Get Mystery Box with random crypto!

ማዕተብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bale_maeteb — ማዕተብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bale_maeteb — ማዕተብ
የሰርጥ አድራሻ: @bale_maeteb
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.19K
የሰርጥ መግለጫ

እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። |ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 8፤5-6 |
ለ 10 ሰው ሼር እናድርግ....እኛን ከጠቀመ እነርሱም ይጠቀሙ ።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 09:51:23 "ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል"

[_ ቅዱስ ቆጵሮሳዊ_]
215 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 23:23:18 https://telegra.ph/%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%89%BA-%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%90%E1%88%BD-%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%8B%9A%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%88%94%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8B%98%E1%8C%8B%E1%8B%8D-%E1%89%A0%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%88%88%E1%88%9D-08-31
50 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:30:55 +በመካከላችን ያለችው የእግዚአብሔር መንግስት+

በዚህ ምድር ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር ካልተዛመድን በሰማያት ልንዛመደው አንችልም፤ የመንግሥቱ ጣዕም ያለው በዚህ ነውና። ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ዝምድና እዚህ ምድር ላይ ይጀምራል። ይህም እንደ እግዚአብሔር እንደ ራሱ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ።" ምሳ 23፥26 በሚለው ጥያቄ ይጀምራል። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ልብን አንጽቶ በፍቅር ከሞላው በኋላ በዚያ ራሱን ያሳድራል። ወንጌል "የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና።"ሉቃ 17፥21 ብሎ እንደሚናገር ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ማረጋገጫ ይሆናል።

ስለዚህ የሰማያትን መንግሥት ከማግኝት በፊት ሰው በውስጡ ያለውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ማግኝት መቻል አለበት። ይህ ይሁን እንጂ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያገኝ የሚችለው እንዴት ነው? ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ኅብረት ሊያገኝ የሚችለውስ እንዴት ነው? ሁል ጊዜ ከእርሱ ጋር የሚሆነውስ እንዴት ነው? በዚህ ዙሪያ የምሰጣችሁ ምክር ምንጊዜም ቢሆን በእርሱ እንድትጠመዱ ሲሆን ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው ስለ እርሱ ሥራና ስለ ራሱ በማንበብ የሚከናወን ይሆናል።

ከቅዱሳኑ ጋር ስላለው ዝምድና ስለ ድንቅ ባሕርያቱና በማንኛዎቹም አጋጣሚዎች ውስጥ ስላለው ስለ እርሱ እጅ አንብቡ ። በዚህ ጊዜ ልባችሁ በእርሱ ፍቅር ይንቀሳቀሳል። በማንኛውም ጊዜ ውስጥም ከእርሱ ጋር ይገናኝ ዘንድ ዝግጁ ነው ።

+አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ+
132 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:10:52 https://telegra.ph/%E1%88%88%E1%88%98%E1%8C%B8%E1%88%88%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%8C%B8%E1%88%8E%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%8C%BD%E1%88%90%E1%8D%8D-%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%95-%E1%8B%AB%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%88%8D%E1%8C%8B%E1%88%8D-08-31
1.3K viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:33:09 Watch "መዝሙር አንድ(ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ) ዘማሪ ዘውዱ ጌታቸው" on YouTube


201 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:24:45
204 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:08:26

213 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:56:32 “ድንግል ሆይ ፦ አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል በሱ የተፈረደ መርገመ ስጋ ባንቺ ጠፍቷልና ፡ እግዚአብሄር ሔዋንን የረገማት ርግማን ባንቺ ተሽሯልና፡፡”
“ድንግል ሆይ ባማረ በተወደደ ነገር ሁሉ መሰልሁሽ ምስጋናሽን ግን ለመፈፀም አልቻልኩም፡፡እግዚአብሄርን ባመሰገንሁ ጊዜ ባንቺ ለስሙ ምስጋና አቀርባለሁ ፤ በስምሽም ፀሎቴን በፀለይሁ ጊዜ ፀሎቴን ለልጅሽ አቀረብሁ፤ዳግመኛም ውዳሴሽን ወደማወቅ ባህር ልዋኝ ወደድሁ ፡ ወደ ክብርሽ ገናንነት ወደብ እደርስ ዘንድ ደከምሁ ፡ ያንዲቷን ማእበል ሞገድ ያህል ስንኳን አላለፍሁም፡፡ ወደ ፅርሀ አርያም ጠፈር ለመድረስ የሚቻለው ማነው? ከምድር በታች ወዳለው ባህር መሰረትስ መዋኘት ማን ይችላል? ድንግል ሆይ ክብርሽን ገናንነትሽን ጠንቅቆ መናገር የሚቻለው ማነው?።”
“ድንግል ሆይ የማያከብርሽ ለልእልናሽም የማይሰግድ ለዘላለሙ ርጉም ነው፡፡ በፍፁም ልቦናው የማይወድሽ ፡ ከትልቅ ሃሳቡም የማያከብርሽ ርጉም ነው ፤ በከንፈሮቹ የማያመሰግንሽ፣ ባንደበቱም የማይመርቅሽ ርጉም ነው ፤ ለክብርሽ የማይሰግድ ለገናንነትሽም የማይገዛ እድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ገሃነመ እሳት ነው፡፡”

ድንግል ሆይ በአማላጅነትሽ አትለይን አሜን።

[_አርጋኖን | አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ_]
204 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:47:32
“ድንግል ሆይ ፦ አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል በሱ የተፈረደ መርገመ ስጋ ባንቺ ጠፍቷልና ፡ እግዚአብሄር ሔዋንን የረገማት ርግማን ባንቺ ተሽሯልና፡፡”
“እመቤቴ ማርያም ሆይ ፦ ከልጅሽ ከወዳጅሽ አንደበት የሃይማኖት አለት ተብሎ ጴጥሮስ የተጠራባት አለት አንቺ ነሽ፤ የሐዋርያት ጉባኤ የምትሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ባንቺ ተመሰተች፤ የንጉሱም ሙሽራ ባንቺ ተጌጠች፤ ባንቺም ምሶሶች ቆሙ፤ ሕንፃዋ ባንቺ ፀና፣ ግድግዳዋም ባንቺ ተሰራ፣ ጠፈሯም ባንቺ ተጠፈረ፣ ዋልታዋም ባንቺ ተዋቀረ፣ ጭምጭሟም ባንቺ ተጨመጨመ፤ ደጆቿም ባንቺ ተከፈቱ፤ መቃን መድረኳም በልጅሽ ደም ተረጨ፤ድንግልን በጠራ ጊዜ ልጇን እየጠራ ልጇን የባህርይ መሰረት ሲያደርገው ድንግልን ደግሞ የፀጋ መሰረት ሲያደርጋት ነው። ክርስቶስ የለበሰው ስጋ የነሳው ነፍስ የድንግል ማርያም እንደሆነ ይናገር ዘንድ ይህን አለ።”

“የእውነተኛ ፀሐይ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ላንቺ እገዛለሁ፤ ፍጥረት ሁሉ ላንቺ ይገዛልና፤ የልጅሽ ስም በሁሉ ከተነገረ ዘንዳ ያንቺ ስም ከዚያ ይነገራልና፡፡ የዓለም ሁሉ ክብር የነገስታትም ብዕላቸው ድንግል ሆይ ነገስታትና መኳንንት ዓለምም ሁሉ ከእግርሽ በታች ከጫማሽ ወድቀው ይገዛሉ፡፡”
199 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:06:12
219 viewsንፁህ ልብን ፍጠርልኝ , 16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ