Get Mystery Box with random crypto!

የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ weludebirhane — የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ weludebirhane — የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @weludebirhane
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 646
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ፤ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ገፅ ነው ።
በዚህ ገፅ ፦
● መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ መልዕክቶች ፣ ምክሮች
● መዝሙሮች ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች
● ወቅታዊ የቤተክርስቲያን እና የሰ/ት/ቤት ጉዳዮች
● የሰ/ት/ቤት መልዕክቶች ፣ ማስታወቂያዎች ይቀርቡበታል።
ኦዲዮቪዥዋል ክፍል
ለመቀላቀል ➠ @weludebirhane

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 11:21:54
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ምስለ ኖኅ
ኪዳነ ዘአቀምከ፤ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወሥነ
ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወከመ
ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ
ዘወይጠል፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ
ፈጠርከ፤ ፀሐየ ወወርኀ ዘአስተዋደድከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት፤ ወአልዓላ
እምኵሉ ዕለት፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ፤
#ትርጉም
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳን የገባህ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው
ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድክ፤ ምድርን በአበቦች
ያስጌጥክ፤ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው ? የምድረ በዳውን
አራዊት ከወዳጆችህ ጋር ያስማማህ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ
ማነው፤ ጉንጮቹ እንደ ዋልያ እንቦሳ ፈጣኖች ናቸው፤
አንደበቱ ጣፋጭ ነው፤ ተወዳጅነቱ እንደ ፌቆ ግልገል ነው፤
ሰማይና ምድርን የፈጠርክ፤ ፀሐይና ጨረቃን ያስማማህ፤
ሰማይን በከዋክብት የሸፈንክ፤ ምድርን በአበቦች ያሸበረቅህ፤
ሰንበትን ያከበርካት ከዕለታትም ለይተህ ከፍከፍያደረግኻት፤
አቤት!! እንዳንተ ይቅር ባይ ማንም የለምና ኹሉም አንተን
ተስፋ ያደርጋሉ።
#እንኳን_ለዓለም_ጌታ_ለፍጥረታት_አምላክ_ለነገስታት_ንጉስ_ልዑለ_ባህሪ_ለሆነው_ለአምላካችን_ለመድሐኒታችን_መድኃኒዓለም_ወርሀዊ_በዓል_አደረሰን !

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
97 viewsSAMI ✞, 08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 04:51:32 አድራሻ በተለምዶ ኪንባ ሠፈር ተብሎ የሚጠራ አከባቢ ነው
144 viewsSAMI ✞, 01:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 04:51:32 የሀዘን መግለጫ የደብራችን የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት የአቶ እሸቱ አሽኔ ባለቤታቸው ስላረፉ ነገ በ26/11/2014 ዓ.ም ከ8-9 ሠዓት በደብራችን ሥርዐተ ቀብሩ ይከናወናል አንዲሁም በዕለቱ በ26/11/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት የማፅናኛ መርሃ ግብር ይከናወናል በዕለቱ የሆነበት ምክንያት ባለፈው ሕሮብም በማፅናኛ ምክንያት የሕሮብ ኘሮግራም (ወቅታዊ የቤ/ያን ጉዳይ) መታጠፉ ይታወቃል አሁንም መርሃ ግብሩ እንዳይታጠፍ ስለተፈለገ ነው
145 viewsSAMI ✞, 01:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:56:43
165 viewsSAMI ✞, 15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:55:53
146 viewsSAMI ✞, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:54:04 ‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡››

#ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

#ሀምሌ 24/2014 ዓ.ም በእንጦጦ መንበረ ስብሀት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው #የሰ/ት/ቤታችን አባል ወንድማችን ዲ/ን ታምራት ስዪም እና እህታችን ራህዋ የማነ ፤ የፈጸማቹሁት ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሣራን፣ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላችሁ፡፡

<<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>>

#ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡

<ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ፡፡ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፈቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>>
#ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:22)
----------
22፤ ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤

23፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

24፤ ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።

25-26፤ ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

27፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።

28፤ እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤

29-30፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል።

31፤ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

32፤ ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።

33፤ ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።

የመንበረ ስብሐት ቅ/ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን የውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
#ኦዲዮቪዥዋል ክፍል

ለመቀላቀል ➠
Facebook https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl

Telegram
https://t.me/weludebirhane

YouTube



◈ ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ያድርጉ!.
149 viewsSAMI ✞, edited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:01:00
205 viewsSAMI ✞, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 05:15:41 Watch "EOTC TV | ዐውደ ስብከት | ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ" on YouTube


234 viewsSAMI ✞, 02:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 05:15:41
216 viewsSAMI ✞, 02:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 05:15:40 በቅዱስነታቸው ጉዞ በተፈጠሩ ችግሮች ዙርያ የተሰጠ መግለጫ።
(ኢኦተቤ ቴቪ ሐምሌ ፳ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም )
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጉዞ ላይ ባጋጠማቸው እክሎች ዙርያ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላላ ድ/ቤት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ;ብፁዕ ዶ/ር  አቡነ ጴጥሮስ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፤ መልአከ ሕይወት ቆምስ አባ ኃ/ገብርኤል የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሐፊ  በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል::
በመግለጫውም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክነት በቃለ ወዋዲው እና በሕገ ቤተክርስቲያን  የተረጋገጠ መሆኑን ተገልጿል።
ከቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለሕክምና ከሀገር ውጪ እንደሚሄዱ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ባስታወቁት መሠረት በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ለህክምና ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘዋል። ጉዞውም ሕጋዊና ምክንያቱ የሕክምና ክትትል ለማድረግ መሆኑን የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች የሚያውቀት መሆኑን ተናግረዋል ::
ቅዱስነታቸው በሕገ ቤተ ክርስቲያን ባላቸው ሥልጣን  ታቦት የመባረክ;  የአብያተ ክርስቲያናትን ቡራኬ ማከናውን አንዱ መሆኑ በመግለጫው የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስነታቸው ሊወስዷቸው የነበሩ ታቦታት በቤተክርስቲያኗ እውቅና ቅዱስ ፓትር ያርኩ በሰጡት  መመሪያ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላላ ጽ /ቤት ትዕዛዝ በቅርፃ  ቅርፅ ክፍል ተዘጋጅቶ ይዘውት እንዲሄዱ የተዘጋጀ የተለመደና ሕጋዊ አሠራርን የተከተለ መሆኑን ገልጸው በጉዞው ወቅት ቅርጻ ቅርጽ  የሚለውን "ቅርሳ ቅርስ" መባሉ አግባብ አለመሆኑን ገልጸዋል ::
በመግለጫው በየምክንያቱ የቤተክርስቲያንን ክብር መንካት በየተቋማቱ እየታየ በመሆኑ የቤተ ክርስቲያኗን ጥንታዊነት ለሀገር ያበረከተችውን አስተዋዖ በማስብ ክብር ሊጠበቅ
እንደሚገባ ተነግሯል።
EOTC TV
++++++++++++++++++++++++++++++++
የወቅታዊ መረጃ ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ የፌስ ቡክ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ሊንኮች በመጫን ሰብስክራይብ እና ላይክ ያድርጉ፡፡ ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
197 viewsSAMI ✞, 02:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ