Get Mystery Box with random crypto!

Kingdom of God🏥🏥🏥

የቴሌግራም ቻናል አርማ kingdom_ofgod — Kingdom of God🏥🏥🏥 K
የቴሌግራም ቻናል አርማ kingdom_ofgod — Kingdom of God🏥🏥🏥
የሰርጥ አድራሻ: @kingdom_ofgod
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 487
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የተሰቀለውን ኢየሱስን የምንሰብክበት ስፍራ ነው ።
መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎች ጥበብን ይሻሉ👉 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ይህ ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው.
1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ1:22
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 08:30:43 ለእግዚአብሔር ደሰታ እናገልግል!

አገልግሎት ሰዎች ማስደስት ሳይሆን አገልግሎት እግዚአብሔርን ማስደሰት ነው።የአንድ አገልጋይ ውድቀት የሚጀምረው የጠራውን እግዚአብሔር ማስደሰት ትቶ ለሰዎች ደስታና ዕርካታ ለማገልገል ሲሮጥ ነው።

የትውልዱን ስስት እያወራህ የጌታ ባሪያ ልትሆን አትችልም።ትውልዱ የሚፈልገውን እየጠነቆልክ የእግዚአብሔር ሀሳብ አገልጋይ ለመሆን በጣም እረፍዶብሃል።

ትውልዱ የሚድነው የሚፈልገውን ስትነገረው ሳይሆን እግዚአብሔር የፈለገውን ስትነገረው ነው።ቤተክርስቲያን የተጨናነቀችው የእግዚአብሔርን ለመስማት በሚፈለጉ ሰዎች ሳይሆን የራሳቸውን መስማት በሚፈልጉ ሰዎች ነው።ይህ የሆነበት የመጀመሪያው ምክንያት የእግዚአብሔርን ሀሳብ እርሱም ክርስቶስን የሚያገለግሉ ሳይሆን ልብ ወለዳቸውን የሚተርኩ ስለ በዙ ነው።

መድኃኒታችን የፕሮግራም ማድመቂያ አይደለም እርሱ የማያልቅ ፕሮግራማችን ነው።እርሱ የፕሮግራማችን መጀመሪያ ነው መካከለኛም ነው መደምደሚያም ነው።ስንጀምርም እርሱ ነው ስንጨርስም እርሱ ነው።
481 views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 09:11:13 ሐምሌ 2014 የመለኮታዊ ፍቅር

“እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።ኤርምያስ 31፥3

በዚህ ወር የፍቅር አምላክ በፍቅሩ ይጎበኛችኋል።በፍቅሩ እንደገና ያነሳችኋል ደግሞ ያቆማችኋል።በኢየሱስ ስም አሜን!!!
683 views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:41:57 እግዚአብሔር እንደ መጨረሻ ዝናብ ሆኖ ይመጣል!!

“እንወቅ፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ እንደ ዝናብም ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ መጨረሻ ዝናብ ይመጣል። ሆሴዕ 6፥3
1.4K views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 07:41:44 ምናልባት ጠላት መጥቶ የወርቁን ጋሻ ማርኮ ወስዶት ይሆናል፡፡ የተወሰደብህን የወርቁን ጋሻ አስመልስ እንጂ በእርሱ ፈንታ ተመሳሳዩን የናስ ጋሻ አትስራ አይበጅህምና፡፡ እንደዋናህም አይሆንልህምና፡፡

ዋናውን ጥለን/አስማርከን ተመሳሳዩን አናነሳም ዋናውን እናነሳለን/እናስመልሳለን እንጂ፡፡

"... የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ መጣ።... ሰሎሞንም የሠራውን የወርቁን ጋሻ ሁሉ ወሰደ። ... ንጉሡም ሮብዓም በፋንታው የናስ ጋሾችን ሠራ... " 1ኛ ነገ 14፥25-27
598 views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 10:12:04 ሁሉም ፍጥረት በኖረ ቁጥር ያረጃል እየኖረ አዲስ እየኖረ የማያረጅ እግዚአብሔር ብቻ ነው።በዘመናት መካከል ያላረጀ እግዚአብሔር ብቻ ነው።

“ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።”
ሰቆ. 3፥23
759 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:02:35 የእግዚአብሔር የሆነ ነገር ሁሉ አይቅለልባችሁ የእርሱ የሆነውን የሚያቀልባችሁን ማንኛውንም ምክንያት አስወግዱት።

የእግዚአብሔር ነገር አክብዶ የቀለለ የለም።የእግዚአብሔር የሆነውን አቅልሎ የከበረ የለም።ዋናው ነገር ዋናውን ነገር ዋና ማድርግ ነውና ዋናውን ሊያቀልባችሁ የተነሳው ተራ አጀንዳ በመተው እግዚአብሔር መጀመሪያ ያለውን አንሡ።

የእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ ዋጋ መስጠት የሚጀምረው ከvalue system ነው።ማንም ሰው ለእግዚአብሔር ነገር ያለው value system እንድ እግዚአብሔር ሃሳብ ወይም እንድ እግዚአብሔር ቃል አቆጣጠር እስካልሆነ ድረስ መቼም የእግዚአብሔር ነገር በእርሱ ዘንድ አያከብርም።

የእግዚአብሔር ጉዳይ በእግዚአብሔር እውነት ይተረጎማል እንጂ በእኛ መረዳት አይብራራም።
781 views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 10:42:13 መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ማድረግ መንፈሳዊነት አይደለም።መንፈሳዊነት የእግዚአብሔር ሃሳብና ፈቃድ ማድረግ ነው።

ትውልድ የፈለገውን የሚያድርግ ከሆነ በትውልድ መካከል ንጉስ የለም ማለት ነው።ጌታ ኢየሱስ የነገሰበት ህይወት እንደ ፈለግን የምናደርገው ሳይሆን እንደፈለገ የሚያደርገው ነው።

“በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።መሳፍንት 21፥25
812 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 22:00:23 በህይወት በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም አይነት ሁኔታ በመከራ ቢሆን በችግር በመገፋት ቢሆን በመከዳት ተስፋ አልቆርጥም።

ተስፋ የማልቆረጠው ተስፋ የማያስቆረጥ ነገር ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን ተስፋ የማይስቆርጥ ተስፋ በውስጤ ስላለ ነው።እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ኢየሱስ የማያልቅ ግን የሚያስጨርስኝ ተስፋዬ ነው።ክብር ለእርሱ ይሁን!!!

“በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤ፊልጵስዩስ 1፥6
432 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 06:00:23 በእርሱ ዘንድ ምንም ነገር:-
ሊጠገን እስከማይችል ድረስ አይበላሽም:
ሊገኝ እስከማይችል ድረስ አይጠፋም:
ሊታደስ የማይችል እስኪሆን ድረስ አይበሰብስም:
ሊነሳ እስከማይችል ድረስ አይሞትም:
ተስፋ የሌለው እስኪሆን አይዘገይም::

ስለዚህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተበላሽቶ የሚቀር: ጠፍቶ የሚያበቃ: በስብሶ የሚጣል: ሞቶ የሚቀበር: ዘግይቶ ጊዜው የሚያልፍ ጉዳይ ፈፅሞ አይኖርም:: እግዚአብሔር የጊዜም : የሁኔታም: የነገሮችም አምላክ ነውና::

የምናመልከው እርሱ ለሞተው ህይወት የሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ እርጎ የሚጠራ አምላክ ነው ።
740 views03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 10:05:10 ጨለማው ለብርሃናችሁ ስፍራ ይለቃል።ብርሃን ባለበት ጨለማው አይበረታም።ጨለማውን አታወደሱት ብርሃናችሁን አብሩበት።ምከንያቱም እግዚአብሔር ብርሃን በጨለማ ላይ ይብራ ተብሎአልና።

ማንኛውም አይነት challenge እግዚአብሔር እጀ ላይ ካለው መልስ አይበልጥም።

“በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።”
2ኛ ቆሮ 4፥6
632 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ