Get Mystery Box with random crypto!

አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!! ባንካችን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም. | Bank of Abyssinia

አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!!
ባንካችን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ላይ ከብር 10 ሺህ እስከ 100 ሺህ የገንዘብ ሽልማቶች የተዘጋጀበት “አበባ አየሽ ወይ” ባሕላዊ ጨዋታ ውድድር ማካሄዱ ይታወቃል፡፡
በውድድሩ በርካታ ቡድኖች ከተለያዩ ክልሎች የተሳተፉ ሲሆን፣ የውድድር መስፈርቱን ያሟሉ ወደ 300 የሚጠጉ የቪዲዮ ሥራዎች ለባለሙያዎች ግምገማ ብቁ ሁነው ዳኞች አስቀድመው በአስቀመጡት መሥፈርቶች 15 ሥራዎች ተገምግመው ተመርጠዋል። ይኽንን ተከትሎ፤ በዳኞች ተገምግመው የተመረጡት 15 ሥራዎች ለተመልካች ቀርበው በአጠቃላይ 3655 የህዝብ ድምፅ ተሰጥቶባቸዋል። በመጨረሻም በሕዝብ ድምጽ እንዲሁም በዳኞች ድምጽ ድምር ውጤት የተመረጡት የመጨረሻዎቹ አስር (10) አሸናፊዎች ተለይተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በቅደም ተከተል ከ 1ኛ እስከ 10ኛ የወጡት ተወዳዳሪዎች በተሰጣቸው ኮድ መሠረት ተለይተው ታውቀዋል።

በውድድሩ ላይ በመሳተፍና አስተያየት በመስጠት ያገዛችሁን የባንካችን ቤተሰቦች በሙሉ እጅግ አድርገን እናመሰግናችኋለን፡፡ባንካችን አቢሲንያ መሰል ውድድሮችን በተሻለ ዝግጅት ወደፊት ስለምናቀርብ ተሳትፏችሁ እንዲቀጥል መልዕክታችንን በዚሁ አጋጣሚ እናስተላልፋለን!

አሸናፊዎች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!