Get Mystery Box with random crypto!

Bank of Abyssinia

የሰርጥ አድራሻ: @boaeth
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 161.28K
የሰርጥ መግለጫ

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 29

2022-10-12 15:02:04
ከ 1200 በላይ በሆኑ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ የሚገኙት የአቢሲንያ POS ማሽኖች ሁሉንም የአገር ውስጥ ATM ካርዶችን እንዲሁም ንክኪየለሽ (Contactless) ካርዶችን የሚቀበሉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቪዛ እና ማስተር ካርድ ያሉትን አለም አቀፍ ካርዶችን በመጠቀም ክፍያዎን መፈፀም ይችላሉ።

#BankofAbyssinia #Banking #POSMachines #VisaCard #MasterCard #ContactlessCards #DigitalBanking #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
3.4K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 14:37:15
Bank of Abyssinia is taking part as a strategic sponsor of the 3rd National Cyber Security Month to be held at the Ethiopian Skylight hotel from October 11, 2022 to October 12, 2022. The event was warmly inaugurated today in the presence of H.E. Deputy Prime Minister Demeke Mekonnen and other high government officials.
Visit us and learn more about the latest bank technology in the industry.

#banks #bankofabyssinia #cyber #CyberSecurity #banksinethiopia #ethiopia #tech
13.7K views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 19:00:50
እንኳን ለነብዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) አደረሳችሁ
በዓሉ የደስታ እና የሰላም ይሁንልን!

#BankofAbyssina #Banking #BankingService #Holiday #Mawlid2022 #Malwlid #IslamicHolidays #AddisAbaba #Ethiopia
1 view16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 15:13:21
የተቀዳሚ ደንበኞች ፤ የ”እንሸልምዎ”፤ ”መቆጠብ ያሸልማል” ፤ እንዲሁም የ”አበባ -አየሽ ወይ”የሽልማት እና ዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ፡፡
ሐሙስ መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ፤ ሸራተን አዲስ በላሊበላ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ዝግጅት ፤ ከተለያየ ዘርፍ የተመረጡ የባንካችን ተቀዳሚ ደንበኞች የዕውቅና ሰርተፍኬት፣ የዋንጫ እንዲሁም የቅድሚያ ሰርቪስ የሚያገኙበት ፕላቲንየም ኮርፖሬት ካርድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የ”እንሸልምዎ”እና ”መቆጠብ ያሸልማል” የሽልማት ክዋኔ የእለቱ ሁለተኛ ዐብይ ዝግጅት ነበር፡፡ በ”መቆጠብ ያሸልማል” የሽልማት መርሐ-ግብር ፤ ባለሁለት መኝታ አፓርታማ ቤትን ጨምሮ 147 ሽልማቶች ለዕድለኞች የተላለፉ ሲሆን፤ የ”እንሸልምዎ”የሽልማት መርሐ-ግብር ደግሞ የቤት አውቶሞቢልን ጨምሮ 42 ሽልማቶችን የተካተቱበት ነበር ፡፡ በዝግጅቱም ላይ በቁጥር 16 የሚደርሱ ዕድለኞች በመድረኩ በመገኘት ሽልማቶቻቸውን ከባንካችን የበላይ አመራር እጅ ተቀብለዋል፡፡
የዕለቱ ሶስተኛው አብይ ዝግጅት በባንካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳው የ”አበባ -አየሽ ወይ”የሽልማት ውድድር አሸናፊዎችን መሸለም ሲሆን ፣ በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ አሸናፊዎች በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ ተገኝተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡
12.3K views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 11:47:25 Bank of Abyssinia (BOA) - Ethiopia’s leading bank partnered with Xpert Digital for the implementation of Temenos Infinity to deliver a digital business banking solution. Read more: https://www.bankofabyssinia.com/boa-temenos-xd/
17.1K viewsedited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 11:41:58
አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!!
ባንካችን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ላይ ከብር 10 ሺህ እስከ 100 ሺህ የገንዘብ ሽልማቶች የተዘጋጀበት “አበባ አየሽ ወይ” ባሕላዊ ጨዋታ ውድድር ማካሄዱ ይታወቃል፡፡
በውድድሩ በርካታ ቡድኖች ከተለያዩ ክልሎች የተሳተፉ ሲሆን፣ የውድድር መስፈርቱን ያሟሉ ወደ 300 የሚጠጉ የቪዲዮ ሥራዎች ለባለሙያዎች ግምገማ ብቁ ሁነው ዳኞች አስቀድመው በአስቀመጡት መሥፈርቶች 15 ሥራዎች ተገምግመው ተመርጠዋል። ይኽንን ተከትሎ፤ በዳኞች ተገምግመው የተመረጡት 15 ሥራዎች ለተመልካች ቀርበው በአጠቃላይ 3655 የህዝብ ድምፅ ተሰጥቶባቸዋል። በመጨረሻም በሕዝብ ድምጽ እንዲሁም በዳኞች ድምጽ ድምር ውጤት የተመረጡት የመጨረሻዎቹ አስር (10) አሸናፊዎች ተለይተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በቅደም ተከተል ከ 1ኛ እስከ 10ኛ የወጡት ተወዳዳሪዎች በተሰጣቸው ኮድ መሠረት ተለይተው ታውቀዋል።

በውድድሩ ላይ በመሳተፍና አስተያየት በመስጠት ያገዛችሁን የባንካችን ቤተሰቦች በሙሉ እጅግ አድርገን እናመሰግናችኋለን፡፡ባንካችን አቢሲንያ መሰል ውድድሮችን በተሻለ ዝግጅት ወደፊት ስለምናቀርብ ተሳትፏችሁ እንዲቀጥል መልዕክታችንን በዚሁ አጋጣሚ እናስተላልፋለን!

አሸናፊዎች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!
13.5K viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 16:06:00
አቢሲንያ ባንክ ለወለድ-ነጻ የባንክ አገልግሎት (IFB) በLegal Advisor እና Financing Administration ፣ ለሕግ ክፍል በLegal advisor እና Senior Legal Advisor የሥራ መደቦች እንዲሁም በጊዜያዊነት በቀን ሰራተኛ (Laborer) የሥራ መደብ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

ለሥራ መደቡ የሚያስፈልገውን መስፈርት፣ የሥራ ልምድ እና የመሳሰሉትን ዝርዝር መረጃዎች ለማግኘት በባንኩ ድረገፅ https://vacancy.bankofabyssinia.com በመግባት ማግኘትና መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
15.3K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 13:09:37
ድምፅ ለመሥጠት ከታች የተቀመጡትን የፌስቡክ መሥፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ:
https://fb.watch/fV728DY8Bz/
https://fb.watch/fV6V0iVcY_/
https://fb.watch/fV70ws63V4/
10.8K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 12:26:17 የ"አበባየሽ ወይ" ውድድር ድምፅ አሰጣጥ ለተጨማሪ ሰዓታት ተራዘመ!
በርካታ የባንካችን ቤተሰቦች በማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን በተለይ በፌስቡክ ገፃችን ላይ የድምፅ መስጫ ጊዜው እንዲራዘም ጠይቀዋል።
ይኽንን ጥያቄ መነሻ አድርገን በተጨማሪም በበዓላት መደራረብ፣ በኔትወርክ እክል እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያቶች መምረጥ ያልቻሉትን ታሳቢ በማድረግ፤ የድምፅ መስጫ ጊዜውን እስከ ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ጧት 2:00 ሰዓት ድረስ ያራዘምን መሆኑን በደስታ እናበስራለን።
በቀረው ጊዜ ማሸነፍ ይገባቸዋል ብለው ላመኑባቸው ቡድኖች ድምፅዎን በመስጠት እንዲያሸንፉ ያግዟቸው!
መልካም ዕድል!
12.6K viewsedited  09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 14:56:40 ዓመታዊው “Dine-and-Learn with your CEO” መርሃ ግብር በተለያዩ ኩነቶች ታጅቦ በከፍተኛ ድምቀት ተካሄደ።
//
ባንካችን አቢሲንያ፣ በአዲስ ዓመት መባቻ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ለሁለተኛ ጊዜ “Dine-and-Learn with your CEO” ዓመታዊ መርሃ-ግብር እጅግ በደመቀ ሁኔታ አካሄደ።
በዝግጅቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዲስትሪክት የስራ ኃላፊዎች፣ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የቅርንጫፍ ሥራ-አስኪያጆች፤ የተሸላሚ ቤተሰቦች፤ እንዲሁም በፕሮግራሙ ላይ የማነቃቂያ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት ዶ/ር ወዳጄነህ መሃርነን ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
በዝግጅቱ እና በአይነቱ ረገድ በደመቀው በዚህ መድረክ፤ በ2021/22 የበጀት ዓመት በአፈፃፀም ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡት 56 ቅርንጫፎች የዕውቅና ምስክር ወረቀት የመስጠት ስነ-ስርአት ተከናዉኗል።
በተለይም በአፈጻጸማቸዉ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 26 ቅርንጫፎች እና ከ1-3ኛ ለወጡ ዲስትሪክቶች፤ እንዲሁም በልዩ ሁኔታ የደሴ ዲስትሪክትን ጨምሮ ለ8 ቀናት የውጭ ሃገር ስልጠና ዕድል ተመቻችቶላቸዋል።
የባንካችን አቢሲንያ መገለጫ እየሆነ በመጣው “Dine-and-Learn with your CEO” ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባንካችን ዋና ሥራ-አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ’’Strategy Workshop’’ በሚል ርዕስ ያላቸዉን ጥልቅ እዉቀትና ተሞክሮ ከባንካችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ጋር አያይዘዉ ለታዳሚዎች በስፋት አካፍለዋል።
በሌላ በኩል የእለቱ የማነቃቂያ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ወዳጄነህ ማህርነ፣ አቢሲንያ ባንክ በከፍተኛ እድገት ላይ ያለ ባንክ መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸዉን የጀመሩ ሲሆን አክለዉም የህይወት መርሆች ወይም principles of life በሚል መሪ ቃል እዉቀታቸዉን ለመድረኩ አካፍለዋል።
ለአንድ ቀን በተካሄደው በዚህ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ በርካታ የተሸላሚ ቤተሰቦች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ሁሉም ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ሙሉ ወጪያቸውን ባንካችን አቢሲንያ በመሸፈን ቆይታ አድርገዋል።
በአጠቃላይ የፕሮግራሙን ይዘት በተመለከተ ሁሉም ተሳታፊዎች ደስተኛ የነበሩ ሲሆን በተለይም የተወዳዳሪነት መንፈስ በመፍጠር ረገድ ለባንካችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለዉ መሆኑን አጽኖት በመስጠት ወደፊት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሠራተኞች እና የትዳር አጋሮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ፕሮግራሙ ያማረና የደመቀ ይሆን ዘንድ አስተዋጽኦ ላደረጉ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና የስራ ክፍሎች ምስጋና በመቸር እንዲሁም መልካም አዲስ ዓመት ይሆን ዘንድ በመመኘት አመታዊዉ የደመቀዉ መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!


12.3K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ