Get Mystery Box with random crypto!

ብራና አፕስ Birana Apps

የቴሌግራም ቻናል አርማ biranapps — ብራና አፕስ Birana Apps
የቴሌግራም ቻናል አርማ biranapps — ብራና አፕስ Birana Apps
የሰርጥ አድራሻ: @biranapps
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.09K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ብራና Apps እንኳን በደህና መጡ። ታላላቅ መጻሕፍትን የያዙ አፕሊኬሽኖችን ያውርዱ ይግዙ ።
ውይይቶችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ማብራሪያዎችን ከፈለጉ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉን ።
Website: https://biranapps.com
Email: support@biranapps.com
Phone: 251901008562

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-21 22:47:51 አስደሳች ዜና

#አዲስ_አፕሊኬሽን_ተለቀቀ

መጽሐፍ ቅዱስ ፹፩ በግእዝ ፣ ትግርኛና እንግሊዝኛ

በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በትግርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ/የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ የተዘጋጀ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሁም የቀኖና መጻሕፍት ብላ በ1962 ዓ.ም ያሳተመችውን መጽሐፍ ቃል በቃል ለቅሞ መዝግቧል።

መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል:: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ በስልካቸው እንዲጠቀሙ ይረዳል::

የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት
• ሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው።
• ሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝ፣ በትግርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ነው።
• የአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው።
• የኢትዮጵያ/ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍትን ያካተተ ነው።
• ፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በትግርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።
• የፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው።
• በቀንና በጨልማ ለማንበብ የራሱ ማስተካከያ ተካቶበታል።
• ማስታወሻ መያዣ፣ ማቅለሚያ፣ ዕልባት ማድረጊያ ተካቶበታል።
• ማጣቀሻዎች በየቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን በቀላሉ አንድ ጊዜ ብቻ ጠቅ በማድረግ ገጹን ሳይለቁ ማንበብ ያስችላል።
• በጣም ፈጣንና የፍለጋ ውጤቶችን በማቅለምና በቁጥር የሚያሳይ መፈለጊያ ተካቶበታል።
• የአማርኛ፣ የግእዝና የእንግሊዝኛ ዕትሞችን ጎን ለጎን፣ መስመር በመስመር ፣ ከላይና ከታች አድርገን ለማንበብ ያስችላል።
• የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በአኅጽሮት ወይም በሙሉ ስም ለመዘርዘር ማስተካከያ ተደርጎበታል።
• የፊደል መጠኑን በቀላሉ ማሳነስና ማሳደግ የሚያስችል ማስተካከያ ተካቶበታል።
• የመጽሐፍ ቅዱስ መስመሮችን እንድፍላጎትዎ ማስተካከል ይችላሉ።
• ከዚህ በፊት ያነበቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ በፊት የተነበቡ በሚለው ስር ያገኟቸዋል።
• የተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም የመጽሐፉን ይዘት መተርጎም ይችላሉ።

በመጽሐፉ የተካተቱ መጻሕፍት ዝርዝር
ብሉይ ኪዳን
1. ኦሪት ዘፍጥረት
2. ኦሪት ዘጸአት
3. ኦሪት ዘሌዋውያን
4. ኦሪት ዘኍልቍ
5. ኦሪት ዘዳግም
6. መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ
7. መጽሐፈ መሳፍንት
8. መጽሐፈ ሩት
9. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
10. መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
11. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
12. መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
13. መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
14. መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
15. መጽሐፈ ዕዝራ
16. መጽሐፈ ነሐምያ
17. መጽሐፈ አስቴር
18. መጽሐፈ ኢዮብ
19. መዝሙረ ዳዊት
20. መጽሐፈ ምሳሌ
21. መጽሐፈ ተግሣጽ)
22. መጽሐፈ መክብብ
23. ማሕልየ መሓልይ ዘሰሎሞን
24. ትንቢተ ኢሳይያስ
25. ትንቢተ ኤርምያስ
26. ሰቈቃወ ኤርምያስ
27. ትንቢተ ሕዝቅኤል
28. ትንቢተ ዳንኤል
29. ትንቢተ ሆሴዕ
30. ትንቢተ ዓሞጽ
31. ትንቢተ ሚክያስ
32. ትንቢተ ኢዮኤል
33. ትንቢተ አብድዩ
34. ትንቢተ ዮናስ
35. ትንቢተ ናሆም
36. ትንቢተ ዕንባቆም
37. ትንቢተ ሶፎንያስ
38. ትንቢተ ሐጌ
39. ትንቢተ ዘካርያስ
40. ትንቢተ ሚልክያስ
41. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልድ ኮርዮን (ያልተጠናቀቀ)

የብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት
42. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል
43. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
44. መጽሐፈ ጦቢት
45. መጽሐፈ ዮዲት
46. መጽሐፈ አስቴር
47. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
48. መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ
49. መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ
50. መጽሐፈ ሲራክ
51. ጸሎተ ምናሴ
52. ተረፈ ኤርሚያስ
53. መጽሐፈ ሶስና
54. መጽሐፈ ባሮክ
55. መጽሐፈ ጥበብ
56. መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ
57. ተረፈ ዳንኤል
58. መጽሐፈ ኩፋሌ
59. መጽሐፈ ሔኖክ

ሐዲስ ኪዳን
60. የማቴዎስ ወንጌል
61. የማርቆስ ወንጌል
62. የሉቃስ ወንጌል
63. የዮሐንስ ወንጌል
64. የሐዋርያት ሥራ
65. ወደሮሜ ሰዎች
66. 1ኛ ወደቆሮንቶስ ሰዎች
67. 2ኛ ወደቆሮንቶስ ሰዎች
68. ወደገላትያ ሰዎች
69. ወደኤፌሶን ሰዎች
70. ወደፊልጵስዩስ ሰዎች
71. ወደቆላስይስ ሰዎች
72. 1ኛ ወደተሰሎንቄ ሰዎች
73. 2ኛ ወደተሰሎንቄ ሰዎች
74. 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
75. 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
76. ወደ ቲቶ
77. ወደ ፊልሞና
78. ወደ ዕብራውያን
79. 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
80. 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት
81. 1ኛ የዮሐንስ መልእክት
82. 2ኛ የዮሐንስ መልእክት
83. 3ኛ የዮሐንስ መልእክት
84. የያዕቆብ መልእክት
85. የይሁዳ መልእክት
86. የዮሐንስ ራእይ

የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት
87. መጽሐፈ ዲድስቅልያ
88. መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
89. መጽሐፈ አብጥሊስ
90. መጽሐፈ ግጽው
91. መጽሐፈ ሥርዓተ ጽዮን
92. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
93. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ
94. መጽሐፈ ትእዛዝ
686 viewsBirana Apps Customer Service, edited  19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:46:22
445 viewsBirana Apps Customer Service, edited  19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:13:38 Watch "የደብረ ታቦር መዝሙሮች ስብስብ" on YouTube


593 viewsBirana Apps Customer Service, edited  09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:12:24 Watch "የደብረ ታቦር ወረቦች ስብስብ" on YouTube


547 viewsBirana Apps Customer Service, edited  09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 08:02:05 Watch "የደብረ ታቦር /ነሐሴ 13 / ምስባክ" on YouTube


577 viewsBirana Apps Customer Service, edited  05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:31:53 #በዓለ_ደብረ_ታቦር እና #ቡሄ

ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር በሠላም አደረሰን ።

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበ ዕለት ስለ ኾነ ‹የብርሃን› ወይም ‹የቡሄ› በዓል ይባላል፡፡

ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፤ ወደ መፀው የሚገባበት፤ ወገግታ የሚታይበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚሸጋገርበት ወቅት በመኾኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናቱ ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮኹ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለዚህ በዓል የሚኾን ዳቦ ለመጋገር ስንዴያቸውን ሲያጥቡ፣ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ (ነሐሴ ፲፪ ቀን) ሕፃናት በየቤቱ እየዞሩ ‹‹ቡሄ ና በሉ፤ ቡሄ በሉ፡፡ ቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ፤ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ …›› እያሉ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሡ ይሰጧቸዋል፡፡ ሕፃናቱ ‹ቡሄ› የሚሉትም ዳቦውን ነው፡፡

ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡ የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡

መምህረ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ በደብረ ታቦር ምሥጢር መግለጡን በማስታዎስ የአብነት ተማሪዎች ከመምህራቸው ጋር በመኾን በዓለ ደብረ ታቦርን (ቡሄን) ያከብራሉ፤ ስሙን ይጠራሉ፡፡ የአብነት ተማሪዎች ‹‹ስለ ደብረ ታቦር›› እያሉ እኽል ከምእመናን በመለመንና ገንዘብ በማዋጣት ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምእመናን በመጋበዝና እርስበርስ በመገባበዝ፣ እንደዚሁም ቅኔ በማበርከት በዓለ ደብረ ታቦርን በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህም እስከ አሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሠራበት ነባር ትውፊት ነው፡፡

ነገር ግን በአንድ አካባቢዎች በተለይ በከተማ ዙሪያ በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) ሃይማኖታዊ ትውፊቱን የለቀቀ ይመስላል፡፡ ለዚህም ልጆች የሚጫወቱበት መዝሙር ግጥሙና ዜማው ዓለማዊ መልእክት የሚበዛበት መኾኑ፤ በወቅቱ ችቦ ከማብራት ይልቅ ርችት መተኮሱና በየመጠጥ ቤቱ እየሰከሩ መጮኹ፤ ወዘተ. የበዓሉን መንፈሳዊ ትውፊት ከሚያደበዝዙ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም በዚህ በዓል ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሚሽቀዳደሙ ነገር ግን የበዓሉን ታሪካዊ አመጣጥ የማያዉቁ ልጆችም ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ስለዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የበዓለ ደብረ ታቦርን መንፈሳዊነት፣ የመዝሙሮቹን ያሬዳዊነትና አከባበሩን ከቤተ ክርስቲያን መምህራን በመጠየቅ ማስተማር፤ ልጆችም ከወላጆች ወይም ከመምህራን በመጠየቅ የበዓሉን አከባበር መረዳትና የዚህን በዓል መንፈሳዊ ትውፊት ሳይበረዝ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡ ‹‹ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና፤ የቡሄው ብርሃን ለእኛ በራልን …›› የሚለውንና ይህን የሚመስሉ መንፈሳውያን መዝሙራትን እየዘመሩ በየቤቱ በመዘዋወር የሚያገኙትን ዳቦና ገንዘብ ለነዳያንና ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ልጆችንም ማበረታታትና አርአያነታቸውን መከተል ይኖርብናል፡፡

ምንጭ: ማህበረ ቅዱሳን blog

https://eotcmk.org/
724 viewsBirana Apps Customer Service, 15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:31:42
580 viewsBirana Apps Customer Service, 15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 15:23:31

945 viewsBirana Apps Customer Service, 12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 14:02:11
#ብራና_አፕስ #Biranapps

የሚፈልጉትን መጽሐፍት እንደ ፍላጎትዎ ከ50 ብር ጀምሮ ከ15 በላይ አፖችን ማግኘት የሚችሉበት ትክክለኛ ቦታ #ብራና_አፕስ ። ።ምናልባትም በህትመት ቢሆኑ ይዘው ለመንቀሳቀስ የሚያስቸግሩ በጣም ብዙ መጽሐፍትን በቀላሉ በየትኛው ቦታ በስልክዎ ጭነው መጠቀም ያስችልዎታል ምንም አይነት የኢንተርኔት ግንኙነት ማይፈልጉ በመሆናቸው ደግሞ የበለጠ ተመራጭ ያደርጋቸዋል ።

ሁሉንም አፖች ለመግዛት ለሚፈልግ ደግሞ 600 ብር ብቻ በመክፈል ያለገደብ መጠቀም ይችላሉ ።

አሁኑ ይግዙ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ በስጦታም ያበርክቱ ለበለጠ መረጃ

Web: https://biranapps.com
Email: Biranapps@gmail.com
Tel: +251901008562

#ብራና_አፕስ
926 viewsBirana Apps Customer Service, edited  11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 08:44:11
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ

#ጾመ_ፍልሰታ

<ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት ይነገራል።

ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሣቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።
944 viewsBirana Apps Customer Service, 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ