Spirit Life Movement/leader sol/ — የቴሌግራም ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ spirit_life_leader_sol — Spirit Life Movement/leader sol/ S
የቴሌግራም ቻናል አርማ spirit_life_leader_sol — Spirit Life Movement/leader sol/
የሰርጥ አድራሻ: @spirit_life_leader_sol
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 435
ተመሳሳይ ቻናሎች ያልተመደበ
የሰርጥ መግለጫ

በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠውን እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ ተረድተን ታግዘን በምድር የእግዚአብሔርን መንግስት ህያው እናደርጋለን።
@Sol_LifeGiver

የቻናል ስታትስቲክስ
56.6% የተሳትፎ መጠን
246 እይታዎች / ልጥፍ
0 ልጥፎች / ቀን

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

26 mai 2022
'የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ (homosexuals) ነን' ብለው ስለሚያስቡ ሰዎች ምን አስባለሁ?!

በልጅነት ባደኩበት በሐዋሳ ከተማ ከምሰማቸው ነገሮች መካከል "እከሌ እከሌን አደረገው" ተብሎ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ወንዶች ልጆች መካከል ስለተደረገ ወሲብ እሰማ ነበር። የዚያኔ በልጅነት እንደ ትልቅ ጉዳይ ስለማይታሰብ እነኚያ ወንድ ልጆች ሲያድጉ ደንበኛ የሴት አፍቃሪ ሆነው እና አግብተው ፣ ልጅ ወልደው የተረጋጋ ትክክለኛ የፍቅር ህይወት ሲኖሩ አይቻለሁ። መቼም አንድ ነገር በልጅነትህ ወይም በሆነ አጋጣሚ አደረከው ማለት አንተ እንደዚያ ነህ ማለት አይደለም ፤ መለወጥ ትችላለህ። ይህ ነገር እያደግን ስንሄድ ግን ለጆሮ የሚሰቀጥጥ አስነዋሪ ነገር እንደሆነ ፤ መጽሐፍ ቅዱስም ላይ ከባድ ኃጢአት መሆኑን ሳውቅ እነኚያ ልጆች ያንን በልጅነት አእምሯቸው ቢያውቁት ኖሮ " እኔ በቃ እንዲህ (ጌይ) ነኝ" ብለው ይቀጥሉበት ነበር ብዬ አስባለሁ። እንኳንም አላወቁት። ምክንያቱም አእምሮ ከባድ ተርጓሚ ማሽን ስለሆነ ማለት ነው።

ውድ ወዳጆቼ! ይህንን አስተሳሰብ በጣም ከባድ የሚያደርገው በአጋንንት ትምህርት በደንብ እየተቃኘ (indoctrinate እየተደረገ) ስለመጣ ነው። ዛሬ ትምህርቱ ሲመታ ይህ መንፈስም እየተመታ ይሄዳል።ምናልባት በዚህ ህይወት ውስጥ አለሁ ብለው የሚያስቡ ሰዎች ዛሬ በተወሰነ መልኩ ነፃ ሊወጡበት ይችላሉ ብዬ አምናለሁ።

ውድ ወዳጄ! " ወንድ ሆኜ ከሴት ይልቅ ሌላ ወንድ ይስበኛል" ብለህ አስበህ " ስለዚህ እኔ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ (gay) ነኝ " ብለህ አታስብ። በፍፁም አይደለህም። በአንዳንድ ሁኔታዎች ይህ ገጥሞህ ወደ ፍቅር ገብተህ ይሆናል። ለምሳሌ :- መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ዳዊትም ለሳኦል መናገሩን በፈጸመ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፥ ዮናታንም እንደ ነፍሱ ወደደው።” ይላል(1ኛ ሳሙኤል 18:1)። በሌላ ስፍራ ላይ ደግሞ “ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፤ በእኔ ዘንድ ውድህ እጅግ የተለየ ነበረ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበረ።” ይላል ( — 2ኛ ሳሙኤል 1፥26)። ውድ ወዳጄ! ትርጉምህን አስተካክል ፤ ፍቅር ማለት ወሲብ ማለት አይደለም። ፍቅር የነፍስ ትስስር ነው። ዳዊትና ዮናታን የነፍስ ትስስር ነበራቸው ፤ በጣም ይዋደዳሉ ፤ እንደውም ከሴት ፍቅር ይልቅ የባሰ ነበር ፍቅራቸው ። አየህ ይህ ማለት የተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ውስጥ ነበሩ ማለት አይደለም ። ይህንን ጥቅስ በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም ዳዊትና ዮናታን gay ነበሩ የሚሉ እንዳሉ አውቃለሁ ። አንተ ግን አእምሮህን አስተካክል። ለነፃነትህ ነው የማወራው። ወደ ወንድ ስለተሳብክ gay ነህ ማለት አይደለም ፤ ወደ ሴት ስለተሳብሽ ሌዝቢያን ነሽ ማለት አይደለም። በጣም የምትወዳቸው ፣ ነፍስህ በእነርሱ የታሰረ ሰዎች በእርግጥም ሊኖሩ ይችላሉ። በዚህ ግራ አትጋባ። በህይወትህ እንደ ሞዴል የምትመለከታቸው ፣ አስተሳሰባቸው የሚማርክህ ፣ ጨዋታቸው ነፍስህን የሚገዛ ፣ መንፈሳዊ ህይወታቸው የሚስብህ ፣ ትሁት የሆኑ ፣ እንደ ዳዊት ጀግና የሆኑ ፣ የፍቅር ሰዎች የሆኑ ፣ ከራሳቸው ይልቅ ለሌሎች መልካምነት የሚኖሩ ፣ ወዘተ ሰዎች ነፍስህን ሊማርኳት እና ከነፍስህ ልትወዳቸው ትችላለህ። ያንን ወደ ሌላ አትተርጉመው።

ሁለተኛ ፤ ስትፈጠርም እንደዚህ ሆነህ ነው የተፈጠርከው (You're born gay) ብለው የነገሩህ ውሸት ነው። እንደዚህ አይነት ትምህርቶች በተለይ ሰለጠነ (ሰየጠነ) በሚባሉ አገሮች በትምህርት ስርዓታቸው ውስጥ አካተው ያስተምራሉ። ኢትዮጵያ ላይም ለማስገባት ተደጋጋሚ ጥረት እያደረጉ ነው ፤ ነገር ግን አይሆንም። ወዳጄ! በተደጋጋሚ ወደ ወንድ ስትሳብ "እኔ በዚህ መልኩ ነው የተፈጠርኩት" ብለህ ማሰብህ ሰይጣን ህይወትህን ፣ ፍፃሜህን ለማበላሸት የነገረህ ክፉ ትምህርት ነው። ውድ ወዳጄ! ፍቅር የመላመድ ጉዳይ ነው። አብረህ ከሴቶችም ጋር እያሳለፍክ በመጣህ ቁጥር እየተላመድክ ትመጣለህ። አስተሳሰብህን ቀይር ሴቶችንም ማፍቀር ትችላለህ። ውሎህን አስተካክል።

ሦስተኛ ፤ አንድ ጊዜ በተመሳሳይ ፆታ የመደፈር አደጋ ስለደረሰብህ የአንተ ህይወት ያ ነው ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ በቀለኛ በመሆን ያንን ህይወት ለመቀጠል ካሰብክ ዛሬ አቅጣጫህን ቀይር። ህይወት ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አይደለም። "የተደፈረች ሴት ሁሉ ሴተኛ አዳሪ ትሆናለች ፤ የተደፈረ ወንድ ሁሉ ወንደኛ አዳሪ ይሆናል" ያለህ ማን ነው? ወዳጄ ንቃ! አንተ ትልቅ ፍፃሜ ያለህ ሰው ነህ። ምንአልባት ስትደፈር የኤች አይ ቪ (HIV) ቫይረስ ተጠቂ አድርገውህ ሊሆን ይችላል። ወዳጄ! ማራዘሚያም ቢሆን እየተጠቀምክ የህይወት ግብህን እየፈፀምክ ቀጥል እንጂ "አንዴ ህይወቴ ስለተበላሸ የሌሎችንም ህይወት በማበላሸት እቀጥላለሁ" አትበል። ጌታ ኢየሱስ ደግሞ ከHIV በሽታም ቢሆን ይፈውስሃል።

አራተኛ ፤ በሴቶች እህቶችህ መካከል ያለ አባት በማደግህ የወንድ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አላወቅህም ማለት አንተ ሴት ነህ ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ አካሄድህ (አክትህ) እንደ ሴት ስለመሰለ ሴት ነህ ማለት አይደለም። አንዳንድ ወንዶች አይተውህ " ሴታሴት ነህ" ስላሉህ አትቀበላቸው። አንተ ወንድ ነህ ፤ እንደ ወንድም አክት ማድረግ መለማመድ ትችላለህ። ህይወት ልምምድ ስለሆነ የማይቀየር ነገር የለም። ስጋህም ፣ ነፍስህም በባህሪያቸው ለማዳ ናቸው።

አምስተኛ ፤ እናትህ ሴት ልጅ መውለድ እየፈለገች ወንድ ልጅ በመውለዷ እንደሴት ልጅ እየጠራችህ ወይም እንደሴት ልጅ እያለበሰችህ ስላደግህ ፣ የሰፈርም ሰዎች እንደሴት ስለጠሩህ አንተ ሴት ነህ ማለት አይደለም። ዛሬ አስተሳሰብህ ላይ ሰብረህ መውጣት ትችላለህ። አንተ ወንድ ነህ። ለራስህ ደጋግመህ እንዲህ ብለህ ተናገር። " እኔ ወንድ ነኝ እንጂ እነርሱ እንዳሉኝ ሴት አይደለሁም!! "

ስድስተኛ ፤ ድንገት የወንድ ለወንድ የወሲብ ፊልም አይተህ ወይም ፅሑፍ አንብበህ ከጓደኛህ ጋር በዚያ ኃጢአት ወደቅህ ሊሆን ይችላል። ይህ ማለት ግን አንተ ሁሌም እንደዚያው ነህ ማለት አይደለም። አንዴ ያመነዘረ ሁሌም አመንዝራ ሆኖ ይቀጥላል ያለው ማን ነው? ወዳጄ ነቅተህ አምልጥ። ከዚህ ጋር ተያይዞ ፌስቡክ ላይ ወይም በሌላ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተዋወቅኸው ሰው አብሮህ ለመተኛት ሲጋብዝህ እንዴት ተንደርድረህ ትሄዳለህ? እባክህ አንተ ልጅ ተረጋጋ። ለወሲብ የፈለገህ ሁሉ ይወድሃል ማለት አይደለም። ተሳስተህም ወሲብ ፈፀምክ ማለት አትወጣም ከዚህ ህይወት ማለት አይደለም።

ሰባተኛ ፡ ወንድ ጓደኛህ " ሴት ብትሆን አገባህ ነበር " ስላለህ እውነት መስሎህ እንዴት ራስህን እንደሴት ትቆጥራለህ? ሰይጣን አእምሮህን ለክፉ እያዘጋጀው ነው። ተጠንቀቅ። አንተ ሴት አይደለህም ፤ ወንድ ነህ። በተለይ ወንዶች "አማላይ (Sexy) ነህ" እያሉ ደጋግመው ይህንን የሚጠቀሙ ከሆነ ጥንቃቄ አድርግ። ዝም ብለህ አትሳቅላቸው ፤ እያሰቡት ያለ ነገር ስላለ አስተውለህ ተራመድ።

ስምንተኛ ፡ ቆንጆ ወንድ ሁሉ ጌይ ነው ያለህ ማን ነው? ቆንጆ ስለሆንክ ሴት ነህ ያለው ማን ነው? በተደጋጋሚ ቆንጆ እንደሆንክ የሚነግሩህ ወንዶች እንዴት አእምሮህን ማረኩህ? አብረን እንደር ሲሉህ እንዴት ሰማሃቸው? ወደ ወጥመድ ውስጥ እየከተቱህ እኮ ነው። በተለይ ቲክቶክ ፣ ፌስቡክ ላይ የምትሰሩ "ቆንጆ" ወንዶች ጥንቃቄ አድርጉ። የቃላቸው ሰለባ አትሁኑ።
246 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ Spirit Life Movement/leader sol/ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

Spirit Life Movement/leader sol/ 435 ተመዝጋቢዎች ያሉት የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ ግምገማዎች፣ ደረጃ እና ዝርዝር ስታቲስቲክስ ይገኛሉ።
በዚህ ገጽ ላይ "ወደ ቻናል ይሂዱ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ወይም @spirit_life_leader_sol ን በቴሌግራም መተግበሪያ ውስጥ ይፈልጉ። እንዲሁም የቻናሉን የተጠቃሚ ስም ገልብጠው በቴሌግራም መፈለጊያ ውስጥ መለጠፍ ይችላሉ።
አዎ፣ Spirit Life Movement/leader sol/ ነፃ የቴሌግራም ቻናል ነው። ሁሉንም ልጥፎች ያለምንም ክፍያ መከታተል እና ማንበብ ይችላሉ።
የSpirit Life Movement/leader sol/ ቻናል በአሁኑ ጊዜ 435 ተመዝጋቢዎች አሉት። የተመዝጋቢዎች ቁጥር በመደበኛነት ይዘመናል።
Spirit Life Movement/leader sol/ ይዘቱን በዋናነት በአማርኛ ቋንቋ ያትማል። መልእክቶቹን ለማንበብ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ ቻናሉን በቴሌግራም ይክፈቱ።
አዎ፣ ተመሳሳይ የያልተመደበ ቻናሎችን ከታች "ተመሳሳይ ቻናሎች" በሚለው ክፍል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። ተዛማጅ የቴሌግራም ቡድኖችን፣ ቦቶችን እና ተለጣፊዎችንም እናሳያለን።
መልእክቶቹ በቴሌግራም ውስጥ ይነበባሉ፦ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ Spirit Life Movement/leader sol/ ን ይክፈቱ። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ የተመዝጋቢዎች ብዛት፣ ግምገማዎች እና ስታቲስቲክስ ያገኛሉ።
Spirit Life Movement... avatar
Spirit Life Movement... @spirit_life_leader_sol
በቴሌግራም ይክፈቱ