Get Mystery Box with random crypto!

የወጣቶች ጥያቄ.... ጥያቄ_ #የመጨረሻ_ክፍል ለፍቅረኛዬ መታመኔን እንዴት ላሳይ? | ብርቱ ወጣት | Bertu Wetat

የወጣቶች ጥያቄ....

ጥያቄ_ #የመጨረሻ_ክፍል
ለፍቅረኛዬ መታመኔን እንዴት ላሳይ?

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ፍቅረኛ ከመያዛቸው በፊት ስለራሳቸው ያላቸው አመለካከት ፍቅረኛ ከያዙ በኋላ በዛው ላይቀጥል ይችላል። እንበልና አንድ ወጣት ፍቅር ውስጥ ከመግባቱ በፊት ታማኝ እንደሆነ ሊያስብ ይችላል ፤ አልፎ ተርፎም የወደፊት የፍቅር ጓደኛውን በመታመን ጉዳይ ሊያስከፋት እንደማይችልም ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ሊሆን ይችላል። ይህን ማሰቡ መልካም ሆኖ ሳለ አንዳንዴ ግን "እኔ እንዲህ ነኝ!" ብለህ የተማመንክበት ነገር በጊዜ ፣ በሁኔታ ፣ በጠባይ መቀየር ፣ በአዋዋል ወ.ዘ.ተ ምክንያት ተቀይሮ ታገኘዋለህ። የዛን ጊዜ አንተ በጊዜው የሆንከው ነገር እንጂ አንተ ስለ አንተ ታስብ የነበረው ነገር ልክ እንዳልሆነ ይገባሃል።

አብዛኛው የፍቅር ግንኙነት የሚጠለሸው ባለማመንና ባለመታመን ችግር ነው። አንዳንዴ ታምኖ መገኘት ብቻም ሳይሆን ታማኝ መሆንህን በተጨባጭ የምታሳይበት መንገድም ለፍቅር ግንኙነት መሳካት ትልቅ ሚና አለው።

መታመኔን እንዴት ላሳይ?

➪ የፍቅር አጋርህ ተብላ መጠራቷ ያንተ የሆነን ነገር ፣ ካንተ የመጣን ነገር ፣ ላንተ የሚደረግን ነገር ሁሉ የምትጋራህ ከመሆኗ አንጻር እንደመሆኑ የምታደርገውን ነገር ፣ የዋልክበትን ፣ ያደርክበትን ሁሉ በግልጽ ንገራት!

➪ ቅናት ሊፈጥርባት የሚችሉ ነገሮችን ከጎንህ አርቅ! አንዳንድ ሰው ቅናት የፍቅር መገለጫ ይመስለዋልና እውነታው ግን ቅናት አጥንትን የሚያነቅዝ መርዝ ነው።

➪ ዘወትር ፍቅርህን ለመግለጽ አትታክት! ከቃላት ባለፈ ደግሞ ተግባርህም የተጠና ይሁን።

➪ የሷን ታማኝነት አትጠራጠር! ለመታመን የመጀመርያው መስፈርት አምኖ መገኝት ነውና ፍቅረኛዬ ታማኝ ባትሆንስ? እያሉ በመጠራጠር መታመን ፈጽሞ አይቻልም።

በርቱ!

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat