Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን     ✥••┈┈┈ | ማኅቶት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን


    ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ክፉ ሃሳብን እንዴት እናሸንፍ?
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

ክፉ ሀሳብ የሚባሉት ለምሳሌ የዝሙት ሀሳቦች፣ የሰውን መጥፎነት ማሰብ፣ ትንኮል እና ክፋትን ማሰብ፣ የቂምና በቀል ሀሳቦች፣ አሁን አሁን ደሞ የአብዛኛው ችግር እየሆነ የመጣው የሌሉ ነገሮችን እየፈጣጠሩ ዝምብሎ እያለሙ መደሰት (የቀን ቅዥት) ፣ የበዛ ሀዘን፣... ወዘት

በአእምሮአችን የሚመላለሱ ክፉ ሀሳቦች ወደ ድርጊት ሳይደርሱ በፊት ማቆም ይገባል፤ ምናልባት ከሀሳብም አልፈን በድርጊት ለምናከናውናቸው ኃጢአቶችም እታች ያሉትን መንገዶች መከተል መፍትሄዎች ናቸው።

ሰው ልተወው አልቻልኩም ይሄን ሀጥያት የሚለውን ሀጥያት በእነዚህ መንገድ መንገድ መተው ይችላል።

➊ ክፉ ሃሳብን በመልካም መተካት

ክፉ ሃሳብ ከኛ ዘንድ መጥተው እስኪያስጨንቁን እስኪያደክሙን መቆየት አይገባም አስቀድሞ ከእኛም ዘንድ እንዳይደርሱ እድል አለመስጠት ዋነኛ ማራቂያ መንገድ ነው፡፡

ይህውም በትርፍ ጊዜ ስራ ፈቶ እግር ዘርግቶ ከመቀመጥ ይልቅ መልካም በሆኑና ለነፍሳችን ሐሴት የሚሰጡ ነገሮችን በመስራት ማሳለፍ ያስፈልጋል፡፡

አእምሮን ዘወትር መልካም በሆኑ ተግባራት በሞላነው ቁጥር ጠላት ሰይጣን እኛን ለመጣል ሲመጣ አእምሮዋችን በመልካም ነገሮች ተይዞአልና ሊፈትነን አይቀርብም፡፡

ሰይጣን በከፉ ሃሳብ ሊጥለን ሲያደባ ክፍት ሆኖ ሲያገኘው የሰይጣንን ሃሳብ ለመቀበል የተመቸ ይሆናል፡፡

ክፉ ሃሳብ በአእምሮዋች ተፈጥሮም ከሆነ መልካም ነገሮችን በማሰብ መተካት ያስፈልጋል፤ አእምሮዋችን በአንድ ጊዜ ሁለት ነገሮች አእምሮዋችንበተመሳሳይ ተመስጦ (ጥልቀት) ሊያስብ አይችልም፡፡

ስለዚህም በክፉ ሃሳብ ፈንታ የምናስበው ሃሳብ ክፉውን ሃሳብ ለማጥፋት ይችል ዘንድ ጥልቅ ሊሆን ይገባዋል፡፡

ለምሳሌ

በስራ ሊጠምዱ የሚችሉ የሚያመራምሩ ጥያቄዎች የሃይማኖት ጥያቄዎችና ትምህርቶች የቀደሙ መልካም ገጠመኞችን በማሰብ መመሰጥ የመሳሰሉት ጠቃሚ መንገዶች ናቸው፡፡

➋ ማንበብ

አንድን ነገር በተመስጦ በምናነብት ጊዜ አእምሮዋችን በንባብ ይያዝና ክፉውን ሃሳብ ይረሳዋል፡፡

መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፣ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ ያላነበብናቸውን መጻህፍት ለምሳሌ፦ ልብወለድ የታሪክ መጻህፍት... ማንበብ ጠቃሚ ናቸው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንዶቻችን ሰነፎች ነን እና ለማንበብ ስብከቶችን፣ ትምህርቶችን ማዳመጥ።

➌ በጸሎትና በስግደት

እግዚአብሔርን ክፉ ሃሳብን እንዲያርቅልን በመማጸን በፊት በመንበርከክ ስግደትን በማቅረብ መማጸን ያስፈልጋል፡፡

ጌታ በወንጌል
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኀለሁ" ብሎናልና ችግራችንን በጸሎት በልመና መጠየቅ አለብን፡፡
ማቴ 11፥28

ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ
"በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ተብሏልና ሁሉ ወደ ሚቻለው ጌታ ጸሎት ምልጃን ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
ፊልጵ 4፥6

➍ በስራዎች በመጠመድ

በስራዎች መጠመድ የሰውን ትኩረት ወደ አንድ በመወሰን ሃሳቡ ወደ ሌላ እንዳይሄድ ያደርጋል፤ ምንም ሳይሰሩ ተዘልሎ መቀመጥ ግን በክፉ ሃሳብ ለመውደቅ ክፍት ይሆናል፡፡

ለዚህም ነው አበው "ሰው ስራ ሲሰራ አንድ ሰይጣን ይፈትነዋል፤ ሳይሰራ ተዘልሎ ሲቀመጥ ግን በብዙ ሰይጣናት ይፈተናል" የሚሉት፡፡

በገዳም ያሉ አባቶችም ስራን በመስራት ከኃጢአት ለመራቅ ይጠቀማሉ "ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል" የሚለውም ምሳሌያዊ አነጋገር የገደማውያ አበውን በስራ መጠመድ ህይወት ያሳያል፡፡

➎ ከሰው ጋር በማውራት

ክፉ ሃሳብ ባስጨነቁን ጊዜ ከወዳጆቻችን ጋር ስለ ልዩ ልዩ ጉዳዮች በማውራት ክፉውን ሃሳብ መርሳት ይቻላል፤ እያወሩ ማሰብ አይቻልምና፤ ራስን በማዝናናት በመጻፍ በማንበብ ክፉ ሃሳብን መርሳት ይቻላል፡፡

በሕይወታች የሚመጡብን ክፋ ሃሳቦች አምላከ ቅዱሳን ያርቅል፤ የእናቱ ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን

   ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                    ይቆየን 

@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto