Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ወጣትነት የሰው ልጅ በተለይ እኛ ወጣቶች የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ሁሉም ግልጽ | ብርቱ ወጣት | Bertu Wetat

መንፈሳዊ ወጣትነት

የሰው ልጅ በተለይ እኛ ወጣቶች የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ሁሉም ግልጽ የሆነ መፍትሔ ላይገኝላቸው ይችላል። ፈተና ስንል የግድ የመከራና ችግር መፈራረቅ ብቻ ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ ያሰቡት(ያቀዱትን) በዕለቱ እንዳንፈጽም የሚያደርግ ፈተና ፣ ምክንያቱ ያልታወቀ የጠባይ ለውጥ ፣ ወይም ደሞ የስሜት መለዋወጥን ብንመለከት ትናንት ወደድኩህ ከጎኔ አትራቅ ብለን የፍቅሩን ናፍቆት መጋፈጥን እንዳልፈራን ዛሬ ላይ ያ የቀድሞ ስሜታችን ጠፍቶ ይባስ ብሎ ለዐይናችንም እስክንጠየፈው የሚያደርሰን ዓይነት ፈተና ሁሉ ውሉ የማይጨበጥ የኛ የወጣቶች ፈተና ነው።

ስለዚህ ለእንደዚህ ዓይነት ፈተናዎችም ሆነ ኑሮን በስክነት ለመምራት መንፈሳዊነትን የመሰለ ጋሻ ፣ አማኝነትን የመሰለ ዋሻ የለም! ጋሻ ከተሰበቀ ጦር እንደሚከላከል ሁሉ መንፈሳዊነትም ከክፉ(ከማይጠቅም) ፈተና ይጠብቀናል ፤ ዋሻ ከዱር አውሬ ጥቃት የምናመልጥበት መጠለያ እንደሆነ ሁሉ አማኝነትም ከጠላት ክፉ ምክርና ሐሳብ መደበቂያ ባዕታችን ናት።

"የዘመኑ ኃላፊ ዘመናዊነት በፈረንጅ ኢ-አማኒነት ቢለካም እኛ ግን አማኞች በመሆን የማያልፈውን ዘመን እንዋጃልን! ምክንያቱም #ብርቱ_ወጣቶች ነን! "

በርቱ!

ለሐሳብ አስተያየትና ተሞክሮ ለማካፈል @productive_habeshaa እና @Tnx4Deshet

@bertuwetat
@bertuwetat