አንዳንዱን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ቀላል ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን የተሻለ ይገኛል በማለት እጅ የገባን መልካም እድል ማሳለፍ የማይመጣን እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም ያመለጠ መልካም አጋጣሚ መልሶ እራሱ አይመጣም፡፡ ይህ ማለት ግን ሌላ መልካም አጋጣሚ የለም ማለት አይደለም፡፡ የከፋ ወይም የተሻለ ይኖራል፤ይመጣልም፡፡ እራሱ የበፊቱ ግን አይመጣም፡፡ አንዴ ካመለጠ መልሶ እንደማይገኝ ሲናገሩ መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው ይሉታል፡፡ ቁንጮ ልጆች በአብዛኛው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ፊት ለፊት ላይ ቁጢጥ አድርገው የሚተውት የፀጉር አቆራረጥ ነው፡፡ መልካም አጋጣሚም እንደመጣ ፊት ለፊት ካልይዙት ዘወር ካለ መላጣ ስለሆነ መያዝ አይቻልም ፡፡ ስለሆነም ሁሌም ከፊትህ የመጣን መልካም አጋጣሚ ይዋል ይድር ሳትል ተጠቀምበት ነው መልዕክቱ፡፡

ምንጭ፡ NEVER MISS FIRST OPPORTUNITY !!

https://telegram.me/counselingA
484 viewsÃsh€ Ġ, 12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 09:10:35 ፓኒክ ዲስኦርደር- "ፍርሀትን መፍራት"
=======================
ፓኒክ በድንገት የሚመጣ ከፍተኛ ፍርሀት ሲሆን አእምሯዊም አካላዊም ምልክቶች አሉት፡፡ ትንፋሽ ማጠር፣ ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ ማላብ፣ መደንዘዝ፣ ማቅለሽለሽ "ልሞት ነው?"  "አእምሮዬን ልስት ነው?" የሚሉ ሀሳቦች፡፡ ፓኒክ ግፋ ቢል አስር አስራአምስት ደቂቃየሚቆይ ይሁን እንጂ ፓኒክ ያጋጠማቸው ሰዎች ያላሰቡት ቦታ ወይም ሁኔታ ውስጥ ድጋሚ እንዳያግጥማቸው መፍራት እና መጨነቅ ይጀምራሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከቤት ውጭ ፓኒክ እንዳያግጥማቸው በመፍራት ከቤት የማይወጡ ሰዎች አሉ፡፡ ለዚህ ነው ፓኒክ ዲስኦርደር "የፍርሀት ፍርሀት" የሚባለው፡፡

ፓኒክ ዲስኦርደር ከመቶ ሰው ከአንድ እስከ አራት ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ሴቶች ላይ የመከሰት እድሉ ከወንዶች ይልቅ ሁለት እጥፍ ነው፡፡ የፓኒክ ዲስኦርደር መንስኤዎች ብዙ ሲሆኑ በባህሪያቸው የሚጨነቁ እና ጭንቀት ጎጂ ነው ብለው በሚያስቡ ሰዎች ላይ ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም የህይወት ጫና፣ ከሚወዱት ሰው አለመግባባት ወይም መለየት ሊቀሰቅሱት ይችላሉ፡፡ ፓኒክ ዲስኦርደር ያለባቸው ብዙዎቹ ሰዎች ቡና ሲጠጡ የመጨናነቅ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡

የፓኒክ ምልክቶች አካላዊ ስለሆኑ ታካሚዎች ወደ የውስጥ ደዌ ወይም የልብ ስፔሻሊስት ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ በምርመራ ግን የሚገኝ ነገር አይኖርም፡፡ ፓኒክ ዲስኦርደር ውጤታማ በሆነ ሁኔታ በንግግር ህክምና ወይም በመድሀኒት ሊታከም ይችላል፡፡

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
https://telegram.me/counselingA
493 viewsÃsh€ Ġ, 06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 07:12:48
“ተጓዝ ግን ለማንም አትንገር፣
የምር አፍቅር ግን ዝም በል፣
በደስታ ኑር ግን ለማንም ትንፍሽ እንዳትል፣
ለማንም ምንም አትበል
በቃ - ዝም በል…
ሰዎች ቆንጆውን ነገር ያጠፉብኻል”

                     ኻሊል ጂብራን

          
608 viewsÃsh€ Ġ, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 10:37:35 አልሰራህም ማለት ነው!
፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨
ካልተጠላህ፣ የሆነ ሰው ካልተቸህ፣ መነጋገሪ ካልሆንክ በእርግጥም ምንም አልሰራህም ማለት ነው። ስራህ የሚያስወራብህ፣ የሚያነጋግር፣ መቀኞችህን የሚያናድድ፣ ወዳጆችህን የሚያስደስት መሆን ይኖርበታል። ልዩነት መፍጠሩን ከሃሳብ ትጀምራለህ፤ በተግባር ትደግመዋለህ። ከብዙዎች ጋር በተመሳሳይ እድገት ብታድግም ምርጫህ ግን ልዩነትን መፍጠር ይሆናል። አስተውሎትህ በጨመረ ቁጥር ውሎህ፣ አዳርህ፣ ጓደኛህ፣ ወዳጅህ ይቀየራል።

አዎ! ጀግናዬ..! አልሰራህም ማለት ነው! የማያውቅህ ሰው ያውራብህ፣ አለመቻልህን ይናገር፤ በማያገባው ይግባ፣ ብዙ ያውራ። ተፈላጊው ነገር እርሱ ነው። ካልተወራብህ የተለየ ነገር እንዳረክ በምን ታውቃለህ? ነቃፊዎችህ አይናቸው ካልቀላ፣ ዘወትር የቡና መጠጫ ካላደረጉህ፣ ያንተ ስራ ትልቅነቱ የቱጋር ነው? የጥላቻቸው ሌላኛው ትርጉም ምንድነው? እነርሱ ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር ግን ያልቻሉትን አንተ ስላደረከው፣ ችለህ ስላሳየሃቸው ይጠሉሃል፤ ይጠየፉሃል። እርሱ ግን ላንተ ሃይል መሆኑን አያውቁትም፤ ቢያንስ ዝም ቢሉ ጥሩ ነበር ግን አይችሉም። ስለዚህ አንተም ለእነርሱ ሲሆን መስማቱን አትቻል፤ አትስማቸው።

አዎ! የሰው ምላስ ያስፈራል፤ "ምን ይሉኛል" ያሸማቅቃል። እንዲወራብህ ካልፈለክ፣ ስድቡን፣ ትቺቱን ነቀፋውን ከፈራህ ሃሳብህን ይዘህ፣ ህልምህን ታቅፈህ መቀመጥ ያንተ ምርጫ ነው። የፈጣሪ ተዓምር፣ የአምላክ ጥበብ ባንተ ላይ እንዲገለጥ ስትፈቅድ ብቻ ተዓምራቱን ታያለህ፤ ድንቅ ስራውን ትመለከታለህ። በስንት መድረክ ስትጠበቅ በትንሽ የመንድር ወሬ ተጠልፈህ ከወደክ አንተን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን የሚጠቅመውን ህልምህን ይዘህ ትጠፋለህ።

አዎ! እራስህን ተመልከት፤ ስለማን፣ ለምን፣ ስንቴ፣ በምን ጉዳይ በየቀኑ ታወራለህ? ትኩረትህ ነቀፋ ነው ወይስ ሙገሳ? ትቺት ነው ወይስ ምስጋና? የአዎንታዊነትህ ማሳያ ሙገሳ፣ ብርታትና ምስጋና ነው። በእራስህም ሆነ በሌሎች የማብጠልጠልንና ፅንፍ የወጣ ትቺትን አስከፊ ገፅ በሚገባ ተመልክተሃል። ወዳጅህ ሲደግፍህ ጠላትህ መውደቂያህን ሲያመቻች አይተህም ይሆናል። እናም ጠላትህን የሚያስደግጥ ወዳጅህን የሚያስፈነድቅ ግሩም ስራ ከመስራት ወደኋላ አትበል። ትቺት፣ ነቀፋና ዘለፋ ልማዱ የሆነ ሰው የለመደውን ያድርግ ዘንድ ተወው፤ አንተም ትልቁንና አስደማሚውን ህልምህን መኖርህን ቀጥል። አለማቆምህን ሲያይ ሁሉም ዝም ይላል፤ ከነቀፌታው ይገታል፤ ተስፋ አለመቁረጥህን፣ ብርታትህን ሲመለከት ስድቡን ያዝ ያደርገዋል፤ ውጤትህንም ሲመለከት መከተሉን ይጀምራል።

https://telegram.me/counselingA
746 viewsÃsh€ Ġ, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:38:01 #የአእምሮ_ህመም_የማይመስሉ_የአእምሮ_ህመሞች

ማህተመ ጋንዲ ከአንድ ሰው ጋር ይጣላል። ጥፋቱ የሰውየው ነው። ማህተመ ጋንዲ ይቅርታ ሊጠይቀው ይሄድና እግሩ ስር ይወድቃል። ሰውየው በእግሩ ፊቱን ይጠልዘዋል። ጋንዲ ጥርሱ ተነቃንቆ ደም በደም ይሆናል። ቀና ብሎ ሰውየውን እየተመለከተ "ወንድሜ ፊቴ እግርህን አልጎዳህም አይደል?" ብሎ ጠየቀው አሉ።

ብዙ ሰው ይህንን ታሪክ ሲሰማ "እንዴት ትሁት ሰው ነው?" ሊል ይችላል። አንዳንድ ሳይካትሪስቶች ደግሞ "Moral masochism" የሚባል ህመም እንዳይሆን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ማሶኪዝም (Masochism) በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ሲገረፉ ብቻ የደስታ ጥግ ላይ የሚደርሱ ሰዎችን ይገልፃል። የሞራል ማሶኪዝም ደግሞ በስቃይና በእንግልት ደስታ የማግኘት ስነ ልቦናዊ ክስተት ነው።

የጋንዲ ጉዳይ አከራካሪ ሊሆን ንችላል። ነገር ግን አንዳንድ ህመም የማይመስሉን ፀባዮች የአእምሮ ህመም ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ስራ በጣም መስራት፣ ብዙ እቃ መግዛት፣ መኮላተፍ....ዝርዝሩ ረጅም ነው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
https://telegram.me/counselingA
586 viewsÃsh€ Ġ, 09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 11:29:56 Tell yourself every day:

"I am where I am because of my decisions!
If I want better results: I must take better actions.
I will learn the lessons. I will see the blessings.
I will not stop until my goals are realized. When I reach that goal I will set a bigger goal!"
https://telegram.me/counselingA
499 viewsÃsh€ Ġ, 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 11:22:39 #ሰው_ሁን!

ሰው ከመሆንህ በፊት ዶክተር (ሐኪም) አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት መሐንዲስ አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት መምህር አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት ፖለቲከኛ አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት ጋዜጠኛ አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት መሪ፣ መካሪ፣ አውሪ፣ ዘማሪ፣ ጸሐፊ፣ ለጣፊ፣ ሰባኪ፣ ሹመኛ፣ ወገኛ.... ሌላም አትሁን፡፡

ዓለም፣ ኢትዮጵያም ያጣችው ይህንን ሁሉ አይደለም፡፡ ሰው የሚሆንላትን እንጂ፡፡ ይልቁንስ ከሁሉ በፊት ሰው ሁን፡፡ ሰው መሆን ከእነዚህ ሁሉ የተሻለ ማንነት ነውና፡፡

"ሰብአዊነት የጎደለው ሙያ በመርዝ ዕቃ ላይ እንደተቀመጠ ጣፋጭ ምግብ ነው" ይላሉ አበው፡፡ የችግሮቻችን ሁሉ መነሻም ሰብአዊነት የጎደለው ግብራችን ነው፡፡
#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ
https://telegram.me/counselingA
505 viewsÃsh€ Ġ, 08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ