Get Mystery Box with random crypto!

በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper

የቴሌግራም ቻናል አርማ bekurnewspaper — በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper
የቴሌግራም ቻናል አርማ bekurnewspaper — በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper
የሰርጥ አድራሻ: @bekurnewspaper
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.53K
የሰርጥ መግለጫ

የሰኞ ጋዜጣዎ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-13 11:57:16 ጠቁመዋል::
ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደተናገሩት የንፁሀንን ጭፍጨፋ ለማዳን የተቀናጀ የፀጥታ እና የደኀነት መዋቅር ተገንብቷል:: ሕዝባችንን አንቅተን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንዲተባበር አድርገን እርምጃ በመውሰድ አሸባሪ ቡድኖች ይጠፋሉም ብለዋል:: ሕዝብ እና መንግሥት አብረው ከቆሙ አሸባሪዎች መጥፋታቸው አይቀርምም ብለዋል:: “እኛ ባለመግባባታችን ምክንያት ጠላቶቻችን ብዙ ጥፋት እያደረሱ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ውስጣዊ ሀገራዊ መግባባት ለውጭ ጠላቶች የመካችነት ሚና እንዳለው አመላክተዋል::
ጠቅላይ ሚንስትሩ የተከፈተብን “የግራጫ ጦርነት ነው” ብለዋል:: ጦርነቱ በተልዕኮ የሚፈጸም ሆኖ በመረጃ በዲፕሎማሲም በሳይቨርም የተቀናጀ ነው ብለዋል:: እንዲህም ሆኖ የሀገር ደኀንነትን ለመጠበቅ መከላከል፣ መከታተል፣ መጠበቅ እና መዘጋጀትን እንደ ስትራቴጂ በመጠቀም አሸናፊነታችንን እናረጋግጣለን ብለዋል::

(የሺሃሳብ አበራ)
በኲር ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።
668 views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:57:16 የፈተናዉ አቅጣጫ ከየት ነው?
ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም
በዘውጌ አወቃቀር ላይ ጥላቻን ደርቦ ስርዓት የተዘረጋለት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መረጋጋት ርቆታል። የከረረው ዘውጌነት (ጽንፈኛ ብሄርተኝነት) ራስን የመውደድ መገለጫው ሌላውን አብዝቶ መጥላት አስመስሎ አስተርጉሞታል። ይህም በጋራ የማዘን እና በጋራ የመደሰትን ስሜት አንጥፎታል።
የጋራ ነባር እሴቶች፣ ወላዊ መገለጫዎች፣ ኢትዮጵያዊያን እንደ ዜግነት ብሎም እንደሰውነት የሚጋሯቸው ለረጅም ዘመን የቆዩ የአብሮነት ልምዶች ወደ ፈተና ገብተዋል። ለዚህ ምክንያት ትልቁ በዘውግ ላይ የተተከለው እና ጥላቻን እንደ ስርዓት የሚመለከተው ፖለቲካ ሲሆን ለዚህ ማጀቢያ ደግሞ ውጫዊ ጫናዎች ይኖራሉ።
በተለይ ዘውግ ተኮሩ ፖለቲካ ከችሎታ ይልቅ የተወለደበት አፈር አካባቢ እና ዘር ማንዘሩ፣ ከምክንያት ይልቅ የመንጋ እሳቤ፣ ከእውነት የራቀ ፖለቲካዊ ተረክ፣ የጥላቻ ዘመቻዎች የኢትዮጵያን የፖለቲካ አየር ተቆጣጥረውታል። ይህም ለውስጣዊ አንድነት ፈተና ሆኗል::
ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያው አቶ ሄኖክ አበበ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ለውጥ መጣ ከተባለበት ጊዜ በፊት እና በኃላ ነገሮች በመደበኛ ሁኔታቸው እየፈሰሱ አይደለም የሚል ምልከታ አላቸው። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር በመደበኛው የመንግስት አሰራር እና የፖለቲካ አመራር የሚፈቱ ባለመሆናቸው ተጨማሪ የመፍትሄ አምጭ አደረጃጄቶች አስፈላጊ መሆናቸዉን ጠቁመዋል። በሀገር ውስጥ የታጠቁ ቡድኖች እንደ አሸን ፈልተው ንፁሃንን በግፍ ይጨፈጭፋሉ። እነዚህ የታጠቁ ቡድኖች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በውጭ ሀገራት ድጋፍ ሊደረግላቸው ይችላል።

የአማራ ፖለቲካ
በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ውስጥ በተለይም ከ1983 ወዲህ በአማራው ላይ የማያባራ ማንነታዊ መገለል እና ጭፍጨፋ ደርሷል:: አልጀዚራ “አማራነት በኦሮሚያ ክልል የሞት ቅጣት ውሳኔ” መስሏል ሲል ትንታኔውን አቅርቧል::
አቶ ሄኖክ የአማራ ህዝብ ትግል ከግብ እንዳልደረሰ እና ጥያቄዎቹንም ማስመለስ እንዳልቻለ ይናገራሉ:: አሁን የአማራ ጥያቄ ከፖለቲካ መብት ወጥቶ ወደ ሕልውና ጥያቄ ወርዷል:: የአማራ ክልል መንግሥት የአማራ ጥያቄዎችን በስርዓት እና በተቋም ደረጃ ባለመውሰዱ የአማራ ፖለቲካ የዋይታ እና የጫጫታ መስሏል::
አቶ ሄኖክ እንደተናገሩት የአማራ ህዝብን መንግሥታዊ መዋቅር የያዘው አካል የመንግሥት ተቋማትን፣ ስልጣን (authority)፣ መረጃ፣ ገንዘብና የፀጥታና የደኀንነት ተቋማት ይዞ የአማራን ህዝብ ትግል የራሱ ጥያቄዎች አድርጎ ለትግሉ ድጋፍ ቢሰጥ ኑሮ በብዙ መልኩ የአማራ ጥያቄዎች ላይ ለውጥ ይኖር ነበር::

የግጭቶች እና የጭፍጭፋው መንስኤ
ኢትዮጵያ የአባይ ግድብን ልትሞላ ነውና የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ፍጅት ይህንን ለማስተጓጎል ጠላቶቻችን የዘየዱት መላ ነው የሚለው አባባል ስህተት ነው የሚል ምልከታ አቶ ሄኖክ አላቸው:: እንዲህ አይነት አባባሎች ንፁሃን ዜጎችን የመጠበቅ ግዴታ ካለበት የመንግሥት አካል ሲሰማ መንግሥትን ይበልጥ ትዝብት ውስጥ ይጥላል::
የአማራ ህዝብ በየቦታው ሲገደል የኖረ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከመጀመሩ አስርት አመታት በፊት ጀምሮ ነው:: የአማራ ህዝብ የዘር ፍጅት የጀመረና ሲተገበር የኖረ ላለፉት በርካታ አመታት ነው:: የጭፍጨፋው ምንጭም በጥላቻ ላይ የበቀለው ስርዓታዊ እና ተቋማዊ መዋቅሩ ነው፤ ጭፍጨፋው መዋቅራዊ ነው:: መዋቅሩ በግብጽ ወይም በሌላ ሀገር ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ገዥ መንግሥታት የተሰራ በመሆኑ መፍትሄዉ የህግ እና የስርዓት ማስተካከያ ማድረግ መሆኑንም አቶ ሄኖክ ይጠቁማሉ ::
በሁለተኛ ደረጃ የአማራ ህዝብ የዘር ፍጅትን እያካሄዱ ያሉት ኢትዮጵያ እንድትዳከም የሚፈልጉና የአባይን ግድብ ሙሌት ለማስተጓጎል የሚፈልጉ ሃይሎች ቢሆኑ እንኳ ለአማራዎች ዘር ፍጅት እንደ ምክንያት ሊቀርብ የሚችል ጉዳይ እንዳልሆነም የህግ ባለሙያው ተናግረዋል:: በእርግጥ የውጭ ኃይሎች ጨፍጫፊውን አካል (የትጥቅ ቡድኖችን) በመደገፍ፣ እንደነ ሱዳን ያሉት ደግሞ በቀጥታ ወረራ በመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ እንዲኮስስ በማድረግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እየተዳፈሩ ነው::
አቶ ሄኖክ እንዳብራሩት የውጭ ጫናን መመከት የሚቻለው ውስጣዊ አንድነትን በማምጣት ሲሆን ውስጣዊ አንድነት ደግሞ ፍትህን እና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ይመጣል:: አንዱ ጨፍጫፊ ሌላው ተጨፍጫፊ ሆኖ ግን ሀገራዊ አንድነት አይኖርም::
መንግሥት ጠንካራ እና የጠራ መስመር ስሌለው የጎራ መደበላለቅ ተፈጥሯል:: ብዙ የመንግሥት ኃላፊዎች የትጥቅ ቡድኖችን በመደገፍ ጭፍጨፋውን እንደ ደገፉት ከጥቃቱ የተረፉት ብቻ ሳይሆን የምክር ቤት አባላትም እየተናገሩ ነው:: ይህ ደግሞ ሀገራዊ አንድነትን ያዳክማል፤ የውጭ ጫና የሚመጣው የተዳከመ አንድነት እና የተዳከመ ዲፕሎማሲ ባላት ሀገር ውስጥ ነው::
ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫናዎች እንዴት እልባት ይሰጣቸው?
አቶ ሄኖክ ግብጽ ወይም ሱዳን አተራመሰችን ብሎ ችግርን ውጫዊ ከማድረግ የገዥው መንግሥትን አለመጠንከር፣ የፖለቲካ ልሂቃን ተቃርኖ እና አካታች መንግሥት አለመፈጠሩ የበለጠ ለሀገር ሕልውና አስቸጋሪ እንደሆነ ያምናሉ:: የውጭ ጫናን መቀልበስን ከማንሳት በፊት ለውስጥ ጉዳይ እልባት መስጠትን በቀዳሚ መፍትሄነት ያነሱታል::
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር በእውቀቱ ድረስ የምስራቅ አፍሪካ ግጭቶችን መንስኤ እና የአፍሪካ ድርጅቶች ምላሽ በተመለከተ ጥናት አድርገዋል:: በጥናታቸው ላይ እንዳመላከቱት የምስራቅ አፍሪካ ማህበረ ፖለቲካ እና መልካዓ ፖለቲካ ተመሳሳይ የችግር ቀለበት ውስጥ ይገኛል::
የአፍሪካ ሀገራት በጉርብትናቸው እንደ አውሮፓ ሕብረት ተባብረው ከመነገድ እና ሰላማቸውን ከማስጠበቅ ይልቅ የርስ በርስ ሽኩቻ ውስጥ ናቸው:: የሚገርመው ደግሞ ከጎረቤት ሀገራትም፤ በራሳቸው በሀገራቸው ውስጥም የርስ በርስ ጦርነት እና ግጭቶች አሉ:: ውጫዊ እና ውስጣዊ ግጭቶች ተዳምረው በተለይ ምስራቃዊ የአፍሪካ ክፍልን ረሃብ በየጊዜው እንዲጎበኘው በሩ ተከፍቶለታል::
ዶክተር በእውቀቱ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ብለው በጥናታቸው ያመላከቱት ሀገር አቀፍ እና ሀገር በቀል የመፍትሄ አማራጮችን መተግበር እና ፊትን ወደ ልማት ማዞር ነው:: ልማት የሌለው ሀገር ተበዳሪ ስለሚሆን ሉዓላዊነቱ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባበታል:: ተግባራዊ የሚሆነውም የውጭ ሐሳብ በመሆኑ ሀገራዊ እሴቶች እንዳይዳብሩ ያደርጋል:: የአፍሪካ ተቋማት ያለመዳበራቸው እና መፍትሄ ሰጭ ያለመሆናቸው ምስጢርም ሐሳብ እና ገንዘብ ከሀገር ሳይሆን ከውጭ በመምጣቱ በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ውስጥ ስለሚገቡ ነው::
ዶክተር በእውቀቱ ውስጣዊ አንድነት በአንድ ሀገር ውስጥ ግጭትን አቁሞ ወደ ሰላም እና ልማት ለመጓዝ አስቻይ መንገድ መሆኑንም በጥናታቸው አመላክተዋል::
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት ጨፍጫፊዎች እግርም ጭንቅላትም የላቸውም፤ አስቦ የሚልካቸው ሌላ የውጭ ኃይል ነው ብለዋል:: ኢትዮጵያ በታሪኳ እና በተፈጥሮ ሐብቷ ምክንያት በጎ እይታ የሌላቸው የውጭ ሀይሎች መኖራቸዉን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ አካላት ኢትዮጵያን በማተራመስ ማዳከም ቢፈልጉም፤ እንደማይችሉ ተናግረዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውስጥ ያሉ ሀይሎችን የውጭ ጠላቶች መጠቀሚያ እንዳያደርጓቸው የሰላም በር ሁሌም ክፍት ነውም ብለዋል:: ለሰላም እና ለሀገራዊ አንድነት ሲባል ከሕወሓት ጋርም የድርድር ሐሳቦች እንዳሉ
949 views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:56:07
1.0K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:04:05
2.6K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:03:57 የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ
ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ለአማራ ክልል መልሶ ማቋቋምና ግንባታ የሚውል የድጋፍ ስምምነት አድርጓል።
በስምምነቱ ወቅት በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ቱርሃን ሳለህ እንዳሉት በጦርነቱ ምክንያት በአማራ ክልል ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል፤ ይህንንም ድርጅታቸው እንደተገነዘበ ተናግረዋል። በመሆኑም ለመልሶ ግንባታው ከአማራ ክልል ጋር በቅርበት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
በጦርነት የደረሰውን ውድመት መልሶ ከመገንባት በተጨማሪም ሠላምና ደኅንነት እንዲሰፍን የፍትሕ ተቋማትን እንደሚደግፉ ተናግረዋል። ለዚህም ከክልሉ ጋር በቅርበት እንደሚሠሩ አመላክተዋል። በተመሳሳይ ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚሠራም ነው ተጠሪው የተናገሩት።
አማራ ክልልን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ጥላሁን መሐሪ ለተደረገው ድጋፍ ድርጅቱን አመስግነዋል፤ መሰል ተቋማትም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራምን አርዓያነት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በስምምነቱ ወቅት እንደተነገረው ድጋፍ የተደረገው አጠቃላይ 14 የመስክ ተሽከርካሪዎችን እና ላፕቶፖችን ጨምሮ ከሦስት መቶ ሚሊዮን ብር (6 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) በላይ ነው።
(ጌትሽ ኃይሌ)
በኲር ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።
2.3K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:03:36
1.7K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:03:23 በቀን ዘጠኝ ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነዉ
ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
በቀን ዘጠኝ ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን የነዳጅ እና የኢነርጂ ባለስልጣን ገለፀ፤ የነዳጅ አቅርቦቱ በቂ ነው ቢባልም እጥረት መከሰቱ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል።
በየከተሞች ነዳጅ ለመቅዳት ረጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች መመልከት የተለመደ ክስተት ሆኗል። ይህም በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ መስተጓጎልን ፈጥሯል። የኢትዮጵያ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ለኢቢሲ እንደገለፀው ከሀምሌ ጀምሮ የሚደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በማሰብ ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ሆን ተብሎ እንዲዘገዩ ይደረጋል።
ከዚህም ባለፈ አራት እና አምስት ማደያ ያላቸው ባለሀብቶች በአንዱ አገልግሎት እየሰጡ፣ ሌላኛውን ዝግ በማድረግ በቀጣዮ የሚስተካከለው የነዳጅ ጭማሪ የሚጠብቁ እንዳሉም ተጠቁሟል።
ባለስልጣኑ በሀገሪቱ 1 ሺ 200 ማደያዎች እንዳሉ ጠቅሶ በአግባቡ በማይሰሩ የነዳጅ ማደያዎች እና በሕገወጥ የነዳጅ ንግድ ዙሪያ በተሰማሩ ሁሉ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ብሏል። ለዚህም በየክልሎች ሰፊ ቁጥጥር እንደሚደረግ ባለስልጣኑ አሳውቋል።
በቀጣይ ሀምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንደሚደረግበት ይጠበቃል።
(የሺሃሳብ አበራ)
በኲር ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።
1.6K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:02:57 ጠላት አማራን ማፍረስ ለስኬት ያበቃኛል የሚል ዓላማ ይዞ እየሠራ መሆኑ ተገለፀ
ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
በውስጥ እና በውጭ ጠላቶቻችን በመታገዝ ለጠላት የሚላላኩ አካላት ዜጐቻችንን በመጨፍጨፍ በብሔረሰቦች መካከል ግጭት በመፍጠር የአማራን ሕዝብ አንድነት የማፍረስ ዓላማ ይዘው እየሠሩ መሆኑ ተነገረ::
ሰሞኑን የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት የክልሉን አሁናዊ ሁኔታ የገመገመ መሆኑን አስመልክቶ የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት ጋዜጣዊ እንዳሉት የጠላትን ዓላማ በማክሸፍ የክልሉን ሕዝብ አንድነት ለመጠበቅ ሕግና ሥርዓትን ማስከበር ተጀምሯል። የሕዝቡ ጥያቄ መነሻ ያደረገው የሕግ ማስክበሩ ሂደት ኅብረተሰቡ በልማት ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ዕድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል::
“ኅብረተሰቡ ሰላሙ እና ደኅንነቱ እንዲከበር በተለያዩ ሕዝባዊ መድረኮች ይጠይቅ ነበር” ያሉት ቢሮ ኃላፊው በሕግ ማስከበሩ ሂደት በፀጥታ መዋቅሩ፣ በፖለቲካ አመራሩ እና በሕዝቡ ቅንጅት መልካም እና ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል::
ውስጣዊ አንድነታችንን ለማጠንከር የሕግ ማስከበሩ ሥራ ሲከናወን መቆየቱን ያወሱት አቶ ግዛቸው ክልሉ በተፈናቃዮች እንዲሞላ፣ ዜጐችን በማቋቋም እና በመመገብ ሥራ እንዲበዛበት በማድረግ በእሳት ማጥፋት ሥራ ብቻ እንዲወጠር ታስቦ እየተሠራ መሆኑን የፀጥታ ምክር ቤቱ ግንዛቤ ወስዷል ብለዋል::
“የሕዝቡን አንድነት የሚያናጉ ድርጊቶችን በማፍረስ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በተጠና መልኩ በመሄድ በዋና ዋናዎቹ የጠላት ኃይል ዙሪያ ማተኮር አለብን” ያሉት አቶ ግዛቸው ውሳጣዊ ሁኔታዎችን በማጥራት ከኋላ የሚወጋንን ኃይል ለማስወገድ ከፍተኛ ዝግጅት አየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል::
በውስጣችን ያለ ጫጫታ በበረከተ ቁጥር ትልቅ ብትር ለማሳረፍ የተዘጋጀ የጠላት ቡድኖች ሁሌም አሰፍስፈው እየጠበቀ በመሆኑ በየዕለቱ አዳዲስ የብጥብጥ አጀንዳዎችን በመምዘዝ አንድነታችንን ለማላላት ለሚፈልጉ የጠላት ኃይሎች ኅብረተሰቡ መሣሪያ እንዳይሆንም አሳስበዋል::
በየጊዜው በሚጨፈጨፉ ዜጐቻችን የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶታል ያሉት ቢሮ ኃላፊው ችግሩን ከሥሩ ለማስወገድ ከአጐራባች ክልል መንግሥታት ጋር በከፍተኛ መግባባት የተመሰረተ ሥራ በታቀደ መልኩ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል::
“በዜጐቻችን ላይ አየደረሰ ያለውን ጥቃት እስከወዲያኛው ለመከላከል እንዲቻል ውስጣዊ አደረጃጀትን በማጠናከር ላይ አተኩረን እየሠራን ነው” ያሉት አቶ ግዛቸው ጠንካራ እና መሠረት ያለው የሚሊሺያ እና ሌሎች አደረጃጀቶችን በማጠናከር ከፀጥታ ሥራ ጐን ለጐን የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል::
(ደረጀ አምባው)
በኲር ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።
1.4K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:02:32
1.1K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ