Get Mystery Box with random crypto!

የዛምቢያን እግር ኳስ የለወጠው አሳዛኙ የአውሮፕላኑ አደጋ ክስተት ሰላሳ አመት ሞላው ሚያዝያ 28 | 16.09.2018

የዛምቢያን እግር ኳስ የለወጠው አሳዛኙ የአውሮፕላኑ አደጋ ክስተት ሰላሳ አመት ሞላው

ሚያዝያ 28 1993 እ.ኤ.አ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ሴኔጋል ዳካር ማቅናት ነበረበት።

የብሄራዊ ቡድኑ አባላት የያዘው አውሮፕላን ነዳጅ ለመሙላት በሚል በጋቦን ሊብረቪል አረፈ።

ከደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ ጉዞ ለማድረግ የተነሳው እድሜ ጠገቡ የካናዳ ስሪት አውሮፕላን ደ ሀቪላንድ የመከስከስ አደጋ አጋጥሞት ባህር ላይ ለመውደቅ ተገደደ።በውስጡ የነበሩ አስራ ስምንት ተጫዋቾችን ጨምሮ አስራ ሁለት ሌሎች በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ተጓዦች በአደጋው ህይወታቸውን አጡ።

አንድም ሰው ከአደጋው መትረፍ አልቻለም።
" የወርቃማው ትውልድ "  የነበረው ወጣት ተጫዋቾች ስብስብ በብዛት የነበሩበት ቡድን  ህይወት የቀጠፈው አደጋ በአፍሪካ እግር ኳስ ከደረሱ መካከል አስከፊው ነው።

ዛምቢያ ከእዛ ከባድ አደጋ አገግሞ እግር ኳሷ በትንሳኤ መነሳት ግን  ችሏል።

ከ19 አመታት በኋላ በጋቦን በተዘጋጀው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በፈረንሳዊው አሰልጣኝ ሀርቪዬ ሬይናርድ እየተመራች የአህጉራዊውን መድረክ ዋንጫ አነሳች።

በወቅቱ ከአደጋው ከተረፉ በአውሮፓ ይጫወቱ ከነበሩ ጥቂት የማይባሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ካሉሺያ ቡዋሊያ እና ቻርልስ ሙሶንዳ ይጠቀሳሉ።

እነዚህ ሁለት ተጫዋቾች ለአውሮፓዎቹ ክለቦች ፒኤስቪ አይንድሆቨን እና አንደርሌክት ይጫወቱ ስለነበር ወደ ዳካር ያቀኑት በሌላ አውሮፕላን ነበር።

ካሉሺያ ታሪኩን አሁንም መልስ ብሎ ሲያስታውሰው ለመግለጽ አዳጋች እንደሆነ ይናገራል።

ከዚያን ጊዜው የሀገሬው ፕሬዝዳንት ፍሬድሪክ ቺሉባ ጋር ለቀብሩ ወደ ሀገር ቤት ሲመለስ ማውራቱንም ያስታውሳል።

በወቅቱ ቹሉባ ዛምቢያ ከሀዘኑ በቶሎ ወጥታ ብሄራዊ ቡድኗን እንደ አዲስ መገንባት እንዳለባት እንዳወሩት ካሉሺያ ይናገራል።

በፈረንጆቹ ሀምሌ 4 1993 ቺፖሎፖሎዎቹ ከአደጋው ስልሳ ሰባት ቀናት በኋላ በአለም ዋንጫ ማጣሪያው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ከሞሮኮ ጋር አደረጉ።

ከሴኔጋል ጋር በዳካር የነበረው ጨዋታ መራዘሙን ተከትሎ ማለት ነው።

እሱን ቡድን በድጋሚ አዋቅሮ በመስራት በኩል ዴንማርካዊው ሮአልድ ፖውልሰን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።

ከአደጋው በኋላ ፖልሰን በወቅቱ በአውሮፓ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ይዞ በኮፕንሀገን ካምፕ የሶስት ሳምንት ቆይታ በማድረግ በሀገሪቱ ሊግ ከሚሳተፉ የተለያዩ ክለቦች የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን አደረገ።

በወቅቱ ቡድኑ 16 ተጫዋቾችን፣ ሁለት የአሰልጣኝ ስታፍ አባላት እና ፊዚዮቴራፒስት ይዞ ነበር።

ዛምቢያ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሞሮኮ ጋር የምድብ የመልስ ጨዋታ በአወዛጋቢ ሁኔታ ተሸንፋ ከአለም ዋንጫው ቀረች።

ከአውሮፕላን አደጋው አስራ ሁለት ወራት በኋላ ግን በአስደናቂ ሁኔታ ቱኒዚያ ባሰናዳችው የአፍሪካ ዋንጫ ለፍጻሜ መድረስ ቻለች።

በፍጻሜው በጠንካራዋ ናይጄሪያ ሁለት ለአንድ ተረታ ዋንጫውን አጣች።

ሬይናርድ በዛምቢያ እግር ኳስ እንደ ልዑል ሊታይ ይችላል።ምክንያቱም ንጉሱ የነበረው  ከአስከፊው አደጋ በኋላ ብሄራዊ ቡድኑን የሰራው ዴንማርካዊ ፖልሰን ነው።

Website : www.hattricksportofficial.com

Website : www.bestsportet.com

Facebook : facebook.com/hattricksportofficial

Facebook : facebook.com/bestsportet

Telegram : t.me/bestsportet

Twitter : twitter.com/bestsportet

#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...