Get Mystery Box with random crypto!

በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪

የቴሌግራም ቻናል አርማ bemaledanek — በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
የቴሌግራም ቻናል አርማ bemaledanek — በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
የሰርጥ አድራሻ: @bemaledanek
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.09K
የሰርጥ መግለጫ

♥አላማው
☞መንፈሳዊ ወንድምነት እህትነት ማጠናከር
☞መንፈሳዊ ምግብን ተመግበን ንስሀ ገብተን በቅዱስ ቁርባኑ የበቃን መሆን
☞ተሞክሮዎችን በማካፈል መልካም ፍሬዎችን ማግኘት
አስተያየት ከለዎ👉 @Hiyab_Nat ያድርሱን 👉ወደ ግሩፕ ለመቀላቀል @egzabehertalakenew

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-05-27 12:54:32 1• ፍቅር     1.2• ፍቅር ካለ ምን አለ? ክፍል - ፪ ✞ ፍቅር ወደ እምነት፥ እምነት ወደ ተስፋ፥ ተስፋ ወደ ምሪት    የሰው ልጅ የማንነቱ መልክ የሆነውን ፍቅር በተቀደሱ መልካም ነገሮች ሁሉ ውስጥ እየፈለገና እየገለጠ በዘመኑ ላይ መመላለስ ሲጀምር፤ የባሕሪይው መዝገብ የሆነው የአዳም ቤተሰብ በሥጋ ምኞት የተነሣ በመውደቁ ምክንያት፤ ከውጪኛው የሥጋ አካሉ ላይ ተገፍፎ የተሸጎረበትን…
908 views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:22:21    በእውነት በእውነት፥ ፍቅር አልፋ ነው፡፡ ፍቅር ዖሜጋ ነው፡፡ በፍቅር የጀመረ ሰው በፍቅር ለመጨረስ የሚከፍለው ሰማዕትነት ራሱን የቻለ አምኃ ይሆንለታል፡፡ ከፍቅር የተነሣ ሰው ወደ ፍቅር መድረሻ የሚሄድበት መስመር የራሱን ዓላማና ትርጉም ይይዝለታል፡፡ ፊተኛውን ፍቅር ያደረገ ሰው ኋለኛውን ለመንካት ሲንጠራራ ወደታች የሚጎትቱ እልፍ ምክንያቶች ቁመቱን አያሳጥሩበትም፡፡

   ፍቅር ያለው ሰው በሰላማዊው ጊዜ ደስተኛ ነው፡፡ ፍቅር ያለው ሰው በመከራውም ሰሞን ያው ደስታው እንዳለ ነው፡፡ ምክንያቱም ፍቅር "ይታገሣል፤ በሁሉ ይጸናል፤ ለዘወትርም አይወድቅም።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13)

   ፍቅር ያለው ሰው ሲሞላለት ያካፍላል፡፡ ፍቅር ያለው ሰው ሲጎድልበትም ያለውን ማከፈል አያስቀርም፡፡ ምክንያቱም ፍቅር "ቸርነትንም ያደርጋል፤ የራሱንም አይፈልግም፤" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13)

   ፍቅር ያለው ሰው በጥርጣሬ ወጀብ አይታመስም፡፡ ፍቅር ያለው ሰው በዝግ በር ውስጥ ማለፍን ከምርጫ አያጎድልም፡፡ ምክንያቱም ፍቅር "ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13)

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን...
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
1.4K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:21:47    ፍቅር ሲኖር እምነትም ይኖረናል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የወሰንንበት ምክንያት ፍቅር ከሆነ፤ ከእርሱ ጋር በእምነት ሰንሰለት ለመያያዝ አንቸገርም፡፡ አምላክን እንደ አባት አቅርቦ የመውደድ ዕድል በሐዲስ ኪዳን ተሰጥቶአል፡፡ "አባታችን ሆይ" የሚል ጸሎት የመጣውም የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን ሥልጣን በዳግም መወለድ በኩል ስለተካፈልን ነው፡፡ እናስ አጠገባችን አብረው እንዳሉ ሰዎቻችን [እንኳ] እግዚአብሔርን አቅርበን ስንወድድ፤ ከዚህ የፍቅር ነጥብ ወዲህ ባለው መንፈሳዊ ሕይወት ከመለኮታዊ ኃይል ጋር በእምነት ተናብቦ መቀጠል አስቸጋሪ አይሆንብንም፡፡

                 ✞ እምነት ወደ ተስፋ

    እምነት በፍቅር ከተወለደ በኋላ፤ እርሱ ደግሞ ጊዜው ሲደርስ የሚወልደው ሁለተኛ ልጅ ተስፋ ይባላል፡፡ ፍቅር የተስፋ አያት ነው፡፡

   ስለወደድን ስናምን፥ ስላመንን ደግሞ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ኋላሳ የማያምን ሰው ምንን ተስፋ ሊያደርግ ይቻለዋል?" ("እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።"
(ወደ ዕብራውያን 11፥1))

    ተስፋ ነገን በዛሬ ውስጥ የሚያስኖር የእምነት ውጤት ነው፡፡ ተስፋ በዋሻ ጫፍ ያለውን ብርሃን ሳያዩ በጨለማ የመጓዝ ብርታት ነው፡፡ ተስፋ የሚመጣውን የቃልኪዳን መገለጥ በሐሴት የሚያስጠብቅ የሕልውና ስንቅ ነው፡፡ ተስፋ የኑሮ ወዝ ደርቆ እንዳይጠወልግ ልምላሜ የሚሰጥ የነፍስ ውኃ ነው፡፡ ተስፋ አድካሚና አሰልቺ በሆነ የጊዜ ምዕራፍ ላይ ስንደርስ ቀጣዮቹን ገጾች የሚያስገለብጥ መንፈሳዊ ጉልበት ነው፡፡ ተስፋ የመከራን እስራት የሚያሳጥር በጠባይ ወረቀታችን ላይ የተጻፈ አለኝታ ነው፡፡

    ተስፋ የሚባለው ጉዳይ በባሕሪያችን ላይ የተቀረጸው ከዔድን ገነት ስንወጣ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ አንድ ቀን እየሆኑ የተዘረዘሩት ሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ሁሉ ሲያስገኙ፤ የመጨረሻዋ ሰባተኛዋ ቀን ዕረፍት ሆናለች፡፡ በአዳም አቆጣጠር በኩል አዳም 6ተኛዋን የተፈጠረባት የቀን ሥርዓት ሳይጨርስ ነው የወደቀው፡፡ ማለትም 1000 ዓመት ሳይሞላው በ930 ዓመቱ በዛፏ ፍሬ ምክንያት ሞተ፡፡ አዳም ከገነት ሲባረር ወይንም ከፈቃደ እግዚአብሔር ሲለይ፤ እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ አስቀድሞ ያየለትና የማያውቃት ሰባተኛዋ የዕረፍት ቀን በውስጡ ተስፋ የምትባለዋን የስብእና ባሕሪይ ቋጥሯ ቀርታለች፡፡ (ወደ ዕብራውያን ሰዎች ምዕ.4)

    የተስፋ ርዝመት የሚለካው በእምነታችን ጥንካሬ ነው፡፡ የእምነት ጥንካሬ ምንጭ ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ እነሆም ፍቅር፥ እምነትንና ተስፋን አጽንተን የምንኖርበት ድንቅ ኃይል ነው ማለት ነው፡፡

    ነገራችንን ስለ ፍቅር በማውሳት የጀመርነው ስለዚህ ነው፡፡ ምንም አይነት መንፈሳዊ አሳብ፣ ቃልና ሕይወት እንዲኖረን፤ ለመንፈሳዊው ዓለም እስትንፋስ የሆነው እምነት የግድ ያስፈልገናል፡፡ እምነት ደግሞ ወይ ከፍቅር ወይ ከምክንያት ይወለዳል፡፡ (ፍቅር ምንም ምክንያት የሌለው የመለኮት ቅዱስ ባሕሪይ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ዓለሙን "እንዲሁ" ወዶአልና የሚለው የዮሐንስ ወንጌል 3፥16 ቃል ይህንኑ ይነግረናል፡፡ ምክንያት ግን ሁልጊዜ መሥፈርት አለው፡፡ እምነት ከምክንያት ከተወለደ አስተዳደጉ የቀነጨረ ነው፡፡ ፍላጎቱ በአመንክዮ ድንበር የታጠረ ነው፡፡ ኃላፊነትን የመሸከም ጫንቃው በኵነቶች የተወሰነ ነው፡፡)

    ፍቅር ያልያዘው እምነት የተስፋ አድራሻ የለውም፡፡ ፍቅር የሌለበት እምነት የማይታየውን የሚያይበት፣ የማይጨበጠውን የሚደገፍበት፣ ያልተቀጠረውን የሚጠብቅበት የነፍስ ሕዋስ የለውም፡፡ ፍቅር የሌለበት እምነት መሥዋዕትነትን እንደ ዋጋ የሚቆጥርበት የሞራል ከፍታ የለውም፡፡ ፍቅር የሌለበት እምነት በተንገዳገደ ወቅት ይዞት የሚቆመው የመጽናኛ ግንብ የለውም፡፡ ፍቅር የሌለበት እምነት የምስጋን መባዕ በቀን ደስታም ሆነ በሐዘን ማታ የማቅረብ መሻቱ የለውም፡፡ "ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፥2)

                 ✞ ተስፋ ወደ ምሪት

    ተስፋ ካለ ወደፊት የሚቀጥል አንድ ጉዞ አለ፡፡ ጉዞ ደግሞ ምሪት ያስፈልገዋል፡፡ አቅጣጫ የሚያሳየው፣ መንገድ የሚጠቁመው፣ አካሄድ የሚያስተካክለው፣ የመጣበትን ርቀት የሚያስመዘግበው፣ የሚቀረውን ርዝመት የሚያሳውቀው ምሪት ይፈልጋል፡፡ ይሄ ምሪት ደግሞ ከእምነት ልጅ ከተስፋ ይወለዳል፡፡ አሁን ፍቅር የምሪት ቅደመ አያት ሆነ፡፡ (ፍቅር የሁሉ ነገር መጀመሪያ አልፋ ነው ብለናላ! ጌታም የትእዛዛት ሁሉ በኩር ፍቅር እንደሆነ በወንጌለ ድምፁ አሰምቶናል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 22፥38 ፤ የማርቆስ ወንጌል 12፥31፤ የሉቃስ ወንጌል 10፥27)

    ምሪት የዘር ግንዱ ከፍቅር የሚወጣ ከሆነ፤ ቀኛችንን ይዞ እየመራ የሚወስደን ከውጪ ወደ ውስጥ ሳይሆን ከውስጥ ወደ ውጪ ይሆናል፡፡

    ሰዎች ይጠይቃሉ፡፡ "ከእግዚአብሔር ጋር መኖር የምችለው እንዴት ነው? ምን ያህል ብጸልይ ነው ጥሩ የሚሆነው? ስንት ብሰግድ ነው መለኮታዊ ኃይል የሚገኘው? እንዲህ እንዲህ ያለ ስንፍና አለብኝ ምን ይሻላል? ከሥጋዊው አኗኗር መላቀቅ እየፈለኩኝ አልሆነልኝም፡፡ ምን ላድርግ? ወዘተ..." አይነት ጥያቄዎች ይጠየቃሉ፡፡ ካለማወቅ የሚመነጨው ጥያቄ መጠየቁ አግባብ ቢሆንም፤ ለእግዚአብሔር እንጥፍጣፊ ፍቅር የሌለው ማንነት ግን፤ በፍቅር መኖር ምክያትነት በራሱ መልስ ሊያገኝላቸው የሚገቡትንም ጥያቄዎች ጨምሮ ይጠይቅ ዘንድ ይገደዳል፡፡

   በምሳሌ እንየው፡፡ አንድ በጣም የምትወዱትን ሰው የአእምሮችሁ ሸራ ላይ ሳሉ፡፡ ወዳጃችሁንም ለማግኘት አስፈላጊ ቀጠሮ ኖሯችሁ በሰው መኪና እየሄዳችሁ ሳለ የትራፊኩ መንገድ ተዘጋጋ እንበል፡፡ በቃ ከዚህ በኋላ ያለው ጉዞ የሚወሰነው ለግለሰቡ ባላችሁ የመወደድ ልክ ነው፡፡ ሳታዩት ማደር የማይሆንላችሁ ሰው ከሆነ በእግር ወርዳችሁም ይሁን፣ በሌላ አቋራጭ መንገድ አሳብራችሁም ይሁን ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ ስለተዘጋጋው አስፓልት እልህ ሳይሆን ስለ ወደዳችሁት ሰው ፍቅር ስትሉ ታደርጋላችሁ፡፡ ወደ ማትወዱት ሰው እየሄዳችሁ ከሆነ ግን ወደኋላ ለመመለስ እንደ መንገድ መዘጋጋት ያለ በቂ ምክንያት ሳይሆን የጎማው የመሽከርከር ሁኔታ ራሱ ሰበብ ሊሆንላችሁ ይችላል፡፡ ሃይማኖታዊ መንገድም እንዲህ ያለ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ካለ በገደልም ውስጥ ምሪት አለ፡፡ ፍቅር ሳይሆን አንድ ሥጋዊ ምክንያት ወደ እግዚአብሔር የሚወስደን ከሆነ ግን ለጥ ያለው አውድማ ብዙ ቋጥኝ የተከመረበት ረጅም ተራራ መስሎ ይታየናል፡፡ በመሆኑም ሁሉንም ነገር በድጋፍ እየተመረኮዝን ካልሆነ በራሳችን የምንሻገረው አንድም ክፍተት አይኖረንም፡፡

   በተመሳሳይ ገለጻ የበለጠ ግልጽ ስናደርገው፤ የፍቅርን ምሪት ከውስጡ ያገኘ ሰው ስንት መስገድ እንደተገባው የፍቅሩ መጠን ይነግረዋል፡፡ የፍቅርን ብርሃን የሚከተል ሰው ጨለማን እየለየ የሚቃወምበትን ስልት ከእውቀቱ አያጣም፡፡ የፍቅርን ዱካ እየቆጠረ መንገዱን ያቀና አማኝ "ይህንን ባደረግ አምላኬ ይደሰታል ወይስ ያዝናል" እያለ ሁሉን የሚመዝንበት የነፍስ ልኬት ከሥጋው ማኅደር ውስጥ አለ፡፡ በፍቅር ረመጥ ልቡ ያልተቃጠለ ከሆነ ግን፤ ከውስጥ የሚደመጠው የሕሊና በጎ ሹክሹክታ ዝም ስለሚል ከውጪ የሚሰማ "ይህን ይህን አድርግ" የሚል ውትወታን ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴው የግድ ይፈልጋል፡፡
1.1K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:21:11 1• ፍቅር 1.1• ፍቅር ምንድነው? ክፍል - ፩   ✞ የሰው መልኩ ፍቅር ነው "እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 2፥7)     አምላክ ፍጥረታትን ሁሉ በስድስት ቀን ተከታታይነት ፈጥሮ ሥራውን ካበቃ በኋላ፤ በመጨረሻው ላይ ከፈጠራቸው ፍጡራን ሁሉ ለየት ያለ አንድ ፍጡርን…
940 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:11:37
ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
1.0K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 11:39:16    "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና" ካልን፤ እግዚአብሔር ደግሞ ፍጹም መልካምና ቅዱስ ነው፡፡ (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፥8) ስለዚህ ፍቅርን የምናውቀው ቅዱስ በሆነው መልካም ነገር ሁሉ ውስጥ ነው ማለት ይሆናል፡፡

    ከጥንት የሰዎች መነሻ ታሪክ አንስቶ እስከ ዛሬው ዘመናችን ድረስ ክፉ መናፍስት የተቀደሰውን መልካም ነገር ባላንጣ ሆነው የሚዋጉት ፍቅርን እንዳንኖረው ነው፡፡ እግዚአብሔርን የማያውቅ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ ትውልድ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሕይወት፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ አሳብ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ እውቀት፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ ጥበብ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ ንብረት፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሥልጣን በምድራችን ላይ እንዲንሰራፋ ሰፊውን ድርሾ ወስዶ ሚናውን በሚገባ የተጫወተው የዲያብሎስ ሠራዊት፤ የአዳም ልጆች መልካቸውን ማስታወስ አቅቶአቸው፤ የዘመኑን ሥጋዊ መልክ መስለው እንዲኖሩ የፍቅርን ምንነትና ኃይል ከነፍሳችን እንዳይገለጥ ከጽድቅ መንፈስ በጣም የራቀ አኗኗር ለዓመታት አስለምዶን ቆይቶአል፡፡

   በመሆኑም አብዛኞቻችን የፍቅር እውነተኛ ትርጉም ተደብቆብናል፡፡ ፍቅር የሕይወታችን ብቻ ሳይሆን የሰብአዊነታችን አካል መሆኑን ስለዘነጋን፤ ፍቅርን አስፈላጊና በተመረጠ ቦታ ላይ የምንገልጸው ስጦታ አድርገነዋል፡፡ ከሌላ ሰው በተሰጠን ጊዜ የምንመልሰው ምላሽ አድርገነዋል፡፡ በቤተሰብ፣ በጾታና በትውውቅ ግንኙነቶች መካከል የተወሰነ የመግባባት አጥር አድርገነዋል፡፡ ሲመቸን፣ ደስተኛ ስንሆን፣ ጉድለት ሲጠፋልን፣ ችግር ሲርቅልን የምንገለጽው ስሜት አድርገነዋል፡፡ ፍቅር ግን እጅግ በጣም ትንሽ ከምትባለው የሰኮንዶች መልካም ነገር ጀምሮ ሁሉንም የተቀደሰ መልካም አሳብ፣ መልካም ቃልና መልካም አኗኗር የሚጠቀልል የመለኮት ውበት ነው፡፡

   ለዚህ ደግሞ መታመኛ ምስክራችን የተፈጠርንበት የልዩ ሦስትነት መልክ ነው፡፡ መልካችን የሆነው ወላዲ አባት እግዚአብሔር አብ መለኮታዊ አሳብ(ልብ) ነው፡፡ ተወላዲ ልጁ እግዚአብሔር ወልድ መለኮታዊ ቃል ነው፡፡ ከአብ የሠረፀው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሕይወት(እስትንፋስ) ነው፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 1፥1)

    ነፍስ የነዚህን ሦስት አካላት መልክ በሕልውናዋ በመያዝ፤ ልባዊ(የምታስብ)፣ ነባቢ(የምትናገር) እና ሕያው(የምትኖር) ሆናለች፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ፍቅር ነው ካልን፤ እንግዲያ በልዩ አካላዊ ሦስትነቱም እንዲሁ አሳቡም ፍቅር፣ ቃሉም ፍቅር፣ ሕልውናውም ፍቅር ነው ማለት ነው፡፡ (አብ ፍቅር ነው፣ ወልድ ፍቅር ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ፍቅር ነው)

   ስለዚህ የእኛ ሰው የመሆናችን ቁልፍ እዚህ ውሰጥ አለ፡፡ የሰብአዊነት መልካችን እግዚአብሔር ሲሆን፤ እንደ መልካችን በመገለጥ ፍቅርን ስናስብ፣ ፍቅርን ስንናገር እና ፍቅርን ስንኖር ሰውነትን አግኝተነዋል፡፡

   አንድ አሳብ፣ አንድ ቃልና አንድ ድርጊት በፍቅር ወለል ላይ ቆሞ እርምጃ ሲጀምር፤ መልኩ የሰውነትን ቅርጽና የሰውነትን መንፈስ ይይዛል፡፡ የእግዚአብሔርንም ኃይል ይሸከማል፡፡ (አንዱ ቃል በፍቅርና በጥላቻ ባሕሪይ ሲነገር የተለያየ ተጽዕኖ የሚፈጥረው በዚህ ምክንያት እንደሆነ ልብ ይሏል!) ከዚህ ባሻገር ግን፤ የሰው እጅና እግር፣ የሰው ጭንቅላት፣ የሰው ቆዳና በአጠቃላይ የሰውን ውጪያዊ መልክ መያዝ ብቻውን "ሰው" አያሰኝም፡፡ በዚህ ልኬት ላይ የሰውነት ሚዛን ቢሰፈር ኖሮ፤ ራሳቸው የሰው ልጆች ከሠሯቸው ተንቀሳቃሽ ሮቦቶች(artificial intelligence) ጀምሮ ብዙ ቁሳዊ ነገሮች ሰው የመሆንን ስያሜ ይጋሩት ነበር፡፡

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን...
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
1.3K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 11:38:49    "እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ" የሚለው ቃልም እንደሚነግረን፤ በጨለማው ዓለም ላይ ብርሃን በተገለጠ ጊዜ አብረው በቅድስና የተገለጡት መላእክት መልካም(ታማኝ፣ ታዣዥ፣ ንጹሕና ጽኑ) እንደሆኑ እግዚአብሔር አየ፡፡ ስለዚህም ለእነርሱ የመንፈሱን ኃይልና ግርማ አካፍሎ አገልጋዩ ሲያደርጋቸው፤ በጨለማው ጊዜ የካዱት መላእክት ከዚህ ሹመት የተለዩ ሆኑ፡፡ ይህንንም መለየት መጽሐፍ "ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም" በማለት ይገልጸዋል፡፡ (የዮሐንስ ራእይ 12፥8)

   መላእክትን እንዲመራ አክብሮ የፈጠረው ሳጥናኤል በክፉነት ፍላጎቱን ገልጾ ርኩስ በመሆን ከሰማይ ቅድስና ሲለይ፤ ከድቶ ባፈነገጠው ነገድ ፋንታ፤ ፍጥረታትን የሚያስተዳድር፣ እንደ ተቀደሱት መላእክት በብርሃን ጸጋ የሚመላለስ፣ በክብርም ከፍ ያለ ፍጡር መቶኛው ሙሉ ነገድ ይሆን ዘንድ "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር(በፍቅር) መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።" (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥27)

    "ከሰማይ(ከብርሃን) ስፍራ ያልተገኘለት" ጨለማው ዲያቢሎስ፤ እርሱ በተዋረደበት ቦታ ላይ እኛ ባለ ክብር ሆነን መፈጠራችን በእጅጉ ያስቀናዋል፡፡ ይባስ ብሎ በእግዚአብሔር ምሳሌ ተፈጥረን በብርሃን ጸጋ በመክበር አስተዳዳሪ መሆናችን ደግሞ ተመኝቶ ያጣውን ገዢነት በኛ ተፈጥሮ ላይ ስላየው መገመት በማንችለው የጥላቻ ጥግ አምርሮ እንዲጠላን አደረገው፡፡ (የተፈጠርንበት ቀን 6፥ ዲያቢሎስ ጥላቻን ያለማቋረጥ ወደኛ እንዲገልጽ የአሳቺነት መታወቂያን ያተመበት ቀን ነው)

    በፍጥረት ወገኖቹ ከሆኑት መላእክት ጋር በመጀመሪያ ተዋግቶ የተሸነፈው ዲያቢሎስ፤ ከመላእክትም በላቀ ክብርና ግርማ የተፈጠረውን የሰው ልጅ በቀጥታ ተፋልሞ ሊጥለው እንደማይችል ከቀደመ ሽንፈቱ ተሞክሮ ወስዶአል፡፡ በአዳምና በሔዋን ላይ መልቶ የነበረውም የብርሃን ጸጋ ጨለማነቱን በመቃወም ማንነቱን እንደሚገልጥበት ያውቃል፡፡ ስለዚህ እውነተኛ መልኩን(ጥላቻውን) በሥጋ ደብቆ በእንስሳ አካል ተሰውሮ ወደ ሔዋን ሄደ፡፡ (ይሄ በሥጋ የመደበቅ ጉዳይ፥ ዘግይቶ ክፉው መንፈስ በኛ የሥጋ ባሕሪይ ላይ የርሱን መለያ እንዲያስቀመጥ ፈለግ የተወ ምሪት ሆኖአል፡፡ ጥላቻንም በባሕሪያችን የማፍለቅ ግፊት የመጣው ከዚህ በኋላ ነው፡፡ የመጀመሪያው ጥላቻን በሰው አካል የመግለጥ የመናፍስት ሴራ በቃየን ባሕሪይ ላይ ተጀመረ)

    እዚህ ጋር ያለው እቅድ ተነድፎለት የታለመው የእባቡ ምኞት፤ አዳምና ሔዋን በራሳቸው ፈቃድ ወስነው ከራሳቸው ላይ ያለውን የብርሃን ጸጋ እንዲገፍፉት ነው፡፡ የተሰጣቸውን መልክ እንዳይኖሩት ሌላ በር መክፈት ነው፡፡ እንዲህ የሚሆነው ደግሞ ከእግዚአብሔር አምላካቸው ፈቃድ ሲለዩ እንደሆኑ ገልጽ ስለሆነ፤ ከሴቲቱ ጠጋ ብሎ "በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።" (ኦሪት ዘፍጥረት 3፥1)

   ዲያቢሎስ ወደ ሔዋን እንደደረሰ ተቀዳሚ ሥራው ያደረገው የእግዚአብሔር የሆነውን አሳብ ከውስጧ መለወጥ ነው፡፡ "በውኑ አትብሉ ብሎአልን?" ሲል በአንጻራዊ ጎን ያለውን፥ ትእዛዝ ተላልፎ የመብላትን አሳብ፥ እንደታውጠነጥን ዕድል አመቻቸላት፡፡ ሔዋንም የእግዚአብሔር መልክ ያላት የፍጥረታት ንግሥት ከመሆን ባለፈ፥ እግዚአብሔርነት አገኛለሁ በሚል ዲያቢሎሳዊ ቅዠት አትንኩ የተባለውን የዛፍ ፍሬ ከባልዋ ጋር ወስዳ በላች፡፡

    በዚህ ጊዜ ከእነርሱ መልክ ውጪ ያለውን፥ የነፍስ ባሕሪይ የማታውቀውን፥ በልዑል አምላክ እቅድ ውስጥ ያልተቀመጠውን፥ "ክፋትን" የማገናዘቢያ ዓይኖቻቸው ሲከፈቱ፤ ከሰውነታቸው ላይ የብርሃናቸው ጸዳል ተገፍፎ "ዕራቁታቸውን እንደሆኑ አወቁ" (ኦሪት ዘፍጥረት 3፥6)፡፡ (ባዕድ አምልኮት የሚባለው ገለጻ ይህንን ያመለክተናል፡፡ ነፍስ ባሕሪይዋ ከተሠራበት ውጪ ያለውን መልክ አታውቀውምና የጣዖታት አምላክነት ለርሷ ባዕድ ይሆናሉ)

    ብርሃናዊነታቸው ከሥጋዊ አካላቸው ላይ የተነሣው አዳምና ሔዋን፤ የተፈጥሮአቸው ጸዳል ተሰብስቦ በለስ የቀጠፉበት የእጅ ጣታቸው ላይ የወቀሳ ማስታወሻ ሊሆን ጥፍር ሆኖ በቀለ፡፡ ነፍስም በሥጋ ላይ የነበራት ቁጥጥር ተነሥቶ ከአፈርማው ተክለ ቁመና በታች ተሸሸገች፡፡ የዚህ ጊዜ አዳምና ሔዋን ተስምቶአቸው የማይታወቅ አዲስ ሥጋዊ ስሜትን አስተናገዱ፡፡ ፈሩም፡፡ ስለዚህም ወደ ጫካው ዘልቀው ገቡና ከብርሃን እግዚአብሔር ፊት ተሸሸጉ፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 3፥8)

    እነሆም አዳም በባሕሪይው ከእንግዲህ ብርሃንን በመፍራትና ባለመፍራት መካከል የሚዋልል አዲስ ጠባይ ያለው ሰው ሆነ ማለት ነው፡፡ መልኩን በመግለጥና ባለመግለጥ ፈንታ የሚዋትት ሕይወትን ጀመረ ማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ ነፍሱ በሥጋው ላይ እንድትሰለጥን መንገዱን በእምነት ጎዳና አድርጎ ከከፈተላት፤ እስትንፋሲቱም ከእግዚአብሔር የተካፈለቺውን መለኮት በሥጋ ላይ በመግለጽ መንፈሳዊ ጠባያቶቿን ታስነብባለች፡፡ ሰው ፍቅርን ፍጹም አጽንቶ ሲመላለስበት፤ ከሞት ቅጣት ጋር ተያይዞ የመጣበትን የቀደመውን ፍርሃት አውጥቶ ይጥላል፡፡ (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፥18)

   ቅዱሳን ሰማእታት ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ተገደው፤ እሳት ውስጥ የሚገቡት፣ በመጋዝ የሚሰነጠቁት፣ ወደ ገደል የሚወረወሩት፣ በፈላ ውኃ የሚቀቀሉት፣ በሰይፍ የሚታረዱት፣ በጦር የሚወጉት ለዚህ ነው፡፡ በጽድቅ አኗኗር ዘመናቸውን ሲያሳልፉት፤ የነፍስ ተፈጥሮአቸው እንደ ቀደመው የአዳም ገጽታ በሥጋ ላይ ብርሃን ሆኖ ስለሚሰለጥን፤ ከነፍስ ወደ ውጨኛው አካል የሚፈልቀው ፍቅር በዓለም ላይ ዲያቢሎስ የሚነዛውን ፍርሃት ሁሉ ገርስሶ ይጥልላቸዋል፡፡

    ሰዎች እንግዲህ ፍቅርን በመኖርና ባለመኖር መካከል ዕለቶቻችን እየዋዠቁ የሚገኙት፤ ነፍስ ከአካሏ እግዚአብሔር ጋር በመሆን ባሕሪያቶቿን እንዳታንጸባርቅ ርኩሳን መናፍስት በብዙ መስመሮች አልፈው ወደ ኑሮአችን እየመጡ የጥላቻን ገጽታ እንድናውቀው በሥጋ ምሽግነት ስለሚዋጉን ነው፡፡

    ሔዋን ስለ ዛፉ ፍሬ እያሰበች ያላትን መለኮታዊ መልክ እንዳታስተውል መንፈሱ የመጤ እውቀት ጥላ ሆኖ ከፊት ወደኋላ እንደሸፈናት፤ ሁላችን የአዳም ዘሮች ትክክለኛውን የፍቅር ትርጉም በዓለማዊ ፍልስፍናዎችና ትንተናዎች አዛብተን መልካችንን እንድናጣ፤ በየዘመኑ በሚነሡ ርዕዮቶች፣ አመለካከቶች፣ ፍልስፍናዎች፣ ንድፈ ሐሳቦች፣ የኑሮ ዘይቤዎችና ሳይንሳዊ አስተንትኖቶች ጀርባ ዲያቢሎስ የራሱን ጽልመታዊ አካሄድ እያስገባ፤ ተፈጥሮአችንን እያበላሸው ይገኛል፡፡
994 views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 11:38:27 1• ፍቅር

1.1• ፍቅር ምንድነው?

ክፍል - ፩

  ✞ የሰው መልኩ ፍቅር ነው

"እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 2፥7)

    አምላክ ፍጥረታትን ሁሉ በስድስት ቀን ተከታታይነት ፈጥሮ ሥራውን ካበቃ በኋላ፤ በመጨረሻው ላይ ከፈጠራቸው ፍጡራን ሁሉ ለየት ያለ አንድ ፍጡርን በረቂቃን እጆቹ ሠራ፡፡ የመሬትንም ጭቃ አንስቶ ከመለኮቱ ኃይል የወጣ እስትንፋስን አሳረፈበት፡፡ በዚህ ጊዜ ሸክላው መንቀሳቀስ ጀመረና ሕይወት ያለው ልዩ አካል ሆነ፡፡  (እግዚአብሔር ከሁሉ የተሰወረ ሕላዌ ያለው መንፈስ ነውና፤ ጭቃ አንስቶ ሠራን ሲባል፥ ይሄ ክንውን መንፈሳዊ አንድምታ እንዳለው መረዳት ይገባናል፡፡ በሥጋ ምናብ እንደምንስለው አፈር የማድቦልቦል አይነት ሥራ ሠራ ማለት አይደለም፡፡ )

   በተገለጸው የአፈጣጠራችን ሂደትም መሠረት የሰው ልጆች ከፍጥረታት ሁሉ በሦስት ነገሮች እንለያለን፡፡ አንደኛ ከሁሉ በስተመጨረሻ የተገኘን የአምላክ አሳብ መጥቅለያና ማረፊያ በመሆናችን እንለያለን፡፡ ሁለተኛ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ያስገኛቸው በቃሉና በአርምሞ ሲሆን፤ እኛን ሁላችን ግን የእጁ ሥራ ነን፡፡ (ኢሳይያስ 64፥8) ሦስተኛ ምድራዊ አካል አፈር እና ሰማያዊ አካል የመለኮት እስትንፋስ ተዋሕደው ባሕሪያችንን ገንብተዋል፡፡ እነዚህ ሦስቱ ልዩነቶችም የሰው ልጅ ከሁሉ ፍጥረታት ይልቅ በእጅጉ የከበረ ፍጡር ስለመሆኑ ያሳያሉ፡፡

    በሦስተኛነት የተጠቀሰው የልዩነታችን እውነት ግን የከበረን ፍጡራን ብቻ ሳንሆን የእግዚአብሔር መልክ የተሳለብን የንጉሥ ልጅ ንጉሦች እንደሆንን ያስረግጣል፡፡ "እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤" (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26)

    እግዚአብሔር በራሱ መልክ አምሳል አድርጎ ሰዎችን የፈጠረው በእስትንፋሱ በኩል ነው፡፡ ሁሉንም ፍጡራን ሲያስገኝ ከክሂሎቱ እውቀት ወይንም ከሌላ ተፈጥሮ በመውሰድ በሥልጣኑ ጥበብ ሲፈጥር፤ አዳምን ግን ያስገኘው ከራሱ ውስጥ ካለ መለኮት አካፍሎ፥ እስትንፋሱን ነፍስ አድርጎ በመለገስ ነበረ፡፡

    የሰው ልጅ አርአያ አምላክ ነው ሲባል፤ በተክለ ቁመናው፣ በአካላዊ ገጽታውና በተፈጥሮ ቅርጹ አይደለም፡፡ ይልቅስ በነፍሱ ነው፡፡ ነፍስ ከእግዚአብሔር አካል እስትንፋስ በመውጣት ሳትጎድል፥ በኛ ሥጋ ውስጥ በማደሯ፤ የርሱን ረቂቅ ባሕሪያት ማንነቷ አድርጋ በመያዝ ፈጣሪን የሚመስል ሕልውና ይዛ ትገኛለች፡፡

    ነፍስ የእግዚአብሔር ክፍል እንደመሆኗ መጠን፤ እርሱ የሆነውን ነች፡፡ አምላክ መለኮታዊ ባሕሪይ እንዳለው እርሷም ከዚህ ባሕሪይ ተካፋይ ነች፡፡ አምላክ ረቂቅ ኃይል እንደሆነ እርሷም መንፈሳዊ አካል ነች፡፡ አምላክ በልዩ ሦስትነትና አንድነት ማንነቱ ሲገለጥ፤ እርሷም ሦስት ባሕሪያትን በአንድ አካል ላይ ሳትቀላቅልና ሳትነጣጥል ይዛለች፡፡ አምላክ የማይለወጥ አንድ ፈጣሪ እንደሆነው፤ ነፍስም መሞት፣ መጥፋትና መቀየር የማያገኛት ጽኑዕ ነች፡፡ አምላክ የሁሉ አስተዳዳሪ ንጉሥ እንደሆነ፤ የንጉሥ አካል ንጉሥ የሆነቺው ነፍስም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ አዳም እንዲገዛ ምክንያት ነበረች፡፡ "...የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26)

    አሁን ይህንን ግንዛቤ እንደ መሠረታዊ ብያኔ ወስደን፤ ወደተነሣንበት ርዕስ ስንመጣ "ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው?" የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፥8 ላይ "እግዚአብሔር ፍቅር ነው" በማለት ያስቀምጣል፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ ዘንዳ፥ ነፍስም ደግሞ ፍቅር ናት፡፡ በሌላ አገላለጽ፤ ፍቅር ማለት የነፍስ ጠባይ ነው፡፡ ፍቅር ማለት የሰው መለኮታዊ መልክ ነው፡፡

    ፍቅር የተሰኘውን የእግዚአብሔርነት አካል፤ የምንማረው፣ የምንሰለጥነውና እንደ መረጃ የምንቀበለው ግኝት ወይንም እውቀት አይደለም፡፡ (ከሰው ልጆች መካከል የገዛ መልኩን ከሌላ ሁለተኛ አካል የሚቀበል ማነው?)

    ፍቅር ስንወለድ አብሮን የሚወለድ ማንነት ነው፡፡ ፍቅር ስናድግ አብሮን የሚያድግ አካላችን ነው፡፡ ፍቅር ባለ የሕይወት ዘመናችን ሁሉ ላይ የማይጠፋ፣ የማይቆረጥ፣ የማይለይና የማይጣል ውሳጣዊ ክፍለ ባሕሪይ ነው፡፡

    አንዳንዴ ሰዎች "እኔ ፍቅር የለኝም" ብለው በደፈናው ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ አላወቁትም እንጂ እያሉ ያሉት "እኔ መልክ የሌለኝ ሕይወት አልባ ፍጡር ነኝ" ነው፡፡ ያለ ነፍስ የተፈጠረ አንድም የሰው ዘር እንደሌለ ሁሉ፤ ያለ ፍቅርም የተገኘ ነፍስ ሊኖር አይችልም፡፡

    ፍቅርን ከሕልውናው መዝገብ አውጥቶ የጣለ ብቸኛው ፍጡር ዲያቢሎስ ነው፡፡ (አሁን ያለንበት ዓለም የፍቅርና የጥላቻ ፍትጊያ መነሻ ሰበዙ የሚመዘዘው ከዚህ ፍጡር የዓመፃ ታሪክ ላይ ነውና እስቲ ነገሩን በዝርዝር እንየው)

    ከሁሉ አስቀድሞ በራሱ ዓለም ይኖር የነበረው ቅዱስ እግዚአብሔር፤ በአርምሞ ኃይል "ሰማይንና ምድርን በመጀመሪያ ከፈጠረ" በኋላ፤ በቃል በመናገር ደግሞ እግዚአብሔር በፈጠረው ዓለም ላይ "ብርሃን ይሁን አለ፡፡" ኦሪት ዘፍጥረት 1፥3)

    የእግዚአብሔር ቃል ብርሃንን ወደ ዓለም ከማስገባቱ በፊት፤ ሰማይና ምድር በተፈጠሩበት የመጀመሪያው ቀን አብረው ስለተፈጠሩት መቶ የመላእክት ነገድ በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች በርካታ መንፈሳዊ መጽሐፍት ላይ ተመዝግቦ እናገኛለን፡፡ ከእሳትና ከነፋስ በልዩ ጥበብ የተፈጠሩት መላእክት፤ ሁሉ ጨለማ በነበረበት የዓለም ገጽታ ውስጥ ፈጣሪያቸውን ለማግኘት በተሰጣቸው የእውቀት ፈቃድ መመራመር ያዙ፡፡ መላእክቱን ሁሉ መርቶ ወደ አምላካቸው እንዲያደርስ አለቃ ሆኖ የተመረጠው ሳጥናኤል ነበረ፡፡

    ይህ መልአክም የእግዚአብሔር ሕልውናና ኃይል በብርሃን ባልተገለጠበት ሁኔታ ከእርሱ ማዕረግ ከፍ ያለ ሕይወት ያለው ፍጥረት አለመኖሩን ከተረዳ በኋላ በልቡ የመታበይን አሳብ አፈለቀ፡፡ (ዲያቢሎስ ክፉ ማንነቱን ከባሕሪዩ ወይንም ከልቦናው ነው ያነቃት፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ በጭራሽ የማይታውቅ ጠባይን ከእውቀቱ ውስጥ በራሱ ፈቃድ አፍልቆታል፡፡ (ትንቢተ ኢሳይያስ 14፥8-20 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 8፥44) በእርግጥም በባሕሪይው ፍጹም ቅድስና ያለው እግዚአብሔር፤ ሃያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረታት ሲፈጥር አንድም ቅዱስ ያልሆነ ፍጥረት አላስገኘም፡፡ ኦሪት ዘልደትም በመነሻው ላይ ከፍጥረታት መገኘት በኋላ "መልካም እንደሆነ አየ" በማለት ስድስት ጊዜ በተደጋጋሚ ያስቀመጠው የእግዚአብሔር እይታ፤ በስድስት ቀን ውስጥ የተፈጠሩት ሁሉም ፍጡራን በፈጣሪያቸው ቅድመ አሳብ መልካም እንደሆኑ ያስረዳል፡፡)

    ከዚህ ጊዜ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በዓለም "ብርሃን ይሁን" የሚለውን አምላካዊ ሥልጣን ገለጠ፡፡ በተፈጠሩበት የቅድስና አሳብ ጸንተው የቆዩት መላእክት ይህንን ኃይለ ጸዳል ለብሰው ብርሃናውያን ሲሆኑ፤ ክሕደትን ያስገኘው ሳጥናኤልና ያመኑበት መላእክት ደግሞ ጽልመትን ማንነት ጨለማን መገለጫ አድርገው ቀሩ፡፡ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፥12)
959 views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ