Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ #ጾመ_ፍልሰታ የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ | ብራና አፕስ Birana Apps

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ

#ጾመ_ፍልሰታ

<ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት ይነገራል።

ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሣቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።