Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንዴት ናችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። ይቅር | FINX Tube - ፊኒክስ ቲዩብ

ሰላም ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንዴት ናችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። ይቅርታ ሰሞኑን ትንሽ ጠፍቻለሁ። የሥራ መብዛት ነው። እንግዲህ ዛሬም እንደተለመደው በቡሬ ወረዳ ስለሚገኘው የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ እናወራለን። ከዚህ በፊት በተለቀቁት ቪዲዮዎች ለማስታወስ እንደተሞከረው ይህ ታላቅ ቤተክርስቲያን ሊዘጋ ነው። አገልግሎት ሊቋረጥ ነው። ካህናትም ያለ ደመወዝ እያገለገሉ ነው። ምዕመናን ያለ ወንጌል እየኖሩ ነው።
•••

√ በእውነት ይህ ከባድ ነው። ያለ ወንጌል መኖር ለክርስቲያን ከባድ ነው። ዓሣ ያለ ባሕር መኖር እንደማይቻለው ሁሉ ክርስቲያንም ያለ ወንጌል መኖር አይቻለውም። በጠዋታ በማታ ወንጌልን እየተመገብን ልባችን ያልተመለሰ ብዙዎች ባለንበት ዓለም እነዚህ የሽማጎ ምዕመናን ግን ወንጌልን የሚሰብክላቸው በሌለበት ቦታ ጸንተው እየኖሩ ነው። እባካችሁ የክርስቶስ ቤተሰብ የሆናችሁ ሁሉ ይህ ጉዳይ #የሁላችንም ጉዳይ ነው። እንኳንስ ቤተክርስቲያን ተዘግታ ቀርቶ በሮቿ ተከፍተውም መከራው በዝቶብናል። ወጀቡ አናውጾናል። የምንሰማው ሁሉ የጦርነት ወሬ በሆነበት በዚህ ዘመን ስለምን ገንዘባችንን ለጽድቅ ዓላማ ማዋል አልቻልንም? በእውነት በጥልቀት ልናስብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ዛሬም በድጋሚ ስለዚሁ ቤተክርስቲያን የማውቀውን እናገራለሁ። ችግራቸውንም አስተጋባለሁ። በረከትን የሚሻ ቢኖር ይህንን ለሌሎች በማጋራት የበኩሉን ይወጣ። ብዙም ወሬ አላበዛም። ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ለዛሬ ያዘጋጀሁትን #ቪዲዮ ይዠላችሁ ብቅ እላለሁ። በዩቲዩብ በኩል እንገናኛለን። እስከዚያ ይህችን መልዕክት ለብዙዎች እንዲደርስ የበኩላችሁን አድርጉ። ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብላችሁ ነው እንጂ ስለ ግለሰብ ብላችሁ የምታደርጉት አንዳችም ነገር የለም። ደግሞም አይኖርም።

"እኛ እያለን ቤተክርስቲያን አትዘጋም!!!"