Get Mystery Box with random crypto!

አትሮንስ 🙏🙏🙏

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronstube — አትሮንስ 🙏🙏🙏
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronstube — አትሮንስ 🙏🙏🙏
የሰርጥ አድራሻ: @atronstube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 174
የሰርጥ መግለጫ

atronstube
#በዚህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
✿መዝሙሮች
♥ትምህርቶችን
★መንፈሳዊ ምስሎችን
@atronstube
★ለ
@Atronstube የዩትዩብ ቻናሉ
t.me/@Atronstube

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-26 10:27:19 https://t.me/Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
159 viewsedited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 09:35:12 +++ ‹ወዴት ነው የምናየው?› +++

ለጌታ ቅዱስ ሥጋ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀችውን ሽቱ በመያዝ የጨለማውን ግርማ ሳትፈራ መግደላዊት ማርያም በሌሊት ገስግሳ ወደ መቃብሩ መጥታለች፡፡ አይሁድ ያቆሟቸው ወታደሮች ጥቂት ርኅራኄ ካደረጉላት እንደ ልማዱ የጌታዋን ሥጋ ሽቱ ለመቀባት ትፈልጋለች፡፡ ነገር ግን በቦታው ደርሳ የተመለከተችው ነገር በድንጋጤ ሐሞቷን አፈሰሰው፡፡ ጎመድ የታጠቁ ብርቱዎቹ የመቃብሩ ጠባቂዎች የሉም። አይሁድ በሰንበት በመቃብሩ ያተሙትም ማኅተም ከነመዝጊያ ድንጋዩ ወዲያ ተንከባሏል፡፡ በስፍራው አንዳች መልእክት ያለው ዝምታ ነግሧል፡፡ ይህን ጊዜ መግደላዊት ማርያም ኃዘን ባደቀቀው አቅሟ እየወደቀች እየተነሣች ሐዋርያቱ ወደ ተሰበሰቡበት ቤት ሄደች፡፡ ለስምዖን ጴጥሮስ እና ለዮሐንስም ‹ጌታን ከመቃብር ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም› ስትል እንባ እየተናነቃት ነገረቻቸው፡፡

ይህን የሰሙ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ወደ ጌታ መቃብር መንገድ ጀመሩ፡፡ አብረውም ሮጡ፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ዮሐንስ በወጣትነት ጉልበት ከፊት ከፊት እየፈጠነ ቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ፡፡ አረጋዊው ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ቢሮጥም እንኳን እንደ ዮሐንስ ሊሆን አልቻለም፡፡ በእርግጥ ለክርስቶስ ከነበረው ፍቅር የተነሣ በእርጅና ጉልበቱ ቢሮጥም የሐሙስ ምሽቱ ክፉ ትውስታ (ዶሮ ሳይጮህ መካዱ) ግን ከዕድሜው ጋር ተደምሮ ጥቂት ሳያዘገየው አልቀረም፡፡ ወደ መቃብሩም ቀድሞ የደረሰው ሐዋርያው ዮሐንስ ከመጓጓት ብዛት ራሱን ዝቅ ቢያደርግ የመግነዙን ጨርቅ ተመለከተ፡፡ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ግን ‹አክብር ገጸ አረጋዊ› - ‹ሽማግሌውን አክብር› የምትለው ደገኛይቱ ሕግ ከለከለችው፡፡ ዘግይቶ የመጣው ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ መቃብሩ ቀድሞ በመግባት በመልክ በመልክ የተቀመጡትን የተልባ እግር ልብሱንና ፣ የራስ ጨርቁን አየ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ወደ ውስጥ ገብቶ ይህኑ ተመለከተ፡፡ ነገር ግን በመጽሐፍ የተጻፈውን የክርስቶስን ትንሣኤ አላመኑም ነበርና ማየታቸው ከኃዘን በቀር የጨመረላቸው ነገር የለም፡፡ ለካስ ማወቅ ብቻ ሳይሆን አለማወቅም ትካዜን ይጨምራል?!

ሐዋርያቱ ‹አይሁድ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ ለማንገላታትና ለማዋረድ ከዚህ አውጥተው ሌላ መቃብር ውስጥ አድርገዉት ይሆናል› የሚል ግምት ቢኖራቸውም፣ ነገር ግን እነርሱን ‹የት አደረጋችሁት?› ብሎ የመጠየቅ ድፍረቱ ስላልነበራቸው አንገታቸውን እንደ ሰበሩ በዝምታ ወደ መጡበት ቤት ተመለሱ፡፡ ማርያም መግደላዊት ግን ከመቃብሩ ውጭ ቆማ የፍቅር እንባን ታፈስ ነበር፡፡

በኋላም ወደ መቃብሩ ውስጥ ዝቅ ብላ ብትመለከት ሁለት ነጫጭ የለበሱ መላእክትን የክርስቶስ ሥጋ ተኝቶ በነበረበት ራስጌና ግርጌ ተቀምጠው አየች፡፡ ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ ማርቆስ ግን በወንጌላቸው ያናገራትን መልአክ ብቻ በመቁጠር መግደላዊት ማርያም አንድ መልአክ እንደታያት ይጽፋሉ፡፡ ይህችም ሴት ከደረሰባት የኃዘን ጽናት የተነሣ እንዳትሰበር የሚያረጋጉ መላእክት ተላኩላት፡፡ እነዚህም መላእክት ቀድሞ በጥል ዘመን (በኦሪት) እንደ ነበረው የምትገለባበጥ ሰይፍ ይዘው በዓይነ መአት (በቁጣ ዓይን) እያዩ ሳይሆን፣ የደስታ ምልክት የሆነውን ነጭ ልብስ ተጎናጽፈው ደስ በተሰኘ ብሩህ ገጽ ተገለጡላት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ከነፋስ የረቀቁ፣ ሥጋዊ ጉልበት የሌላቸውን መላእክት በመቃብሩ ውስጥ ‹ተቀመጡ› ሲል ይነግረናል፡፡ ይህም አንደኛ መቆም መቀመጥ በሚስማማው ሰው አምሳል መገለጣቸውን የሚያሳይ ሲሆን፤ ሁለተኛ ደግሞ መቀመጥ ዕረፍትን፣ መረጋጋትን እንደሚያሳይ የመቃብር አስፈሪነት ፣የሞትም ጣር እንደ ጠፋ ሲያመለክቱ በመቃብር ውስጥ ተቀምጠው ታዩአት፡፡

ከሁለቱ አንዱም መልአክ ‹አንቺ ሴት ለምን ታለቅሻለሽ?› ሲል ጠየቃት፡፡ ላዘነነ እና ለተጨነቀ ሰው በቀዳሚነት ሸክሙን የሚያቀሉለት በነጻነት ችግሩን እንዲናገር እድል በመስጠት ነውና መልአኩም አላዋቂ መስሎ ጥያቄውን አቀረበላት፡፡ እርሷም ‹ጌታን ከመቃብር ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም› ስትል መለሰችለት፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ማርያም መግደላዊት በእነዚያ መላእክት ፊት ላይ የተመለከተችው ነገር እጅግ ትኩረት የሚስብ ነበር፡፡ ልክ ሕፃን ልጅ ገበያ ቆይታ የመጣች እናቱን ሲመለከት በጉጉት እንደሚንሰፈሰፈውና በደስታ የሚሆነውን እንደሚያጣ ፣ መላእክቱም እንደ እናት እንደ አባት የሚመግባቸውን ፣ ዘወትር ‹ሊያዩ የሚመኙትን› የፈጣሪያቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ገጽ ባዩ ጊዜ እንደ እነዚያ ሕፃናት ሆኑ፡፡ ገጻቸውን ከእርሷ መለስ አደረጉባት፡፡ ይህን ጊዜ በአንድ አቅጣጫ የተተከለውን የእነርሱን ዓይን ተከትላ ወደ ኋላዋ ብትመለከት ‹ኢየሱስን ቆሞ አየችው›፡፡ ምንም ለጊዜው ባታውቀውም በስሟ ሲጠራት ግን ወዲያውኑ ለይታዋለች፡፡ ከዚህ ሁሉ በፊት ግን መጀመሪያ ክርስቶስን ያየችው የመላእክቱን የእይታ አቅጣጫ ተከትላ ነበር፡፡

እኛስ የእግዚአብሔር ቃል ባለ አደራ የሆንን የወንጌል መልእክተኞች ወዴት ነው የምናየው? ከፊታችን አስቀምጠን ለምናጽናናቸው ምእመናን የዓይናችን አቅጣጭ ወዴት እንዲመለከቱ ይመራቸዋል? አሁን ሕዝብ ሁሉ ጭልጥ ብሎ ወደ ፖለቲካው በመግባት ለሃይማኖቱ ግድ የለሽ ሆኗል፡፡ የእኛን የዓይን አቅጣጫ ተከትለው ይሆን?

በዘመናችን ሰውን ማክበር ፣እግዚአብሔርን መፍራት ብርቅ ሆኗል፡፡ ፍቅር ቀዝቅዞ ጥላቻ ነግሧል፡፡ ግድ የላችሁም ዓይናችን የፍቅር አምላክ የሆነው ክርስቶስን ሳይስት አልቀረም? ምክንያቱም የእኛን የእይታ አቅጣጫ ተከትለው የተመለከቱት ምዕመናን ከጥላቻ እና ይህን ከመሳሰሉት ክፋቶች በቀር ምንም አላተረፉምና? እስኪ አንዳፍታ ቆም ብለን ራሳችንን እንመርምረው? ግን ወዴት ነው የምናየው?


በዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/Atronstube
170 views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 19:16:39 “ሰውን ስለ መውደድህ ይህን ሁሉ አደረግህ፤ ከሙታን ተለይተህ ‹መቃብር ክፈቱልኝ፤ መግነዝ ፍቱልኝ› ሳትል ተነሣህ፡፡ ከእግረ መስቀል ሙታንን አስነሣህ ነፍሳትን ከሲኦል ማርከህ ለአባትህ አቀረብህ፤”
(ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ፩፥፳፬)፡፡
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ! መልካም በዓል !
https://t.me/Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
124 views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 22:34:00
ስቅለት






በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን "በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን።" ኢሳይያስ 53÷5

በአጋንንት የተያዙ ብዙ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ እርሱም መናፍስትን በቃሉ አወጣ በሽተኞችን ሁሉ ፈወሰ። <<እርሱ ደዌያችንን ተቀበለ ህማማችንም ተሸከመ>>
ማቴዎስ 8÷16-17
370 viewsedited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 08:51:50
@Atronstube
282 views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 16:13:59 @Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
150 viewsedited  13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 01:31:11
@Atronstube
@Atronstube
@Atronstube
144 viewsedited  22:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 10:59:00
@Atronstube
358 viewsedited  07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 10:58:49
@Atronstube
332 viewsedited  07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 10:57:32
@Atronstube
314 viewsedited  07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ