Get Mystery Box with random crypto!

የወጣቶች ጥያቄ... ጥያቄ_24 #ክፍል_2 የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር መቸኮል የሌለብህ ለምንድን | ብርቱ ወጣት | Bertu Wetat

የወጣቶች ጥያቄ...

ጥያቄ_24 #ክፍል_2
የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር መቸኮል የሌለብህ ለምንድን ነው?

  ዝግጁ ሳትሆን የፍቅር ጓደኝነት እንድትጀምር የሚደረግብህ ጫና በደንብ ያልተማርከውን ትምህርት እንድትፈተን ከመገደድ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ይህ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ግልጽ ነው! ፈተና ላይ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች መመለስ እንድትችል ትምህርቱን ለማጥናት ጊዜ ያስፈልግሃል።

 'የፍቅር ጓደኝነት በመመሥረት ረገድም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።'

  የፍቅር ጓደኝነት መመሥረት እንደ ዋዛ የሚታይ ነገር አይደለም። በመሆኑም ከአንዲት ወጣት ጋር የፍቅር ጓደኝነት ስለ መጀመር ከማሰብህ በፊት በጣም አስፈላጊ የሆነን አንድ “ትምህርት” ለማጥናት ይኸውም ወዳጅነት መመሥረት የሚቻልበትን መንገድ ለመማር በቂ ጊዜ ያስፈልግሃል።

  እንዲህ ካደረግህ ከጊዜ በኋላ፣ የምትሆንህን ወጣት ስታገኝ ጠንካራ ግንኙነት ለመመሥረት የተሻለ አቋም ይኖርሃል። ጥሩ ጋብቻ የሁለት ጥሩ ጓደኛሞች ጥምረት መሆኑን አትዘንጋ።

 የፍቅር ጓደኝነት ሳትጀምር መቆየትህ ነፃነትህን እንደሚገድብብህ ማሰብ የለብህም። እንዲያውም ‘የወጣትነትህን ጊዜ አስደሳች’ በሆነ መንገድ ለማሳለፍ የበለጠ ነፃነት ይሰጥሃል። ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ባሕርያትን በማዳበርና ከምንም በላይ ደግሞ መንፈሳዊነትህን በማጠናከር ራስህን ለማዘጋጀት የሚያስችል ጊዜ ይኖርሃል።

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat