Get Mystery Box with random crypto!

ዩአንገሊዎን

የቴሌግራም ቻናል አርማ yoangeliwon — ዩአንገሊዎን
የቴሌግራም ቻናል አርማ yoangeliwon — ዩአንገሊዎን
የሰርጥ አድራሻ: @yoangeliwon
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

,እንኳን ደና መጡ ! ይህ የዩአንገሊዎን ቻናል የክርስቶስን ወንጌልና ዳግም ምጽአት እያስተማረ ወንጌል እየሰበከ ለእግዚአብሔር መንግስት ትውልድን የማብቃት ዓላማን ሰንቆ የያዘ በመሆኑ ወቅታቸውን በጠበቁ መልክትች በማስታጠቅ ለእግዝአብሔር ስራ የተዘጋጀ ቻናል ነው።
ዩአንገሊዎን አቤኔዘር ዳዊት

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-25 09:01:23 Watch "ABENEZER LEGESE-በቃ በለን BEKA BELEN [NEW-official music video-2022]" on YouTube


100 views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 16:17:00
ሚሽነሪ ዩኒቨርሲቲ #ሐዋሳ ካምፓስ በዲፕሎማ፣ በዲግሪ እና በማስተርስ ፕሮግራም እውቅና ባገኘባቸው በነገረ መለኮት፣ በክርስቲያን ሊደርሽፕ፣ በቤተክርስቲያን ተከላ እና በክርስቲያን ካውንስሊንግ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ በኦንላይን እና በርቀት እያስተማረ ይገኛል፡፡

በኦንላይን ለመማር ይመዝገቡ Register Online https://bit.ly/3y46rtB

#አድራሻ፦ ደቡብ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት አከባቢ ባለው ሪፍት ቫሊ ሚሽን ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን

ለበለጠ መረጃ @musupport

+251960848001 / 0468220581
Join our Telegram Channel

https://t.me/+Yw31B1PZTQIzZThk
101 views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 22:52:05 ድንቅ የሆነ መዝሙር ነው ተባረኩበት ዘማሪውን እግዚአብሔር ይባርከው ያብዛለት በረከታችን ነው

https://t.me/Yoangeliwon
202 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 07:36:55 Watch "ላንተ ከተባለ worship deep pray May 27, 2022" on YouTube





https://t.me/Yoangeliwon
268 views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 07:36:55




https://t.me/Yoangeliwon
199 views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 07:58:23 አስቸኮይ የጸሎት ጥሪ


በአፍጋኒስታን ነገ ከሰዓት በኋላ የሞት ፍርድ ለተፈረደባቸው 229 ክርስቲያን ሚስዮናውያን ጸልዩ ሊጎዱ ነው ብዙ ሰዎች መጸለይ እንዲችሉ እባክዎን ይህንን መልእክት በተቻለ ፍጥነት ያስተላልፉ። ይህ መልእክት የተላከው በጁዲት ካርሞና ሚስዮናዊው በአፍሪካ ከሚገኘው ከቺዋዋዋ ነው። መላው ፕላኔት በጸሎት አንድ ሆነ። እርስዎ ማስተላለፍ ከቻሉ እባክዎን በአፋጣኝ ጸሎት እኛን ይቀላቀሉ ፣ ምክንያቱም አክራሪ እስላማዊ ቡድኑ በኢራቅ ውስጥ ትልቁን የክርስቲያን ከተማ ኳራጎሽን ሰለተቆጣጠሩት አሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያን ወንዶች ፣ ሴቶች እና ልጆች ሊገደሉ ባሉበት ሰአት የጸሎት ሽፋን እየተጠየቀ ነው። እባክዎን አንድ ደቂቃ ወስደው ጸልዩላቸው። ለሚችሉት ሁሉ መልዕክቱን ያስተላልፉ። ኳራጎሽ ቀድሞውኑ ብዙ ጊዜ ተወስዷል። ፀሎት ጠይቀውናል እባክዎን ለሌሎች ያስተላልፉ።

https://t.me/Yoangeliwon
326 views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 04:55:35
በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት የአንድነት ጊዜ ላይ (DBUCESF) የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው በሚል ሀሳብ ከአገልጋይ አቤነዘር ዳዊት የቀረበ ድንቅ የሆነ መልዕክት ተባረኩበት

ወንጌል የልጅነታችን ውበት የወጣትነታችን ጉልበት የእርጅናችን ምርኩዝ ነው ።
https://t.me/Yoangeliwon
195 viewsedited  01:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 09:29:54 ክፍል ሁለት

ስለ ወንጌል invest እናድርግ።

1ኛ ቆሮንቶስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።
²⁵ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።


ወዳጆች የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን እንዲሆን ስለ ወንጌል invest እናድርግ ስለ ወንጌል እንሩጥ የክርስቲያን ሕይወት እና ኑሮ ወንጌልን ማዕከል ያደረገ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳችን ሲናገር 1ኛ ቆሮንቶስ 9²³ በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። ምን ማለት ነው እግዚአብሔር በወንጌል ውስጥ ባስቀመጠልና በጻሐፈልን መሠረት እንኖራለን ።።።ስለዚህ ሕይወታችን እና ኑሮችን በሙሉ ለክርስቶስ ወንጌል የሚገባ መሆን አለበት መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደተናገረው ማለት ነው ፊልጵስዩስ 1፥27 “ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ።”
ሕይወታችን በተመለከተ አገልግሎታችንን በተመለከተ ዘመናችንን በተመለከተ ሁሉ ስለ ወንጌል invest ማድረግ አለብን ስለ ወንጌል መሮጥ አለብን ። invest ስናደርግ ወይም ስለ ወንጌል ስንሮጥ እግዚአብሔር ባደለን ወንም እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ላይ መሆን አለበት ጊዜአችንን ፍቅራችን ጉልበታችን እድሜአችንን ዘመናችንን በሙሉ እግዚአብሔር ባደለን ወይም በሠጠን ነገር invest ማድረግ አለብን ለምን ካለን የወንጌል ማሕበርተኞች እንድንሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን ማድረግ ስለሚገባን ወዳጆች እግዚአብሔር በሕይወት ያልሠጠን ነገር ነገር የለም ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠን መልሰን መስጠት ሲከብደን እንዲሁም የግላችን ለማድረግ ስንሞክር ከስኬት እንጎላለን ከእግዚአብሔር ደስታ እንጓላለን ደስታ አልባ ስኬት አልባ እንሆናለን ።
ስኬት የሚባል ነገር በሕይወታችን ሊታይ አይችልም ከእግዚአብሔር ፍቃድ ውጪ የሚደረጉ የስኬት ጉዞ ላም በሌለበት ኩበት እንደመልቀም ያህል ነው። ስለዚህ እንድንኖጥ በተፈቀደልን መንገድ በመሮጥ የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ማድረግ አለብን ።በተፈቀደልን መንገድ እሮጠን እናገኛለን invest አድርገን እንደሰታለን ስለዚህ እግዚአብሔር ስለሁሉም ስራችን ይከፍለናል ።
“የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥25 እንደሚለሁ ቃሉ የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ማድረግ እንድንችል እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልን ።

https://t.me/Yoangeliwon
192 viewsedited  06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 09:29:54 “በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23

ክፍል አንድ

የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው።


እኛ ሁላችንም አሁን ባለንበት በዚህ ዘመን የወንጌል ጉዳ ጉዳያችን ነው ለማለት ድፍረት ይኖረን ይሁን? ቅዱሳን አባቶች ለወንጌል የከፈሉት ዋጋ ለወንጌል ያደረጉትን ትግል ተመልክተን የእኛን ዘመን ክርስቲያኖችን እያመዛዘንን ብናይ እውነት የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው ብለን ልንናገር ድፍረት እናገኝ ይሁን ? ቅዱሳን አባቶች ወንጌልን ሲሰብኩ የመጣባቸውን የመከራ ዶፍ ስቃይና እግልትት ለእምነታቸው የነበራቸው ቆራጥነት ኢየሱስን ለማሳየት እና ለሞተላቸው ለመኖር ያላቸው ፍላጎት ወንጌልን ለትውልድ ለማድረስ ያደረጉት ጥረት አስተውለን ይሁን?
በአገራችን በኢትዮጵያ የተሐድሶ ለውጥ ጥያቄ የፕሮስታንት አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ከምታውቃቸው ከ614 ዓመታት በፊት ተነስቶ እንደነበረ ያውም ሀገር ደም ተብላ መጠራት በነበረባት በጥንት ስሟ ኢባ ተብላ በምትጠረው በደብረብርሃን ከተማ በደም የታተመ ታሪክ እንዳለንስ እናውቅ ይሁንን?
ይህም የተሐድሶ ጥያቄዬ የወንጌል እውነትህ ያሸነፋቸው ስግደት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ መሆንና ድነት በእምንት በክርስቶስ ብቻ የሚገኝ ነጻ ስጦታ መሆኑ የተረዱ ደቂቀ እስቲፋኖሳዊያን ወይም ክርስቶሳዊን በአስራ አምስተኛው ምእት ዓመት በኢትዮጵያ በነበረችው ቤተክርስቲያን ወደ ቃሉ የመመለስ ጥያቄ በይበልጥ የተነሳበት ዘመን መኖሩን አሁን ያለን ሰዎች ይሄን ታሪክ እናውቃለን ወይ?
በኢትዮጵያ ነገስተ ነገስት ታሪክ መካከከል ዓፄ ዘረዓ ያዕቆብ ለእግዚአብሔር በሚመስል ቅናት የወንጌል አርበኞችን ዘግናኝ ጭካኔ ይፈፅም እንደነበረ የሚነገልለት ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለደቂቀ እስጢፋኖስና ለተከታዮቹ በተደጋጋሚ የሚያቀርብላቸው ጥያቄ ይሄን ይመስላል ነበር ።
መምራቹን ስደብ (ወንጌልን ያስተማራቸውን አባ እስጢፋኖስን ማለት ነው ) እንዲሁም ለእኔ ስገዱ የሚል ነበር እነርሱም በበኩላቸው ደማቸው እንደጎርፍ እየፈሰሰ ገላቸው እንደ ቋንጣ እየተተለተለ ደረታቸው በጦር ዓይናቸው በእሾህ እየተወጋ ንጉስ ፊት በቀረብ ቁጥር ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር አንሰግድም መምህራችንን አባ እስጢፋኖስን አንሰድብም በማለት የእግዚአብሔር ፍቅር ልባቸውን እንደሞላ ለስጋቸው ሳይሳሱ በእምነታቸው የንጉስን ጥያቄ ድል እንደነነሱ እንመለከታለን::
ታድያ እኛ ለራሳችን ምኞት በብዙ እየሰገድን በልባችን ያለውን የእግዚአብሔር ፍቅር ችላ እያልን የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው ለማለት አሁንም ድፍረት ይኖረን ይሁን? በእኛ ዘመን በነጻነትን ወንጌል ሰምተን በነጻነት እየኖርን የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ለመድረግ ለምን ከበደን?
የወንጌል ጉዳ ጉዳያቸው አድርገው በአገራችን በኢትዮጵያ ቅድሳን አባቶች ለትውልድ እውነተኛው ወንጌል እንዲደርስ የከፈሉትን መስዕዋትነት መምህር ብርክ ገበረ ሊባኖስ ተስፋዬ የሰው ያለህ በሚል መጽሐፍ ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ መጽሐፍ ለብቻ የለለቀሙትን የእስጢፋኖሳዋን ለወንጌል ያላቸውን ቆራጥነት ለእምነት ያላቸውን መሠጠት ያልደበረዘ ንፁ ወንጌል በመሥበካቸው ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ በማለታቸው የከፈሉትን ዋጋ ሲዘረዝሩ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አስቀምጠዋል


1.በእጆቻቸውና እግርቻቸው ያሉትን ጅማቶች በምላጭ እየተለተሉ ያወጡባቸው ነበር ይህም ብርታት እንዳያገኙ ሽባ ለማድረግ ነው።
2.ምላሳቸውን ይቆርጧቸው ነበር ይህም ተቀባይ ያገኘውን ትምህርታቸውን ማስተማር እንዳይችሉ ለማድረግ ነው።
3.አፍንጫቸውን እና ጆሮቸውን ይቋርጧቸው ነበር ይህም በሰው ዘንድ አስጠሊታዎች እንዲሆኑ ነው።
4.ቋንጃቸውን ይቋርጧቸው ነበር ይህም ከቦታ ወደ ባታ ተዘዋውረው ማስተማር እንዳይችሉ ለማድረግ ነው።
5.በጋለ ጉጠት ወስፌ ዓይናቸውን ያወጡባቸው ነበር ይህም ወንጌልን ሰምተው ተከታይ ለመሆን የሚመጡት ለማስደንገጥ ነው።
6.በጋለ ብረት ፊታቸውን ይተኩሷቸው ነበር ይህም ሰው በሩቅ አይቶ እንዲርቃቸው ነው ።
7.ቀኝ እና ግራ ጉንጫቸውን በምላጭ በመተልተል የተለያዩ ቅርጾችን ያወጡባቸው ነበር ይህም የነገስታቱ ባሪያዎች ናቸው ለማለት ነው።
8.የላይና የታች ከንፈራቸውን በመግፈፍ ጥርሳቸውን ባዶ ያስቀሩ ነበር ይህም በሰው ዘንድ መሳለቂያ ለማድረግ ነው።
9.ዒላማ በማድረግ በጦርና በቀስት ይወጎቸው ነበር ይህም የሚፈራ ካለ ለማስፈራራት ነው።
10.አንዳንድ ሴቶችን ጡታቸውን ይቆርጣቸው ነበር ኃፍረተ ሥጋቸው ውስጥ እሳት ይጨምሩባቸው ነበር ይህም ድርጊት ከእነርሱ በኃላ የእስጢፋኖሳዎን ትምህር ለሚከተሉት ለማስፈራራት የተደረገ ጭካኔ ነው።
11.የእጆቻቸውን የእግሮቻቸውን ጣቶች አንድ በአንድ እያሉ ይቄርጦቸው ነበር ይህም የሕመም ነርቦች በጣቶቻቸው ጣፍ በብዛት ስላሉ ስቃዩ ሲበዛባቸው አቋማቸውን ይቀይሩ ይሆናል ተብሎ ነው።
12.የሚገርማችሁ በእንደዚህ አይነት ስቃይ አልፈው ሲሞቱ እንኳን መቃብር በመከልከላቸው ለአራዊት ይሰጡቸው ነበር። በኢባ ሀገር ማለትም በደብረብርሃን ከተማ የቀሩትን ደቂቂ እስጢፋኖሳዎ ንጉሱ ሰብስቦ ከአንገት በታች ቀብሮ በራሳቸው ላይ ፈረስ ያስጋልብ ነበር ሰዎቹ ክርስትና ቀርቶ ሰበዓዊነትም አልነበራቸውም ቄሳር ከዚህ የሚበልጥ ግፍ ምን ሠራ ።
ንጉስ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ በእንደዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ደቂቀ እስጢፋኖሳዋን ጨፍጭፎ ከገደለ በኃላ በከተማዋ ላይ ታላቅ ብርሃን ሲበራ የከተማዋን ስም ደብረብርሃን በማለት ሰየመው መባል ያለበት ደብረብርሃን ወይስ ሀገር ደም
ይህን ለወንጌል የተከፈለውን መሥዋዕትነት ስናስብ አሁን በእኛ ዘመን ድረ ዘመናዊነት በተስፋፋበት እንዲሁም የነጻነት ኑሮን እየሮርን እውነትም የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው ለማተለት አሁንስ ድፍረት ይኖረን ይሁን ? ወንጌል ላልሰሙት ወንጌል ወንጌልን እንስበክ ስንባል የወንጌል ስራን የጥቂት ሰዎች አገልግሎት እንደሆነ እያሰብን የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ይሆናል ወይ መልሱ እኛው ጋር ይቆይ ።

https://t.me/Yoangeliwon
183 viewsedited  06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 16:08:51 Watch "#መፈለግ "Mefeleg" ድንቅ ትምህርት በአገልጋይ አቤኔዘር ዳዊት #Abenezer_Dawit" on YouTube





https://t.me/Yoangeliwon
191 viewsedited  13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ