Get Mystery Box with random crypto!

Bank of Abyssinia

የሰርጥ አድራሻ: @boaeth
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 161.28K
የሰርጥ መግለጫ

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-09-29 12:03:44
አቢሲንያ ባንክ ለባህር ዳር፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ሐዋሳ እና ጅማ ዲስትሪክቶች በተለማማጅ ባንከኛ የሥራ መደብ ላወጣው ማስታወቂያ የተሰጠውን የጽሁፍ ፈተና የወሰዱ ተወዳዳሪዎች የፈተና ውጤት ከዚህ በታች የተገለጸ መሆኑን እያሳወቅን፤ አብዛኛው አመልካቾች የመለያ ቁጥራቸውን ያልያዙ መሆኑን በገለጹልን መሠረት ሙሉ ስምና የፈተና ውጤት እንዲለጠፍ የተደረገ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
19.0K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 13:56:31
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት እጅግ ዘመናዊ በሆኑ አውቶቡሶቹ ከመስከረም 19/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከአደስ አበባ ሀዋሳ፣ ወላይታና አርባ ምንጭ የደርሶ መልስ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
ዋይ ፋይ፣ ማቀዝቀዣና መጸዳጃ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ምቾትን የሚያላብሱ ቴክኖሎጅዎች በተገጠሙለት አውቶቡስ ፈልሰስ ብለው ይጓዙ፣ ትኬቶችንም ከ700 በላይ በሆኑት የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፎች በኩል በቀላሉ ያግኙ።

መልካም ጉዞ!
8.8K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 09:31:58
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
13.7K views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 09:59:55
18.5K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 09:59:46 አቢሲንያ ባንክ እና ቪዛ ለፊፋ የዓለም ዋንጫ ኳታር 2022 “ ወደ አለም ዋንጫ የሚወስዶት ብቸኛ ካርድ ፣ከቪዛ የተበረከተ” በሚል መሪ ቃል የአጋርነት ፕሮግራም ይፋ አደረጉ!
አቢሲንያ ባንክ፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ በፍጥነት እያደገ ያለ የግል ባንክ ሲሆን፣ በኳታር 2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ይፋዊ አጋር ከሆንው ከቪዛ ጋር በመተባበር እንደሚሰራ በታላቅ ደስታእያበሰረ ፤ አላማውም በኢትዮጵያ ገበያ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ባለቤቶችን እና ተጠቃሚዎችን በካርድ መገበያየት በማበረታታት የዲጂታል ከፍያ አገልግሎቶችን ማሳደግ ነው።
የአቢሲኒያ ባንክና የቪዛ አጋርነት ዋና ሁነት የሚሆነው ሁለት እድለኛ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎችና እነሱ የሚመርጧቸው ሁለት ተጫማሪ የቤተሰብ አባላት ወይም ጓደኞች ፣ በአጠቃላይ አራት ሰዎች ወደ ኳታር ለመጓዝ እስፖንሰር የሚደረጉበት ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ለመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎች፣ ቀሪ ሁለቱ ደግሞ የሁለተኛው ዙር የምድብ ጨዋታዎችን ለመመልከት ከቪዛ የቀረበ ስጦታ ነው ። ይህ ታላቅ ሽልማት ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ውስጥ ለሁለት ምሽቶች ማረፊያ ፣የገበያ አበል ፣ከመድረክ ጀርባ በቅርበት ትእይንት የማየት ልምድ እና ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን የማየት እድል ያካተተ ነው ። በዚሁ የፊፋ የዓለም ዋንጫ ኳታር 2022 ዘመቻ ፤ባለ 55'' ቴሌቪዥኖች፣ ላፕቶፖች፣ ስማርት ስልኮች፣ ፓወር ባንኮች እና ሌሎች አስደሳች ሽልማቶችም ለአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች የቀረቡ ሲሆን በሽልማት እጣ ውስጥ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን በመጠቀም ብዙ ግብይት የፈጸሙ የካርድ ደንበኞች ይካተታሉ።
በዚህ ዘመቻ፤ የተለያዩ አዝናኝ እና አስደሳች እንቅስቃሴዎች የሚኖሩ ሲሆን ከአቢሲኒያ ጋር በካርድ ግብይት አብረው የሚሰሩ የንግድ ተቋማትና የባንኩ የተለያዩ ቅርንጫፎች የሚሳተፉባቸው ትእይንቶች፣ የመንገድ ላይ ትርኢቶች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም ከእግር ኳስ ጋር የተያያዙ የጎዳና ላይ መዝናኛዎች ላይ በማሳተፍ የሚሰጡ ሽልማቶች እንዲሁም በተመረጡ ቦታዎች ወይም የስፖርት ባሮች ውስጥ አስደሳች ጊዜያትን በመፍጠር የሚካሄዱ ይሆናሉ ።
የአቢሲንያ ባንክ እና የቪዛ ተወካዮች እንደገለጹት በዚህ አስደሳች የአጋርነት ዘመቻ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ደንበኞች እና ተጠቃሚዎች ቪዛ ካርዳቸውን በተለያዩ የግብይት ማዕከላት በመጠቀም እንዲገበያዩ በማበረታታት ፤ ለሁሉም የእጣው ተሳታፊዎች መልካም ዕድል እንደሚመኙ ገልጽዋል ።
18.7K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 14:59:09
ወደ ፊፋ የዓለም ዋንጫ የሚወስደው ብቸኛው ካርድ የትኛው ነው?
መቼም ቢጫ ወይም ቀይ ካርድ ኣይሆኑም!
በኳታር በሚዘጋጀው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ለመታደም የሚያስችለው ብቸኛው ካርድ
የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርድ ነው!!! ቪዛን እናመሰግናለን!
ወደፊትም ለልጅዎ፥ ለልጅ ልጅዎ “አቢሲንያ ባንክ እና ቪዛ አለሜን አሳየኝ” ብለው
በኩራት የሚነግሩት ልዩ ኣጋጣሚ!!!
ከእርስዎ የሚጠበቀው ከ1000 በላይ በሆኑ የአቢሲንያ የPOS ማሽኞች ሲከፍሉ እና
ሲሸምቱ እንዲሁም ከሁሉም የአቢሲንያ ቅርንጫፎች አዲስ ካርድ ሲያወጡ
ወዲያውኑ የመወዳደሪያ ዕጣ በስልክዎ ይገባልዎታል፡፡
በቪዛ ካርድዎ ደጋግመው ሲከፍሉና ሲሸምቱ የማሸነፍ ዕድልዎ ይበልጥ
ይጨምራል። ታድያ ዕድሉ ለእርስዎ ብቻ ኣይደለም: የመረጡትን ወዳጅዎን ይዘው
በ5ኮከብ ሆቴል እየተዝናኑ የፊፋ ዓለም ዋንጫን ይታደማሉ።
ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው።
32.1K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 15:02:03
አቢሲንያ ባንክ በ inventory controller, Junior officer (warehouse management) እና store keeper የሥራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
ለሥራ መደቡ የሚያስፈልገውን መስፈርት፣ የሥራ ልምድ እና የመሳሰሉትን ዝርዝር መረጃዎች ለማግኘት በባንኩ ድረገፅ https://vacancy.bankofabyssinia.com በመግባት ማግኘትና ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
42.7K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 14:57:04
ወደ ፊፋ የዓለም ዋንጫ የሚወስደው ብቸኛው ካርድ የትኛው ነው?
መቼም ቢጫ ወይም ቀይ ካርድ ኣይሆኑም!
በኳታር በሚዘጋጀው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ለመታደም የሚያስችለው ብቸኛው ካርድ
የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርድ ነው!!! ቪዛን እናመሰግናለን!
ወደፊትም ለልጅዎ፥ ለልጅ ልጅዎ “አቢሲንያ ባንክ እና ቪዛ አለሜን አሳየኝ” ብለው
በኩራት የሚነግሩት ልዩ ኣጋጣሚ!!!
ከእርስዎ የሚጠበቀው ከ1000 በላይ በሆኑ የአቢሲንያ የPOS ማሽኞች ሲከፍሉ እና
ሲሸምቱ እንዲሁም ከሁሉም የአቢሲንያ ቅርንጫፎች አዲስ ካርድ ሲያወጡ
ወዲያውኑ የመወዳደሪያ ዕጣ በስልክዎ ይገባልዎታል፡፡
በቪዛ ካርድዎ ደጋግመው ሲከፍሉና ሲሸምቱ የማሸነፍ ዕድልዎ ይበልጥ
ይጨምራል። ታድያ ዕድሉ ለእርስዎ ብቻ ኣይደለም: የመረጡትን ወዳጅዎን ይዘው
በ5ኮከብ ሆቴል እየተዝናኑ የፊፋ ዓለም ዋንጫን ይታደማሉ።
ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው።
57.5K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 16:11:23
ምስጋና!
ላሰናዳነው “የአበባየሽ ወይ” የሽልማት ውድድር በቁጥር በርካታ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡ እውነት ለመናገር ካሰብነውም፣ ከጠበቅነውም፣ ከገመትነውም በላይ ስለነበር ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል፡፡ ለተሳተፋችሁትም በሙሉ ከልብ የሆነ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
በዘርፉ አንቱ የተባሉ ሦስት አንጋፋ ዳኞች የተላኩትን የውድድር ተንቀሳቃሽ ምስሎች አስቀድመው ባወጡት መስፈርት መሠረት እየገመገሙ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በዳኞች የሚለዩትን 15 ሥራዎች ለቀሪው የ50 በመቶ የሕዝብ ድምፅ በተቻለ ፍጥነት ይፋ እናደርጋለን፡፡
አቢሲንያ ባንክ!
52.7K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ