Get Mystery Box with random crypto!

ብራና አፕስ Birana Apps

የቴሌግራም ቻናል አርማ biranapps — ብራና አፕስ Birana Apps
የቴሌግራም ቻናል አርማ biranapps — ብራና አፕስ Birana Apps
የሰርጥ አድራሻ: @biranapps
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.09K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ብራና Apps እንኳን በደህና መጡ። ታላላቅ መጻሕፍትን የያዙ አፕሊኬሽኖችን ያውርዱ ይግዙ ።
ውይይቶችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ማብራሪያዎችን ከፈለጉ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉን ።
Website: https://biranapps.com
Email: support@biranapps.com
Phone: 251901008562

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-01-06 17:56:29 “ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ” (ቅ. ያሬድ)

እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

በጌታችንና በአምላካችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተደረገልን ፍፁም ሥርየትና እርቅ ግልጥ ሆኖ የተጀመረው በነገረ ልደት ነው።

የጌታችን ልደት በነገረ ድኅነት ትልቅ ስፍራ የያዘና እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ፍፁም ልዩ መሆኑን ያሳየ ነው። መስተፃርራን የነበሩ ሰማይና ምድር፣ ሰውና መላእክት በአንድነት ለምስጋና ታድመዋል። የእረኞች አንደበትከመላእክት ጋር ለሰማያዊ ምስጋና ብቁ የሆነበት፤ ግዕዛን የሌላቸው እንስሳት ሰራኢ መጋቢያችን፣ በዘባነ ኪሩቤል በሰማያት የምትገለጥ አንተ ነህ ሲሉ እስትንፋሳቸውን የገበሩለት፤ የምድር ነገስታት በሥልጣንህ ሽረት በመንግሥህ ህልፈት የሌለብህ የነገስታት ንጉሥ አንተ ነህ ሲሉ ወርቅን ለመንግሥቱ፣ ዕጣንን ለክህነቱ፣ ከርቤን ለህማሙ ዕጅ መንሻን ያበረከቱለት፤ ወላዲተአምላክ ቅድስት ድንግል ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ያን ልዩ ክብር የዩበት፤ ይህ ልደት በእውነት ልዩ ነው።

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በረቡዕ ውዳሴ ማርያም በጌታ ልደት የተደረገልንን ድንቅ የማዳን ሥራ በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ ነበር ያለው፦ "በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰዉ ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፣ ስለተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋህዷልና ቅድምና የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ይህች ቤተልሔም መንግሥተ ሰማያትን መሰለች" አለ፤ የጌታን ልደት በተናገረበት አንቀጽ። በአባታችን በቀዳማዊ አዳም ምክንያት ያጣናትን ልጅነት ሊሰጠን ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ የመንግሥተ ሰማያትን የምስጋና ኑሮ በቤተልሔም ገልጧልና።

ስለዚህ ነገር ነቢየ እግዚአብሔር ሚክያስ "አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ አንቺ ከይሁዳ አእላፍ መካከል ትሆኝ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤል ላይ ገዢ የሚሆን ይወጣልና፤" በማለት የተነበየውም ስለዚህ ነበር ፤ ሚክ 5፥2።

“ወአንቲኒ በቤተልሔም ምድረ ኤፍራታ ኢትቴሃቲ እምነገሥተ ይሁዳ እስመእምኔኪ ይውጽእ ንጉሥ ዘይርዕዮሙ ለህዝብየ እስራኤል” እንዲል ቅዱስ ኤፍሬም።

ቤተልሔም ማለት ቤተ ህብስት፣ የህብስት ቤት፣ የእንጀራ ቤት ማለት ነው። ይህም ካሌብ እስራኤል ዘሥጋ ምድረ ርስት፣ ኢያሪኮን "ሃይል ዘእግዚአብሔር ኲናት ዘኢያሱ" ብለው በኢያሱ መስፍንነት ሲወርሱ ከኢያሱ የተሰጠችው ምድር፣ ኬብሮን ነበረች። ይህችም የይሁዳ ምድር በኋላም የቅዱስ ዳዊት ከተማ የሆነች ናት። አስቀድሞ ካሌብ ከብታ የምትባል ሚስት አግብቶ በሚስቱ ከብታ አላት ትርጓሜውም የምስጋና ቤት ማለት ነው፤ ይህም ካሌብ በመንፈሰ እግዚአብሔር በዚህች ምድር የሚገለጠውን የክርስቶስ የልደቱን ነገር፣ እና የመላእክትን ምስጋና ስለተረዳ ነበር። በኋላም ካሌብ ኤፍራታ የምትባል ሚስት አገባ ቦታዋን በዚህች ሚስቱ እንደገና ኤፍራታ ብሎ ጠራት። ኤፍራታ ማለት ፀዋሪተ ፍሬ፣ ፍሬ በውስጧ ያለባት ማለት ነው። ይህችውም የእመቤታችን ምሳሌ ናት የህይወት ፍሬ ክርስቶስን ወልዳልናለችና፤ አንቲ ውእቱ ዕፅ ቡሩክ ፍሬኪኒ ፍሬ ሕይወት እንዳለ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን።

ቤተልሔም ይህን ስያሜዋን ያገኘችው ካሌብ ከኤፍራታ ባገኘው ልጁ በልሔም ነው፤ ልሔም ማለት ህብስት፣ እንጀራ ማለት ነው ይህም ምሳሌነቱ የጌታ ነው፤ ይኸውም አማናዊ፣ እውነተኛ የሕይወት እንጀራ፣ህብስትክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ሊያድነን የመወለዱ ምሳሌ ነው። "ከሰማይ የወረደ ህያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል እኔም ስለዓለም ህይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።" እንዲል ዮሐ 6፥51።

በክርስቶስ ልደት መላእክት ባልተለመደ ሁኔታ ከሰዎች ጋር ተባብረው “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ሰላምም ለሰው ልጅ በምድር እርሱ በሚፈቅደው እያሉ ንጉሥ ክርስቶስን አመሰገኑ። ሉቃ 2፥14። በሰማያት በዘባነ ኪሩቤል የሚገለጥ፤ ፍፁማን ግሩማን በሚሆኑ መላእክት፣ ሊቃነ መላእክት፣ ሥልጣናት፣ አጋእዝት የሚመሰገን ሰማያዊው ንጉሥ ዛሬ ስለእኛ ፍቅር ሲል ሊነገር በማይችል ፍፁም ትህትና ከመ ሕጻናት ታቅፎ፣ ከኀጢአት ብቻዋ በቀር የኛን ባህሪ ባህርዩ አድርጎ ፍፁም አምላክ ሲሆን ፍፁም ሰው ሆኗልና።

”ሕፃን ተወልዶልናልና፥ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይኾናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ኀያል አምላክ፥የዘለዓለም አባት፥የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” ትኢሳ 9፥6።

ለዚህ ለክርስቶስ ፍቅር አንክሮ ይገባል፤ በሙሉ አፍአዊና ውሳጣዊ ህሊናችን እርሱን ዘውትር እናመስግን። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ይህን ፍፁም ፍቅር ለሰው ልጅ በኀጢዓት ተዳድፈን ለነበርን መደረጉን እያሰበ በአንክሮ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው፧ ወይስ ትጐበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው፤ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አሳነስኸው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንኽለት፥በእጆችኽም ሥራ ላይ ሾምኸው፤ዅሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛኽለት” በማለት ይናገራል። ዕብ 2፥6።

እኛም በክርስቶስ የተጠራን ሁላችን ይህን ያምላክ ፍቅር ዘወትር በልቡናችን እንድንስልና ከባልንጀሮቻችን ጋር በትህትናና በፍቅር እንድንኖር ሲመክረን፦ “እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለች ይህች ሃሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ትኑር፤ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከሰው ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባአልቆጠረም ነገር ግን፥የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ባዶ አደረገ፤” ይለናል፤ ፊል 2፥5።

ይህ የጌታ ልደት የቤተ ክርስቲያን አንድነት ነው። ሁሉ በአንድነት የተሰባሰቡበት በጋራ የዘመሩበት፤ በዚይች በበረት፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በሆነችው ጌታችን ከመሀል ከእናቱ ጋራ እንዲሁም አረጋዊ ዮሴፍ ከማሕበረ ጻድቃን፣ ሰማያውያን መላእክት፣ እረኞች፣ ሰባሰገል ነገሥታት፣ እንስሣትም ሳይቀሩ ባንድነት የተገኙባት የፍቅርና ያንድነት ቤት ናት።ስለዚህ እኛም የክርስቶስ አባግዓ መርዔቱ፣ የመንጋው በጎች፣ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በፍፁም አንድነት መኖር እንዳለብን “ወንድሞች ሆይ፥ዅላችኹ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፤ ባንድ ልብና ባንድ ሃሳብም የተባበራችኹ እንድትኾኑ እንጂ መለያየት በመካከላችኹ እንዳይኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችዃለኹ።” የተባለውም ስለዚህ ነውና። 1ኛቆሮ 1፥10። በማለት ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ያስተምረናል።

የጌታችንና የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ በዓል በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
2.1K viewsBirana Apps, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 17:53:30
1.4K viewsBirana Apps, 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 09:15:39
#ደስ_የሚል_ዜና

#ታላቅ_ቅናሽ_እንዳያመልጥዎት

የገናን ጾም ምክኒያት በማድረግ በሁሉም አፖች ላይ የ #50% ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው።በዚህ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ ለዘመድዎ እና ለጓደኛዎም ያጋሩ ተጠቃሚ ያድርጉ ።


በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚፈልጓቸውን መጻሕፍት በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ይዘው ይንቀሳቀሱ ፣ ባሉበት ቦታ ሆነው ያንብቡ። ብዙ አሥር ሺ ብር የሚጠይቁ መጻሕፍትን በማይታመን ዋጋ ያገኛሉ ።

ሆኖም ቅናሹ የሚቆየው ከህዳር 22 እስከ ታህሳስ 29 2014 ብቻ በመሆኑ በቅናሹ ተጠቃሚ ይሁኑ ለወዳጅ ዘመድዎም ያጋሩ ።

ሁሉም አፕሊኬሽኖች #ለAndroid እና #IOS ስልኮች ዝግጁ ናቸው ።

⒈ መዝገበ ሕይወት: 200ብር
⒉ መዝገበ ሃይማኖት = 150ብር
⒊ መዝገበ ጸሎት = 50 ብር
⒋ መጽሐፍ ቅዱስ ፹፩ = 50 ብር
⒌ ጸዋትወ ዜማ = 50 ብር
⒍ መጽሐፈ ሰዓታት = 25 ብር
⒎ መጽሐፈ ቅዳሴ = 25 ብር
⒏ መጽሐፈ ስንክሳር = 25 ብር
⒐ መጽሐፈ ግብረ ሕማማት = 25 ብር
⒑ መልክአ ቅዱሳን= 25 ብር
11. ማኅሌተ ጽጌ ወሰቆቃወ ድንግል = 25 ብር
12. Utubaa Amantaa = 25 ብር
13. አብነት ዘኦርቶዶክስ = 25 ብር
14. ግእዝ መዝገበ ቃላት = 25 ብር
15. አማርኛ መዝገበ ቃላት = 25 ብር
16. ትግርኛ መዝገበ ቃላት = 25 ብር

#ክፍያ ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ #ቴሌብርን ጨምሮ በሞባይል ባንኪንግ ወይም ደግሞ #በCBE_BIRR እና #HelloCash መጠቀም ይችላሉ ።

ስልክ: +251901008562
ይደውሉ፣ መረጃ ይጠይቁ ።

ለማውረድ ድረ ገጻችንን ወይም የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።

Https://t.me/biranapps

ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይጎብኙ ። https://biranapps.com
2.1K viewsBirana Apps, 06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-29 09:04:21 * #ማኅሌት_ዘኅዳር_ጽዮን(ህዳር 21) ***

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለኅዳር ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

፩. ነግሥ

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ፦

ሃሌ ሉያ ለአብ ፨ ሃሌ ሉያ ለወልድ፨ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ፨ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት፨ እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት፡፡

፪. ነግሥ

ሰላም ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ

ዘዘካርያስ ተቅዋም ዘወርቅ፨ ዘሕዝቅኤል ነቢይ ዕፁት ምሥራቅ ፨ ለመሠረትኪ የኃቱ ዕንቁ፨ ሰአሊ ለነ ማርያም በአሚን ንጽደቅ፡፡

፫. ነግሥ

ነቢያተ እሥራኤል ጸሐፉ በመጽሐፎሙ እሙነ፤
ነገረ ሰቆቃው ወላህ በዘመኖሙ ዘኮነ፤
ውስተ አፍላጋ አመ በጼዋዌ ነበርነ፤
ውስተ ኵሃቲሃ ፡ እንዚራቲነ ሰቀልነ ፤
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን እምነ፡፡

ዚቅ

ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ፨ እንተ ረከበተነ በእንተ ጽዮን ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ ፡፡

ወረብ፦

ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ እንተ ረከበተነ፤
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ።

፬. ለዝክረ ስምኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤
እምነ ከልበኑ ወቍስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትዕዛዝ፤
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡

ዚቅ፦

ሃሌ በ፫ እምነ ጽዮን በሀ፨
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት በስብሐት፨
ዓረፋቲሃ ዘመረግድ፤ ሥርጉት በስብሐት፨
ወማኅፈዲሃ ዘቢረሌ ፤ ሥርጉት በስብሐት፨
እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት፤ ሥርጉት በስብሐት፨
ታቦተ ሕጉ ለንጉሥ ዐቢይ፤ ሥርጉት በስብሐት፨
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ጽድቅ ይበርህ ለኪ፡፡

ወረብ፦

እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐይ ጽድቅ፤
ለሰማዕት ሥርጉት በስብሐት ሥርጉት በስብሐት።

፭. ለአስናንኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለአስናንኪ ሐሊበ ዕጐልት ዘተዛወጋ፡
ወመራዕየ ቅሩፃተ እለ እምሕፃብ ዐርጋ፡
ማርያም ድንግል ለደብተራ ስምዕ ታቦተ ሕጋ ፡
አፍቅርኒ እንበለ ንትጋ ለብእሴ ደም ወሠጋ፡
ዘየዐቢ እምዝ ኢየኃሥሥ ጸጋ፡፡

ዚቅ፦

ታቦ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕጽርት፨
ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት፨ንጉሥኪ ጽዮን፨ ኢይተመዋዕ በጸር ወኢየኀድጋ ለሀገር፡፡

ወረብ፦

ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕጽርት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት፤
ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ ለፀር ወኢየኃድጋ ለሀገር።

፮. ለከርሥኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለከርሥኪ ዘአፈድፈደ ተበጽዖ፤
እምታቦተ ሙሴ ነቢይ ለጽሌ ትእዛዝ ዘየኀብኦ፤
ማርያም ድንግል ጊዜ ጸዋዕኩኪ በአስተብቍዖ፤
ለጸርየ ብእሴ አመጻ ኀይለ ዚአኪ ይጽበኦ፤
እስከነ ያሰቆቁ ጥቀ ድኅሪተ ገቢኦ፡፡

ዚቅ፥

ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፨ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ፨ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡

ወረብ፦

ሃሌሃሌሉያ በጾም ወበጸሎት፤
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ አሥሮነ ቃለተ።

፯. ለመከየድኪ / መልክአ ማርያም /

ሰላም ለመከየድኪ እለ ረከቦን መከራ፤
እምፍርሃተ ቀተልት ሐራ እንበለ አሣእን አመ ሖራ፤
ማርያም ጽዮን ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ፤
ዕጐላት እምዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፤
አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ፡፡

ዚቅ፦

ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ ፨ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ ፨ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ፨ ከመ እኅትየ ኀለይኩ፨ እምድኅረ ጉንዱይ መዋዕል፨ ወእምዝ እምድኅረ ኅዳጥ ዓመታት ፨ ካዕበ ርኢክዋ ወትትሐፀብ በፈለገ ጤግሮስ ፡፡

ወረብ፦

ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ፤
ለቤተክርስቲያን ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ለቤተክርስቲያን።

፰. በዝንቱ ቃለ ማኅሌት / መልክአ ማርያም /

በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤
ለዘይስእለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤
ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤
ማርያም ዕንቍየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤
ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ ፡፡

ዚቅ፦

አበርሂ አብርሂ ጽዮን ፨ ዕንቍ ዘጳዝዮን ፨ ዘኃረየኪ ሰሎሞን ፡፡

ወረብ፦

አበርሂ አብርሂ ጽዮን፤
ዕንቍ ዘጳዝዮን ዘኃረየኪ ሰሎሞን ንጉሥ ።

፱. ዘካርያስ ርእየ / ማኅሌተ ጽጌ /

ዘካርያስ ርእየ ለወርኃ ሳባጥ በሠርቁ፤
ተአምረኪ ለዘይት ማእከለ ክልኤ አዕጹቁ፤
ማርያም ጽዮን ለብርሃን ተቅዋመ ወርቁ፤
ዕዝራኒ በገዳም አመ ወዓለ ዉዱቁ፤
ለኅበረ ገጽኪ ጽጌ ሐተወ መብረቁ፡፡

ዚቅ፦

ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰብዓቱ መሐትዊሃወሰብዓቱ መሣውር ዘዲቤሃ፨ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት
ዘኩለንታሃ ወርቅ ወያክንት፨ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት፡፡

ወረብ፦

ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን መኃትዊሃ ሰብዓቱ መኃትዊሃ፤
ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት።

++++++++++ አንገርጋሪ ++++++++++

ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርሑቅ፤
ከመ ማኅቶት ብርህት ከመ ፀሐይ
ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ፡፡

+++++++++++ እስመ ለዓለም +++++++++

ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኲለንታሃ ወርቅ፨ በየማና ወበጸጋማ አዕፁቀ ዘይት፨ደብተራ ፍጽምት ሀገር ቅድስት ፨ብነቢያት ይትፌሥሑ በውስቴታ ፨ ሐዋርያት ይትኃሠዩ በውስቴታ ፨ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ ፨ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ ፨ ወይብሉ ኲሎሙ ሃሌ ሉያ።

++++++++++ አቡን በ፩ ++++++++++

ከመዝ ይቤሎ እግዚአብሔር ለኤርምያስ ነቢይ፨ ሃብ ዚአሃ ለቤተክርስቲያን ፨ መራኁተ አወፍዮ ለፀሐይ ፨ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ለኢሳይያስ ነቢይ ፨ አስምዕ ሰብአ መሃይምና ወአርያሃ ፨ ወዘካርያስ ወልደ በራክዩ።

++++++++ ሰላም +++++++

ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፨ገነተ ትፍስሕት መካነ ዕረፍት፨ እንተ ይእቲ ማኅደር ለካህናት ለእለ የኃድሩ በፈሪሃ እግዚአብሔር፨ይእቲኬ ቤተ ክርስቲያን፨
በውስቴታ የዓርጉ ስብሐተ ካህናት በብዙኅ ትፍስሕት ወሰላም፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
1.6K viewsBirana Apps, 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-23 21:20:19 #ጾመ_ነቢያት

ይህ ጾም ከ7ቱ የቤተክርስትያናችን የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው ። ይህን ጾም በዋናነት ነብያት የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ፣ መወለድ በትንቢት መነጸር እየተመለከቱ የጾሙት ታላቅ ጾም ስለሆነ ጾመ ነብያት ተብሏል።ስለጌታችን መውረድ፣ የአምላክ ሰው መሆንን/መወለዱን/ የምንረዳበትም ጾም ነው ።

ይህ ጾም የራቀውን አቅርቦ፣ የረቀቀውን አጉልቶ ስላሳያቸው እስከሞት ድረስ ቢደበደቡም ፣ ከመከራው ጽንአት የተነሣ ዋሻ ለዋሻ፣ ፍርኩታ ለፍርኩታ ቢንከራቱም ፣ የፍየል ሌጦ ለብሰው ቢዞሩም የተስፋው ቃል ሁሉን አስረስቶአቸው ከትንቢቱ ባለቤት ጋር በመንፈስ ተዋሕደው አልፈዋል ። ጾሙም ከህዳር 15 እስከ ጌታችን ልደት ድረስ እንዲጾም ቅድስት ቤተክርስትያናችን በስርዓት ደንግጋ አስቀምጣልናለች።



#የጾመ_ነቢያት_ሌሎች_ሥያሜዎች


ጾመ አዳም

ጾመ ነቢያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ስለሆነ ጾመ አዳም ይባላል፡፡

ጾመ ሐዋርያት

ጾመ ነቢያት ሐዋርያት ምን ሠርተን የክርስቶስን ልደት እንቀበለው ብለው ስለጾሙት ጾመ ሐዋርያት ተብሎ ይጠራል፡፡

ጾመ ማርያም

ጾመ ነቢያት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ወልደ አብን ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ በማለት ጾማዋለችና ጾመ ማርያም ይባላል፡፡ ይህን ያለችው በመደነቅ፣ አንድም በትሕትና አንድም ቀደምት አባቶቿ ነቢያት ሲጾሙት አይታ ጾማዋለች፡፡ እንዴት ፀንሼ እወልደዋለሁ ማለት ጥርጥር ሳይሆን ተደሞ፣ መደነቅ የነገረ ልደቱን አይመረመሬነት ይገልጻል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ትሕትና ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በብስራተ መልአክ አማካኝነት ክርስቶስን እንደምትወልድ ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ ስትል ጾማዋለች፡፡

ጾመ ፊልጶስ

ይህ ጾም ጾመ ፊልጶስም ይባላል፡፡ ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡

የጾመ ነቢያት መግቢያው ኅዳር አስራ አምስት ሲሆንም ማብቂያው ልደት ነው፡፡
1.4K viewsBirana Apps, 18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-23 21:20:19
1.2K viewsBirana Apps, 18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-19 11:05:27
#ጸዋትወ_ዜማ

ምዕራፍ ዘቅዱስ ያሬድ
ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ
መዋሥዕት እምዮሐንስ እስከ ዮሐንስ
ዝማሬ ዘቅዱስ ያሬድ
የተክሌ አቋቋም ወዝማሜ ምስለ መዝሙራት
መጽሐፈ ዚቅ ወመዝሙር

የ#12ቱም ወራት የበዓላት ዋዜማና ማህሌት
የአመቱ እሁድ መዝሙራት ከነትርጓሜያቸው

ሊጦን ዘ፯ቱ ዕለታት ወዘበዓላት
መስተብቍዓት
ዘይነግሥ
ፍትሐ ዘወልድ ወበእንተ ቅዱሳት
ትምህርተ ኅቡዓት

መጽሐፈ ሠዓታት በግዕዝ
ማህሌተ ጽጌ
ሰቆቃወ ድንግል
ስርአተ ቅዳሴ
ጸሎተ ኪዳን ዘ፫ቱ ጊዜያት

ይህን ጠቃሚና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ መተግበሪያ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ጭነው ይጠቀሙት ይወዱታል ።

ዋጋው 100 ብር ሲሆን

ስለአከፋፈሉና ሌሎች መረጃዎችን አፑ ላይ ያገኛሉ።
አፑን ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ

Https://play.google.com/store/apps/details?id=org.goranda.tsewatiw

ለበለጠ ይደውሉ

+251901008562
1.5K viewsBirana Apps, edited  08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 21:42:23
#እንኳን_ለጾመ_ፅጌ_በሰላም_አደረሰን።

ማኅሌተ ጽጌ Version 5.0 ተለቀቀ!

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 06 ያሉ ቀናት ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ አቋቋም ተጨምሮበት እንዲሁም የተለያዩ ጠቃሚ ጽሑፎች ታክለውበት በአዲስ ዲዛይን ቀርቦላችኋል ።
ክፍያውን ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ;
#በሞባይል_ባንኪንግ
#ኢንተርኔት_ባንኪንግ እንዲሁም
#በቴሌብር
#በሲቢኢ_ብር እና
#ሄሎ_ካሽ
በዚህ ቁጥር +251901008562 በቀላሉ መክፈል ይችላሉ።
#ዋጋ:
» 50ብር

ለማውረድ playstore ውስጥ ይግቡ ወይም በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል ። https://t.me/joinchat/AAAAAFH0puPPfp7qlWTfdg

Birana Apps
Web: https://biranapps.com
Email: support@biranapps.com
Tel: +251901008562
1.9K viewsBirana Apps, edited  18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-20 21:27:10
#ለቴሌብር_ተጠቃሚዎች_በሙሉ

ብራና አፕስ በቴሌብር ክፍያ መቀበል ጀመረ ።
በዚህ ፈጣንና ቀልጣፋ በሆነው አማራጭ ይጠቀሙ።

ክፍያ ለመፈጸም በዚህ ስልክ ቁጥር ይጠቀሙ
+251901008562

ለበለጠ መረጃ

Web: https://biranapps.com
Email: support@biranapps.com
Tel: +251901008562
1.9K viewsBirana Apps, edited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 15:17:53
እንኳን ከዘመነ #ማቴዎስ ወደ ዘመነ #ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን ። ዘመኑ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የበረከትና የመተሳሰብ ይሁንልን ።

አዱሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በሁሉም አፕሊኬሽኖቻችን ላይ የ50% ቅናሽ ስናደርግ በደስታ ነው ።

አፕሊኬሽኖችን አውርደው በአፑ ላይ ከተጠቀሰው ዋጋ ግማሹን ብቻ ከፍለው የራስዋ ማድረግ ይችላሉ ።

አፖቹን ለማግኘት
https://biranapps.com
Telegram: https://t.me/joinchat/AAAAAFH0puPPfp7qlWTfdg

Phone: +251901008562

መልካም አዲስ ዓመት ።
2.9K viewsgEcH, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ