ኮሎ ቱሬ ምባፔና ሀላንድ የሜሲና የሮናልዶ አልጋ ወራሾች ይሆናሉ አለ
የቀድሞ ኮትዲቯራዊ ኢንተርናሽናል ኮሎ ቱሬ ወጣቶቹ ኮከቦች ክልያን ምባፔ እና አርሊንግ ብራውት ሀላንድ የሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ አንጻባራቂ እግር ኳስ ህይወት ወራሾች ይሆናሉ ሲል ተናግሯል።
ሀላንድ ባሳለፍነው ክረምት የፕሪሚየር ሊጉን ክለብ ማንቺስተር ሲቲ ከተቀላቀለ በኋላ በሁሉም ውድድሮች አርባ ዘጠኝ ጎሎችን ከመረብ ማገናኘት መቻሉ ይታወቃል።
ምባፔ በበኩሉ በውድድር ዘመኑ እንደ ቀደሙት አመታት ሁሉ አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ የሚገኝ ሲሆን በኳታሩ 2022 አለም እግር ኳስ ዋንጫ ከሀገሩ ፈረንሳይ ጋር እስከ ፍጻሜ ከመጓዙ በተጫማሪ የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማውን ማግኘት ችሏል።
Website : www.hattricksportofficial.com
Website : www.bestsportet.com
Facebook : facebook.com/hattricksportofficial
Facebook : facebook.com/bestsportet
Telegram : t.me/bestsportet
Twitter : twitter.com/bestsportet
#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...