Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Universities Muslim Association /Ethio-UMA/

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioumachannel — Ethiopian Universities Muslim Association /Ethio-UMA/ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioumachannel — Ethiopian Universities Muslim Association /Ethio-UMA/
የሰርጥ አድራሻ: @ethioumachannel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 322
የሰርጥ መግለጫ

ሙስሊም ተማሪዎች በያሉበት ትስስር ማድረግ: ተውሒድና ሱናን መሰረት ያደረገ ኢስላማዊ እውቀትን መገብየት: ብሎም እርስ በርሳቸው መተዋወቅና መወዳጀት!
"ቁርአን እና ሱናን በሰለፎች አረዳድ"

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-25 20:46:08 ኒቃብ የአረቦች ባህል ወይስ የሃይማኖቱ ድንጋጌ?

የተካተቱ ነጥቦች።
የሂጃብ ትርጓሜ።
የጅልባብ ትርጓሜ።
የመሸፈን አንቀፆች የወረዱበት ምክንያት።
ስለ ሂጃብ የወረዱ አንቀፆች እና የመጡ ሃዲሶች።
ለሴት ልጅ ፊቷን መሸፈን ግዴታ አይደለም ለማለት የሚነሱ መረጃዎች እና መልሶቻቸው።
ምክር ሂጃብ ሂጃብ(ኒቃብ) ለለበስሽው እህቴ።
የሂጃብ መስፈርቶች እና ለሚገላለጡ አስደንጋጭ ነብያዊ መልእክት።


ከተለያዩ ኪታቦች የተወጣጣ
ጥንቅር H.M
ለሃሳብ አስተያየቶ

@Dsiaunivbot

https://t.me/amhakfelagijemaa
82 viewsحيدر مزمل, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:49:05 قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله:

" القلوب لها صيدليات فاذهب إليها وخذ منها الأدوية: صيدلية القرآن، صيدلية الذكر، صيدلية الأعمال الصالحة؛ خذ دواء لقلبك، مثل ما تذهب للصيدليات تأخذ أدوية لجسمك، لا تعتني بجسمك وتهمل قلبك ".
شرح إغاثة اللهفان
ታላቁ የዘመናችን የሱና ኢማም ሸይኽ ፈውዛን – ሐፊዘሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –
" ልቦች ፋርማሲ ( መድሃኒት ቤት) አላቸው ሂድና መድሃኒት ውሰድ ። የቁርኣን መድሃኒት ቤት ፣ የዚክር መድሃኒት ቤት ፣ የመልካም ስራ መድሃኒት ቤት ሂድና ለልብህ መድሃኒት ውሰድ ። ልክ ማንኛውም መድሃኒት ቤት ሄደህ ለሰውነትህ መድሃኒት እንደምትወስደው ። ለሰውነትህ ትኩረት ሰጥተህ ልብህን ችላ አትበል " ።
ሸርሕ ኢጓሰቱ ለኸፋን
https://t.me/bahruteka
84 viewsحيدر مزمل, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 15:19:43 ሂጃብ (ሴት ልጅ በኒቃብ ሙሉ አካሏን መሸፈኗ) ሀይማኖታዊ ድንጋጌ ወይስ የአረቦች ባህል?
497 viewsحيدر مزمل, 12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-01 09:35:33 ግጥም

ለወንድም ኑረዲን ኢብኑ አል–ዓረቢ
ፕላኔት ነሽ አንቺ ለሚለው ግጥሙ የተሰጠ ምላሽ

#የፕላኔቶች_አውራው_ፀሀይ

ሀሳብ አስተያየት ካለዎ

@Dsiaunivbot

@amhakfelagijemaa
422 viewsحيدر مزمل, 06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-27 22:54:34 ስማኝማ

ጀግናዬ ካለህበት መጥፎ ተግባር ለመላቀቅ ወደ መልካሙ ለመምጣት ትፈልጋለህ

አዋ ምን ጥርጥር አለው እንደምትለኝ እርግጠኛ ነኝ። ግን ለምን መላቀቅ እንደከበደህ ታውቃለህ?
በመጀመሪያ ያለህበትን መጥፎ ተግባር መጥፎ መሆኑን እመን፣ ከእርሱ ለመላቀቅም ወስን፣ወደ መልካሙም ተግባር ገስግስ፣ወደ መጥፎው መመለስህ ከልብህ ጥላው። ነገር ግን ጉዳዩን ቀለል አድርገህ እንዳታስበው እንቅፋቱ ብዙ ነውና። የለመድካቸው ጓደኞችህ ትዝ ይሉሃል፣ የሰዎች መሳለቅ ያሳፍርሃል፣የነፍስያ እና የሸይጧን ጉትጎታ ያሰንፍሃል፣አጠቃላይ ነገሩ ይወሳሰብብሃል። ብቻ እንቅፋቱ ብዙ ነው።
አንተ ግን ጀግናዬ ጆሮ ዳባ ብለህ ወደ አላማህ ገስግስ። ዛሬ እነርሱን ማስከፋት የሚከብድህ የሃራም ወይም ከመልካም የሚያግዱ ጓደኞችህ ነገ አላህ ፊት ላንተ አይጠየቁም፣ሊከዱህም ይችላሉ(ቁርአን 43:67)፣ዛሬ በመለወጥህ የሚሳለቁብህ ደግሞ ነገ ያደንቁሃሉ፣ የተወሳሰቡብህ ሁሉ በአላህ ፍቃድ መስመር ይይዛሉ። ብቻ ወስን፣ተመለስ፣ፅና።

ሀይደር ሙዘሚል

@amhakfelagijemaa
174 viewsحيدر مزمل, 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 08:31:22
የትርጉም ስራዎች ቁጥር:

ቃል በገባነው መሰረት በድምፅ ትርጉም መጥተናል።

ለአኼራ ስለ መዘጋጀት በሸይ ሶላህ ጋ’ኒም (ረሂመሁላህ)

መጠን 4.7 ሜጋ ባይት ብቻ
ርዝመት 1 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ

#join #share እንዳይረሱ
ለሃሳብ አስተያየቶ

@Dsiaunivbot

@amhakfelagijemaa
166 viewsحيدر مزمل, 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 20:57:56 አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ......

በድጋሚ ተመልሻለው

ወንድማችን ኡስታዝ ቢላል ኑረዲን ከአልከሶ በቅርብ ርቀት የመናከሪያ ተወላጅ የአንድ ልጅ አባት ሲሆን በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ ከአረቅጥ በአቅራቢያ በሚገኝ ያሞራዘር የሚባል ሰፈር በኡስታዝነት በማገልገል ላይ ነበር

ወንድማችን አላህ ይድረስለትና በሚያገኛት ደምወዝ ከጅ ወደ አፍ ኑሮውን ከመግፋት ውጭ ሌላ አንድም የገቢ ምንጭ አነበረውም

እንደሰው የቅሙን ከተማ ገብቶ መስራት ከመቻሉጋ እንዲህ እየተቸገረ ዲኔን ልርዳ ብሎ በዛ ማብብራት ወሃ መሰል ነገር ባሌለበት በጨለማ ሰፈር ገብቶ እያስቀራ እያለ ህመም ስየጣድፈው በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሀኪም ቤት ሄዶ ሲታይ ስኳር ነው ብለው መድሀኒት ሰጡተ ሆኖም ሊሻለው አልቻለም መልሶ ወደሌላ ሀኪም ቤት ሲሄድ ሱኳሩ ተስተካክሏል ግን ደምህ በጣም ከልክ በላይ ሆኖዋል ብለው የደም ክኒን ሰጡት ሁኔታውን ሲያየው ሲከበደው ቡታጀራ እሄዳለው ብሎ ወደሰፈሩ ሄደ ቡታጀራ ደግሞ ኩላሊትህ ስራ ሊያቆም ነው አሉት ከዚያም በኋላ እየጨመረበት ሲመጣ ከትናንት በስቲያ ሲያጣድፈው ወራቤ ሆስፒታል ሲያስገቡት ከአቅማቸው በላይ ሆኖ ወዲያው ወደ አዲስ አበባ በኦክስጂን እየተነፈሰ በአምፑላን ላኩት ኩላሊቱ ስራ እዳቆመ እና የሽነት ቧንቧው እና የደም ቱቦው ስለተዘጋ ዎፖራሲዮን ቀዶ ጥገና አደረጉት ከዛበኋላ ደግሞ አንኳ ለሱ አይነት ምስኪን ይቅርና ለማንም ሰው በጣም የሚያስደነግጥ ነገር ለቤተሰቦቹ ተቀየቁ እሱም ደግሞ ኩላሊቱ ለሶት ቀን ለመታጠብ 50 ሺ ብር ጠይቀዋል በየሳምንቱ ደግሞ ሁለቴ መታጠብ እንዳለበት ነግረዋል አስቡ እንግዲህ በየሳምንቱ ሲታጠብ ቡዙ ወጪ ነው የሚጠይቀው ለዘኛው ወጪ ደግሞ አንደሱ አይነት ደረሳ ይቅርና ለማንም አካል ከባድ ነው ለሰ ደግሞ ከአሏህ በኋላ እኛው ካልተረባረብን ማንም ዞር ብሎ የሚያየው የለምእና ስለዚህ ሁላችንም ባቅማችን ልክ እጃችንን ለወንድማችን እንዘርጋለት

ወሏሂ ነው የምላቹህ ይህ ወንድ ችግር እና መጎሳቆል ደም እምባ ነው የሚያስለቅሳቹህ አሏህ ይድረስለት


ለበለጠ መረጃ

ሸረፈዲን አብራር
0941213251

ሰዒድ መሀመድ
0919574170

ደውሎ መጠየቅ ይቻላል


ለወገን ደራሽ ወገነው ከታች በማስቀምጠው አካውንት ላኩልን

የንግድ ባንክ
1000327546094

ሸረፈዲን አብራር

የንብ ባንክ
238Ifw3840

ሸረፈዲን አብራር



አደራ የምላቹህ ነገር ቢኖር ይህንን መልክት ካያችሁት በኋላ ገንዘብ ያላቹህ በገንዘባቹህ፣ ቻናል ያላቹህ በቻናላቹህ ፣ግሩፕ ያላቹህ በግሩፓቹህ እና ለጓደኛቹ በመላክ እድትተባበሩት እና እንዳነበባችሁት ዱዓ እንድታደርጉለት በአሏህ እጠይቃቹዋለው።
167 viewsحيدر مزمل, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-02 07:08:59 አንብቡት እጅጉን ትገረሙበታላቹ
-----------------------------------------------
መስቀል አምላኪዎች(በኢብኑ ሙነወር)

ጎበዝ ክርስቲያኖች የሚያመልኩት ስንት አምላክ ነው? ኢንፍሌሽን እዚያ አካባቢም አለ እንዴ? ስማቸውን ተመልከቱማ፡- ገ/ስላሴ፣ ገ/ማርያም፣ ገ/መስቀል፣ ገ/ሚካኤል፣ ወ/ስላሴ፣ ወ/ማርያም፣ ወ/መስቀል፣ ኃ/ስላሴ፣ ኃ/ማርያም፣ ኃ/መስቀል፣ ኃ/ሚካኤል፣ … መቼም እነሱ እየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እየተወገረ እንደተገደለ እንደሚያምኑ ይታወቃል፡፡ በርግጥ ይሄ የኛ እምነት አይደለም፡፡ እነሱም እምቢ ብለው እንጂ መፅሀፋቸው “በመስቀል ላይ የሚሞት የተረገመ ነው” ይላል፡፡ ማየት ማመን ነው [ዘዳግም 21፡ 23] ግለጡና አንብቡ፡፡ ለነገሩ እዚያ አካባቢ ማየት ማመን ላይሆን ይችላል፡፡ አሁን ርእሴ ይሄ አይደለም፡፡ ግን እንዳው የሚገርመው የሚያመልኩት ብዛቱ!
1. ሶስቱን ስላሴዎች ያመልካሉ፡፡ ይሄውና ማስረጃው፡-
- “ክርስቶስ ላንተ እንሰግድልሃለን ከሰማያዊ ከቸር አባትህ ጋራ አዳኝ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ጋራ እንሰግድልሃለን… ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ/3 ጊዜ/ ፡፡ አንድ ሲሆን ሶስት፣ ሶስት ሲሆኑ አንድ፣ በአካል ሶስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ እሰግዳለሁ” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 7-8]
- “በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ህይወትን የሚሰጥ ከአብ የሰረፀ ከአብ ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 8]
2. ቅድስት ማርያምን ያመልካሉ፡፡ ይሄውና ማስረጃው፡-
- “አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም እሰግዳለሁ፡፡” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 8]
- “እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማፅነንብሻል ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ድንግል ማህበራችንን ዛሬ ባርኪልን” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 10]
3. እልፍ አእላፍ ታቦቶችን ያመልካሉ፡፡ ማየት ማመን ነው፡፡
4. መስቀል ያመልካሉ፡፡ በየእለቱ የምናየው ቢሆንም መጥሀፍ መጥቀሱ አይከፋም፡፡
- “ዓለምን ለማዳን ሲል እየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እሰግዳለሁ፡፡ መስቀል ሀይላችን ነው፡፡ ሃይላችን መስቀል ነው፡፡ የሚያፀናን መስቀል ነው፡፡ መስቀል ቤዛችን ነው፡፡ አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን፡፡ ያመነውም እኛም በመስቀሉ እንድናለን፡፡ ድነናልም” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 8]
- “… ለእየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል፡፡” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 9]
ክርክር እንዳይረዝም ሰጋሁ እንጂ ሌሎችም በተጨባጭ የሚያመልኳቸውን መቁጠር ይቻል ነበር፡፡
ግን እኔን ለጊዜው የበለጠ የገረመኝ መስቀሉ ነው፡፡ አጃዒብ አትሉም!!! አምላካቸው የተሰቀለበትን፣ የተዋረደበትን መስቀል ማምለክ ምን የሚሉት እብደት ነው? ከመስቀሉ ላይ ያሰቃዩት ጠላቶቹ እንኳን ቢያደርጉት ግርምታችን ይቀል ነበር፡፡ ጉራቸው ቢደብርም ከባድ ጠላታቸውን በመገላገላቸው ደስታቸውን ለመግለፅ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ምናልባት፡፡ ግን እኮ የተገደለበት መስቀል እንደ ቅዱስ ከታየና ከተመለከ በመስቀሉ የሰቀሉትና ያሰቃዩት ይበልጥ ቅዱሳን ናቸው ማለት ነው፡፡ እነሱ ባይሰቅሉላቸው የሚመለክ መስቀል የለ የሚከበር ስቅለት የለ፡፡ ግን አምላኩ ይቅር፣ ሰው ወንድሙ ወይም አባቱ የተገደለበትን ጩቤ የቤቱን ግድግዳ አሸብርቆበት ብታዩት ምን ትላላችሁ? በኪሱ ይዞት ቢዞርስ? ካንገቱ ላይ ቢያስረውስ? ቢስመውስ? ቢሳለመውስ? ቢሰግድለትስ? እዕምሮው እያለ ሰው ይህን ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል? ዘወትር ስለምናየው ለምደነው እንጂ ይሄ እኮ እጅግ በጣም የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ ሰው በራሱ ጊዜ በህሊናው ላይ ይሳለቃል እንዴ? ወይ ነዶ! ወዶ አይደለም ለካ ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ሐዝም “እኔ አላህ በቁርኣኑ ባይነግረኝና በአይኔ ባላያቸው ኖሮ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ይኖራሉ ብዬ አላምንም ነበር” ያለው:: እዚህ ላይ አንድ የህንድ ንጉስ የተናገረውን ባሰፍር አይከፋም:: እንዲህ ነበር ያለው “የሌሎች እምነት ተከታዮች ክርስቲያኖችን ለእምነታቸው ሲሉ ቢፋለሟቸውም እኔ ግን ለህሊና ሲባል ሊፋለሟቸው ይገባል ነው የምለው፡፡ ምንም እንኳን ማንንም በመዋጋት ባላምንም እነዚህን ግን ከዓለም በሙሉ ለይቼ አወጣለሁ፡፡ ምክኒያቱም ነገረ ስራቸው ከህሊና ጋር መፃረር ነውና፡፡ ጥላቸው ከህሊና ጋር ነውና፡፡ …” [ሂዳየቱል ሐያራ፡ 21]
የመሲህ ባሮች ሆይ አንድ ጥያቄ አለን
የተረዳው ካለ መልሱን እንሻለን
ጌታ ግፍ አቅቶት ሰዎች ከገደሉት
አለቀ አከተመ የታል አምላክነት?!
ሰዎች የሰሩትን በሱ ላይ ሲያደርሱ
ጌታ ግብራቸውን ፈቅዶ ነው በራሱ?
እንዲያ ከሆነማ ምንኛ ታደሉ?!
ፍቅሩን ይቸራሉ ፈቃዱን ሲሞሉ::
ባደረሱት ሁሉ አልፎ ከተከፋ
እንግዲህ ምን ይባል?
ሀይሉ ከኮሰሰ ሀይላቸው ከሰፋ?!
ግን እንጠይቃለን ለመልስ አትንፈጉ
ማለባበስ ይቅር ይመለስ በወጉ
ፈጣሪዋን አጥታ ዐለም ስትዋትት
ሰው ወደ ማን ነበር የሚያስበው ፀሎት?
ፍጡር ፈጣሪውን ካፈር ሲያደባየው
ሰባቱን ሰማያት ማን ነበር ያቆየው?
ምስማር ተቸንክሮ ሲያሸልብ ፈጣሪ
አለም ቀርታ ነበር ያለ አስተናባሪ?
የሰማይ መላእክት ምንኛ ለገሙ?!
እጁ ተቸንክሮ ዋይታውን ሲሰሙ?
እንጨቱም ታምር ነው አቅሙ መቋቋሙ
አምላክ ያክል ነገር ችሎ መሸከሙ
ስለቱስ ጭቃኔው ብረቱ ምስማሩ
አካሉን ሰንጥቆ ስቃይ ማሳደሩ
ጉድ በሉ እሄን ጌታ
በአይሁድ የሚረታ
ማጅራቱን ታንቆ ታስሮ የሚመታ
ኋላስ ራሱ ነቃ ከሞት አንሰራራ
ወይስ ጌታ አገኘ ህይወት የሚዘራ?!
ጉድ በሉ ለቀብር ጌታ አቅፎ ለያዘ
የባሰም ሆድ አለ አምላክ ያረገዘ
ዘጠኝ ወር ታሽጎ ሲኖር በጨለማ
ሐይድ እየተጋተ ደም እየተጠማ
ብልት ቀዶ ወጣ አቡሻ ህፃኑ
አፉን ለጡት ከፍቶ አቤት ማሳዘኑ!
አስቡ እሄን አምላክ ሲጠጣ ሲበላ
ከዚያም ያስገባውን ሲያስወጣ በሌላ
ጌታዬ ከፍ አለ ከነሳራ ቅጥፈት
ሁሉም ይጠየቃል ለቀባጠረበት
የመስቀል ባሮች ሆይ ግራ ገባኝ እኔ
ይህን ማሽቀንጠሩ ፅድቅ ነው ኩነኔ
ማቃጠል ሰባብሮ ፈቃጁን ጨምሮ
ህሊና ከዚህ ውጭ ይፈርዳል አምሮ?
አምላክ አቅም አንሶት ለተጠፈረበት
ሰብሮ እንደማቃጠል ጭራሹን አምሎኮት?!
እውነትም እርጉም ነው ለምንስ ይዘንጋ
በመሳለም ሳይሆን በእግር ይሰጥ ዋጋ!
ለተዋረደበት ጌታህ ከነነፍሱ
አንተ ካመለክከው የሱ ነህ የነሱ?
‘ጌታን ስላዘለ’ ከሆነ አክብሮቲ
አስተዋሽ ቅርፃቅርፅ ቢሆን እንጂ እንጨቱ
መስቀሉ ከጠፋ ሺ ስንት አመታቱ?!
እንዲያ ከሆነማ ሂሳቡ ቀመሩ
ለመስገድ አትቦዝን ለየመቃብሩ
ያስታውሳልና ነገረ ስርኣቱ
ጌታህ ካፈር በታች ለነበረበቱ::
የመሲህ ባሪያ ሆይ ንቃ ተረጋጋ
ይሄ ነው እውነታው ካልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡

ግጥሙ “አዑባደል መሲሒ ለና ሱኣሉን” የሚለው የኢብኑ ቀይም አልጀውዚያህ ረሒመሁላህ ድንቅ ግጥም ግርድፍ ትርጉም ነው፡፡ [ኢጋሠቱል አልለህፋን፡ 2/290]


https://t.me/amhakfelagijemaa
130 viewsحيدر مزمل, 04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-03 20:43:58 ከትዝብት መንደር ቁጥር:16

ሁላችንም የአላህ ነን፣ነገራቶቻችንም በአጠቃላይ የአላህ ናቸው። ግን መቼ ይሆን አላህ የሰጠንን ለአላህ የምናደርገው? ከዚህ ጋር በተያያዘ  በጁሙዓ ኹጥባ ዙሪያ የታዘብኩትን ሹክ ልበላቹ። በአንዱ ጁሙዓ የጁሙዓ ሶላትን ለመታደም አላህ ባገራልኝ ወቅት ላይ ገብቼ ከመጀመሪያዎቹ ሰልፎች ላይ ተጣድኩኝ። ሰአቱ ሲደርስ ኢማሙ ኹጥባ ለማድረግ ወደ ሜምበሩ ብቅ አለ። እኔም አቀማመጤን አስተካክዬ ወደ ኢማሙ እየተመለከትኩ ቁጭ አልኩኝ። ምክሩ ስለ ተወሱል ምንነት፣አይነቶቹ እና ዛሬ ላይ ብዙዎች ስለሚያቀርቧቸው ማምታቻዎችም ጭምር የሚተነትን ነበር። ኢማሙ በመጀመሪያው ኹጥባ በአረብኛ ተኖግሮ በሁለተኛው በአማርኛ እያብራራ ስለነበረ፤የኹጥባው ሰአት ትንሽ ረዘም ያለ  ነበር። ከመሆኑም ጋር ግን የኢማሙ የአነጋገር ዘይቤ እና የመረጃ አቀራረቡ እጅጉን የሚመስጥ ስለነበር ብዙዎች በተመስጦ ይከታተሉት ነበር። ብዙ ሰው ግን በተቀመጠበት እያንቀላፋ ተመለከትኩ። በጣም ገረመኝ። ምን አልባት ድካም ሲኖር እንቅልፍ የሚያስቸግር ቢሆንም፤ይህን የሚያክል ትልቅ እና አንገብጋቢ፣ብዙዎችን የፈተነ እና ብዙዎች ለመንገዳቸው ማምታቻ የሚያደርጉት ርእስ እይተወራ እንዴት እናንቀላፋለን?  በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አብዛኞቻችን ኹጥባ ላይ ማንቀላፋት ልምድ አድርገነዋል። እንቅልፋችን ሲመጣ እንኳን ላለማንቀላፋት ትግል አናደርግም። ግን ለምን? ስብሰባዎች፣የአክሲዮን ውይይቶች፣ የዱንያዊ ትምህርቶች፣ ረጃጅም የቲቪ መስኮት ዜና እና ፊልሞች፣የሌሊት ኳሶች በተመስጦና በጋለ ወኔ እየተከታተልን የመስጅድ የ20፣የ30 ደቂቃ ኹጥባ ለማዳመጥ ለምን እንሰንፋለን? እናስተውል ወዳጆቼ ይህ ትልቅ ስንፍና፣ከስንፍናም በላይ አስነዋሪ ተግባር ነው። ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገር ቅድሚያ እንስጥ። ለዲናችነን ያለንን ትኩረት ከፍ እናድርግ።

27/4/1443

ቁጥር:15


https://t.me/amhakfelagijemaa/1270


https://t.me/amhakfelagijemaa
141 viewsحيدر مزمل, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 22:39:08 እኛ እና ፖለቲከኛ

https://t.me/Muhammedsirage
297 viewsحيدر مزمل, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ