Get Mystery Box with random crypto!

ማኅቶት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahetotorto — ማኅቶት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahetotorto — ማኅቶት
የሰርጥ አድራሻ: @mahetotorto
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.11K
የሰርጥ መግለጫ

ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች!
ልትጠቀሙበት የሚገባ ምርጥ ቻናል!
✔ማህቶት ብርሃን ነዉ!❤
✔መንፈሳዊ እዉቀትን እያገኙ❤
✔ስለሐይማኖቶ ማወቅ የፈለጉትን እየጠየቁ ❤
✔ጊዜዎን በፍሬ የሚቀይሩበት❤
✞ይቀላቀሉን✞
✋ሐሳብ አስታየት ማንኛዉም መንፈሳዊ ጥይቄ ካልዎት ታች በላዉ link ያድርሱን🙏
@Mahetotbot
Mahetot

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 10:36:58 #ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!!


@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
158 views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 00:21:47 «ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።"
1ኛ ዮሐ. 4 ፥ 20-21


የሰው ልጅ የተፈጠረበት አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ምሳሌነታቸው እንደምንድን ነው ቢሉ፦
# እሳት ፡- በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ይመሰላል። ለምን ቢሉ እሳት ፈቃድ ፈጻሚ ነው አንድ ቦታ ላይ ብንጭረው ሃገርን ሊያወድም ይችላል እግዚአብሔርም ሁሉን ማድረግ የሚችል ምንም ማይሳነው አምላክ መሆኑን።


# ውሃ ፡- በእግዚአብሔር ርህራሄ ይመሰላል። ውሃ እድፍን እንደሚያጠራ በኃጥያታችን ተጸጽተን ንስሐ ብንገባ ይቅር ሊለን፣ ከኃጢአታችን ሊያነጻን የታመነ መሆኑን።


# ንፋስ፡- በእግዚአብሔር ፈራጅነት ይመሰላል። ንፋስ ገለባውን ከስንዴ እንደሚለይ እግዚአብሔርም በዳግም ምጽዓት ጊዜ ኃጥኡን ከጻድቁ በእውነተኛው ፍርዱ የሚለይ መሆኑን።


# መሬት (# አፈር):- በእግዚአብሔር ታጋሽነት ይመሰላል። መሬት ጥቁር፣ ቀይ፣ ወፍራም፣ ቀጭን ፣ ኃጥእ፣ ጻድቅ ሳትል ሁሉንም ችላ ትኖራለች ፈጣሪም እንዲሁ በማንነታችን ሳይለየን የሚታገሰን መሆኑን።ነው እግዚአብሔር ለንስሐ ያብቃን ቃሉን ሰምተን 30-60-100 እንድናፍራ ያድርገን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
336 views21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 09:17:15 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን


    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ክፉ ሃሳብን እንዴት እናሸንፍ?
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

ክፉ ሀሳብ የሚባሉት ለምሳሌ የዝሙት ሀሳቦች፣ የሰውን መጥፎነት ማሰብ፣ ትንኮል እና ክፋትን ማሰብ፣ የቂምና በቀል ሀሳቦች፣ አሁን አሁን ደሞ የአብዛኛው ችግር እየሆነ የመጣው የሌሉ ነገሮችን እየፈጣጠሩ ዝምብሎ እያለሙ መደሰት (የቀን ቅዥት) ፣ የበዛ ሀዘን፣... ወዘት

በአእምሮአችን የሚመላለሱ ክፉ ሀሳቦች ወደ ድርጊት ሳይደርሱ በፊት ማቆም ይገባል፤ ምናልባት ከሀሳብም አልፈን በድርጊት ለምናከናውናቸው ኃጢአቶችም እታች ያሉትን መንገዶች መከተል መፍትሄዎች ናቸው።

ሰው ልተወው አልቻልኩም ይሄን ሀጥያት የሚለውን ሀጥያት በእነዚህ መንገድ መንገድ መተው ይችላል።

➊ ክፉ ሃሳብን በመልካም መተካት

ክፉ ሃሳብ ከኛ ዘንድ መጥተው እስኪያስጨንቁን እስኪያደክሙን መቆየት አይገባም አስቀድሞ ከእኛም ዘንድ እንዳይደርሱ እድል አለመስጠት ዋነኛ ማራቂያ መንገድ ነው፡፡

ይህውም በትርፍ ጊዜ ስራ ፈቶ እግር ዘርግቶ ከመቀመጥ ይልቅ መልካም በሆኑና ለነፍሳችን ሐሴት የሚሰጡ ነገሮችን በመስራት ማሳለፍ ያስፈልጋል፡፡

አእምሮን ዘወትር መልካም በሆኑ ተግባራት በሞላነው ቁጥር ጠላት ሰይጣን እኛን ለመጣል ሲመጣ አእምሮዋችን በመልካም ነገሮች ተይዞአልና ሊፈትነን አይቀርብም፡፡

ሰይጣን በከፉ ሃሳብ ሊጥለን ሲያደባ ክፍት ሆኖ ሲያገኘው የሰይጣንን ሃሳብ ለመቀበል የተመቸ ይሆናል፡፡

ክፉ ሃሳብ በአእምሮዋች ተፈጥሮም ከሆነ መልካም ነገሮችን በማሰብ መተካት ያስፈልጋል፤ አእምሮዋችን በአንድ ጊዜ ሁለት ነገሮች አእምሮዋችንበተመሳሳይ ተመስጦ (ጥልቀት) ሊያስብ አይችልም፡፡

ስለዚህም በክፉ ሃሳብ ፈንታ የምናስበው ሃሳብ ክፉውን ሃሳብ ለማጥፋት ይችል ዘንድ ጥልቅ ሊሆን ይገባዋል፡፡

ለምሳሌ

በስራ ሊጠምዱ የሚችሉ የሚያመራምሩ ጥያቄዎች የሃይማኖት ጥያቄዎችና ትምህርቶች የቀደሙ መልካም ገጠመኞችን በማሰብ መመሰጥ የመሳሰሉት ጠቃሚ መንገዶች ናቸው፡፡

➋ ማንበብ

አንድን ነገር በተመስጦ በምናነብት ጊዜ አእምሮዋችን በንባብ ይያዝና ክፉውን ሃሳብ ይረሳዋል፡፡

መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፣ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ ያላነበብናቸውን መጻህፍት ለምሳሌ፦ ልብወለድ የታሪክ መጻህፍት... ማንበብ ጠቃሚ ናቸው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንዶቻችን ሰነፎች ነን እና ለማንበብ ስብከቶችን፣ ትምህርቶችን ማዳመጥ።

➌ በጸሎትና በስግደት

እግዚአብሔርን ክፉ ሃሳብን እንዲያርቅልን በመማጸን በፊት በመንበርከክ ስግደትን በማቅረብ መማጸን ያስፈልጋል፡፡

ጌታ በወንጌል
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኀለሁ" ብሎናልና ችግራችንን በጸሎት በልመና መጠየቅ አለብን፡፡
ማቴ 11፥28

ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ
"በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ተብሏልና ሁሉ ወደ ሚቻለው ጌታ ጸሎት ምልጃን ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
ፊልጵ 4፥6

➍ በስራዎች በመጠመድ

በስራዎች መጠመድ የሰውን ትኩረት ወደ አንድ በመወሰን ሃሳቡ ወደ ሌላ እንዳይሄድ ያደርጋል፤ ምንም ሳይሰሩ ተዘልሎ መቀመጥ ግን በክፉ ሃሳብ ለመውደቅ ክፍት ይሆናል፡፡

ለዚህም ነው አበው "ሰው ስራ ሲሰራ አንድ ሰይጣን ይፈትነዋል፤ ሳይሰራ ተዘልሎ ሲቀመጥ ግን በብዙ ሰይጣናት ይፈተናል" የሚሉት፡፡

በገዳም ያሉ አባቶችም ስራን በመስራት ከኃጢአት ለመራቅ ይጠቀማሉ "ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል" የሚለውም ምሳሌያዊ አነጋገር የገደማውያ አበውን በስራ መጠመድ ህይወት ያሳያል፡፡

➎ ከሰው ጋር በማውራት

ክፉ ሃሳብ ባስጨነቁን ጊዜ ከወዳጆቻችን ጋር ስለ ልዩ ልዩ ጉዳዮች በማውራት ክፉውን ሃሳብ መርሳት ይቻላል፤ እያወሩ ማሰብ አይቻልምና፤ ራስን በማዝናናት በመጻፍ በማንበብ ክፉ ሃሳብን መርሳት ይቻላል፡፡

በሕይወታች የሚመጡብን ክፋ ሃሳቦች አምላከ ቅዱሳን ያርቅል፤ የእናቱ ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን

   ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                    ይቆየን 

@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
483 views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 09:59:09 ማኅቶት pinned «ምንተ ንነግረኪ ውስተ ልብነ ዘሀሎ እስመ አንቲ ተአምሪ ኀዘንነ ኩሎ (በልባችን ካለው ምኑን እንነግርሻለን አንቺው ኀዘናችንን ሁሉ ታውቂዋለሽ) ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋዋን ሽተው የጾሙት ጾም በኁዋላም ትንሣኤዋን ያዩበት ጾም ነው:: ዘንድሮ የምንጾመው ከብዙ ብሶትና ኀዘን ጋር ነው:: እመቤታችንን ሐዋርያት ሥጋዋን ይዘው ሊቀብሩ ባሉ ጊዜ አይሁድ የላኩት አንድ ታውፋንያን ነበር:: ዘንድሮ…»
06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 09:58:43 ምንተ ንነግረኪ ውስተ ልብነ ዘሀሎ
እስመ አንቲ ተአምሪ ኀዘንነ ኩሎ
(በልባችን ካለው ምኑን እንነግርሻለን
አንቺው ኀዘናችንን ሁሉ ታውቂዋለሽ)

ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋዋን ሽተው የጾሙት ጾም በኁዋላም ትንሣኤዋን ያዩበት ጾም ነው::
ዘንድሮ የምንጾመው ከብዙ ብሶትና ኀዘን ጋር ነው:: እመቤታችንን ሐዋርያት ሥጋዋን ይዘው ሊቀብሩ ባሉ ጊዜ አይሁድ የላኩት አንድ ታውፋንያን ነበር:: ዘንድሮ የሰማዕታት አስከሬን ላይ የሚሆነው ታውፋንያ ምን አደረገ የሚያስብል ሆነብን:: ወላዲተ አምላክ የልባችንን ኀዘን ለማን እንነግራለን? ከአንቺ በቀር ማን ያጽናናል?
ዘንድሮ ፍልሰታን ከሞቀ ቤታቸው ፈልሰው በደጅ ፈስሰው
በዚህ አጥንት የሚሰብር ብርድ ከደጅ የሚያድሩ ሱባኤያተኞችሽን ተመልከቺ:: በልጅሽ ያመኑ ባለማተቦችሽን እመብርሃን ሆይ ተመልከቺ::
ከአንቺ በቀር የልባችን ኀዘን ለማን እንነግራለን?
ሱባኤያችንን የኢትዮጵያ ሰላም የቤተ ክርስቲያን ዕረፍት የኃጢአታችን ሥርየት ሱባኤ አድርጊልን::
በጾመ ፍልሰታ ንስሓ እንግባ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበል::
379 views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 21:36:24 እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 23 2013 ዓ ም
Translated from Mighty arrows publications

@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
461 viewsedited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 22:03:11 Watch "#ዲ/ን_ሄኖክ_ሐይሌ_ተሞሸረ_wedding_ceremony dn_henok_haile!" on YouTube


446 views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 09:54:11 Watch "#በእዩ_ጩፋ_የታለሉ_ሰዎች_አጋለጡ_666_የአዉሬ_ዉመንፈስ! #ድብቁ_ሴራ_ይፋ_ሲወጣ" on YouTube


841 views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 22:27:58 Watch "አረብ እንዲህ ነዉ " on YouTube


1.1K views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 11:00:57 እስኪ አስቡት በሆሳዕና ዕለት ክርስቶስ የተቀመጠባት አህያ ዘንባባ ሲነጠፍለት የሰዎች ልብስ ፤ ሲዘረጋላት ያማረዉ ሲጎዘጎዝላት... በሌላኛዉ ቀን እራሷ አህያ ብቻዋን ብትመጣ በሽመል መደብደቧ አይቀርም ምክንያቱም ብቻዋን ናታ ...#ክብር_ከክርስቶስ_ጋር_ሲኮን_ነዉ!
1.1K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ