Get Mystery Box with random crypto!

በይስሀቅ በላይ(የሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣና ቤስት ስፖርት ኢትዮጵያ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር) ዛምቢያዎ | 16.09.2018

በይስሀቅ በላይ(የሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣና ቤስት ስፖርት ኢትዮጵያ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር)

ዛምቢያዎች በአትሌቲክስ ቡድናችን ላይ ግፍ ፈፅመዋል

በአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ወደ ዛምቢያ የተጓዘው የአትሌቲክስ ብ/ቡድናችን በዛምቢያ ከፍተኛ መጉላላት ደርሶበታል።

የነገ የአትሌቲክሱን ኮከቦች የያዘው የአትሌቲክስ ብ/ቡድናችን በቂ ማረፊያ ሳይዘጋጅለት እንዲሁም ውድድሩ ከሚካሄድበት 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንዲያርፍ በማድረግ የዛምቢያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የውድድሩ አዘጋጅ ኮሜቴ ተገቢውን ክብርና መስተንግዶ ተነፍጎ የከፋ ግፍ ተፈፅሞበታል።

ቡድኑ ውድድሩ ከሚካሄድበት 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንዲጓዝ መደረጉ ሳያንስ የሚያርፉበት ሆቴል ሳይዘጋጅለት በአንድ ሎቢ ውስጥ መሬት ላይ ተኝተው ማድራቸው ብዙዎችን ለከፍተኛ ብስጭት ዳርጓል፤እንደ ሀገርም አንገት አስደፍቷል።

ጀግናዋ አትሌት ረዳት ኮሚሽነር የአህጉሪቱን አትሌቲክስ በምክትል ፕሬዘዳንትነት ለቀጣይ አራት አመታት እንድትመራ መመረጧ ከተሠማባት ዛምቢያ በሁለት ቀናት ልዩነት ይሄ ልብ ሰባሪ አሳዛኝ ክስተት መሰማቱ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

ይህ የዛምቢያዎች ድርጊት በቸልታ የሚታይ ካለመሆኑም ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑም እንደ መንግስትም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም ከአዘጋጅ ኮሚቴው በቂ ማብራሪያና ይቅርታ ሊጠይቅበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ በርካቶች ቁጭት በተሞላበት ስሜት እየጠየቁ ይገኛሉ።


ፎቶ ክሬዲት:የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ