Get Mystery Box with random crypto!

FINX Tube - ፊኒክስ ቲዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ finx_tube_21 — FINX Tube - ፊኒክስ ቲዩብ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ finx_tube_21 — FINX Tube - ፊኒክስ ቲዩብ
የሰርጥ አድራሻ: @finx_tube_21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 711
የሰርጥ መግለጫ

√ ይህ የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካውንት ነው። 1000057909769 ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ እያላችሁ የቻላችሁትን አበርክቱ። ✍️ 0904706897 ቀሲስ መሐሪ ይመር
https://www.youtube.com/@Arkeledis_21
https://bit.ly/3CtACfS
https://bit.ly/3TdqIFd
✍🏾 ለአስተያየት @AmdE_MeleK_13

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-04 17:28:35 • • •

በዓለም ዳርቻ ሁሉ የምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የእግዚአብሔር ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን እንዴት ናችሁ ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። ሁላችሁም እንደምታውቁት በዚህ ቻናል ስለ ደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ መልዕክት ስናሰራጭ እንደነበረ ይታወቃል። አሁንም ይኸው በጎ ተግባር ይቀጥላል። ለጽድቅ ሥራ ድንበር የለውም በሚለው ብሒለ አበው መሠረት የጀመርነውን የጽድቅ ሥራ እንቀጥላለን። መጽሐፍ "ለእያንዳንዱ መክሊቱን ይጠቀም!" እንዲል እናንተ በገንዘባችሁ እና ለሌሎች በማድረስ እኔም በመጻፍ መልዕክቱን በማሰራጨት የበኩላችንን እየተወጣን እንገኛለን። ነገር ግን የዚህ ቤተክርስቲያን ጉዳይ በዚሁ አያልቅም። ብዙ ነገሮች ያስፈልጉታል። እነዚህን ለማሟላት ደግሞ የእኔን እና የእናንተን እርዳታ ይፈልጋል። አሁንም ተባበሩን ለማለት ነው። እንግዲህ አጠር በማድረግ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ቀና ትብብር ያደረጉልንን እና የሚያደርጉልንን በቅደም ተከተል እናመስግናቸው።

•••
|
#ገብረ_ማርያም ይህ ቅን ወንድማችን ሹፌር ነው። ከሚያገኘው ላይ ዓሥራት በኩራቱን ለዚሁ ቤተክርስቲያን እንደሚሰጥ ቃል ገብቶልናል።
|
#ወለተ_መድኅን የበኩሏን እንደምታደርግልን ቃል ገብታልናለች።
|
#ገብረ_እግዚአብሔር ለሰማዕቱ ቤት መሥሪያ ይሁናችሁ በሚል እርዳታ አድርጎልናል።
•••

|
#ፍቅርተ_ዐማኑኤል ይች እህታችን በጣም ተባብራናለች። እየተባበረችንም ነው። በሃሳብ ሳይቀር የበኩሏን አሻራ እያስቀመጠች ነው። እህታችንን በጸሎታችሁ አስቡልን። የልቡናሽን ሃሳብ ይሙላልሽ በሉልን። ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጣት እህታችን ናት። አባቶች ካህናትም ሱባኤ ይይዙላታል። እናንተም እኔም ጸሎት እናድርግላት። ወደፊትም ተስፋ የተጣለባት እህታችን ናት።

|
#ገብረ_እግዚአብሔር ይህ ወንድሜ ደግሞ አቢሲኒያ ባንክ ለሥራ ተወዳድሯል። ይህንን ሥራ ካለፈ ለሰማዕቱ ቤት መሥሪያ የበኩሉን ያደርግልናል።

|
#የባንክ_ሠራተኞች እነዚህ ደግሞ የሥራ ባልደረቦቻችን ናቸው። ለሰማዕቱ ቤት መሥሪያ የበኩላቸውን ያደርጉ ዘንድ ቃል ገብተዋል።

እንግዲህ የሰማዕቱን ቤት ለመሥራት ብዙኃኑ ፍላጎት አለው። እናንተን ፍላጎት ያላችሁን ያብዛልን። ሌሎቻችሁንም ፎደግሞ ልቡናችሁን ያራራልን።
• • •

ዐምደ ብርሃን
288 viewsዐምደ ብርሃን, edited  14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 20:36:25

319 viewsዐምደ ብርሃን, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 14:30:02 ውድ ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦቼ ሰላማችሁ ይብዛ እንዴት ናችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። እንግዲህ እንደሚታወቀው ሰሞኑን በቡሬ ወረዳ ስለሚገኘው የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እርዳታ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን። በዚህም መሠረት እነሆ በዛሬው ዕለት 14200 (፲፬፻ወ፪፻) #ዓሥራ አራት ሺሕ ሁለት መቶ ብር) በራሱ በቤተክርስቲያኑ አካውንት ገቢ አድርገናል። ከእናንተ ከደጋግ ኢትዮጵያውያን ያገኘነውን ይህን ብር በታማኝነት ማስገባታችንን ለማረጋገጥ እነሆ በምስል (Photo) የታገዘ መረጃ ይዘን ቀርበናል። እናንተም ይህንን ሥራችንን እና እርዳታችንን በመመልከት የበኩላችሁን እርዳታ እንድታበረክቱልን በሰማዕቱ ስም እንጠይቃለን።

ዋጋችሁን ከእግዚአብሔር ዘንድ ትቀበላላችሁ። ቤተክርስቲያኑ ከመዘጋቱ በፊት። አገልግሎት ከመቋረጡ በፊት። ምዕመናን ኢ_አማንያን ከመሆናቸው በፊት የተቻለንን በማድረግ እንድረስላቸው። ለጊዜው ሶላር (Solar) ስለሚያስፈልጋቸው በተባበረ ክንድ እንግዛላቸው። 65000 ብር አካባቢ ይቀረናል። የሚፈልጉትን ለመግዛት ብር ጎድሎብናል። ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ተባብራችሁ ሙሉልን። በጎደለው እርሱ ይሙላላችሁ።
400 viewsዐምደ ብርሃን, edited  11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:48:33
ሰላማችሁ ይብዛ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ዛሬ ታላቁ ጻድቅ አባታችን አቡነ ዘርዓቡሩክ የተወለዱበት ዕለት ነው፡፡ ግሩማን የሆኑትን የብሔሞትን እና ሌዋታንን ጥርሳቸውን የቆጠሩ አባት ናቸው፡፡ማንም ጻድቅ ያላየውን አዲስ ዓለም ያዩ አባትም ናቸው፡፡ ስለ ትምባሆ ለማንም ጻድቅ ያልተነገረውን ነገር ለእርሳቸው ተገልጾላቸዋል፡፡ ፀሐይን ያስቆሙ አባትም ናቸው፡፡ የግዮንን ወንዝ በጸሎታቸው ያስባረኩ አባትም ናቸው፡፡ ቃልኪዳናቸው ተነግሮ አያልቅም፡፡ በረከታቸው ቅድስት ምድር ኢትዮጵያን ይጠብቅልን፡፡
85 viewsዐምደ ብርሃን, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:05:49
ሰላማችሁ ይብዛ ውድ የኦርዶክስ ተዋሕዶ ልጆች እንዴት ናችሁ ? እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እንዲሁም ለእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፡፡
607 viewsዐምደ ብርሃን, 08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:50:09 ከናታኒም ተስፋለም ጋ በአጋጣሚ ተገናኘን። አድራሻውን የምታውቁ በውስጥ መስመር ላኩልኝ። ልጁን ማግኘት እፈልጋለሁ። በእውነት #ናታኒም'ን አፋልጉኝ።
113 viewsዐምደ ብርሃን, edited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:48:26
563 viewsዐምደ ብርሃን, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:00:46 ሰላማችሁ ይብዛ ውድ የኦርቶዶክስ ልጆች እንዴት አደራችሁ ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ፡፡ ትላንት የተለቀቀውን ቪዲዮ እንዳያችሁት ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ ታዲያስ ምን ወሰናችሁ? ምን ለማድረግ ለራሳችሁ ቃል ገባችሁ? ዛሬ ደግሞ በሚገርም እና በሚደንቅ ሁናቴ ዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው፡፡ እንግዲህ በዕለተ ቀኑ ተዓምራቱን ለእኛ ያድርግልን፡፡ ‹‹እምኩሉ ምግባረ ጽድቅ ይኄይስ ውኂብ›› ከጽድቅ ምግባራት ሁሉ መስጠት ይበልጣል እንዲል መልክዓ ኤዶም፡፡ ስለዚህ ወገኖቼ ለህክምና ከምናወጣው ይልቅ ለሰማዕቱ ቤት መስሪያ ብናውለው የተሻለ አይሆንምን? ዘመኑ የመጨረሻ ዘመን መሆኑን ልብ ይሏል:: የጦርነት ወሬ ልንሰማ ግድ ሆኖብናል:: በመጽሐፍ የተጻፈው ሁሉ ተፈጸመ፡፡ እንግዲህ ምን ቀረ? የክርስቶስ በገሃድ መምጣት ብቻ ነው የቀረው፡፡ ሌላው ሁሉ ሆኗል፡፡ ከተመረጡት መካከል ለመሆን ለመመረጥ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ በእውነት እኔ እና እናንተ የዚህ ዘመን ትውልዶች በስራችን ለመዳን አይቻለንም፡፡ ለመዳን ቅዱሳንን የሰጠንን አምላክ እያመሰገንን እስኪ በገንዘባችን እንኳን እንጽደቅበት፡፡ ስራ የለን፡፡ ምግባር የለን፡፡ እናም የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን አሁኑኑ እናስከፍት፡፡ ከመዘጋታቸው በፊት ቀድመን እንድረስላቸው፡፡ እመኑኝ በቅርብ ቪዲዮ ይዘን እንቀርባለን፡፡ እኔ እጽፋለሁ እንጂ በዙሪያየ ብዙ ጓደኞቼ አሉ፡፡ ሃሳቡን የጀመሩትም እነርሱ ናቸው፡፡ እኔ ቻናሌን በመጠቀም ሃሳብ አስተጋባለሁ፡፡ ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ እኔ እንኳን #በመጻፍ ለመጽደቅ እሻለሁ፡፡ እናንተ የምትመጸውቱትማ ምን ያክል #ትጸድቁ ይሆን? በእውነት ብዙ ኃጢአት ባለበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ኃጢአት በዝቷል፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ ቢበዛ እንጂ ባይበዛማ እስካሁን እንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች እንጠፋ ነበር፡፡ ስለታገሰን ብቻ ማመስገን አለብን፡፡ መነኮሳት ሲደፈሩ፡ ሕጻናት ያለ ወላጅ፡ አረጋውያን ያለጧሪ ........ ምን ያልተደረገ አለ፡፡ ጊዜ የሰጠንን እናመስግነው፡፡ 120 ዘመን ተሰጥቷቸው ያልተመለሱትን እኛ በ 30 ዘመን አንችለውም፡፡ ለእነርሱ እኮ 120ው ዘመን የንሥሓ ብቻ ነበር፡፡ የእኛ ግን ዕድሜያችን ራሱ 40 መች ይሆናል፡፡ ራሳችንን በመሸወድ ራሳችንን አንጉዳ፡፡ በሉ ወደ ዋናው ርዕሰ ጉዳይ ልመለስ እና የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በአስቸኳይ ሶላር ይፈልጋል፡፡ ብትችሉ በገንዘብ እርዱን ካልሆን ቲክቶክ ላይ ከምንጃጃል መልዕክቱን ቢያንስ ሼር እናድርገው፡፡ እኛ የተውነውን በረከት የተፈቀደላቸው ይውሰዱት፡፡ ወይ አንጸድቅ ወይ ደግሞ አናጸድቅ፡፡ በቃን እንግዲህ፡፡ #1000057909769 ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይህ የቤተክርስቲያኑ የባንክ አካውንት ነው፡፡ የምትችሉትን እርዱን፡፡ ለመጠጥ ከምናወጣው ላይ ቀንሰን እንስጥ፡፡ ዓሥራት በኩራታችሁን ብቻ ስጡ፡፡ ብትችሉ ለመስጠት ልክ የለውም፡፡ እስኪ እኔንም በውስጥ መስመር እየገባችሁ ሃሳብ ስጡኝ፡፡ እኔ ደካማ ነኝ፡፡ ምን ማደርረግ እንዳለብኝ እንኳ አላውቅም፡፡ በሃሳብ ራሱ ብትረዱኝ ለውጥ ይመጣ ነበር፡፡
#1000057909769
587 viewsዐምደ ብርሃን, edited  06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:36:29

1.4K viewsዐምደ ብርሃን, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:09:25 ሰላም ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንዴት ናችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። ይቅርታ ሰሞኑን ትንሽ ጠፍቻለሁ። የሥራ መብዛት ነው። እንግዲህ ዛሬም እንደተለመደው በቡሬ ወረዳ ስለሚገኘው የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ እናወራለን። ከዚህ በፊት በተለቀቁት ቪዲዮዎች ለማስታወስ እንደተሞከረው ይህ ታላቅ ቤተክርስቲያን ሊዘጋ ነው። አገልግሎት ሊቋረጥ ነው። ካህናትም ያለ ደመወዝ እያገለገሉ ነው። ምዕመናን ያለ ወንጌል እየኖሩ ነው።
•••

√ በእውነት ይህ ከባድ ነው። ያለ ወንጌል መኖር ለክርስቲያን ከባድ ነው። ዓሣ ያለ ባሕር መኖር እንደማይቻለው ሁሉ ክርስቲያንም ያለ ወንጌል መኖር አይቻለውም። በጠዋታ በማታ ወንጌልን እየተመገብን ልባችን ያልተመለሰ ብዙዎች ባለንበት ዓለም እነዚህ የሽማጎ ምዕመናን ግን ወንጌልን የሚሰብክላቸው በሌለበት ቦታ ጸንተው እየኖሩ ነው። እባካችሁ የክርስቶስ ቤተሰብ የሆናችሁ ሁሉ ይህ ጉዳይ #የሁላችንም ጉዳይ ነው። እንኳንስ ቤተክርስቲያን ተዘግታ ቀርቶ በሮቿ ተከፍተውም መከራው በዝቶብናል። ወጀቡ አናውጾናል። የምንሰማው ሁሉ የጦርነት ወሬ በሆነበት በዚህ ዘመን ስለምን ገንዘባችንን ለጽድቅ ዓላማ ማዋል አልቻልንም? በእውነት በጥልቀት ልናስብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ዛሬም በድጋሚ ስለዚሁ ቤተክርስቲያን የማውቀውን እናገራለሁ። ችግራቸውንም አስተጋባለሁ። በረከትን የሚሻ ቢኖር ይህንን ለሌሎች በማጋራት የበኩሉን ይወጣ። ብዙም ወሬ አላበዛም። ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ለዛሬ ያዘጋጀሁትን #ቪዲዮ ይዠላችሁ ብቅ እላለሁ። በዩቲዩብ በኩል እንገናኛለን። እስከዚያ ይህችን መልዕክት ለብዙዎች እንዲደርስ የበኩላችሁን አድርጉ። ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብላችሁ ነው እንጂ ስለ ግለሰብ ብላችሁ የምታደርጉት አንዳችም ነገር የለም። ደግሞም አይኖርም።

"እኛ እያለን ቤተክርስቲያን አትዘጋም!!!"
573 viewsዐምደ ብርሃን, 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ