Get Mystery Box with random crypto!

ብራና አፕስ Birana Apps

የቴሌግራም ቻናል አርማ biranapps — ብራና አፕስ Birana Apps
የቴሌግራም ቻናል አርማ biranapps — ብራና አፕስ Birana Apps
የሰርጥ አድራሻ: @biranapps
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.09K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ብራና Apps እንኳን በደህና መጡ። ታላላቅ መጻሕፍትን የያዙ አፕሊኬሽኖችን ያውርዱ ይግዙ ።
ውይይቶችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ማብራሪያዎችን ከፈለጉ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉን ።
Website: https://biranapps.com
Email: support@biranapps.com
Phone: 251901008562

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-30 12:45:46 ብራና አፕስ Birana Apps pinned a photo
09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 12:44:56
#መጽሐፈ_ሰዓታት

ፆመ ፍልሰታን ሰአታት ለመቆም አስበዋል እንግዲያውስ መጽሐፈ ሰአታት ያስፈልግዎታል ።ይህን መጽሐፈ ሰአታት ደግሞ በአፕሊኬሽን አዘጋጅተን በተንቀሳቃሽ ስልክዎ አውርደው መጠቀም እንዲችሉ በቀላል ክፍያ #50ብር ብቻ ማንም ሰው መክፈል በሚችለው ዋጋ ተዘጋጅቶ ቀረበ ።

ክፍያውን ወቅቱን ባገናዘበ የክፍያ አማራጮች #በሞባይል_ባንኪንግ ወይም #ኢንተርኔት_ባንኪንግ እንዲሁም #በቴሌብር በቀላሉ ባሉበት ሆነው መክፈል ይችላሉ ።

የአፕሊኬሽኑ ይዘት
መጽሐፈ ሰዓታት በግዕዝ (ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀመው)
መጽሐፈ ሰዓታት ዘደብረ ዓባይ በግዕዝ (በይዘቱ ከዋናው ሰዓታት የተወሰነ ይለያል)
መጽሐፈ ሰዓታት ከአማርኛ ትርጉም ጋር (የአማርኛውን ትርጉም ለሚሹ)
️ የቃላት ግድፈቶች በአብዛኛው ታርመዋል ።

ዋጋው: 50  ብር (ከኢትዮጵያ ውጪ 10 USD)

ለማውረድ https://play.google.com/store/apps/details?id=org.goranda.seatat
1.2K viewsBirana Apps Customer Service, 09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 15:40:07 ብራና አፕስ Birana Apps pinned a photo
12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 15:21:52
#መዝገበ_ህይወት

13 ነባር አፕሊኬሽኖችን በአንድ ላይ የያዘና ከ500 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ጽሑፎችን በአንድ ላይ ያከተተ ግዙፍ መተግበሪያ ነው ። ለእያንዳንዱ አፕሊኬሽን መክፈል ሳይኖርብዎት የሚፈልጉትን ሁሉ በአንድ መተግበርያ ያንብቡ ።
ይህን አፕሊከሽን ከተጠቀሙ የማያገኙት መንፈሳዊ መጽሐፍ የለም ።
በመሆኑም ይህን መጽሐፍ በህትመት ማግኘት ስለማይቻል በቀላሉ በትንሽ ክፍያ አውርደው መጠቀም ይችላሉ ። ከያዛቸው መጽሐፍት አንፃር ዋጋው ምንም ነው ፈጥነው ይግዙ አይቆጩበትም ለወዳጅ ዘመድዎም ያጋሩ በስጦታም ያበርክቱ ።

#በውስጡ_የተካተቱ_ነባር_አፖች

⒈ መዝገበ ሃይማኖት
⒉ መዝገበ ጸሎት
⒊ መጽሐፍ ቅዱስ ፹፩ በግእዝና በአማርኛ
⒋ ጸዋትወ ዜማ
⒌ መጽሐፈ ቅዳሴ
⒍ መጽሐፈ ሰዓታት
⒎ መልክአ ቅዱሳን
⒏ መጽሐፈ ስንክሳር
⒐ ማኅሌተ ጽጌ
⒑ ግብረ ሕማማት
11. Utubaa Amantaa
12. አብነት ዘኦርቶዶክስ
13. ዓምደ ሃይማኖት በትግርኛ ናቸው ።

#ዋጋ: 400ብር

#የት_ያገኙታል?

https://play.google.com/store/apps/details…

ወይም

https://play.google.com/store/apps/details…

Appstore (for IOS and Ipads)

https://apps.apple.com/app/id1541001866

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ

+251901008562
872 viewsBirana Apps Customer Service, 12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 22:52:27
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ ።

#ትንሳኤ_ክርስቶስ
        ትንሳኤ ማለት ተንሥአ ካለው የግዕዝ ግሥ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም መነሣት አነሣሥ ማለት ነው ።እስራኤል ዘስጋ ያከብሩት የነበረው በዓለ ፋሲካ ከባርነት ቀንበር ወደ ነጻነት የተላለፉበት ከኀዘን ወደ ደስታ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር ።
የሐዲስ ኪዳን በዓለ ትንሣኤ ግን እሥራኤል ዘነፍስ ወደ ከኃጢአት ጽድቅ የተመለስንበት ከሐሳር ወደ ክብር ከአሮጌው ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሸጋገርንበት መንፈሳዊ የነጻነትበዓል ነው ።ፋሲካ በዐረብኛ ፓስኻ ማለት ሲሆን ትርጉሙም ማዕዶት መሸጋገሪያ ማለትነው ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በቀደምት ነቢያት የተነገሩና የተጻፉ አንቀጾች ብዙ ናቸው፡፡ የሞቱና የትንሣኤ ምሥጢር በቅዱሳን መጻሕፍት ሰፊ ቦታ ያለው ነው፡፡ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚነገረው ሞትና ትንሣኤ ከቅርቡ /ከመስቀሉ አካባቢ/ በመነሣት እሱ ራሱ መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ቊርባንን በሠራበት ምሽት የሞቱንና ትንሣኤውን ነገር አንሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ በሰፊው ገልጿል፡፡ “በዚች ሌሊት ሁላችሁ ትክዱኛለችሁ መጽሐፍ እረኛው ይመታል የመንጋው በጎች ይበተናሉ ያለው ይፈጸማል” ብሎ ነግሮአቸዋል፡፡ ከዚህም ቀደም ብሎ በጉባኤው ይሰበሰብ ለነበረው ሕዝብ ዮናስ በከርሠ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት እንደኖረ ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስም ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ያድራል፡፡ ነገር ግን ወደገሊላ እቀድማችኋለሁ እያለ ይነግራቸው፥ ያስተምራቸው ነበር፡፡ ማቴ ፲፪፥፵፣ ፳፯፥፴፩'
1.5K viewsBirana Apps, edited  19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 21:44:12 ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሰለዚኽ ምስጢር ሲገልጸው ፡- “ፍቅርኅ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ዠርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደኅ፡፡ ብዙ ዓይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሠራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደደክ፡፡ በሰማይ ሠራዊት ሠረገላ ተቀምጠኅ ክብርኅን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጠኅ ወደ ሰማይ ሠራዊት መኼድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ያመሰግኑኻል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልኻል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድኽን ያነጥፉልኻል፤ በምድርም ደቀ መዛሙትኽ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድኽን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲኾን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከ መኾን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” በማለት አስተምሯል፡፡
ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት የኾነችው በደመ ወልደ እግዚአብሔር የተመሠረተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ይኽነን በዓል በታላቅ ድምቀት፣ በማሕሌት፣ በቅዳሴ በተለይም ጌታ ቤተ መቅደሱን እየተመሰገነ መዞሩን በማሰብ በአራቱ መኣዝነ ቤተ ክርስቲያን ምስባክ እየተሰበከ ወንጌል እየተነበበ ከጾመ ድጓ ምራት እየተመራ በታላቅ ድምቀት በዓሉ ሲከበር፤ ሕዝበ ክርስቲያኑም በተመስጦ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ በግንባሩ አስሮ “ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት” በማለት ፈጣሪያቸውን የባሕርይ አምላክ የኾነውን ንጉሠ ነገሥት፣ አምላከ አማልክት፣ የጌቶች ጌታ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለውን ፈራጅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያመሰግናሉ፡፡
ከበዓለ ሆሣዕና ረድኤት በረከት ያሳትፈን፡፡

ምንጭ https://gundemeskel.blogspot.com
1.5K viewsBirana Apps, edited  18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 21:44:09 እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና አደረሳችሁ

ሆሣዕና

ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ሲኾን “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸሙት ጌታ በትሕትና በአህያና በውርንጫይቱ በትሕትና ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕጻናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡
ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ስትኾን ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታ ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” ብሏቸዋል፡፡
“ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ፈጣሪ የኹሉ ጌታ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”
በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ፤ ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ፡፡
ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማን እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯል፡- 14ቱ በእግሩ መኼዱ የ10ሩ ቃላት 4ቱ የ4ቱ ኪዳናት ምሳሌ፡፡ 2ቱ በአህያዋ መጓዙ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ፤ 3ቱን በውርንጫዋ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን መዞሩ የ3ትነቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነበር፡፡
ክብር ይግባውና ጌታ ንጉሠ ነገሥት ሲኾን፤ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በፍርሀት በረአድ የሚሸከሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን በፍርሀት የሚያጥኑለት ርሱ በትሕትና የዋህ ኾኖ በተናቁት በአህያና በውርንጫይቱ ላይ ተቀመጠ፤ ይኽም የተናቁትን ሊያከብር እንደመጣና፤ በየዋሀን ምእመናን ልቡና እንደሚያድር ለማሳወቅ በነርሱ ተቀመጠ፤ በአህያ የተቀመጠ አባሮ እንደማይዝ ሸሽቶ እንደማያመልጥ ርሱም ካልፈለጉት እንደማይገኝ ከፈለጉት እንደማይታጣ በምስጢር አመለከታቸው፡፡
ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡- ስለዚኽ ነገር በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ “እነዚኽ እንስሳት መላውን የሰው ልጅ ይወክላሉ፡፡ ኹለቱም አህያ መኾናቸውም የሰው ልጅ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረውን አኳኋን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም አህያ በኦሪቱ ዘንድ ንጹሕ እንስሳ አይደለችም፤ ብዙ ክብደት ያላት የማትወደድ እንስሳ ናት፤ ዲዳ ናት፤ ደካማ ናት፡፡ ሰውም እንደተናገርን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት እንዲኽ ነበረ፡፡” በማለት ሲያመሰጥር ሊቁ ቅ. ቄርሎስ ዘእስክንድርያም፡- “ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ጠቢብ አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ማሰብና ማሰላሰል የሚችል ፍጥረት አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ግን አታለለው፡፡ ምንም እንኳን ሰው በሥላሴ አምሳል ቢፈጠርም መልኩን አበላሸው፡፡ ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ተሳነው፡፡ ክፉው ሰይጣን ሰውን እንስሳ እስኪመስል ድረስ ክብሩን አዋረደው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት፡- “ሰውስ ክብሩን አላወቀም፤ የሚጠፉ እስሳትን መሰለ” ያለውም ስለዚኹ ነው /መዝ.49፡12/፡፡ በመኾኑም አህያይቱ ክብራቸውን አጥተው ተዋርደው የነበሩትን እስራኤል ዘሥጋን ትመስላለች፡፡ እስራኤል ከሕጉ ጥቂት ነገርን ያውቃሉ፡፡ ከነቢያትና ከቅዱሳንም ትንሽ ያውቃሉ፡፡ ከኹሉም በላይ ደግሞ ወደ አሚን የሚጠራቸውን ክርስቶስን አልታዘዙትም፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲላቸውም እንደምን እንደ አሕያይቱ በድንቁርና ተይዘው እንደነበረ ሲገልጥላቸው ነው፡፡ ውርንጫይቱ ደግሞ አሕዛብን ትወክላለች፡፡ ውርንጫ እኽልን ለመጫን እንደማታገለግል ኹሉ አሕዛብም ማኅደረ እግዚአብሔር ከመኾን ርቀው ነበርና፡፡” በማለት ገልጽዋል፡፡
ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡” • አምብሮሲስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑ ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል፡፡
ያን ጊዜ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ይኽንም ማድረጋቸው ስንኳን አንተ የተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባኽም ሲሉ ነበር፤ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር
ይኽም ዘንባባ ብዙ ምሳሌ ያለው ነው፤ ይኸውም በእስራኤል ያለው ሰሌን፣ ተምር፣ ዘይት ነበርና ያነን ቈርጠው አመስግነውታል፤ ይኽም ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኽም ሰሌን እሾኻማ እንደኾነ ትእምርተ ኀይል ትእምርተ መዊእ አለኽ ሲሉ ነው፤ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ እንደማያቃጥለው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
ዳግመኛም ከሰሌን ዝንጣፊ ጋር ተመሳሳይ ተምር ይዘዋል ይኽም ተምር ልዑል ነው አንተም ልዑለ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ፍሬው አንድ እንደኾነ አንተም ዋሕደ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፡፡ በእሾኽ የተከበበ ነው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
የዘይት ዛፍ ነው ቢሉ ዘይት ጽኑዕ እንደኾነ ጽኑዐ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ብሩህ ነው ብሩሀ ባሕርይ ነኽ በትምህርትኽም የሰውን ልቡናን ታበራለኽ ሲሉ፤ ዘይት መሥዋዕት እንደሚኾን መሥዋዕት ትኾናለኽ ሲሉ ነበር፡፡
“የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር” በማለት በአርያም መድኀኒት እንደኾነና እግዚአብሔር አብ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ መስክሮለት የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን የሚያድል መኾኑን ኹሉም መሰከሩለት፡፡
በእጅጉ የሚደንቀው የ40 ቀን የ80 ቀን ሕጻናት የፈጠራቸው ጌታ በአህያና በውርንጫ ተቀምጦ ባዩት ጊዜ በንጹሕ አንደበታቸው አንደታቸው ረቶላቸው ጌታን ዘንባባ በመያዝ ሲያመሰግኑ በእጅጉ ይደንቅ ነበር፤ ነገር ግን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት፤ ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? በማለት በሕጻናት እንደሚመሰገን የነርሱም ጌታ መኾኑን ከዳዊት መዝሙር በመጥቀስ ነገራቸው፡፡
1.2K viewsBirana Apps, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 10:57:26
#ደስ_የሚል_ዜና
መጽሐፈ ግብረ ህማማት በአፕሊኬሽን ቀረበ ።

ይህ መጽሐፍ በጣም ግዙፍ በመሆኑ ሁሉም ሰው ማግኘትና ይዞት መንቀሳቀስ ከባድ ስለሆነ ሁሉም ለማግኘት ቀላል በሆነ መንገድ በአፕሊኬሽን ተዘጋጅቶ ቀረበ።

ይህ መተግበሪያ ሁሉን ሰው እንዲጠቀመው በማሰብ ዋጋው በጣም ቀላልና ማንኛውም ሰው እንዲገዛው ተደርጎ የቀረበ መተግበሪያ ነው ።

#ይዘቶቹ
ከሆሳዕና እስከ ትንሳኤ በየሰአቱ ተከፋፍለው የሚፀለዩና የሚነበቡ

መጽሐፈ ጾመ ድጓ

ከዘወረደ እስከ ሆሳዕና እንዱሁም ስለ ሰባቱ አጽዋማትና ስለ ጽጌ ጾም የተፃፉ የተለያዩ ጦማሮችና ትምህርቶችን የያዘ መተግበሪያ ነው ።
ዋጋው ኪስ አይጎዳም #25ብር ብቻ ሲሆን ክፍያ ለመፈፀም ዘመኑን ባማከለ መልኩ
#በሞባይል_ባንኪንግ
#ኢንተርኔት_ባንኪንግ
#ሄሎ_ካሽ
#ሲቢኢ_ብር እንዲሁም #ቴሌብርን መጠቀም ይችላሉ ።

ማሳሰቢያ ይህ ማስታወቂያ መዝገበ ህይወትን እና መዝገበ ሀይማኖት ተጠቃሚዎችን አይመለከትም ።

አፑን ለማውረድ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ

Https://biranapps.com
ወይም
ከቴሌግራም ቻናላችን
Https://t.me/biranapps

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ

+251901008562
1.7K viewsBirana Apps, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 15:02:14

1.6K viewsgEcH, 12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 20:26:36
#ታላቅ_የዐቢይ_ጾም_ቅናሽ

የዐቢይን ጾም ምክኒያት በማድረግ በሁሉም አፖች ላይ የ #50% ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው።በዚህ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ ለዘመድዎ እና ለጓደኛዎም ያጋሩ ተጠቃሚ ያድርጉ ።


በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚፈልጓቸውን መጻሕፍት በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ይዘው ይንቀሳቀሱ ፣ ባሉበት ቦታ ሆነው ያንብቡ። ብዙ አሥር ሺ ብር የሚጠይቁ መጻሕፍትን በማይታመን ዋጋ ያገኛሉ ።

ሆኖም ቅናሹ የሚቆየው ከየካቲት 23 እስከ ሚያዝያ 16 2014 ብቻ በመሆኑ በቅናሹ ተጠቃሚ ይሁኑ ለወዳጅ ዘመድዎም ያጋሩ ።

ሁሉም አፕሊኬሽኖች #ለAndroid እና #IOS ስልኮች ዝግጁ ናቸው ።

⒈ መዝገበ ሕይወት: 200ብር
⒉ መዝገበ ሃይማኖት = 150ብር
⒊ መዝገበ ጸሎት = 50 ብር
⒋ መጽሐፍ ቅዱስ ፹፩ = 50 ብር
⒌ ጸዋትወ ዜማ = 50 ብር
⒍ መጽሐፈ ሰዓታት = 25 ብር
⒎ መጽሐፈ ቅዳሴ = 25 ብር
⒏ መጽሐፈ ስንክሳር = 25 ብር
⒐ መጽሐፈ ግብረ ሕማማት = 25 ብር
⒑ መልክአ ቅዱሳን= 25 ብር
11. ማኅሌተ ጽጌ ወሰቆቃወ ድንግል = 25 ብር
12. Utubaa Amantaa = 25 ብር
13. አብነት ዘኦርቶዶክስ = 25 ብር
14. ግእዝ መዝገበ ቃላት = 25 ብር
15. አማርኛ መዝገበ ቃላት = 25 ብር
16. ትግርኛ መዝገበ ቃላት = 25 ብር

#ክፍያ ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ #ቴሌብርን ጨምሮ በሞባይል ባንኪንግ ወይም ደግሞ #በCBE_BIRR እና #HelloCash መጠቀም ይችላሉ ።

ስልክ: +251901008562
ይደውሉ፣ መረጃ ይጠይቁ ።

ለማውረድ ድረ ገጻችንን ወይም የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።

Https://t.me/biranapps

ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይጎብኙ ። https://biranapps.com
2.1K viewsBirana Apps, edited  17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ