Get Mystery Box with random crypto!

16.09.2018

የቴሌግራም ቻናል አርማ bestsportet — 16.09.2018 1
የቴሌግራም ቻናል አርማ bestsportet — 16.09.2018
የሰርጥ አድራሻ: @bestsportet
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.98K
የሰርጥ መግለጫ

...

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-30 13:23:39
ኤሪክ ቲንሃግ - “የአጨራረስ ድክመታችን በድጋሚ ዋጋ አስከፍሎናል”

>>>  ሙሉውን ለማንበብ  <<<
https://bestsportet.com/2023/04/30/ኤሪክ-ቲንሃግ-የአጨራረስ-ድክመታችን-በ/

Website : www.hattricksportofficial.com
Website : www.bestsportet.com
Facebook : facebook.com/hattricksportofficial
Facebook : facebook.com/bestsportet
Telegram : t.me/bestsportet
Twitter : twitter.com/bestsportet

#ቤስት_ስፖርት_ኢትዮጵያ
የባለቀለሟ ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ አጋር
438 viewsYishak Belay, edited  10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:11:41 የዛምቢያን እግር ኳስ የለወጠው አሳዛኙ የአውሮፕላኑ አደጋ ክስተት ሰላሳ አመት ሞላው

ሚያዝያ 28 1993 እ.ኤ.አ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ሴኔጋል ዳካር ማቅናት ነበረበት።

የብሄራዊ ቡድኑ አባላት የያዘው አውሮፕላን ነዳጅ ለመሙላት በሚል በጋቦን ሊብረቪል አረፈ።

ከደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ ጉዞ ለማድረግ የተነሳው እድሜ ጠገቡ የካናዳ ስሪት አውሮፕላን ደ ሀቪላንድ የመከስከስ አደጋ አጋጥሞት ባህር ላይ ለመውደቅ ተገደደ።በውስጡ የነበሩ አስራ ስምንት ተጫዋቾችን ጨምሮ አስራ ሁለት ሌሎች በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ተጓዦች በአደጋው ህይወታቸውን አጡ።

አንድም ሰው ከአደጋው መትረፍ አልቻለም።
" የወርቃማው ትውልድ "  የነበረው ወጣት ተጫዋቾች ስብስብ በብዛት የነበሩበት ቡድን  ህይወት የቀጠፈው አደጋ በአፍሪካ እግር ኳስ ከደረሱ መካከል አስከፊው ነው።

ዛምቢያ ከእዛ ከባድ አደጋ አገግሞ እግር ኳሷ በትንሳኤ መነሳት ግን  ችሏል።

ከ19 አመታት በኋላ በጋቦን በተዘጋጀው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በፈረንሳዊው አሰልጣኝ ሀርቪዬ ሬይናርድ እየተመራች የአህጉራዊውን መድረክ ዋንጫ አነሳች።

በወቅቱ ከአደጋው ከተረፉ በአውሮፓ ይጫወቱ ከነበሩ ጥቂት የማይባሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ካሉሺያ ቡዋሊያ እና ቻርልስ ሙሶንዳ ይጠቀሳሉ።

እነዚህ ሁለት ተጫዋቾች ለአውሮፓዎቹ ክለቦች ፒኤስቪ አይንድሆቨን እና አንደርሌክት ይጫወቱ ስለነበር ወደ ዳካር ያቀኑት በሌላ አውሮፕላን ነበር።

ካሉሺያ ታሪኩን አሁንም መልስ ብሎ ሲያስታውሰው ለመግለጽ አዳጋች እንደሆነ ይናገራል።

ከዚያን ጊዜው የሀገሬው ፕሬዝዳንት ፍሬድሪክ ቺሉባ ጋር ለቀብሩ ወደ ሀገር ቤት ሲመለስ ማውራቱንም ያስታውሳል።

በወቅቱ ቹሉባ ዛምቢያ ከሀዘኑ በቶሎ ወጥታ ብሄራዊ ቡድኗን እንደ አዲስ መገንባት እንዳለባት እንዳወሩት ካሉሺያ ይናገራል።

በፈረንጆቹ ሀምሌ 4 1993 ቺፖሎፖሎዎቹ ከአደጋው ስልሳ ሰባት ቀናት በኋላ በአለም ዋንጫ ማጣሪያው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ከሞሮኮ ጋር አደረጉ።

ከሴኔጋል ጋር በዳካር የነበረው ጨዋታ መራዘሙን ተከትሎ ማለት ነው።

እሱን ቡድን በድጋሚ አዋቅሮ በመስራት በኩል ዴንማርካዊው ሮአልድ ፖውልሰን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።

ከአደጋው በኋላ ፖልሰን በወቅቱ በአውሮፓ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ይዞ በኮፕንሀገን ካምፕ የሶስት ሳምንት ቆይታ በማድረግ በሀገሪቱ ሊግ ከሚሳተፉ የተለያዩ ክለቦች የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን አደረገ።

በወቅቱ ቡድኑ 16 ተጫዋቾችን፣ ሁለት የአሰልጣኝ ስታፍ አባላት እና ፊዚዮቴራፒስት ይዞ ነበር።

ዛምቢያ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሞሮኮ ጋር የምድብ የመልስ ጨዋታ በአወዛጋቢ ሁኔታ ተሸንፋ ከአለም ዋንጫው ቀረች።

ከአውሮፕላን አደጋው አስራ ሁለት ወራት በኋላ ግን በአስደናቂ ሁኔታ ቱኒዚያ ባሰናዳችው የአፍሪካ ዋንጫ ለፍጻሜ መድረስ ቻለች።

በፍጻሜው በጠንካራዋ ናይጄሪያ ሁለት ለአንድ ተረታ ዋንጫውን አጣች።

ሬይናርድ በዛምቢያ እግር ኳስ እንደ ልዑል ሊታይ ይችላል።ምክንያቱም ንጉሱ የነበረው  ከአስከፊው አደጋ በኋላ ብሄራዊ ቡድኑን የሰራው ዴንማርካዊ ፖልሰን ነው።

Website : www.hattricksportofficial.com

Website : www.bestsportet.com

Facebook : facebook.com/hattricksportofficial

Facebook : facebook.com/bestsportet

Telegram : t.me/bestsportet

Twitter : twitter.com/bestsportet

#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...
468 viewsYishak Belay, edited  10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 09:37:52
ዋናው የስፖርት አልባሳት

አዳዲስ ባመጠናቸው ዘመናዊ ማሽነሪዎች ያሻዎትን ማንኛውም የስፖርት አልባሳት በፈለጉት ምርጫ ከ "ዋናው " ያገኛሉ ።

የጤና ቡድን ላላችሁ ድርጅት እንዲሁም ማንኛውም አካላት ስም እና መለያ ቁጥር የታተመበት ማልያ ብዛት ከሀያ ጀምሮ በፈለጉት መጠን ይዘዙን።

የፈለጉትን ዲዛይን ሰርተን #ከሀያ ብዛት ጀምሮ በ 500ብር በአስር የስራ ቀናት ውስጥ እናስረክቦታለን።

ከዋናው የስፖርት አልባሳት

ይደውሉ :- 0910 851 535   
                      0901138283

ቻናላችን :- https://t.me/wanawsportwear

አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት
208 viewsYishak Belay, edited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 07:36:14
በይስሀቅ በላይ(የሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣና ቤስት ስፖርት ኢትዮጵያ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር)

ዛምቢያዎች በአትሌቲክስ ቡድናችን ላይ ግፍ ፈፅመዋል

በአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ወደ ዛምቢያ የተጓዘው የአትሌቲክስ ብ/ቡድናችን በዛምቢያ ከፍተኛ መጉላላት ደርሶበታል።

የነገ የአትሌቲክሱን ኮከቦች የያዘው የአትሌቲክስ ብ/ቡድናችን በቂ ማረፊያ ሳይዘጋጅለት እንዲሁም ውድድሩ ከሚካሄድበት 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንዲያርፍ በማድረግ የዛምቢያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የውድድሩ አዘጋጅ ኮሜቴ ተገቢውን ክብርና መስተንግዶ ተነፍጎ የከፋ ግፍ ተፈፅሞበታል።

ቡድኑ ውድድሩ ከሚካሄድበት 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንዲጓዝ መደረጉ ሳያንስ የሚያርፉበት ሆቴል ሳይዘጋጅለት በአንድ ሎቢ ውስጥ መሬት ላይ ተኝተው ማድራቸው ብዙዎችን ለከፍተኛ ብስጭት ዳርጓል፤እንደ ሀገርም አንገት አስደፍቷል።

ጀግናዋ አትሌት ረዳት ኮሚሽነር የአህጉሪቱን አትሌቲክስ በምክትል ፕሬዘዳንትነት ለቀጣይ አራት አመታት እንድትመራ መመረጧ ከተሠማባት ዛምቢያ በሁለት ቀናት ልዩነት ይሄ ልብ ሰባሪ አሳዛኝ ክስተት መሰማቱ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

ይህ የዛምቢያዎች ድርጊት በቸልታ የሚታይ ካለመሆኑም ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑም እንደ መንግስትም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም ከአዘጋጅ ኮሚቴው በቂ ማብራሪያና ይቅርታ ሊጠይቅበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ በርካቶች ቁጭት በተሞላበት ስሜት እየጠየቁ ይገኛሉ።


ፎቶ ክሬዲት:የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ
294 viewsYishak Belay, edited  04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 07:22:33
ኮሎ ቱሬ ምባፔና ሀላንድ የሜሲና የሮናልዶ አልጋ ወራሾች ይሆናሉ አለ

የቀድሞ ኮትዲቯራዊ ኢንተርናሽናል ኮሎ ቱሬ ወጣቶቹ ኮከቦች ክልያን ምባፔ እና አርሊንግ ብራውት ሀላንድ የሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ አንጻባራቂ እግር ኳስ ህይወት ወራሾች ይሆናሉ ሲል ተናግሯል።

ሀላንድ ባሳለፍነው ክረምት የፕሪሚየር ሊጉን ክለብ ማንቺስተር ሲቲ ከተቀላቀለ በኋላ በሁሉም ውድድሮች አርባ ዘጠኝ ጎሎችን ከመረብ ማገናኘት መቻሉ ይታወቃል።

ምባፔ በበኩሉ በውድድር ዘመኑ እንደ ቀደሙት አመታት ሁሉ አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ የሚገኝ ሲሆን በኳታሩ 2022 አለም እግር ኳስ ዋንጫ ከሀገሩ ፈረንሳይ ጋር እስከ ፍጻሜ ከመጓዙ በተጫማሪ የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማውን ማግኘት ችሏል።


Website : www.hattricksportofficial.com

Website : www.bestsportet.com

Facebook : facebook.com/hattricksportofficial

Facebook : facebook.com/bestsportet

Telegram : t.me/bestsportet

Twitter : twitter.com/bestsportet

#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...
265 viewsYishak Belay, edited  04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 07:19:59
ጋሬዝ ቤል ከጡረታ ተመልሶ በድጋሚ ወደ እግር ኳሱ መመለስ የሚችልበት አማራጭ ቀርቦለት ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል

በሆሊውዱ ታዋቂ የፊልም ተዋናይ ሪያን ሬይኖልድስ እና ማክ ኤልሄኒ የጋራ ባለቤትነት የሚተዳደረው እና በቅርቡ ወደ ሊግ ሁለት ያደገው ሬክስሀም ለቀድሞ ኮከብ ጥያቄ ያቀረበ ክለብ መሆኑም ተገልጿል።

ቤል አንጸባራቂ የነበረው የእግር ኳስ ህይወቱ ባሳለፍነው የጥር ወር ማብቃቱን  ማስታወቁ የሚታወስ ነው።


Website : www.hattricksportofficial.com

Website : www.bestsportet.com

Facebook : facebook.com/hattricksportofficial

Facebook : facebook.com/bestsportet

Telegram : t.me/bestsportet

Twitter : twitter.com/bestsportet

#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...
237 viewsYishak Belay, edited  04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 07:16:49
የካታሩ ባለሀብት ሼይክ ጃሲም ቢን ሀማድ ታሂኒ እና ሰር ጂም ራትኪልፍ ኢኖኦስ የመጨረሻ የግዢ ሂሳብ ለማንቺስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ ማቅረባቸውን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል

የክለቡ ባለቤት የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች እስከ ትላንት እኩለ ለሊት ድረስ የመጨረሻ የግዥ ሂሳብ እንዲቀርብላቸው ቀነ ገደብ ማስቀመጣቸው ይታወቃል።

ዩናይትድ ካሳለፍነው የህዳር ወር አንስቶ በይፋ ለሽያጭ መቅረቡ መገለጹ የሚታወቅ ነው።

የካታሩ የባንክ ሰው ጃስሚን ትላንት ምሽት እስከ 5 ቢሊየን ፓወንድ ማቅረባቸውም ታውቋል።


Website : www.hattricksportofficial.com

Website : www.bestsportet.com

Facebook : facebook.com/hattricksportofficial

Facebook : facebook.com/bestsportet

Telegram : t.me/bestsportet

Twitter : twitter.com/bestsportet

#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...
225 viewsYishak Belay, edited  04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 07:12:15
ሉካ ሞድሪች በጉዳት ጨዋታዎች ያመልጡታል

የሪያል ማድሪዱ ክሮሺያዊ አማካይ ሉካ ሞድሪች በጉዳት ምክንያት በኮፓ ዴላሬው ፍጻሜ እና በሻምፒየንስ ሊጉ ግማሽ ፍጻሜ የደርሶ መልስ የሙጀመሪያ ጨዋታ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው ተባለ።

የ 37 አመቱ ድንቅ አማካይ በግራ እግሩ የጭን የኋላ ክፍል ላይ የህመም ስሜት እንዳለበት በራሱ አንደበት መናገሩ ይፋ ተደርጓል።

የስፔኑ ክለብ በኮፓ ዴላሬው ፍጻሜ በፈረንጆቹ ግንቦት 6 ከኦሳሱና እና በሻምፒየንስ ሊጉ ደግሞ ከማንቺስተር ሲቲ ጋር የግማሽ ፍጻሜ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታውን ግንቦት 9 የሚያደርግ ይሆናል።


Website : www.hattricksportofficial.com

Website : www.bestsportet.com

Facebook : facebook.com/hattricksportofficial

Facebook : facebook.com/bestsportet

Telegram : t.me/bestsportet

Twitter : twitter.com/bestsportet

#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...
261 viewsYishak Belay, edited  04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 20:08:36 ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ  ጸንታለች...ቅዳሜ  ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል.....

በአራት አሰልጣኞች ስር  ያገኘሁት  ስልጠና ጠቅሞኛል ሲል ይናገራል...ከልጅነት ጀምሮ ያደኩበት ክለብ ነው... ከቢ ቡድን  የተጀመረ  ታሪክ አለኝ ሲልም ይናገራል...ቢ ቡድን እያለ በአሰልጣኝ ግርማይ ኪሮስ ለሁለት አመት ከሰለጠነ በኋላ  በ2010  አሰልጣኝ ውበቱ  አባተ ፋሲል ከነማን ሲረከብ ለ2011 የውድድር አመት አምስት ተጨዋቾችን በማሳደግ ዋናውን ቡድን እንዲቀላቀሉ ሲወስን እድሉን ካገኙት መሃል  አንዱ እንግዳችን ነው..
ያለቤተሰብ በተለይ ያለ እህቴ ድጋፍ እዚህ አልደርስም ነበር ሲል ያመሰግናቸዋል... "ተጋጣሚዬ ማንም ይሁን ፍርሃት ተሰምቶኝ አያውቅም" የሚለው እንግዳችን የፋሲል ከነማው ተስፈኛ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ ነው.... ከሀትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው ተጨዋቹ  "ኢትዮጵያ ውስጥ የጌታነህ ከበደና የአብዱረህማን ሙባረክ አድናቂ ነኝ" በማለት አድናቆቱን ገልጾላቸዋል..ቃለምልልሱን ይዘናል...

*....የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ  የሃላፊነት ስልጣን ከሀገር ውስጥ   ወደ አፍሪካዊ ሃላፊነት ተሻግሯል... የሀትሪክ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር ይስሃቅ በላይ የደራርቱን አፍሪካዊ ተፅዕኖ  የገለፀበትን ዘገባ አካተናል...

*... የፋሲል ከነማና  የቀድሞ አሰልጣኙ ሃይሉ ነጋሽ
/ቲጋና/ ጉዳይ እልባት አላገኘም የዲሲፕሊን ኮሚቴ ለውሳኔ እንዲረዳው አሰልጣኙ ለክለቡ ያስገባውን እቅድ ባለፈው ማክሰኞ ደርሶታል  የኮሚቴውም ውሳኔ እየተጠበቀ ነው... የሀትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ አሁን ያለበትን የሁለቱን ወገኖች ክርክር አዘጋጅቶታል.....


    ...ከውጪ ዘገባዎቻችን ደግሞ......


*....በእንገሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማን.ሲቲ አርሰናልን በሰፊ ግብ በመርታት የሊጉን ዋንጫ የማንሳት  እድሉን  አስፍቷል...የጋርዲዮላ ቡድን ላሳካው ድል የመጀመሪያ ግብ ያስቆጠረው ኬቨን ዴብሩይነ "የአርሰናሉ ድል የሚገባን ነው" ሲል ምርጥ አቋም ማሳየታቸውን  ተናግሯል.... በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃ ይዘናል..

*... የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ  ዋንጫ ወደ ማን.ሲቲ ፊቱን ማዞሩን በበርካቶች ቢታመንም የመድፈኞቹ ግብ ጠባቂ ግን ተስፋ አልቆረጠም...አሮን ራምስዴል " ከማን.ሲቲ በላይ ሆነን ማጠናቀቅ እንደምንችል እምነቱ አለን" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል...በዚህ ላይ መረጃዎችን ይዘናል...


*.... ማን.ዩናይትድ  ቶተንሃምን 2ለ0 የመራበትን ጨዋታ በ2ለ2  አቻ ውጤት  አጠናቋል....የቡድኑ ተሰላፊ የሆነው ጄደን ሳንቾ ደግሞ " የትኩረት ማነስ  በድጋሚ ነጥብ  እንድንጥል አድርጎናል" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል...በዚህ ዙሪያ ዘገባ አዘጋጅተናል...

*.... ሆላንዳዊው የሊቨርፑል ተጫዋች ኮዲ ጋክፖ ዌስትሃምን ከሜዳቸው ውጪ በማሸነፋቸው ተደስቷል... "በዌስትሃም ላይ ያገኘነው  ድል ዋጋ ከፍ ያለ ነው" ሲል የቡድን አጋሩ አንዲ ሮበርትሰን በበኩሉ "የውድድር ዘመናችን በጥሩ መንገድ እንደሚጠናቀቅ ተስፋ እናደርጋለን" ብሏል..በዚህ ላይ መረጃዎችን ይዘናል

*...እስቲ ስለ ሰር ጂምራች ክሊፍ እናውራ...እኚህ ባለ 6 ቢሊዮን ፓውንድ ባለቤት በአንድ ወቅት ከስራቸው ተባረው የነበሩ ሰው ናቸው ..በወቅቱ የነጡ ያጡ ደሃ የነበሩት የአሁኑ ባለሀብት  ማን.ዩናይትድን ለመግዛት ቆርጠዋል ተብሎ እየተነገረ ነው ...በኚህ ባለሀብትና  ዩናይትድን የመጠቅለል  ፍላጎታቸው ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል...



        .....እናም ሌሎችንም.......

    እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን  
    በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር
     የሚጨብጡበት  አዳዲስ መረጃዎችን  
         የሚያገኙበት  ይሆናል.....

የመጀመሪያዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ የቤስት ስፖርት ኢትዮጵያ እህት ሚዲያ

    ....ቅዳሜና እሁዳችሁ  የተባረከ ይሁን.....
531 viewsYishak Belay, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 20:07:41
412 viewsYishak Belay, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ