2022-07-07 07:58:03
ኧ..ይገርምሀል! አለኝ"በእንባ የረጠቡ ጉንጮን በእጁ በያዘው ሶፍት እያደረቀ "በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ፊት ለጸሎት ለመቆም ወደ መቅደሱም ለመግባት የሌሊቱን ጨለማ መገፈፍ መታገስ የሚሳነኝ ነበርኩ! ...አሁን ግን¡ ...ስሜቱን መቋቋም ስላቃተው አንገቱን በእግሮቹ መሀል ደፍቶ ማልቀሱን ቀጠለ። .. ቀና ላደርገው እንባውንም ልጠርግለት አልፈለግሁኝም ምክንያቱም በእንባው እግዚአብሔርን ያገኘዋል።"[ይህ ጊዜ ይቆየን]
አቡነ ሺኖዳ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላለን ሰዎች ከኃጢአተታችን የእግዚአብሔር ቸርነት እንደሚበልጥ አውቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ሲናገሩ እንዲህ አሉ"እግዚአብሔር ድካምህን እንደሚያውቅና እስካሁን ድረስም እንደሚወድህ እርግጠኛ ሁን ! በኃጢአት ውስጥ ብትሆንም እግዚአብሔር ሊያድንህ ወደ እርሱ ሊያቀርብህና ወደ ቀደመ ደረጃህ ሊመልስህ እንደሚሰራ እመን ። አዳም የዳነው ንሥሐ ለመግባት ባደረገው ሙከራ ሳይሆን አዳምን_በተመለከተው_የእግዚአብሔር_ቸርነት_ነው ።"
በነበርኩ አለኝ!
"እግዚአብሄርን የቀመሰች ነፍስ ኃጢኣት ምን ያክል እሳት ሆኖ እንደሚያቃጥላት ተመልከቱ። ወንድሜ ተነስ! አንተ አስቀድመው ታማኝ አገልጋይ እንደነበሩት ኋላ ግን ሰም አጠራራውቸ ከምድር እንደጠፋ የሚያልፈውን አለም ወደው የሚታየውን እንጂ የማይታየውን ባለማየት አንደጠፋ ዴማሳውያን አትሆንም። ይልቁንም
"የጦር መሪዎች--> ሰማዕታት"
"ቆነጃጅት --> ደናግላን"
"ነገስታት --> መናንያን"
"ገዳዎች-->ሟች"
"ተቃዋሚዎች --> ሐዋርያት"
"አሳዳጆች --> ወንጌላውያን" ለሆኑለት አለታችን ክርስቶስ በቁርጥ ህሊና በትህትና ሆነህ ታገለግለዋለህ!
ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ "ነበርኩ" ሊል ስለፈለገ 'የኋላ ታሪክ ያለው ጻድቅ' መሆኑን ሲገልጥልን የቅዱሳን ሐዋርያትን ስም ሲዘረዝር ራሱን"ቀራጩ ማቴዎስ" ብሎ ፃፈ። ቅዱስ ጳውሎስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ኃይል እንደተሰጠው ታማኝ አገልጋይም ተደርጎ መሾሙን ከገለጠ በኋላ "ነበርኩ" በማለት አሳዳጅነተቱን'ተሳዳቢ አንገላችም ካለ በኋላ ከእግዚአብሔር ትዕግስትና ምህረት የሚበልጥ ኃጢአት የለም ሲል "ምንም"ስሆን በማለት "ምንም" ለሆንን ለእኛ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ አለም እንደመጣ ይነግረናል። ቅዱስ አውግስጢኖስ 'ነበርኩ'በማለት የቀደመ የወንበዴነት ህይወቱን እና አሁን ያለበትን ህይወት የማይነፃፀር መሆኑን ሲገለፅ" አንተ በእኔ ውስጥ እያለህ እኔ አንተን በውጪ እፈልግህ ነበር"አለ። ተፈትነው ወድቀው የቀሩ ይሁዳንና ዲያቆኑ ኒቆላዎስን ደግሞ ተመልከቱ " ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፤ እርስዋም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው። "(መጽሐፈ ምሳሌ 7:26)
እጅግ ልብን የሚመስጥ ህይወት የኖሩትን ከቀራጭነት ከዝሙት ተዳዳሪነት ከክህደት ከምንፍቅና ወደ ቅድስና የገቡትን በዙሪያችን የእግዚአብሔርን ምህረትና ፍቅር የምንመለከትባቸውን ብንመለከት መልካም ነው። እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ ................በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ ............የጸናውን አስቡ።[ዕብ 12:1-3]
ብዙ ጊዜ ብዙዎቻችን እግዚአብሔር ቅዱሳን ትዕዛዛቱን የሰጠን ሰው መሆናችንን ረስቶት ይመስል 'ሰው' መሆናችንን ለደካማነታችን ምክንያት አድርገን አናቀርባለን። አንድ አረጋዊ ለደካማነታችን ሰው መሆናችንን ምክንያት አድርገን ልናቀርብ እንደማይገባ ይልቁንም ሰው በመሆናችን እንደ መላዕክት ልንሆን እንደሚገባን ሲገልፁ እንዲህ አሉ"ሰው መሆንህን ለድካምህ እንደ ምክንያት አታቅርብ በትዕግስት መልዐክ መሆን ትችላለህና! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚወዱትና ፈቃዱን ለሚፈፅሙት እንደ መላዕክት ይሆኑ ዘንድ አስደርጓቸዋልና።" እስኪ ስለዚህ ሰውነት እናውቅ ዘንድ አይኖቻችንን ቅዱስ ዳዊት ለልጁ ለሰለሞን ወደመከረው ምክር እናቅና"" በርታ ሰውም ሁን፤ የምታደርገውንና የምትሄድበትን ሁሉ ታከናውን ዘንድ............ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።"[መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 2:3]
በምድር ላይ እንደ እንስሳ መኖር ስትመርጥ እና እንደ ሰው ለመኖር አቅም ስታጣ እንደ መላዕክት የኖሩ አበው መነኮሳተት በፀጋቸውና በተጋድሎአቸው በፍፁምም አፍቃሪነታቸው ከመላዕክት ይበልጣሉ የተባሉ[እነ ቅዱስ ጳውሎስ] ሰዎችን መኖራቸውን አስታውስ። ይህ ማለት ሰው በመሆናችን የሚመጣብን ፈተና የለም ማለት ሳይሆን ሰው በመሆናችን ኃጢአትን መቃወም እና በእግዚአብሔር ኃይል ድል መንሳት እንችላለን ማለት ነው። ቅዱሳን አባቶች ማለት የዲያቢሎስ ቀስት ያልተወረወረባቸው ማለት ሳይሆኑ እምነታቸው ጋሻ የሆናቸው ማለት ናቸው።[" በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤"(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:16)
ስለዚህ እነርሱ "ገፋኸኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ።"" በማለት ሲዘምሩ። አንዳንዶቻችን ከግዴለሽነታችን እና የዲያቢሎስን ሴራ ካለማወቃችን የተነሳ"እኔ ግን ሳልጨነቅ ሳትሁ" የሚለው መዝሙር እንኳ ልባችንን አልነካንም። ወንድሜ አንዳንድ ጊዜ መንገዳገዳችን ወይንም በእግዚአብሔር ቤት ጸንተን አለመቆማችን ወደ መውደቅ እንጂ ወደ መቆም ሊመራን የማይችል እስኪመስለን ድረስ ተስፋ እንቆርጣለን። ነገር ግን አውነታው እንደዚያ አይደለም እግዚአብሔር ውድቀታችንን የመይሻ አምላክ መሆኑን በመፅሐፍ ብቻ የነገረን አይደለም 'አይተንማል'።
"እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።" ያለ አምላክ የሚተወን ይመስላችኋል? በፍጹም! አቡነ ሺኖዳ እግዚአብሔር በማንኛውም ጊዜ ከእኛ ጋር እንዳለ እና በእኛ የእምነት ማነስ እና የእውቀት ውስንነተት ምክንያት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያልወጣ ለሚመስለን በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ እንድንበረታ እና እግዚአብሔር ተስፋ እንድናደርግ እንዲህ አሉ" ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ። እነርሱ እግዚአብሔር አይሰራም በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል።" እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡" መዝ 26 ፥ 14። " እግዚአብሔር ዘወትር በስራ ላይ ነው ወይ ጉዳያችንን እየሰራ ነው ወይንም እኛን እየሰራን ነው። ይህ ቃል ሊታመንና ሁላችን ልንቀበለው የሚገባ ነው።
እግዚአብሔር አየተንገዳገድንም እየተንፏቀቅንም ቢሆን ወደእርሱ ለመድረስ የምንተጋውን ይቅርና የወደቁትን ለማንሳት ሰው የሆነ ለደካማዎች ኃይል ይሆን ዘንድ በሰው ዘንድ ደካማ መስሎ የታየ እርሱን በመተማመን ለሚጠባበቁትም የማያሳፍር ተስፍ የሚሰጥ ነው።
1.4K viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 04:58