Get Mystery Box with random crypto!

አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronss — አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronss — አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
የሰርጥ አድራሻ: @atronss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.71K
የሰርጥ መግለጫ

መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ እንደፈለግን መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየሀገሩን ወግና ልማድ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው።
ለጥያቄዎና አስተያየትዎ @bsratbot
ለተጨማሪ ት/ት @atronss_bot
https://telegram.me/atronss

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-02 10:47:03
884 views ቀላያት, 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 10:03:35 ሐዋርያቱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ

የጌታችን ዕርገት በመርቀቅ /በርቀት/ ሳይሆን ቀስ በቀስ ሐዋርያት እያዩት  በመራቅ /በርኅቀት/ ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ይህንን ሲያስረዳ “ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው ” (ሐዋ ፩፡፱) በማለት ገልፆታል፡፡ ይህም የሚያመለክተው የሚታይ የሚዳሰስ ሥጋን ይዞት እንዳረገ ነው፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በቅዳሴው “በአካል ወደ ሰማይ ባረግህበት ዕርገትህ ላይ” እንዳለው በአካል ነው ወደ ሰማይ ያረገው። ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በቅዳሴው “በዚያች ሥጋ በመለኮት ኃይል ወደ ሰማይ ወደ ቀድሞ አኗኗሩ ዐረገ” ያለው ይህንን ለማመልከት ነው፡፡ ይህንን ሲያብራራ “ሕማም የሚስማማው ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሔደ፣ ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር፡፡ ሥጋው አልተለወጠምና” በማለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞቱና ከትንሣኤው አስቀድሞ በውኃ ላይ እንደተራመደ ሁሉ፣ በለበሰው ሥጋ ወደ ሰማይ ማረግም እንደሚቻለው አስረድቷል /ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ክፍል ፲፫ ምዕ.፥፹፯፡፲፪-፲፫/፡፡ ቅዱስ ሉቃስም “እያዩት ከፍ ከፍ አለ” ማለቱ በእርግጥ ዕርገቱ በአካል እንደነበር ያስረግጥልናል፤ ምክንያቱም ሰው መለኮትን መመልከት አይችልምና ።
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ስለ ጌታችን ዕርገት  “በደብረ ዘይት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲመገብ እጁን በደቀ መዛሙርቱ ላይ አኖረ፤ እያንዳንዳቸውንም ባረካቸው ከዚያም የእሳት ደመና ተቀበለው፤ ከእነርሱም ሰወረው፤ በጨርቅ የጠቀለሉት ይህ ሥጋ በኪሩቤል ክንፎች ተጋረደ፤ በጒልበት ያቀፉት ይህ ሥጋ በእሳት ሠረገላ ተቀመጠ፤ በዚህ ዓለም የተራበና የተጠማ ይህ ሥጋ እህል መብላት፤ ወይን መጠጥን ውሃም መጠጣት ወደ ማይሻበት ወደ አርያም ከፍታ ወጣ፤ በሊቀ ካህናቱ አገልጋዮችና በጲላጦስ አደባባይ ራቁቱን የቆመ ይህ ሥጋ በምስጋና መብረቅ ተሸፈነ፤ በእሳት ደመናም ተጋረደ፤ ጉንጮቹን በጥፊ የተመታ ይህ ሥጋ ከፍ ከፍ አለ” ብሏል፡፡
ቅዱስ ማርቆስ የጌታችንን ዕርገት በገለጸበት አንቀጽ “ጌታችን ኢየሱስም ከተነጋገራቸዉ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፥ በአባቱም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡” (ማር. ፲፮፡፲፱) ብሏል፡፡ “ወደ ሰማይ” የሚለው ቃል ወደ ሰማየ ሰማያት ማለት ነው ። ይህም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሚሠራበት ወቅት በጸለየው ጸሎት ውስጥ እግዚአብሔርን “በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!” (፩ኛ ነገ. ፰፡፪፯) ብሎ በጸለየው ይታወቃል። “ዐረገ” የሚለውም ( መላእክት አሳረጉት አላለም) በራሱ ኃይል ሥልጣንና ማረጉን ያሳያል፡፡ ከጌታችን በቀር በራሱ ኃይል ያረገ የለም። ሌሎች ቅዱሳን፡ ለምሳሌ ኤልያስ እና ሄኖክም ቢሆኑ እግዚአብሔር ዐሳረጋቸው እንጂ በራሳቸው ስልጣን ዐላረጉም ።
ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይህንን “የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለ መሰላል በሚንቦገቦግ የደመና ተን (ጉም) ዐረገ፤ መለኮቱ ይተጋለታልና ወደ አየራትም ነጥቆታልና፤ ነገደ መናብርት ሊያሳርጉት አልመጡም ርሱ ራሱ በመለኮቱ ኀይል አብን ተካክሎ በቀኝ በኩል ተቀመጠባቸው” ሲል ገልጾታል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም ስለ ዕርገት በተናገረበት አንቀጽ “በራሱ ሥልጣን ተነሣ፤ ርሱን ያስነሣው ማንም አይደለም፤ በሚያርግም ጊዜ ማንም ርሱን ያሳረገ አይደለም፤ ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካይነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚኽም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት (፪ኛ ነገ ፪፥፲፩)፤ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈው ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኰራኲር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኰራኲር አያስፈልገውም” በማለት የእርሱ ዕርገት በራሱ ስልጣን መሆኑን አብራርቶታል፡፡
1.5K views ቀላያት, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 10:03:03
920 views ቀላያት, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:39:10 ++የጣሏቸውን ሰዎች የእሳቱወላፈን ገደላቸው +
1.2K viewsእናት(ነብሴ የወደደችዉን አገኘዉ እርሱም ክርስቶስ ነዉ), edited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 09:57:09
የ ጌታችን የመዳኒታችን የ እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት ሙሉ ፊልም

package ከገዙ ወደ 48.61 ብር
package ከሌለዎት ወደ 81 ብር ይፈጃል
WiFi ብትጠቀሙ ይመረጣል




#ለሁሉም_ሼር_ይደረግ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@atronss zethewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
1.8K views ቀላያት, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 22:29:46 #የሕማማት #ረቡዕ

#ሊቃውንተ_ቤተክርስትያን

#ምክረ #አይሁድ


የማቴዎስ ወንጌል 26:3-4

[3] #በዚያን ጊዜ #የካህናት #አለቆች #የሕዝብም #ሽማግሎች #ቀያፋ #በሚባለው #በሊቀ #ካህናቱ ግቢ #ተሰበሰቡ፥

[4] #ኢየሱስንም #በተንኰል #ሊያስይዙት #ሊገድሉትም #ተማከሩ፤
1.6K viewsእናት(ነብሴ የወደደችዉን አገኘዉ እርሱም ክርስቶስ ነዉ), 19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 17:29:55
+++"ስለ እኛ የታመመውን ምን አንደበት ይናገረዋል?!"+++

እጅግ ጥልቅ የጸሎት ሕይወት የነበረው፣ አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ የሚጾመው ተሐራሚው ቅዱስ አባ ጳጉሚስ ከእለታት በአንዱ ቀን ይህን ተመለከተ፡፡ ቅዱሱ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር አብዝቶ ይሰግድ ነበር፡፡ ከዓይኑ የሚወርደው እንባ ከሰውነቱ ወዝ ጋር እየተቀላቀለ ወደ መሬት በመውረዱ ምክንያት የሚሰግድበትን ቦታ አረጠበው፡፡ አባ ጳኩሚስም ይህን ወደ ጌታው እያመለከተ "ይኸው አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ" ሲል ተናገረ፡፡ በዚህ ጊዜም መድኃኒታችን ለአባ ጳጉሚስ ተገልጦ "እኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሆኜ ተሰቅያለሁ" በማለት በእለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ የተወጋ ጎኑን፣ የፈሰሰ ደሙን አሳየው፡፡ ቅዱሱም የጌታው ሕማም ከሕሊናው በላይ ሆኖበት ወድቆ ምሕረትን ለምኗል፡፡

+++++++++++++

ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን :- ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ›› ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ‹‹መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን?›› ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ‹‹አዎ! አይ ዘንድ እወዳለሁ›› አሉት። ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር። እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል።

‹‹ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ›› - ‹‹ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው!››
1.7K viewsእናት(ነብሴ የወደደችዉን አገኘዉ እርሱም ክርስቶስ ነዉ), edited  14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 14:11:35 "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/

"" ቅዱስ ኒቆዲሞስ ""
(ዮሐ. ፫:፩)


በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

https://telegram.me/atronss

#ለመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን

የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ እንዲደርስ ለወዳጆ share በማድረግለሁሉ እና ድርስ
1.5K viewsኩሉ ሀብት ሠናይ ወኩሉ ፍት ኩሉ እምላዕሉ ያዕ1÷17, edited  11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ