Get Mystery Box with random crypto!

ብርቱ ወጣት | Bertu Wetat

የቴሌግራም ቻናል አርማ bertuwetat — ብርቱ ወጣት | Bertu Wetat
የቴሌግራም ቻናል አርማ bertuwetat — ብርቱ ወጣት | Bertu Wetat
የሰርጥ አድራሻ: @bertuwetat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 802
የሰርጥ መግለጫ

ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ወደዚህ ባለ ራእይ ቻናል በሰላም ተቀላቀሉ!
በቻናሉ በሚነሱ በማናቸውም ሀሳቦችና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ወጣት ተኮር በሆነ መልኩ በጥልቀት ይቃኛሉ።
ኅልቆ-ወመሳፍርት የሆኑት የኛ የወጣቶች ችግሮቻችንን እስከነ መፍትሄ አቅጣጫዎቻቸው እየዳሰስን #ብርቱ_ወጣት እንፈጥራለን።
💚 ከእናንተ_ቅንነት 💛 ለእናንተ_በኛ መጠነኛ ድጋፍ ❤ #ብርቱ_ወጣት እንፈጥራልን።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-24 08:35:29
የ#ብርቱ_ወጣት ቻናል ዓላማ የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
12%
ሀ, የወጣቶችን ድክመት ነቅሶ ማውጣትና በችግሩ ዙርያ አስተያየት መስጠት።
12%
ለ, የዘመኑ ወጣት ስለሚያስደስተው ጉዳይ በስፋት መዳሰስ።
5%
ሐ, የወጣቶችን ድክመትና ጥንካሬ በማጉላት በዛ ዙርያ መተቸት።
42%
መ, ወጣቶች በሃይማኖትና በምግባር የጸኑ እንዲሆኑ እና ችግሮቻቸውን እርስ በእርስ በመወያየት መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ።
27%
ከ "ለ" በቀር ሁሉም መልስ ነው።
73 voters527 views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 18:54:17
ከኬብ ጋር የነበረኝን ቆይታ ተጋበዙልኝ ቢያንስ አንድ ነገር ትማሩበታላችሁ!



134 views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 04:44:27
መንፈሳዊ ወጣትነት

የሰው ልጅ በተለይ እኛ ወጣቶች የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ሁሉም ግልጽ የሆነ መፍትሔ ላይገኝላቸው ይችላል። ፈተና ስንል የግድ የመከራና ችግር መፈራረቅ ብቻ ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ ያሰቡት(ያቀዱትን) በዕለቱ እንዳንፈጽም የሚያደርግ ፈተና ፣ ምክንያቱ ያልታወቀ የጠባይ ለውጥ ፣ ወይም ደሞ የስሜት መለዋወጥን ብንመለከት ትናንት ወደድኩህ ከጎኔ አትራቅ ብለን የፍቅሩን ናፍቆት መጋፈጥን እንዳልፈራን ዛሬ ላይ ያ የቀድሞ ስሜታችን ጠፍቶ ይባስ ብሎ ለዐይናችንም እስክንጠየፈው የሚያደርሰን ዓይነት ፈተና ሁሉ ውሉ የማይጨበጥ የኛ የወጣቶች ፈተና ነው።

ስለዚህ ለእንደዚህ ዓይነት ፈተናዎችም ሆነ ኑሮን በስክነት ለመምራት መንፈሳዊነትን የመሰለ ጋሻ ፣ አማኝነትን የመሰለ ዋሻ የለም! ጋሻ ከተሰበቀ ጦር እንደሚከላከል ሁሉ መንፈሳዊነትም ከክፉ(ከማይጠቅም) ፈተና ይጠብቀናል ፤ ዋሻ ከዱር አውሬ ጥቃት የምናመልጥበት መጠለያ እንደሆነ ሁሉ አማኝነትም ከጠላት ክፉ ምክርና ሐሳብ መደበቂያ ባዕታችን ናት።

"የዘመኑ ኃላፊ ዘመናዊነት በፈረንጅ ኢ-አማኒነት ቢለካም እኛ ግን አማኞች በመሆን የማያልፈውን ዘመን እንዋጃልን! ምክንያቱም #ብርቱ_ወጣቶች ነን! "

በርቱ!

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat
1.3K views01:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 04:28:49 የወጣቶች ጥያቄ....

ጥያቄ_ #የመጨረሻ_ክፍል
ለፍቅረኛዬ መታመኔን እንዴት ላሳይ?

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ፍቅረኛ ከመያዛቸው በፊት ስለራሳቸው ያላቸው አመለካከት ፍቅረኛ ከያዙ በኋላ በዛው ላይቀጥል ይችላል። እንበልና አንድ ወጣት ፍቅር ውስጥ ከመግባቱ በፊት ታማኝ እንደሆነ ሊያስብ ይችላል ፤ አልፎ ተርፎም የወደፊት የፍቅር ጓደኛውን በመታመን ጉዳይ ሊያስከፋት እንደማይችልም ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ሊሆን ይችላል። ይህን ማሰቡ መልካም ሆኖ ሳለ አንዳንዴ ግን "እኔ እንዲህ ነኝ!" ብለህ የተማመንክበት ነገር በጊዜ ፣ በሁኔታ ፣ በጠባይ መቀየር ፣ በአዋዋል ወ.ዘ.ተ ምክንያት ተቀይሮ ታገኘዋለህ። የዛን ጊዜ አንተ በጊዜው የሆንከው ነገር እንጂ አንተ ስለ አንተ ታስብ የነበረው ነገር ልክ እንዳልሆነ ይገባሃል።

አብዛኛው የፍቅር ግንኙነት የሚጠለሸው ባለማመንና ባለመታመን ችግር ነው። አንዳንዴ ታምኖ መገኘት ብቻም ሳይሆን ታማኝ መሆንህን በተጨባጭ የምታሳይበት መንገድም ለፍቅር ግንኙነት መሳካት ትልቅ ሚና አለው።

መታመኔን እንዴት ላሳይ?

➪ የፍቅር አጋርህ ተብላ መጠራቷ ያንተ የሆነን ነገር ፣ ካንተ የመጣን ነገር ፣ ላንተ የሚደረግን ነገር ሁሉ የምትጋራህ ከመሆኗ አንጻር እንደመሆኑ የምታደርገውን ነገር ፣ የዋልክበትን ፣ ያደርክበትን ሁሉ በግልጽ ንገራት!

➪ ቅናት ሊፈጥርባት የሚችሉ ነገሮችን ከጎንህ አርቅ! አንዳንድ ሰው ቅናት የፍቅር መገለጫ ይመስለዋልና እውነታው ግን ቅናት አጥንትን የሚያነቅዝ መርዝ ነው።

➪ ዘወትር ፍቅርህን ለመግለጽ አትታክት! ከቃላት ባለፈ ደግሞ ተግባርህም የተጠና ይሁን።

➪ የሷን ታማኝነት አትጠራጠር! ለመታመን የመጀመርያው መስፈርት አምኖ መገኝት ነውና ፍቅረኛዬ ታማኝ ባትሆንስ? እያሉ በመጠራጠር መታመን ፈጽሞ አይቻልም።

በርቱ!

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat
3.3K views01:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 09:39:52
የወጣቶች ጥያቄ...

ጥያቄ_24 #ክፍል_2
የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር መቸኮል የሌለብህ ለምንድን ነው?

  ዝግጁ ሳትሆን የፍቅር ጓደኝነት እንድትጀምር የሚደረግብህ ጫና በደንብ ያልተማርከውን ትምህርት እንድትፈተን ከመገደድ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ይህ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ግልጽ ነው! ፈተና ላይ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች መመለስ እንድትችል ትምህርቱን ለማጥናት ጊዜ ያስፈልግሃል።

 'የፍቅር ጓደኝነት በመመሥረት ረገድም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።'

  የፍቅር ጓደኝነት መመሥረት እንደ ዋዛ የሚታይ ነገር አይደለም። በመሆኑም ከአንዲት ወጣት ጋር የፍቅር ጓደኝነት ስለ መጀመር ከማሰብህ በፊት በጣም አስፈላጊ የሆነን አንድ “ትምህርት” ለማጥናት ይኸውም ወዳጅነት መመሥረት የሚቻልበትን መንገድ ለመማር በቂ ጊዜ ያስፈልግሃል።

  እንዲህ ካደረግህ ከጊዜ በኋላ፣ የምትሆንህን ወጣት ስታገኝ ጠንካራ ግንኙነት ለመመሥረት የተሻለ አቋም ይኖርሃል። ጥሩ ጋብቻ የሁለት ጥሩ ጓደኛሞች ጥምረት መሆኑን አትዘንጋ።

 የፍቅር ጓደኝነት ሳትጀምር መቆየትህ ነፃነትህን እንደሚገድብብህ ማሰብ የለብህም። እንዲያውም ‘የወጣትነትህን ጊዜ አስደሳች’ በሆነ መንገድ ለማሳለፍ የበለጠ ነፃነት ይሰጥሃል። ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ባሕርያትን በማዳበርና ከምንም በላይ ደግሞ መንፈሳዊነትህን በማጠናከር ራስህን ለማዘጋጀት የሚያስችል ጊዜ ይኖርሃል።

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat
2.3K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 18:03:20

336 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:21:52
የወጣቶች ጥያቄ...

ጥያቄ_24 #ክፍል_1
የፍቅር ጓደኝነት የሚመሠረትበት ዓላማ ምንድን ነው?

  የፍቅር ጓደኝነት የሚመሠረትበት ዓላማ ክብር ያለው መሆን ይኖርበታል ፤ ዓላማው አንድ ወንድና አንዲት ሴት በትዳር መጣመር ይችሉ እንደሆነና እንዳልሆነ ለመወሰን የሚያስችል አጋጣሚ መፍጠር ሊሆን ይገባል።

 እርግጥ ነው፣ አንዳንድ እኩዮችህ የፍቅር ጓደኝነት መመሥረትን በቁም ነገር አይመለከቱት ይሆናል። ምናልባትም ምንም የማግባት እቅድ ሳይኖራቸው ተቃራኒ ፆታ ካለው አንድ ግለሰብ ጋር ልዩ ቅርርብ መፍጠር ያስደስታቸው ይሆናል። እንዲያውም አንዳንዶች እንዲህ ዓይነት ጓደኝነት የሚመሠርቱት እንዲሁ ከተቃራኒ ፆታ ጋር አብረው መታየት ስለሚፈልጉ ሊሆን ይችላል ፤ ወይም ደግሞ ተፈላጊ መሆናቸውን ለማሳየት ይሆናል።

  ይሁንና እንዲህ ዓይነት ብስለት የጎደለው አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሚመሠርቱት የፍቅር ጓደኝነት አብዛኛውን ጊዜ በአጭሩ ይቀጫል።

  ከአንዲት ወጣት ጋር የፍቅር ጓደኝነት ስትመሠርት ለአንተ ልዩ ስሜት ሊያድርባት እንደሚችል ማስታወስ ይኖርብሃል። በመሆኑም የፍቅር ግንኙነት የምትመሠርትበትን ዓላማ በቁም ነገር ልታስብበት ይገባል። የማግባት እቅድ ሳይኖርህ የፍቅር ጓደኝነት መመሥረት፣ አዲስ አሻንጉሊት ሲያገኝ ተጫውቶበት ሲሰለቸው እንደሚጥል ልጅ መሆን ነው።

➣እስቲ አስበው፦ አሻንጉሊቱን ሲፈልግ እያነሳ የሚጫወትበትና ሲሰለቸው ደግሞ የሚጥል አንድ ትንሽ ልጅ ወደ አእምሮህ ለማምጣት ሞክር ፤ አንድ ሰው ልክ እንደዚህ ትንሽ ልጅ በስሜትህ ቢጫወት ምን ይሰማሃል? ደስ እንደማይልህ የታወቀ ነው ፤ አንተም በሌላ ሰው ላይ እንደዚህ አታድርግ!

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat
2.4K views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:43:38

345 views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:45:43
የፍቅር ግንኙነት ጀምረሃል/ሻል ሊባል የሚችለው ምን ስታደርግ/ጊ ነው?
Anonymous Poll
11%
ከአንዲት/ድ ወጣት ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ እየተገናኛችሁ ጊዜ ስታሳልፉ።
14%
ደስ የምትልህ አንዲት ወጣት አለች፤ እሷም ለአንተ ልዩ ስሜት አላት። በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ በሞባይል መልእክት ከተላላካቹ አሊያም በስልክ ካወራችሁ።
4%
ከጓደኞችህ/ሽ ጋር ጊዜ ስታሳልፍ ሁልጊዜ ከአንዲት ሴትጋ ነጠል ብለህ የምታወራ/ሪ ከሆነ።
71%
በነዚህ መለኪያዎች ፍቅርነቱ አይመዘንም
235 voters2.0K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 06:31:52 የወጣቶች ጥያቄ...

ጥያቄ_23
ፖርኖግራፊ መመልከት የሌለብህ ለምንድን ነው?

እውነታው ምን እንደሆነ ማወቅ!

#የተሳሳተ አመለካከት፦ ፖርኖግራፊ መመልከቴ አይጎዳኝም።

#እውነታው፦ ፖርኖግራፊ ፣ አምላክ በሁለት ሰዎች መካከል የጠበቀና ዘላቂ የሆነ ጥምረት እንዲፈጠር አስቦ ያዘጋጀውን ነገር የሚያዋርድ ተግባርን የሚያሳይ ነው። ከጊዜ በኋላ ደግሞ ትክክል እና ስህተት ስለሆኑት ነገሮች ያለህ ስሜት እንኳ እንዲደነዝዝ ያደርጋል። ለምሳሌ ያህል፦ አዘውትረው ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ወንዶች በሴቶች ላይ ስለሚፈጸም ጥቃት ያላቸው ስሜት እየደነዘዘ ሊሄድ እንደሚችል አንዳንድ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ፖርኖግራፊ ለመመልከት እንዳትፈተን ምን ማድረግ ትችላለህ?

➣ ፖርኖግራፊ ለመመልከት እንድትፈተን የሚያደርግ ሁኔታ ሲያጋጥምህ በቆራጥነት እምቢ ማለት እንደምትችል እወቅ። ፖርኖግራፊ ማየት ጀምረህ ከሆነም እንዲህ ማድረግህን ማቆም ትችላለህ። ይህን ማድረግ ብዙ ጥቅም ያስገኝልሃል።

➣ ከ4 ወራት በፊት @bertuwetat ቻናል ውስጥ የተቀላቀለ የአንድ ወጣት ልጅን ታሪክ እንደ ምሳሌ እንመልከት ፤ ይኽ ሰው ፖርኖግራፊ መመልከት የጀመረው በ13 ዓመቱ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ከተማከርንበት በኋላ ካውንስሊንጉን እንደጨረስን እንዲህ ሲል የነበረበትን ነገር ወደኋላ መለስ ብሎ አስታውሷል፦ “እንደሱ ማድረጌ ስህተት እንደሆነ አውቅ ነበር ፤ ይሁን እንጂ ራሴን ተቆጣጥሬ ፈተናውን መቋቋም አልቻልኩም። ሁልጊዜ ፖርኖግራፊ ከተመለከትኩ በኋላ መጥፎ ስሜት ይሰማኝ ነበር። እራሴን እረግማለሁ ፣ መፈጠሬን አማርራለሁ ፣ መሞት ከመኖር አስር እጅ እንደሚሻል አስባለሁ። ከጊዜ በኋላ አባቴ የማደርገውን ነገር አወቀ ፤ እውነቱን ለመናገር ይህ ትልቅ እፎይታ አስገኝቶልኛል! በመጨረሻም የሚያስፈልገኝን እርዳታ ማግኘት ቻልኩ።”

"ያለህን እንደሌለህ ፤ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ነገር ደሞ መቼም እንደማትደርስበት አይነት አድርጎ የሚያሳይ የዘመኑ ክፉ ጋሬጣ ነው!" ፖርኖግራፊ

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat
4.3K viewsedited  03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ