Get Mystery Box with random crypto!

አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronss — አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronss — አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
የሰርጥ አድራሻ: @atronss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.71K
የሰርጥ መግለጫ

መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ እንደፈለግን መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየሀገሩን ወግና ልማድ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው።
ለጥያቄዎና አስተያየትዎ @bsratbot
ለተጨማሪ ት/ት @atronss_bot
https://telegram.me/atronss

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 23:18:48 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






3 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:14:33 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






29 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:11:18 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






62 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:29:42 አቡነ ጴጥሮስ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ እስከተገደሉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሂደት 'ኮርየር ዴላሴራ' (corriere della sera) የተባለው ጋዜጣ ወኪል እና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው 'ፖጃሌ' የተባለ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓም አዲስ አበባ በነበረ ጊዜ ሂደቱን ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽሑፍ አቅርቦ ነበር:-

"ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም ፊታቸውም ዘለግ ያለና መልካቸው ጠየም ያለ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሠየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንት ናቸው፡፡ የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል 'ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም አንዲያምፁ አድርገዋል' የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣሊያንን መንግሥት ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ አርስዎ ለምን ዐመፁ፣ ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?' ሲል ጠየቃቸው ፡፡
አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መልስ መለሱ...

“አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፣ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ አኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ሐላፊነትም ያለብኝ የቤተ ከርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ከርስቲያኔ አቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣረዬ ብቻ የምናገረውን አናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ” አሉ፡፡
ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእከት አስተላለፉ፡፡

''አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፡ እንጂ በጎ ለመሥራት፣ እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ።ነጸነታችሁን ከሚረክስ ሙታቹህ ስማችሁ ሲቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪየ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን።''
ጋዜጠኛው ይቀጥላል

“እኒህ ጳጳስ ሐቀኛ ነበሩ። ነገር ግን ለኢጣሊያ ለጋስዮን ታዝዞ የመጣው አስተርጓሚ ዳኞች የሚሉትን ብቻ ከማስተርጎም በቀር ጳጳሱ የሚናገሩትን ሃቀኛ ንግግር አላስተረጎመም፡፡ እኔ እንኳን የሰማሁት በአዲስ አበበ ለሠላሳ ዓመት የኖረው የእቴጌ ሆቴል ኃላፊ የነበረው የግሪክ ዜጋ ማንድራኮስ አጠገቢ ተቀምጦ ስለ ነበር የተናገሩትን ሁሉ ስለ ገለጠልኝ ነው፡፡ እኔ እንደ ሰማሁት ፍርዱን ለመስማት በብዛት የተስበስቡት ጣሊያኖችና ታዝዞ የወጣው የአዲስ አበበ ሕዝብ ሐቀኛ የሆነውን ንግግራቸውን ቢሰማ ኖሮ ልባቸው ይነካ ነበር"። ሞት የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉና ደክሟቸው ስለነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲቀመጡም ፈቀደላቸው፣በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው።ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር።”
ምንጭ፡ ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን
2.4K viewsኩሉ ሀብት ሠናይ ወኩሉ ፍት ኩሉ እምላዕሉ ያዕ1÷17, 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:29:06 ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ በ1875ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ።ብፁዕነታቸው ጴጥሮስ የሚለውን ስመ ጵጵስና ከማግኘታቸው በፊት መምህር ኃይለማርያም ይባሉ ነበር።ወላጆቻቸውም በትምህርት እንዲያድጉ ልዩ ፍላጎት ስለነበራቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ወስደው ባህታዊ ተድላ ለተባሉ አባት ሰጧቸው።ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በዚያው አጠናቀቁ።የቅኔ ትምህርታቸውን ለማስፋፋት ወደ ዋሸራ ተሻገሩ፣በዚያም በመምህርነት ተመረቁ።የዜማውንም ትምህርት በሚገባ ለመማር ወደ ጎንደር ተጓዙ። እሱንም እንዳጠናቀቁ ወደ ወሎ ቦሩ ሜዳ በመሄድ ደግሞ ከመምህር አካለወልድ የመጽሐፍት ትርጓሜ ትምህርቶች ብሉያትን፣ ሐዲሳትን እና ሊቃውንትን በብቃት አጠናቀቁ።

በ1900 ዓ.ም በምስካበ ቅዱሳን በመሄድ ወንበር ዘረጉ።በዚያም ለዘጠኝ ዓመታት ያህል ቅኔና መጥሐፍትን አስተማሩ።በ1909ዓ.ም ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም በመሔድ ምንኩስናን ተቀበሉ።ሥርዓተ ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ በምሁር ኢየሱስ ገዳም፣በዝዋይ ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም በመምህርነት አገልግለዋል። በ1919 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አበ ንስሐ ሆኑ።

ከአንድ ሺሕ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የራሷን ጳጳሳት ለመሾም ስትነሳ ከተመረጡት አምስት አባቶች መካከል አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ።በዚህም መሠረት ከሌሎች አባቶች ጋር ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መዓርገ ጵጵስና ተቀበሉ።ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ” ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ ሀገረ ስብከት ተሾሙ።

1928 ፋሽስት ወደኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ በመጀመሪያ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር አርበኞቹ ለማበረታታት ተጓዙ። ከዚያም ከተመለሱ በኋላ ወደ ወደ ደብረሊባኖስ በመሄድ የመጣውን ችግር ያሥታግስ ዘንድ እየጸለዩ ለሀገርና ለነጻነት መሞትም ቅዱስ ተግባር መሆኑን በመስበክ ያተጓቸው ነበር።ይሁን እንጂ በሦስት በኩል እየተመራ የመጣው ጦር እል ባለማጥቃቱ ወደየመጣበት ሲመለስ ብፁዕነታቸው ግን “ብችል ጠላት በኢትዮጵያውን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በቅርብ ርቀት የሚመለከተውን ሕዝብ በማትጋት በጠላት ላይ እንዲነሳ አደርገዋለሁ ካልሆነ እዚሁ እሞታለሁ” ብለው ከአርበኞች ተነጥለው በአዲስ አበባ ቀሩ። ጠላት በከተማዋ ባሰማራቸው ባንዳዎች ምክንያት እንደልባቸው መንቀሳቀስም አልቻሉም ነበርና እዚሁ ከተማ ተሰውሬ መኖር አልፈልግም ብለው ሐምሌ 22ቀን 1928 ዓ.ም በወቅቱ የኢጣሊያ እንደራሴ ለነበሩት ለራስ ኃይሉ እጃቸውን ሰጡ።ራስ ኃይሉም ወዲያው ለግራዚያኒ አሳልፈው ሰጧቸው።

ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ "አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ" ሲል ሙሴ ፓይላክን ጠይቆአቸው እርስቸውም የሚክተለውን ተናግረዋል።
"አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝ ቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ክተቱት። ወዲያው ወታደሮች በሩምታ ተኩስው ገደሉ ዋቸው። ይህ እንደሆነ አስገድዶ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።

ማታ ከአስገዳዩ ኮለኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት 'በዚህ ቄስ መገደል አኮ ሕዝቡ ተደሰቷል' እለኝ እንዴት?' ብለው 'አላየህም ሲያጨበጭብ' አለኝ። እኔም 'ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጤበጭባል' አልኩት። 'እንዴት?' ቢለኝ እጄን እያጨበጨብኩ አሳየሁት። እሱም አሳየኝ። ከዚህ በኋላ " የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቼአለሁ" ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የኪስ ስዓታቸውን ጭምር አሳየኝ። መጽሐፍ ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተስንጥቋል።”ብለው ያዩትን መስክረዋል።

ጠላት ድል ተደርጎ ሀገራችን ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የብፁዕነታቸውን አኩሪ ተግባር ትውልድ ሲያዘክርላቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ16 ቀን 1938 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሐውልት ቆሞላቸዋል።
የሐቀኛው አባታችን በረከት ይደርብን!
ምንጭ:- ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን፣
1.3K viewsኩሉ ሀብት ሠናይ ወኩሉ ፍት ኩሉ እምላዕሉ ያዕ1÷17, 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:27:56
864 viewsኩሉ ሀብት ሠናይ ወኩሉ ፍት ኩሉ እምላዕሉ ያዕ1÷17, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:27:38
940 viewsኩሉ ሀብት ሠናይ ወኩሉ ፍት ኩሉ እምላዕሉ ያዕ1÷17, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:27:38
ሐምሌ 22 በዚህች ዕለት ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን በአደራነት የሰጠቻቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ሕዝበ ክርስቲያኑን በጸሎታቸው እየደገፉ በትምህርታቸው እያበረቱ በማስተዳደር ላይ እንዳሉ በ1928 ዓ.ም በአረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ የተገደሉበትና ሰማዕትነት የተቀበሉበት ዕለት ነው።
957 viewsኩሉ ሀብት ሠናይ ወኩሉ ፍት ኩሉ እምላዕሉ ያዕ1÷17, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:35:34 የአባ ዘወንጌል የትንቢት እውነታዎች
የኖኅ መርከብ መድረሻ
የትንቢቱ ፍፃሜዎች
የ666 ደባ በኢትዮጵያ ላይ
,መጽመፈ ሔኖክ
የዕፀ መሰወር ጥናታዊ ፁፍ
ታቦተ ፅዮን
ነጋዴው ታምሪን

open.........open .........open
Open........"open .........open
Open.........open...........open
Open........open............open

እርሶም በዚህ ዙሪያ እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
"ትምህርቱን በናታኒም ቲዩብ ይከታተሉ"።


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘

የተወደዳችሁ የተዋሕዶ ልጆች ዛሬ የማስተዋውቃችሁ ናታኒም ቲዩብን ነው! በናታኑም ቲዩብ የተለያዩ የአውደ ምሕረት ትምህርቶችን፣ስብከቶችን እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬዎችን የምታገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ስለሆነም ሰብስክራይብ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታችሁን የበለጠ እንድታጎለብቱ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እጠይቃችኋለሁ ።
ናታኒም ቲዩብ ሼር ሰብስክራይብ አድረጋችሁ ቻናላችናን ተቀላቀሉ "
ሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌

█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░►OPEN ▒▓█
59 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:25:26 + ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ አለ +

“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"
መጽሐፈ ምሥጢር 24:20

"ከእኛ ወገን ክርስቲያን እየተባሉ በገዛ መንገዳቸው የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ... የእንስሳ ሥጋ ከመብላት የሚከለከሉ የሰውን ሥጋ ለመብላት ግን የሚተጉ እነዚህ ናቸው"

"ስምዖን ጴጥሮስ ከሐዋርያት ሁሉ አብልጦ ክርስቶስን ወደደው:: ክርስቶስ ግን ከሐዋርያት ሁሉ አልቆ ወንጌላዊው ዮሐንስን ይወድደው ነበር::
ስለወደደው ግን አለቃ መሆንን ለዮሐንስ አልሠጠም:: እርሱ ከወደደው በላይ እርሱን የሚወደውን አለቃ አደረገው እንጂ"

"ክርስቶስን መውደድ ከወንድሞቹ ይልቅ በጴጥሮስ ላይ በዛ:: ከወንድሞቹ ይልቅ ወደ ጌታ ኢየሱስ ለመድረስ ቸኩሏልና ከመርከቢቱ ዘልሎ ወደ ባሕር ተወረወረ እንጂ በመርከብ ለመጎተት አልቆየም::
ወደ ወደደው ለመድረስ ቀደማቸው:: ከመርከቢቱ ላይ ያዘለለችው ወደ ጥልቁም ባሕር የወረወረችው ፍቅር እርስዋ የክህደቱን መጽሐፍ ደመሰሰችለት::
ራሱን ወደ ጥልቁ የጥብርያዶስ ባሕር በወረወረ ጊዜ የዕዳው መጽሐፍ ሰጠመ:: እርሱ ግን በብዙ ጭንቅ በብዙም ፍለጋ በዋናተኞችም በብልጠታቸው ጥበብ እንደሚገኝ እንደሚያበራ ዕንቁ ሆኖ ከባሕር ውስጥ ወጣ"

#ከመጽሐፈ ምሥጢር ውብ ገጾች


"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
436 viewsኩሉ ሀብት ሠናይ ወኩሉ ፍት ኩሉ እምላዕሉ ያዕ1÷17, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ