Get Mystery Box with random crypto!

Tsegaye Demeke - Lawyer

የቴሌግራም ቻናል አርማ consultancy2012 — Tsegaye Demeke - Lawyer T
የቴሌግራም ቻናል አርማ consultancy2012 — Tsegaye Demeke - Lawyer
የሰርጥ አድራሻ: @consultancy2012
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.71K
የሰርጥ መግለጫ

Legal Service

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-11-02 18:50:31 5. የሽብር ወንጀል እና የሚያስከትለው ተጠያቂነት በኢትዮጵያ ህግ ስርዓት
በአገራችን በተለያየ ወቅት የሽብር ድርጊቶች የተፈፀሙ ሲሆን በ1970 ዎቹ ሲፈጸም የነበረው የቀይ ሽብርና የነጭ ሽብር ድርጊት በአገራችን በዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋትን ከፈጠሩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚመደብ ነዉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ 1990 ዎቹ በትግራይ ሆቴል፣ በአክሱም ሆቴል፣ በጊዎን ሆቴል እና በድሬ ደዋ በራስ ሆቴል እንዲሁም በ2000 ዓ.ም በታክሲ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በሀገራችን በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ የሽብር ወንጀልን መከላከል እና ለመቅጣት ጥረት የተደረገ ሲሆን ወንጀሉ ካለዉ አስከፊ ባህሪ በ2001ዓ.ም ራሱን የቻለ አዋጅ ቁጥር 652/2001 ሊወጣ ችሏል፡፡ ነገር ግን አዋጅ ቁጥር 652/2001 መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶችን የሚገድብ ሆኖ በመገኘቱ በአዋጅ ቁጥር 1176/2012 እንዲተካ ተደርጓል፡፡

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ 1176/2012 አንቀጽ 3 መሰረት የሽብር ድርጊት ማለት፡-
1) ማንኛውም ሰው የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የርዕዮተ ዓለም ዓላማን ለማራመድ በማሰብ ህዝብን ወይም የተወሰነ የህብረተሰብን ክፍል ለማሸበር ወይም መንግስትን፣ የውጭ አገር መንግስትን ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅትን ለማስገደድ፡- ሀ) በሰው አካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ ለ) የሰውን ሕይወት ለአደጋ ያጋለጠ፤ ሐ) ሰውን ያገተ ወይም የጠለፈ፤ መ) በንብረት፣ በተፈጥሮ ሐብት ወይም አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ ወይም ሠ) የሕዝብ ወይም ማህበራዊ አገልግሎት እንዳይሰጥ በከፍተኛ ሁኔታ ያስተጓጎለ እንደሆነ ከአስር ዓመት እስከ አስራ ስምንት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡

2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተጠቀሰውን አላማ ለማስፈጸም የተፈጸመው ተግባር ሰውን መግደል ወይም በታሪካዊ ወይም የባሕል ቅርስ ወይም የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ እንደሆነ ከአስራ አምስት ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም በሞት የሚያስቀጣ መሆኑን ደንግጓል፡፡

በአዋጁ ከአንቀጽ 3 ውጭ ያሉ የሽብር ወንጀሎች፡-
1. መዛት፡- በአዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 5 መሰረት ከላይ በአንቀፅ 3 ስር የተገለፀውን የሽብር ወንጀል ለመፈፀም መዛት ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ተግባር ተደርጎ ተደንግጓል፡፡ ዛቻ የፈጸመው ሰው አደርገዋለሁ ያለውን ድርጊት ለማድረግ ለመፈጸም ያለው አቅም፣ ዕድል ወይም በሌላ ሰው የሚያስደርግ ከሆነ ይህንን ለማድረግ አቅም ያለው መሆኑ ወይም በመዛቱ ምክንያት ህብረተሰቡ ወይም የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል የተሸበረ ወይም ሽብር ሊፈጥር የሚችል መሆኑን በመመዘን ነው፡፡
2. ማቀድና መሰናዳት- የሽብር ድርጊትን ለመፈጸም ማቀድና ማሰናዳት በራሱ የሚያስቀጣ ተግባር ሲሆን በሁለቱ መካከል ግልጽ ወሰን ማስቀመጥ ያስቸግራል፡፡ የአዋጅ ቁጥር 1176 አንቀጽ 6 በአዋጁ አንቀጽ 3 የተመለከተውን ድርጊት ለመፈጸም ማቀድና መሰናዳት የሚያስቀጣ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ድንጋጌው ለማቀድ ከሶስት እስከ ሰባት ዓመት እንዲሁም ለመሰናዳት ከአምስት እስከ አስራ ሁለት ዓመት የሚያስቀጣ ስለመሆኑ ያስቀምጣል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 6 ማቀድ ማለት በአዋጁ አንቀጽ 3 የተመለከተውን የሽብር ድርጊት ለመፈጸም ከሀሳብ ባለፈ ወንጀሉን ለመፈጸም የሚፈጸምበትን ሁኔታ፣ ቦታ፣ ጊዜ ወይም መሰል ጉዳዮችን የመለየት ወይም የመወሰን ጉዳይ እንደሆነ ትርጉም ያስቀምጣል፡፡ ኢትዮጵያ የፈረመችው የአፍሪካ ህብረት የሽብር መከላከልና መቆጣጠር ኮንቬንሽን ማቀድ የሚያስቀጣ ተግባር ሆኖ እንዲካተት የሚያስቀምጥ ከመሆኑ አንጻር ማቀድ በአዋጁ ውስጥ ተካቷል፡፡

3. ማደም ማለት ሁለትና ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች የወንጀል ድርጊት ለመፈጸም የተስማሙ እንደሆነ ስለመሆኑ ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 38 ይዘት ለመረዳት ይቻላል፡፡ በአዋጁ የሽብር ወንጀልን ለመፈጸም ማደም ከአምስት ዓመት እስከ አስራ ሁለት ዓመት ድረስ ሊያስቀጣ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ ማደም ከማቀድ እና መሰናዳት ለየት የሚያደርገው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሁለትና ከዛ በላይ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን እነዚህ ሰዎች ድርጊቱን ለመፈጸም የተስማሙ መሆኑን የሚጠይቅ ነው፡፡ ስምምነት መኖሩ በማስረጃ መረጋገጥ ያለበት ሲሆን በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ በሰዎቹ መካከል ስምምነት ለመኖሩ የሚያስረዳ ሁኔታ ካለ አድማ ስለመኖሩ ለማረጋገጥ በቂ ይሆናል፡፡

4. በሐሰት ማስፈራራት- በሽብር ድርጊት በሀሰት ማስፈራራት በቀላል እስራት ወይም ጉዳት ያስከተለ እንደሆነ ከሶስት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 8 ላይ ተደንግጓል፡፡ በሀሰት ማስፈራራት በሽብር ህግ ውስጥ እንዲካተት የተደረገበት ዋና ምክንያት ሰዎች በዘፈቀደ የሽብር ጥቃት እንደሚያደርሱ በመግለጽም ሆነ በማስመሰል ዜጎችን ለአደጋ እንዳያጋልጡ ማድረግ ነው፡፡
5. ድጋፍ ማድረግ፡- ወንጀሉን የሚፈፅም ሰው መርዳት ከሰባት እስከ አስራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ድርጊት ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 9 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የድጋፍ ዓይነቶችን ስንመለከት የሽብር ወንጀል አፈጻጸምን ለመርዳት በማሰብ ሰነድ ወይም መረጃ ማዘጋጀት፣ ማቅረብ፣ መስጠት፣ የምክር አገልግሎት፣ የሙያ ድጋፍ፣ ጉዳት ማድረስ የሚችሉ መሳሪያ፣ ኬሚካሎች ወይም ንጥረ-ነገሮች ያዘጋጀ፣ ያቀረበ የሰጠ ወይም የሸጠ ድጋፍ እንዳደረገ ይወሰዳል፡፡

6. ማነሳሳት፡- አንድ ሰው ሌላው ሰው የሽብር ድርጊት እንዲፈጽም ለማድረግ በመጎትጎት፣ ተስፋ በመስጠት፣ በገንዘብ፣ በስጦታ፣ በማስፈራራት ወይም በማናቸውም ሌላ መሰል ዘዴ ያነሳሳ እንደሆነ ለድርጊቱ በአንቀጽ 3 ላይ በተቀመጠው ቅጣት እንደሚቀጣ በአንቀጽ 10(1) ተደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌ ድጋፍ ከማድረግ የሚለየው ድርጊቱን የሚፈጽመው ሰው በራሱ ፍላጎት የሚፈጽመው ሳይሆን ማነሳሳት በፈጸመው ሰው ምክንያት ሲሆን ድጋፍ ማድረግ ደግሞ ወንጀል አድራጊው ሀሳብ ያለው ሆኖ ድጋፍ የሚያደርገው ሰው የድርጊቱ ፈጻሚ ሀሳቡን እንዲያሳካ ማመቻቸት ወይም አስተዋጽዎ ማበርከትን የሚመለከት ነው፡፡

በአጠቃላይ የሽብር ወንጀል ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል አስከፊነት ድርጊት ነው፡፡ ድርጊቱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሀገራችን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል፣ በመወሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይበልጥ ወንጀሉን ለመከላከልና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ እንዲሁም ወንጀሉ ተፈፅሞ ከተገኘ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በተለይ የህግ አስፈፃሚ የተቋማትና የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ወሳኝ ጉዳይ ነዉ፡፡ ህብረተሰቡም ወንጀልን በመከላከልና ወንጀል ፈጻሚዎችን ለህግ እንዲቀርቡ ከማድረግ አንፃር እገዛ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል፡፡
Ministry of Justice
7.0K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-02 18:50:31 የሽብር ወንጀልና የሚያስከትለው ተጠያቂነት

1. መግቢያ
የሽብር ድርጊት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኘ አንድ ወጥ ትርጉም የሌለው በመሆኑ በተለያዩ ሀገራት የድርጊቱ አረዳድ ላይ ልዩነት ይስተዋላል፡፡ በአንዱ አገር የሽብር ተግባር የሆነው ድርጊት በሌላው እንደ የነፃነት ትግል ሆኖ ይቆጠራል፤ በአንዱ የነፃነት ትግል ተደርጎ የሚታየው ተግባር በሌላው የሽብር ተግባር ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በዓለም ሰላም እና ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት ከሆኑ እና ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ከሚገኙ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ስለመሆኑ ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ወንጀሉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሀገራት በተናጠል እና በጋራ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሀገራችንም በተለያዩ ጊዜያት የወንጀሉ ሰለባ የነበረች ሲሆን ወንጀሉን ለመከላከል ህግ ማዕቀፍ ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዳለች፡፡ ከዚህ አንፃር የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ማውጣት አንዱ እርምጃ ሲሆን በአዋጁ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመቅረፍ አዋጁ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 ሆኖ ተሻሽሎ ወጥቷል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ስለ ሽብር ምንነት፣ የሚያስከትለዉ ጉዳት፣ ወንጀሉን ለመከላከል ያለዉ ዓለም ዐቀፍና ሀገር አቀፍ ህጎች እና የወንጀሉ የሚያስከትለው ተጠያቂነት ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

2. የሽብር ወንጀል ምንነት፣ የሚፈፀምበት ዓላማ እና የሚያስከትለው ጉዳት
ሽብር የሚለው ቃል የተሰጠ ወጥ ትርጉም ባይኖርም ከብዙ ሀገራት ህጎች መረዳት የሚቻለዉ አንድን ርዕዮት ዓለም፣ የፖለቲካ ወይም የሃይማኖት አስተሳሰብ በሕዝብ ወይም በመንግሥት ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ወይም ለማሳካት ኃይልን በመጠቀም በዜጎች ላይ ፍርሃትን በመፍጠር የማይፈልጉትን እንዲቀበሉ የማድረግ ተግባር ነዉ፡፡ ከዚህ የምንረዳው ከሌሎቹ ወንጀሎች በተለየ መልኩ የድርጊቱ ፈጻሚ ድርጊቱን ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በሌላቸው ንጹሃን ሰዎች፣ የመንግሥት ተቋማት፣ ባለሥልጣኖች፣ ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ወታደራዊ ተቋማት ወዘተ ላይ በመፈጸም ሌላኛው ወገን መንግሥትና ሕዝብ እንዲገደድና ሃሳቡን ወይም አስተሳሰቡን እንዲቀበል ለማድረግ የሚፈጸም ተግባር መሆኑን ነው፡፡ ሌሎች ወንጀሎች ግን የሚፈፀሙት ቀጥታ ግንኙነት ባለው አካል ላይ ነው፡፡
የሽብር ወንጀል መሠረታዊ ዓላማ ሲታይ ወንጀሉ የሚፈፀመው የፖለቲካ፤ የሐይማኖት ወይም የአይዲዮሎጂ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ ነው። ከዚህ አንፃር በሀገራችን ህግ መሰረት የሽብር ድርጊት ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የርዕዮተ ዓለም ዓላማን ለማራመድ በማሰብ ህዝብን ወይም የተወሰነ የህብረተሰብን ክፍል ለማሸበር ወይም መንግስትን፣ የውጭ አገር መንግስትን ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅትን ለማስገደድ በሚል በሰው ወይም በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ መሆኑ ተገልፆል፡፡ ይህም በአዋጅ ቁጥር 1176/2012 በአንቀፅ 3 ላይ እንደተገለጸው ለሁለት ዓላማ ማለትም የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የርዕዮተ ዓለም ዓላማን ለማራመድ በማሰብ እና ህዝብን ወይም የተወሰነ የህብረተሰብን ክፍል ለማሸበር ወይም መንግስትን፣ የውጭ አገር መንግስትን ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅትን የማስገደድ አላማ ነው።

የሽብር ወንጀል የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትል ሲሆን በአብዛኛዉ በንብረት ወይም አገልግሎት ጉዳት የሚያድርስ፣ የሰውን ህይወትን የሚያጠፋ፣ በታሪካዊ ወይም የባሕል ቅርስ ወይም የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ነው፡፡ እንዲሁም የህዝብ አገልግሎትን ያስተጓጉላል፡፡

3. የሽብር ወንጀል ታሪካዊ ዳራ
የሽብር ወንጀል ጽንሰ ሃሳቡ ሲታይ በአብዛኛዉ ቃሉ ሽብርተኝነት (terrorism) በሚለው ቃል ቢገለፅ ይታያል፡፡ ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በ18ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ አብዮት ወቅት (እ.ኤ.አ መስከረም 1793- ሐምሌ 1794) የተገኘ ቃል እንደሆነ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ወቅት የፈረንሳይ የአብዮታዊ አስተዳደሩ የአብዮቱ ጠላት ናቸው በሚል በሚጠረጠሩ ዜጎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዙን እና ንጉስ ናፖሊዮን የስፔንን መውረር ተከትሎ ሕዝባዊ አመጽ መቀስቀሱንና የሽምቅ ተዋጊዎች መስፋፋትን መሰረት በማድረግ ሽብርተኝነት የ18ኛው ክፍለ ዘመን ክስተት አድርገው ያስቀምጣሉ፡፡

ወንጀሉ በተለያዩ ሀገራት ቅርጽና ይዘቱን እየቀያየረ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ቁሳዊ፤ ማህበራዊ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ጉዳቶችን እያስከተለ እስካሁን የቀጠለ ጉዳይ ነዉ፡፡ በቅርቡ እንኳ እ.ኤ.አ ከ1990 ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦችን ከማሳለፍ ባለፈ፤ ሊብያ፣ ሱዳን እና አፍጋንስታንን ሽብረተኛን ይደግፋሉ በሚል የውሳኔ ሀሳብ በማስተላለፍ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሎባቸዋል፡፡

ሌላዉ በዓለም ላይ አስደንጋጭ ክስተት የነበረው የአሜሪክ መንትዮች ህንጻ ላይ ከተፈጸመበት ከ2001 ጀምሮ ያለው ጊዜን ይመለከታል፡፡ በ2001 ዓ.ም በአሜሪካው ላይ የተፈጸመው ጥቃት ዓለም አቀፍ ተቋማትም ሆኑ አገራት በሽብርተኝነት ላይ ያላቸውን አቋም እንዲፈትሹ ከማድረጉ ባለፈ ጠንካራ የህግ ማስፈጸም ስራ እንዲያከናውኑ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ ክስተት አገራት ድርጊቱን ለመቆጣጠር ቀድሞ የነበራቸውን አጠፋዊ ምላሽ ስትራቴጂ ወደ ቀድሞ መከላከል እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል፡፡ የጸጥታው ምክር ቤትም አልቃይዳን ትኩረት ያደረገ የሽብር መከላከል ትኩረትን በመተው ሁሉን አቀፍ የሽብር ወንጀል መካለከል ላይ እንዲያተኮር፣ ሽብር የዓለም አቀፍ ደህንነትና ሰላምና ደህንነት ስጋት እንደሆነ በመቀበል ሁሉም አባል አገራት ድርጊቱን ወንጀል በማድረግ እንዲደነግጉ እና የህግ ማስፈጸም ስርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ አቅጣጫ በማስቀመጡ በተለይ አባል ሀገራት ሽብር ህግ እንዲያወጡ አስገድዷቸዋል፡፡

4. ወንጀሉን ለመከላከል የሚያስችል አለም አቀፍ የህግ ማዕቀፍ
የሽብር ወንጀል በየትኛዉም ሀገርና ዜጎች ላይ ሊፈጸም የሚችል ወይም የሚፈጸም ዉስብስብንና አስከፊ ወንጀል ነው፡፡ ይህ ማለት የሽብር ወንጀል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች (Transnational Organized Crime) ከሚባሉት ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሽብር ድርጊትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተለያዩ ጊዜ የውሳኔ ሃሳብን አስተላልፏል፡፡ ድርጅቱ እራሱን የቻለ ሁሉን አቀፍ የሽብር ድርጊት መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ዓለም አቀፍ ስምምነት ከማውጣት ይልቅ በጉዳይ የተነጣጠለ የውሳኔ ሃሳብ ሲያስተላልፍና ስምምነቶች እንዲወጡ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህ ወጥ የሆነ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር በወንጀሉ ዙሪያ ያለው አረዳድ የተለያየ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ሀገራት የሽብር ድርጊትን ለመከላከልና ለመቅጣት ህግ ማውጣት እንዳለባቸዉ፣ ለአፈጻጸሙም ትብብር ሊኖር እንደሚገባ እና ልዩ ትኩረት የመስጠት ግዴታ እንደተጣለባቸው ያስረዳሉ፡፡
4.9K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-02 18:48:47 አዲሱን የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አተገባበር የሚያስተባብር ኮሚቴ በፍትሕ ሚኒስትሩ ተሰይሞ ሥራ ጀመረ
*******
የጥብቅና አገልግሎት ተጠቃሚዎች (ደንበኞች) እና የጠበቆችን መብት በተሻለ ሁኔታ ለማስከበር፣ የጥብቅና ሙያ አገልግሎት በአንድ አገር የፍትሕ ሥርዓት ዉስጥ ያለዉን የጎላ ሚና እና የሚያስፈልገዉን የሙያ ነጻነት ከግምት ዉስጥ በማስገባት እንዲሁም አገራችን የደረሰችበትን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖሊቲካዊ ዕድገት ታሳቢ ያደረገ የመንግስትና የባለሙያዉን ተዋፅኦ ያማከለ የጋራ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋትን ዓላማ ያደረገ አዲስ የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፀድቆ ከሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ሆኗል፡፡

በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ፈቃድ የተሰጣቸዉ ሁሉንም የፌዴራል ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በአባልነት ያቀፈ የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር የተቋቋመ ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት ደግሞ ማንኛዉም ፈቃድ የወሰደ ጠበቃና የጥብቅና ድርጅት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማህበሩ አባል እንደሚሆን ሕጉ በአስገዳጅ ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ማህበሩ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ሥራን በጋራ ለመምራት ይችል ዘንድ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት አመራሮቹን መምረጥና የተለያዩ አሰራሮችና አደረጃቶችን ቀርጾ ወደ ሥራ መግባት ይጠበቅበታል፣

ፍትሕ ሚኒስቴር አዋጁ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር 6 ወር ጊዜ ዉስጥ የመጀመሪያዉን የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የመጥራት እና ማህበሩ በአግባቡ ተደራጅቶ ሥራ እስከሚጀምር ድረስ ለመነሻ የሚሆን በጀት የመመደብ፣ ጽ/ቤት የማዘጋጀት እና በሰለጠነ የሰዉ ሃይል ማደረጀትን ጨምሮ የተለያዩ ግብዓቶችን የማሟላት እንዲሁም ማህበሩን ሥራ ለማስጀመር የሚያስችሉ የተለያዩ አደረጃጀቶችና ኮሚቴዎችን አቋቁሞ የሽግግር ሥራዉን የማሳለጥ ኃላፊነት ተሰጦታል፡፡

ስለሆነም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በሽግግር ወቅት ያለዉን የአዲሱን አዋጅ አፈጻጸም የሚከታተል ቀደም ሲል ሥራ ላይ ከነበሩ የተለያዩ የሕግ ባለሙያ አደረጃጀቶች የተወከሉ ጠበቆችን በዋናነት ያካተተ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም በፍትሕ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተሰይሞ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የመንግስት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ እና የአስተባባሪ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አለምአንተ አግደዉ እንደገለጹት ኮሚቴዉ የሽግግር ጊዜ ሥራዎችን የማስተባበር፣ በሂደቱ ዉስጥ የእያንዳንዱን ጠበቃ ተሳትፎ የማረጋገጥ፣ ለዚሁ ሥራ የሚሆን በጀትና ግብዓት የማሟላት ሥራዎችን በአጭር ጊዜ በማከናወን ማህበሩ ሥራዉን የሚጀምርበትን ሁኔታ የማመቻቸትና አዋጁ የወጣበትን ዓላማ ለማሳካት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ማህበሩ ኃላፊነቱን ተረክቦ ሥራ እስከሚጀምር ድረስ በአዲሱ የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር1249/2013 አንቀጽ 98(2)፣ አንቀጽ 98፣ አንቀጽ 100 እና አንቀጽ 101 መሠረት የፍትሕ ሚኒስቴር ቀደም ሲል የተዘረጉ አሰራሮችና አደረጃጀቶችን በመጠቀም ነገር ግን አዲሱን አዋጅ እና ከአዲሱ አዋጅ ጋር የማይቃረኑ በቀድሞዉ አዋጅ መሰረት የወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ሥራዉን ሲያከናዉን እንደሚቆይ ሚኒስትር ድኤታዉ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የአዲሱ አዋጅ ተግባራዊነት ለጥብቅና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ፣ ለጠበቆች ለራሳቸዉ እና አጠቃላይ ለፍትሕ ሥርዓቱ ዉጤታማነት ካለዉ ፋይዳ አንጻር እያንዳንዱ ጠበቃ በሽግግር ወቅት በሚከናወኑ ሥራዎችና ሁነቶች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ፤ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ እና አጋር አካላትም ተገቢዉን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ አቶ ዓለምአንተ አግደዉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
Ministry of Justice
4.2K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-27 15:16:17 ስለወጭና ስለኪሳራ /በክርክሩ ምክንያት የወጡ ወጪዎች የሚመለከተው ወገን/

#ስለ ፍርድ ቤቱ ሥልጣን
በሌላ አኳኋን እንዲፈጸም በግልጽ ካልተደነገገ በቀር በክስ ምክንያት ስለሚከፈለው ስለማናቸውም ወጭና ኪሳራ፣ የሚከፈለውን ወገን የወጭንና የኪሳራውን ልክ የሚከፈልበትን የሃብት ምንጭ የአከፋፈሉን ሁኔታ ሌላውንም ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ወይም ትእዛዝ ፍርድ ቤቱ ትክክል በስሎ በሚገመተው ሁኔታ ሊሰጥ ይችላል፡፡
#ስለወጭና ስለኪሳራ ዝርዝር
ተረቺው ለረቺው ኪሳራና ማናቸውንም ወጭ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ሲያዝ፣ ወጭ ያደረገው ወገን የወጭውን ልክ የሚያሳይ ዝርዝር አዘጋጀቶ ማቅረብ አለበት፡፡
ዝርዝር የሚቀርበው ፍርዱን ለፈረደው ፍርድ ቤት ሲሆን አንዱ ግልባጭ ለከፋዩ ወገን ይሰጣል፡፡
#የወጭው ሂሳብ ስለሚመረመርበት ሁኔታ
የወጭው ሂሳብ ዝርዝር ለፍርድ ቤቱ ከቀረበ በኋላ ትክክለኛነቱ የሚመለመርበትን ቀን ቀጠሮ ወስኖ ባለጉዳዮቹ እንዲቀርቡ ያዛል፡፡
ሂሳቡን መርምሮና ተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚያቀርቡትን ሃሳብ ተቀብሎ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ይፈጽማል፡፡
በቀረበው የሂሳብ ዝርዝር ውስጥ በቂ ባልሆነ ምክንያት ከፍ ብሎ የሚታየውን ገንዘብ ይቀንሳል፡፡ ወይም
በዝርዝሩ ውስጥ የክሱን ጉዳይ ለማስፈጽም ወይም አስፈላጊውን ዳኝነት ለመከታተል ተገቢ ያልሆነ ወጭ ተመልክቶበት የተገኘ እንደ ሆነ ፍርድ ቤቱ ሊቀንሰው ወይም ሊያስቀረው ይችላል፡፡
ወጭው ወይም ኪሳራው ሊከፍለው የሚገባው ወገን የሚጠይቀውን የወጭ ዝርዝር ያላቀረበ እንደ ሆነ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ መዝግቦ ሌሎች ወገኖች ያደረጉትን ወጭ መርምሮ ያረጋግጥላቸዋል፡፡ ወይም የሂሳቡን ዝርዝር አንዱ ወገን ባለማቅረቡ ምክንያት ሌሎች ወገኖች እንዳይጎዱ ላላቀረበው ወገን ተገቢ ግምት ያለው ኪሳር ይወስንለታል፡፡
ማንኛውም የወጭ ወይም የኪሳራ ገንዘብ በፍርዱ መሰረት እስኪፈጸም ድረስ ዋናው ፍርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሕግ የተወሰነ ወለድ ይታሰብበታል፡፡
ፍርድ ቤቱ በኪሳራና በወጭ አከፋፈል ምክንያት ለተነሳው ክርክር ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የፍርድ ቤቱ ሬዢስትራር ወይም የምግብ ቤቱ ሹም የቀረበውን ዝርዝር መርምሮና ተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚያቀርቡትን አሳብ ተቀብሎ የተጣራውን ሂሳብ እንዲያቀርብለት ከማዘዝ የዚህ ቁጥር ድንጋጌ አያግደውም፡፡
#ካሳ ስለሚከፈልበት ምክንያት
በማንኛውም ክስ ወይም ክርከር ላይ በክስ ወይም በመከላከያ መልክ ከሳሹ ወይም ተከሳሹ ያቀረበው የመከራከሪያ ወይም የመከላከያ ማስረጃ ወይም ክርክሩ ራሱ ወይም ማስረጃው አሰተኛ ነው ወይም መከራከሪያውንና አሰተኛ ማስረጃ ያቀረበው ወገን በሐሰት የተከራካሪውና አሰተኛ ማስረጃ ያቀረበው ክርክሩን ለማሰናከል፣ ጊዜ ለመፍጀት ወይም አንደኛውን ወገን ለመበደል ወይም ለማጉላላተር ሆነ ብሎ ያደረገው ነው በማለት ወይም የክርክሩንና የማስረጃውን አሰተኛነት እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ሆን ብሎ ማቅረቡን ሲያመለክትና ፍርድ ቤቱም ተቃዋሚው ወገን ያቀረበውን ነገር እርግጠኛነት ሲረዳው ይህንኑ በመዝገቡ ላይ አስፍሮ አሰተኛ ማስረጃ ወይም ክስ ወይም መከላከያ ያቀረበው ወገን ላቀረበው ለእያንዳንዱ ሀሰተኛ ማስረጃአንዱን ወገን ለመበደል፣ ለማጉላላት ወይም ጊዜ ለመፍጀት ላቀረበው አሰተኛ ክርክር ከማናቸውም ኪሳራና ከሌላው ወጭ በቀር ከ500 ብር የማይበልጥ ካሳ ለተበዳዩ እንዲከፈል ሊወስንበት ይችላል፡፡
#ይህም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በቁጥር 446 በተመለከተው መሰረት ሃሰተኛ ማስረጃና ክርክር በማቅረቡ ከመከሰስና ከመቀጣት ነፃ ሊሆን ይችላል፡፡
ካሳ የተወሰነለት ወገን በሀሰት በመከሰሱ ወይም ሃሰተኛ መከላከያ ወይም ክስ የቀረበበት በመሆኑ ካሳና ኪሳራ ይገባኛል ሲል ሌላ ክስ አቅርቦ ካሳ ወይም ኪሳራ የተወሰነለት እንደሆነ በመጀመሪያው ክስ ላይ ከሚወስንለት ኪሳራና ካሳ ላይ ይቀነስበታል፡፡
#ስለ ይግባኝ
ማንኛውም ተከራካሪ ወገን በስረ ነገሩ ላይ ይግባኝ ባያቀርብም፣ በተወሰነበት የወጭ ወይም የኪሳራ አከፋፈል ብይን ላይ ይግባኝ ለማለት ይችላል፡፡ በዚህም ነገር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
5.0K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-27 15:16:02 New Commercial Code
4.2K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-06 07:42:27 አዲሱ የፌዴራል የጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ አ/ቁ 1249
5.5K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-24 20:08:19 የምርጫ ሥርዓት፣ መርሆች እና ዓይነቶች
=========================
#የምርጫ ሥርዓት
በፌደራል ህገ መንግሥት መሠረት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚደረግ ምርጫ በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሚወዳደሩት ዕጩዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘው አሸናፊ ይሆናል። በክልል ህገ መንግሥታት መሠረት ለክልል ምክር ቤቶች የሚመረጡት ተወካዮች ከአንድ በላይ ሲሆኑ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል በቅደም ተከተል አብላጫ ድምጽ ያገኙ ዕጩዎች አሸናፊ ይሆናሉ፡፡
የክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫን የሚመለከቱ የክልል ህጎች በህገ መንግሥቱና በዚህ አዋጅ ከተቀመጡ ምርጫን የተመለከቱ ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣሙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
#የምርጫ መርሆዎች
ማንኛውም ምርጫ ሁሉን አቀፍ፣ ቀጥተኛ፣ በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ መራጩ ፈቃዱን በነፃነት የሚገልጽበት እና ያለ ምንም ልዩነት በሚደረግ ህዝባዊ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
የመምረጥ ወይም የመመረጥ መብቱ በህግ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተገደበ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መምረጥ ወይም መመረጥ ይችላል፣ ሆኖም ለመምረጥም ሆነ ለመመረጥ አይገደድም፡፡
እያንዳንዱ መራጭ የሚሰጠው ድምፅ እኩል ነው፡፡
እያንዳንዱ መራጭ ድምጽ መስጠት የሚችለው በአካል በመገኘት ነው፡፡
#የምርጫ ዓይነቶች
በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የምርጫ ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፣
1. ጠቅላላ ምርጫ፣
2. የአካባቢ ምርጫ፣
3. ማሟያ ምርጫ፣
4. ድጋሚ ምርጫ፣
5. ህዝበ ውሳኔ፡፡
1. #ጠቅላላ ምርጫ
ጠቅላላ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ የሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡
ጠቅላላ ምርጫ በመላ ሀገሪቱ በተመሳሳይ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ ሆኖም ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እና ጉዳዩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውሳኔ ሲያገኝ በተለያየ ጊዜ እንዲካሄድ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአንድ የምርጫ ክልል አንድ ተወካይ ብቻ ይመረጣል፡፡
የክልል ምክር ቤቶች አባላት ቁጥር በየክልሉ ህግ መሠረት የሚወሰን ሆኖ ከአንድ የምርጫ ክልል ከአንድ ተወካይ በላይ ለክልል ምክር ቤቶች አባልነት ሊመረጥ ይችላል፡፡ ክልሎች የምክር ቤቶቻቸውን አባላት ቁጥር ለመቀየር የሚሰጡት ውሳኔ ከእጩዎች የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ ስድስት ወር አስቀድሞ መሆን ይኖርበታል፡፡
በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 61(3) መሠረት አንድ የክልል ምክር ቤት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በቀጥታ በህዝብ እንዲመረጡ ሲወስን ምርጫው ከጠቅላላ ምርጫ ጋር አንድ ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ይህ ሲሆን የክልል ምክር ቤቱ ቀጣዩ ምርጫ ከመደረጉ ስድስት ወራት አስቀድሞ ውሳኔውን ለቦርዱ ማሳወቅ አለበት።
2. #የአካባቢ ምርጫ
የአካባቢ ምርጫ በህግ በተደነገገው መሠረት በየደረጃው የሚካሄድ የብሔረሰብ ዞን፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ ወይም የቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡
የአካባቢ ምርጫ ከአንድ ምርጫ ክልል በየደረጃው ለምክር ቤቶቹ የሚመረጡት ተወካዮች ቁጥር እያንዳንዱ ክልል በሚያወጣው ሕግ ይወሰናል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግሥት አንቀጽ 55 (2) (መ) እና አንቀጽ 51(15) መሠረት የአካባቢ ምርጫዎችን በተመለከተ ሁሉም ሊያደርጋቸው የሚገቡ መለኪያዎችን የሚያስቀምጥ ህግ ሊያወጣ ይችላል።
የአካባቢ ምርጫን የሚመለከቱ የክልል ህጎች በህገ መንግሥቱ እና በዚህ አዋጅ ከተቀመጡ ምርጫን የተመለከቱ ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣሙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህ አዋጅ ለጠቅላላ ምርጫ የተደነገገው እንደ አግባብነቱ በአካባቢ ምርጫ ላይም የሚፈጸም ሆኖ ቦርዱ በየደረጃው የምርጫ ክልሎች ወይም ጣቢያዎች አደረጃጀት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችና ታዛቢዎች አመዳደብ፣ የመራጭ እና የእጩዎችን ምዝገባ ቦታና ሂደት፣ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የድጋፍ ፊርማ ብዛት እና ሌሎች ጉዳዮችን ይህን አዋጅ መሠረት በማድረግ በሚያወጣው መመሪያ ይወስናል፡፡
3. #የማሟያ ምርጫ
የማሟያ ምርጫ የሚካሄደው:-
በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በተለያየ ምክንያት የተጓደሉባቸው አባላት እንዲሟሉላቸው ለቦርዱ ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ወይም
ተፈጻሚነት ባለው ህግ መሠረት የቀረበ የይውረድልን ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው፡፡
ቦርዱ ጥያቄው በደረሰው ስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማሟያ ምርጫ ያካሂዳል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) የተደነገገው ቢኖርም አንድ ምክር ቤት የሥራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ የቀረው ጊዜ ስድስት ወርና ከዚያ በታች ከሆነ የማሟያ ምርጫ አይካሄድም፡፡
4. #ድጋሚ ምርጫ
ድጋሚ ምርጫ ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ሊካሄድ ይችላል፣
በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና በዚህ አዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቦርዱ የምርጫ ውጤት እንዲሰረዝና ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ሲወስን ወይም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀረበለት አቤቱታ ላይ ተመስርቶ የምርጫ መደገም ውጤትን የሚያስከትል ውሳኔ ሲወስን፣
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 61(3) መሠረት እጩ ተወዳዳሪዎች እኩል ድምፅ በማግኘታቸው ምክንያት አሸናፊውን መለየት ያልተቻለ እንደሆነ፡፡
ድጋሚ ምርጫ ሲካሄድ:-
ሌላ አዲስ የመራጮች ምዝገባ ሳያስፈልግ በምርጫ ክልሉ ወይም ችግሩ በተከሰተባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ተመዝግበው በነበሩ መራጮች እንደገና ይካሄዳል፣
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) (ሀ) መሠረት ምርጫ እንዲካሄድ ሲወሰን አዲስ የእጩዎች ምዝገባ ሳያስፈልግ ቀድሞ በተመዘገቡ እጩዎች መካከል ብቻ ይደረጋል፣
ለድጋሚ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡
የድጋሚ ምርጫ ዝርዝር አፈፃፀም ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡
5. #ህዝበ ውሳኔ
ቦርዱ በህገ መንግሥቱ ወይም በሌሎች ህጎች መሠረት አግባብ ባለው አካል ሲወሰን የህዝብን ፍላጎት ለመለካት ወይም ለመወሰን ድምጽ እንዲሰጥ ህዝበ ውሳኔ የሚሰጥበትን ምርጫ ያዘጋጃል፡፡
ህዝበ ውሳኔው እንዲካሄድ ከወሰነው አካል ጋር በመመካከር ቦርዱ ህዝበ ውሳኔ ያስፈለገበትን ጉዳይ ለመለየት በሚያስችለው መልኩ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎችን በማደራጀት ህዝበ ውሳኔውን ያከናውናል፡፡
ቦርዱ በህገ መንግሥቱ ስልጣን ከተሰጠው አካል ጋር በመመካከር ድምጽ የሚሰጥበትን ቀን፥ በህዝበ ውሳኔው በድምጽ ሰጪነት ለመሳተፍ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች በድምጽ መስጫ ወረቀቱ ላይ የሚሠፍረው ለውሳኔ የቀረበው አማራጭ አጻጻፍ እና የህዝበ ውሳኔውን አስመልክተው የሚደረጉ የቅስቀሳ ዓይነቶችን ይዘት ይወስናል። ዝርዝር አፈፃፀሙ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 4-7 ድረስ ተደንግጓል።

#Join_our_telegram_channel
https://t.me/Consultancy2012
Call us for #Legal_Service
Tsegaye Demeke - Lawyer
7.2K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-24 20:07:38 ለ) የኣቀራረቡ ፎርም ሲታይ ደግሞ በቁ.130 (1) ወይም (2) መሰረት የሚቀርበው መቃወሚያም ሆነ ዓቃቤ ሕጉ ለመቃወሚያው የሚሰጠው መልስ ሁሉ በቃል መቅረብ እንዳለበት ከቁ.131 (1) መረዳት ይቻላል፡፡ ተደጋጋሚ ስልጠናዎች እየተሰጡ ኣሁን ኣሁን እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም በተግባር ሲሰራበት የነበረና ኣሁንም ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል ብሎ በኣስተማማኝ መናገር የማይቻለው፤ መቃወሚያ ለማቅረብ ጊዜ መስጠት ፣ መቃወሚያው በፅሑፍ ማቅረብ ፣ ዓ/ሕግ የመቃወሚያው ግልባጭ እንዲደርሰው ማድረግ ፣ ዓ/ሕግ በሚሰጠው ቀነ ቀጠሮ መልሱ በፅሑፍ ያቀርባል ፣ ተከሳሹ በበኩሉ የመልስ መልስ በፅሑፍ ለማቅረብ ጊዜ ይሰጠዋል ፣ በመጨረሻ ፍ/ቤቱ የተከሳሽ መቃወሚያና የዓ/ሕግ መልስ ከሕጉ ጋር ኣገናዝቦ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይሰጣል፤ ምናልባት ምርመራው ያላለቀ ከሆነ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት እንደተጠበቀ ሆኖ ፍ/ቤቱ ብይን ይሰጣል፡፡ ይህ የተንዛዛ ኣካሄድ ሕጉ ከሚያዘው ውጭ መሆኑን ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል፡፡

ሐ) ከመቃወሚያ ጋር ተያይዞ ሌላ መታየት ያለበት ነጥብ በመቃወሚያነት መቅረብ ያለበት በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ.130 ላይ ከተዘተዘሩት ምክንያቶች ሲገኝ ብቻ ነው ወይስ ከዚያ ውጭ የሆኑ ምክንያቶች ሲገኙም ማቅረብ ይፈቀደል የሚለው ነው፡፡ በዚህ ዙርያ ሁለት ኣስተሳሰቦች ይራመዳሉ፡፡ በአንድ በኩል በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ.130 ላይ ባይሸፈንም የክሱ መሰማት ሂደት እንዳይቀጥል የሚያደርጉ ሌሎቸ ምክንያቶች በተገኙ ጊዜም ተከሳሽ እንዲያነሳ ሊፈቀድለት ይገባል የሚሉ ኣሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ቁ.130 ሌላ የመቃወሚያ ነጥብ በማይጨምር ሁኔታ (exclusively) ዘርዝሮ ያስቀመጠ በመሆኑ ከዚያ ውጭ የሚቀር ተቃውሞ ተቀባይነት ሊያገኝ ኣይገባም የሚል ሓሳብ የሚያራምዱ አሉ ብቻ ሳይሆን ኣብዛኛው ጊዜ በተግባር የሚሰራበትም ይህ ኣቋም ነው ፡፡ እንደ የሞጁሉ ኣዘጋጅ እምነትም በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ. 130 ስር የማይሸፈን የተቃውሞ ነጥብ በሚነሳበት ጊዜ ተቀባይነት ሊያገኝ ኣይገባውም፤ ምክንያቱም በዛ ስር ያልተጠቀሰ ነጥብ በማያካትት እና በተሟላ ሁኔታ (exclusively and exhaustively) የተቀረፀ ነው፡፡

2. መቃወሚያውን ስለመመርመርና ስለመወሰን

በቁ. 13. (2) መሰረት የሚቀርበውን ማንኛውንም መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ በመዝገቡ ከፃፈ በላ ዓ/ሕጉ መልስ እንዳለው ይጠይቃል፡፡ የቀረበውን መቃወሚያ ሕግን በመጥቀስ ለመወሰን የሚቻል ከሆነ ወይም ዓ/ሕጉ መቃወሚያውን ካልተቃወመ ፍ/ቤቱ ወድያው ይወስናል (ቁ. 131 (1)) ፡፡ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማጣራት ማስረጃ መቅረቡ ኣስፈላጊ ሆኖ ካገኘውና ማስረጃ ሳይቀርብ ወድያው ውሳኔ (ብይን) መስጠት የማይቻል በሆነ ጊዜ ኣስፈላጊው ማስረጃ እንዲቀርብ ማዘዝ ይችላል (ቁ. 131 (3)) ፡፡ የተፈለገው ማስረጃ አስቀርቦ ከመረመረ በላ ፍ/ቤቱ ወዲያው ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ቁጥር 131 (4) ይደነግጋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በመቃወሚያው ላይ የሚሰጠው ውሳኔ /ብይን/ እንደየ መቃወሚያው ዓይነት ሊለያይ ይችላል፡፡ ይኸዉም፡-

ሀ) የቀረበው መቃወሚያ የሕግ ድጋፍ የሌለው ከሆነ ወይም በማስጃ ካልተደገፈ መቃወሚያውን ውድቅ ያደርጋል ፣
ለ) በቁ. 130/ 2/ለ/፣ /ሐ/፣ ወይም/ሰ/ መሰረት የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት ካገኘ ክሱን ዘግቶ ተከሳሹን ያሰናብታል ፣
ሐ) በቁ.130/2/ሀ/ መሰረት የቀረበ መቃወሚያ ከሆነ ጉዳዩ በተጀመረበት ፍ/ቤት እንዲቀጥል በማዘዝ መዝገቡን ይዘጋል ፣
መ) በቁ. 130(2) (መ) መሰረት የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት ካገኘ ክሱ ተነጥሎ እንዲታይ ያዝዛል ፣
ሠ) በቁ. 130 /2/ሠ/ የቀረበ መቃወሚያ ከሆነ ኣስፈላጊው ፈቃድ እስኪሰጥ መዝገቡን ለጊዜው ይዘጋዋል ፣
ረ) በቁ. 130/2/ረ/ የቀረበ ከሆነ ደግሞ ኣስቀድሞ መፈፀም ያለበት ስርዓት እስኪፈፀም መዝገቡን ለጊዜው ይዘጋዋል፡፡

ከዚህ በላይ በፊደል “ለ” የተጠቀሰውን እንዳለ ሆኖ ተከሳሹ ሙሉ በሙሉ ሃላፊ ባለመሆኑ ክሱ በተዘጋ ጊዜ የተከሳሹ ሁኔታ በፀጥታ ወይም በህዝብ ሰላማዊ ኑሮ ላይ ሁከት ወይም ኣደጋ የሚያደርስ መስሎ ከታየው ተከሳሹ ተገቢ በሆነ ስፍራ ወይም ሕክምና በሚያገኝበት ቦታ ተወስኖ እንዲቀመጥ ፍ/ቤቱ ያዝዛል ( የወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ. 208 እና የወ/ሕግ ዓንቀፅ 130 እስከ 132 ) ፡፡

#Join_our_telegram_channel
https://t.me/Consultancy2012
Call us for #Legal_Service
Tsegaye Demeke - Lawyer
5.3K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-24 20:07:38 በወንጀል ክርክር የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያ አቀራረብና በፍ/ቤቱ የሚሰጥ ብይን/ትእዛዝ
=========================
1. የመጀመርያ መቃወሚያ

ተከሳሹ ማንነቱ ካረጋገጠ በላ ፍ/ቤቱ ክሱን ለተከሳሹ ያነብለታል፡፡ ክሱ ግልፅ ስለመሆኑም ይጠይቀዋል፡፡ ተከሳሹ ክሱ ግልፅ መሆኑን ካረጋገጠ በላ የመጀመሪያ መቃወሚያ ካለው ይጠይቃዋል፡፡ የመጀመርያ መቃወሚያ ያለው መሆኑን ኣለመሆኑን ሳያረጋገጥ ፍ/ቤቱ የእምነት ክህደት ቃል ወደ መቀበል መሄድ የለበትም፡፡

በተከሳሹ ሊቀርብ የሚችል መቃወሚያ በሁለት መልኩ ሊታይ ይችልል፡፡ ኣንዳኛ በቁ.130 (1) እንደተመለከተው ተከሳሹ በክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም ይዘት ላይ የሚቀርብ መቃወሚያ ነው፡፡ይህ ዓይነቱ መቃወሚያ በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ.111 እና 112 የተዘረዘሩትን ነገሮች የሚመለከት ነው፡፡

(1) በቁ. 111 ላይ የተመለከቱት ነገሮች ስናይ፤ ማንኛውም የክስ ማመልከቻ፡-

ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበትና የተፈረመበት ፣
የተከሳሹ ስም የያዘ ፣
ተከሳሹ የተከሰሰበት እና የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር ያካተተ ፣
ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜና ስፍራ ያመላከተ ፣
የተበደለው ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት (ተገቢ በሆነ ጊዜ) የሚያመለክት፣
ተከሳሹ ወንጀሉን በመፈፀም ተላልፏል የተባለበት የሕግ ዓንቀፅ የያዘ መሆነ አለበት፡፡

(2) በቁ.112 የተመለከተው ደግሞ ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል ለይቶ ኣውቆ መልስ ለመስጠት እንዲችል እያንዳንዱ ክስ ወንጀሉንና ሆኔታውን በዝርዝር መግለፅ እንዳለበት ነው፡፡

ስለዚህ በቁ.111 ወይም 112 ላይ ከተመለከቱት ሁኔታዎች (ነገሮች) ኣንዳንዶቹ በክሱ ማመልከቻ ላይ ያልተካተቱ ሆኖው ያገኛቸው እንደሆነ ተከሳሹ በመቃወሚያ መልክ ሊያነሳቸው እንዲሚችል ነው፡፡

ሁለተኛውና በተግባርም በተደጋጋሚ ሲነሳ የሚስተዋለው መቃወሚያ በቁ.130 (2) ላይ የተደነገገውን ነው፡፡ በዚህ ንኡስ ዓንቀፅ ስር በመቃወሚያነት ሊነሱ የሚችሉ በርከት ያሉ ምክንያቶች ተዘርዝረው የሚገኙ ሲሆን፤ ኣብዛኛዎቹ የመቃወሚያ ነጥቦች በተከሳሹ ወይም በጠበቃው ብቻ ሊነሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ በቁ.130(2) (ሐ) መሰረት የይርጋ ጊዜን ኣስመልክቶ የሚቀርብ ተቃውሞ ግን ተከሳሹ ባያነሳወም ዓቃቤ ሕጉ ሊያነሳው ይችላላ ወይም ፍ/ቤቱ በራሱ ውሳኔ ክሱን መዝጋት ኣለበት (የወ/ሕግ ዓንቀፅ 216 (2)) ፍ/ቤቱ ሌላ ማድረግ ያለበት የተከሳሹ ፍፁም ወይም ከፊል ሃላፊነት ኣጠራጣሪ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ሁሉ ተከሳሹ ተቃውሞ ባያቀርብም ስለዚሁ ነገር ልዩ እውቀት ያለውን የአዋቂ ኣሳብ መጠየቅ ነው፡፡ ቢያስፈልግም በተከሳሹ ጠባይ ፣ ባለፈ ህይወት ታሪኩና በሁኔታዎቹ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ትዝዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

በተለይ ተከሳሹ የኣእምሮ በሽታ ያለበት ወይም በሚጥል በሽታ የሚታወክ ለመሆኑ፤ ወይም መስማትና መናገር የሚሳነው ለመሆኑ ወይም ኣእምሮን በሚያደነዝዝ ነገር ወይም በመጠጥ አዘዉታሪነት በሽታ የተለከፈ ለመሆኑ የሚያመለክቱ ሁኔታዎች በተገኙ ጊዜ ፍ/በቱ ለዚሁ ልዩ እውቀት ያለውን ሰው ኣሳብ የመጠቅ ግዴታ ኣለበት ፡፡
(የወ/ሕግ ዓንቀፅ 51)

በመቃወሚያነት መቅረብ የሚችል ምን እንደሆነና መቃወሚያው ማንሳት ያለበት ማን እንደሆነ ካየን ዘንድ የሚቀርብበት ጊዜ መቼ ነው? የኣቀራረቡ ፎርምስ ምን መሆን ኣለበት የሚለውን ማየት ኣስፈላጊነቱ ኣጠያያቂ ኣይደለም፡፡

ተከሳሹ መቃወሚያ ካለው ማቅረብ ያለበት ክሱ ከተነበበለት በላ መሆኑን ከላይ ተገልፆዋል፡፡ ክሱ ከተነበበለት በላ ብቻ ሳይሆን መቃወሚያ ካለው ወድያው ማቅረብ አለበት፡፡ ይህ ኣባባል ታሳቢ የሚያደርገው ተከሳሹ ክሱ ከሚሰማበት ቀን ኣስቀድሞ እንዲደርሰው ስለሚደረግ ኣንብቦ ሊነሳ የሚችል መቃወሚያ ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ይመጣል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ ክሱን ወዲያው ካልተቃወመ መቃወሚያውን በላ ማንሳት እንደማይችልም በመርህ ደረጃ በስነ ስርዓት ሕጉ ተደንግጓል (ቁ.130 (3)) ፡፡ ሆኖም ይህ ንኦስ ቁጥር መርህ ብቻ ሳይሆን የመርሁን ልዩ ሁኔታም ደንግጓል፡፡ ይኸዉም፤

“… ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወድያው ካልተቃወመ በቀር ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊያነሳ ኣይችልም፡፡ ስለሆነም መቃወም የሚችለው መቃወሚያው የሚፀና ፍርድ ከመስጠት የሚያግድ በሆነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡” የሚል ነው፡፡

እዚህ ላይ መነሳት የሚገባው ጥያቄ “የሚፀና ፍርድ ከመስጠት የሚያግድ” እና ዘግይተውም ቢሆን ሊቀርቡ የሚችሉ መቃወሚያዎች የተኞቹ ናቸው? የሚል ነው፡፡ ለዚህ ጥያቂ መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ሶስት ምሳሌዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡
ቁ.130 (2) (ለ) ተከሳሹ በዚሁ ክስ ከዚህ ቀደም ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ ወይም
ቁ.130 (2) (ሐ) ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ሕግ የታገደ ወይም ምሕረት ወይም የኣዋጅ ምሕረት (ይቅርታ) የተደረገለት መሆኑን ወይም
ቁ.130 (2) (ሰ) ለፈፀማቸው ተግባሮች ሃላፊ ያለመሆኑን ባመለከተ ጊዜ ነው፡፡

የመጀመሪያው ምሳሌ ብንመለከት በስነ ስርዓት ሕጉ ብቻ የተቀመጠ ሳይሆን በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ዓንቀፅ 23 ላይም “ማንኛዉም ሰው በወንጀል ሕግና ስነ ስርዓት መሰረት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሰኔ ጥፋተኛነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና ኣይከሰስም ወይም ኣይቀጣም” በሚል መልኩ ተገልፆ ይገኛል፡፡ በሁለተኛው ምሳሌ የተጠቀሰ ይቅርታን በተመለከተም ሕገ መንግስተዊ እውቅና ያገኘ ነው (ዓንቀፅ 71 (7)) ፡፡ እንዲሁም የይርጋ ጉዳይ በፍርድ ቤት ሳይቀር መነሳት ያለበት መቃወሚያ በመሆኑና ሃላፊ ያለመሆን ጥያቄም ኣስገዳጅ ድንጋጌ ሆኖ በወንጀል ሕግ የሰፈረ በመሆኑ ክሱ እንደተነበበ ወድያው ባይቀርቡም የሚፀና ፍርድ ከመስጠት የሚያግዱ በመሆናቸው በማንኛውም ጊዜ ሊነሱ የሚችሉ መቃወሚያዎች ናቸው፡፡

የሚፀና ፍርድ ከመስጠት የሚያግድ መቃወሚያ ሲገኝ ጊዜ ዘግይቶም ቢሆን ሊነሳ ይችላል ብሎ ሕጉ ሲያስቀምጥ ይህን ተከትሎ የሚነሳ ጥያቄ በስር ፍርድ ቤት ሳይነሳ ቀርቶ በይግባኝ ፍርድ ቤት ይግባኙ በሚታይበት ጊዜ ቢነሳስ ተቀባይነት ኣለው ወይ የሚል ይሆናል፡፡ እንግዲህ ይህ ልዩ ሁኔታ ከኣጠቃላይ የሕገ መንግስቱ መርሆዎችና ከቅጣት ዓላማ ኣንፃር መታየት ስላለበት በይግባኝ ፍርድ ቤት በሚሰማበት ወቅት የተነሳ መቃወሚያ ቢሆንም እንኳ ተቀባይነት ሊያገኝ ይገባል፡፡ የመዝገብ ቁጥሩ ማስታወስ ባልችልም በ1967 ዓ.ም አንድ ሰው የግድያ ወንጀል ፈፅሟል በሚል በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ማእከላዊ /ከፍተኛ/ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛ ሆኖ ስለተገኘ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ይፈረድበታል፡፡ ፍርዱን በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባይ ያቀረበ ሲሆን የጠ/ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎትም መዝገቡ ከመረመረ በላ ክሱ በይርጋ ጊዜ የታገደ ሆኖ ስላገኘው በዞኑ ፍ/ቤት የተሰጠን የጥፋተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ይግባይኝ ባይን በነፃ እንዲለቀቅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
4.1K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ