Get Mystery Box with random crypto!

ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

የቴሌግራም ቻናል አርማ wisdom3in1 — ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪
የቴሌግራም ቻናል አርማ wisdom3in1 — ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪
የሰርጥ አድራሻ: @wisdom3in1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 580
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ሌላ ስለምንም አናወራም...ግን " በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" ስለተባለለት ስለ እርሱ.......እናውጃለን!!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-01 10:19:13
ምሳሌዎች ሁሉ እዉነትን ቢገልጡም፥ እዉነት ሁሉ ግን በምሳሌ አይገደብም፥ ስለሆነም እዉነቱ እና ምሳሌዉ ሳይጋጭ ለመከተል ሞክሩ፥ በነገራችን ላይ የክርስቶስ ህይወት ከቀን ወደ ቀን እየገባን ሲመጣ፥ ዋጋዉም በዚያኑ ልክ እየጨመረ ይሄዳል፤ አስበነዉ ይሆን?፥ ቅድም ወይም አሁን በተረፍነዉ ልክ እግዚአብሔር ነዉ ማለት ግን አይደለም፥ ትላንት እስከምን ያክል እንዳወቅነዉ ያለን ስዕል፥ ዛሬ ከአይምሮ በላይ በሆነ ጭማሬ ያሻቅባል፥ ግን አሁንም ያ ብቻ አይደለም፤ እንኪያስ ይሄ የሚሆነዉ የተለወጠ መዳን ኖሮ ነዉን? በፍፁም! ያ ሊሆን አይችልም ነገር ግን የተለወጠ ማንነት እኛ ዉስጥ ስለሚፈጥር ነዉ።

ተስፋን የሰጠ ዳግም የሚመጣዉ፥ አማንያን ከሩቅ የተሳለሙት፥ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉ፤ ነገር ግን እኛም ከእንግዲህ በሩቅ እንዳንገኝ፥ የሚያፀናዉን፦ ስለተስፋዉ የሚናገረዉን ከመንፈስ ቅዱስ እንሰማ ዘንድ በቀረዉስ ህብረትን አደረግን፥ ስለዚህ በአብ የተተመነዉ ዋጋ፥ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉና፥ ያ አብ ያወጣዉ ተመን ላይ እስክንደርስ ድረስ፥ ስለክርስቶስ የሚመሰክር ቅዱስ መንፈስ፥ በእኛ ዉስጥ ይኖራል፤ ከላይ ባየነዉ ክፍል ዉስጥ "...እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ" የሚል ቃል እናገኛለን፥ ለምን?፥ እነዚህ ሶስቱ ፀንተዉ ይኖራሉ ተብሎ ከተፃፉት መካከል አንዱ "ተስፋ" ነዉ!፤ በመሆኑም እኛም መልሰን በምስክርነታችን እንፀናለን!
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
192 viewsedited  07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 11:37:48 የእግዚአብሔር ስም የፀና ግንብ ነዉ



ሊያደምጡት የሚገባ የጊዜዉ መልዕክት
345 views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 09:33:38
“ለመልካም አሰበው።”
— ዘፍጥረት 50፥20

ከሚያቃጥል እሳት ዉሰጥ፥ የማይቃጠለዉ ማንነት የሚሰራዉ፥ ከእሳቱ በፊት ባገኘን የእግዚአብሔር እሳት እስከሆነ ድረስ፥ ሰባት እቶን እሳት የሚያመጣዉ ሞትን ሳይሆን ኢየሱስን ነዉ!፤ በአባቱ ቤት ዉዱን ሸማ ከለበሰዉ ዮሴፍ፥ ለገዢዎች እንደ በግ እየተስማማ ያለዉን ዮሴፍ፥ ረሃብ በፊቱ ጉልበት ያጣ እንደነበር ማን ለወንድሞቹ ቀድሞ በነገራቸዉ አትሉም፤ እንግዲያዉስ በጥጋቡም በረሃቡም ዘመን መፍትሄዉ ዬሴፍ ጋር ያለዉ እግዚአብሔር ነበር!

የተጣለ፥ ደብዛዉ የጠፋ፥ የእየዬ መነሻ የሆነዉን ዮሴፍ እግዚአብሔር ለመልካም ያጨበት ጊዜ ነበር፥ እንዴት እያዘጋጃችሁ እንደሆነ ባይገባችሁም እንኳን፥ በእናንተ ላይ የተጠራዉን የዋጋ ድርድር፥ ለመልካም የሚያስብ አባት እንዳላችሁ በዚህ አጋጣሚ ጠቁሜአችሁ ልለፍ፥ መልካምነት ከእግዚአብሔር አንፃር እንጂ በምታዩት ልክ ግን አይደለም።

#እንወዶታለን!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
444 views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:33:09
ክፍል 2

ይህንን ብዬ ላብቃ፥ ወዳጆቼ፦ እግዚአብሔር አብረሃምን ወደ ክርስቶስ ጠርቶ፥ የመዳንን ምልክት የሆነዉን መነሻ በሞርያን አገኘ፤ እንግዲያዉስ አብረሃም "እነሆኝ!" ያለዉ ለዚህ ድነት ምስክር እንዲሆን ነዉ!፤ አንድ ነገር እርግጠኞች ሁኑ፥ እግዚአብሔር የሕይወት መገኛ ወደሆነዉ፥ ወደራሱ እንዲህ ባለ ድንቅ አጠራር ጠርቷችኋል፤ ስለዚህ አብረሃም ሆይ! ወደ እኔ ና እያለዉ ነበር፥ ምክንያቱም እርሱ የዘላለም ሕይወት ነዉና!
#እንወዶታለን!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ
375 views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:30:52
ክፍል 1

እግዚአብሔርን በአቅሙ ልክ ካየነዉ፥ ያልተፈጠሩ ግዙፍ ሰማያትንና ምድርን በማየት፥ ልንለካዉ የምንሮጥበትን መንገድ፥ "ከንቱ!" ብለን ከዘጋን፥ እንግዳዉስ በክርስቶስ ስጋ በኩል፥ መርቆ በከፈተልን መንገድ፥ እንደ አብረሃም ወደ ሞርያን ምድር ይወስደናል፤ እንዴትና ለምን?

እንግዲህ አብረሃም በሕይወት አለና "እነሆኝ!" ሊል ቻለ፥ ታዲያ ሰዋ ከሚለዉ ቃል በላይ የቀደመችዉን የሞርያ ምድር አብረሃም እንዲያስባት ተፈለገ፥ እንኪያስ እግዚአብሔር ከወደዳቸዉ ከሺ ተራራዎች በአንዲቷ ላይ ለአብረሃም ቀጠሮ ተያዘለት፥ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

"ሞርያን" ማለት የፍጥረት መጀመሪያ፥ (የመሰረት ዲንጋይ)፥ ወይም የተራራዉ ቤተመቅደስ የሚል ፍቺ ይይዛል፤ እናም እግዚአብሔር አብረሃምን ሂድ እያለዉ ያለዉ፥ ሕይወት ወደሚገኝበት ምድር ነዉ ማለት ነዉ፤ ወዳጆቼ! ይስሃቅን በመስጠት ዉስጥ የመስዋቶቹን ቁሳቁስ በእጃችሁ ቢገኙም እንኳን፥ እግዚአብሔር እያወራዉ ያለዉ በፍጥረት ጅማሬ መንፈስ ነዉ፤ ሰዉ እግዚአብሔር ካሳየዉ ተራራዎች ይልቅ፥ በራሱ የሃሳብ ከፍታ ላይ ተራራዉን ገንብቶ፥ ለማመን ይከብደዋል፤ ይሄ ደግሞ፥ ሰዉ በእንቆቅልሽ እየወጣ፥ በደስታ የሚወርድበትን ፈንጠዝያ ይፈጥርበታል እንደማለት ነዉ፥
ስለዚህ የፍጥረት መነሻ ወደሆነዉ ቦታ ሲያመጣን ክርስቶስን እያስተዋወቀን ነበር ማለት ነዉ!

     @wisdom3in1
176 viewsedited  13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 10:29:11
“ኢየሱስንም፦ ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።”
— ሉቃስ 23፥42

እጅግ ልብ ከሚነኩ ሕያዉ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መካከል ይሄ አንዱ ነዉ፥ ክርስቶስ ያለጠበቃና ያለምህረት፥ በምድር ፊት በእኛ ሁላችን መካከል ኋጥያትን ተጋፈጠ፤ በእርግጥ አመፅ መግደል ይችላል!፥ ሞትም ቢሆን ተሸንፎ አያዉቅም ነበርና ያቅራራል!፥ ብዙ ስሞች በክርስቶስ መስቀል ምክንያት፥ ሲጠብቁት ለነበረዉ አጋጣሚ፥ ነጥረዉ ለመዉጣት በአሸዋ ላይ ተተክለዉ ነበር፤ ወንበዴዉ ግን ዘወር ብሎ፦ ከነበሩት በሚጠይቀዉ ጥያቄ ንግግሩ ያስታዉቅ እንጂ፥ እንደዉም አስቀድሞ ቁርጡን ያወቀ ሰዉ ነበር፤ እዉነቴን ነዉ የምላችሁ!፥ በመቋጫዎች ላይ ሕይወትን ሊቀጥል የሚችለዉን ጌታ፥ መስቀል ላይ ይፈልግ ጀመር፤ በእርግጥ ይሄ ሰዉ እኮ ከነብያት መካከል አንዱም አይደለም!፥ ነገር ግን የሰዉ ምህረት የዘለለዉ ወንበዴ ነበር!

ወዳጆቼ የትኛዉም ነገር ከክርስቶስ ጋር ተካፋይ ላለማድረግ የነበረዉ አቅም ወደ እግዚአብሔር መንግስት በመግባታችን ተጠናቋል፥ ቀላል ሊመስላችሁ ይችላል!፥ ግን ደግሞ በስራዉ ረክሶ በቃሉ የጸደቀዉ ይህ ሰዉ፥ መምህሩን፦ "አስበኝ!" አለዉ፤ የነበረዉን ጊዜ ተጠቀመ!

የመጨረሻ ብዬ ልጨርስ፦ ክርስቶስ ኢየሱስን በተለየ መረዳት፥ ግን ተራ በሆነ የሰዉ ታሪክ ዉስጥ ማወቅ፥ ጩኋት ብቻ ከሆኑ ድምጾች በላይ ፍፃሜን ይወስናል!
አሜን!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
333 views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:20:36 ሰማያዊ ጥበብ pinned a photo
06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:33:15
“የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ።”
— 2ኛ ጴጥሮስ 3፥15


የሁሉ ፍፃሜ በክርስቶስ ይሆን ዘንድ፥ የተስፋዉን ቃል በእኛ አሳድሮ፥ በመጨረሻም ፀፀት የሌለበትን ዉሳኔ በእኛ የድነት ቁጥር ዉስጥ እንድናረጋግጥ አስቀድሞ ተወስናል፤ ሆኖም ለፍርድ በሚያበቃ አመፅ እና በማስረጃዉ ገፅ መካከል ትዕግስቱን በፍፁምነቱ በኩል እንዲያልፍ በዚህ አብ እጅግ ተደሰተ፤ ለወትሮ ታጋሽነት የሆነዉን መቀበል ነበር፥ ማለትም ለበደል የሚሆን ፍሬን በማፍራት ከሕይወት ዛፍ መካከል የተፈቀደዉ መመለስ ሆኖ ሳለ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ግን ትዕግስቱን ወደ መዳን ድረስ በሩን ከፈተዉ፥ ጌታ እየታገሰ ያለዉ ጥፋተኛ ለማድረግ ሳይሆን እንድን ዘንድ ነዉ፥ ትዕግስት በባህሪዉ ነገሩ ከሆነ በኋላ ያበቃል፥ ወይም በይቅርታ ሲዘጋ ይቀራል፥ እሱን እኛም እናዉቀዋለን ግን የክርስቶስ ከዚህ ይለያል፥ የክርስቶስ መከራ የእኛ ድነት ሆነ፥ ለካስ ሲታገሰኝ ቀን እየጠበቀልኝ ሳይሆን መዳንን እያየልኝ ነበር!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
266 viewsedited  08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 11:05:12
“ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤”
— ማቴዎስ 6፥13

እነሆ ደስ ከማይል የሰዉኛ ምኞት ፍፃሜ ተስቦ፥ ከአባቱ ቤት ደስታ ዘንበል ከሚል ፍጥረት፥ ምህረትን በእሱ ዘንድ እንደ ደሞዝ ቆጥሮ ይወጣል።

የምንፈልገዉ ስጋን ከሆነ፥ በአባታችን ቤት የሚያኖረን መንፈስ በራሳችን አይምሮ የተነሳ እናጣለን ማለት ነዉ፤ ይሄ ደግሞ የሚያመለክተዉ፥ የተጠጋነዉ ፍሰቱን የማያቆም ወንዝ እንደሆነ ማዘናጊያ ነዉ።

እርያዎቹ ስለምግባቸዉ ሲያስቡ፥ ከእነሱ ጋር መብላት የፈለገ እንዳለ ግን አያዉቁም ነበር፥ አገልጋዩ ልጅ ከአባቱ መድረክ ሲወርድ፥ የሳተዉ ቦታ የምኞቱን ግብ እንጂ፥ ባባቱ ቤት የነበረዉን ክብር እንደማይደርስበት ሳይቆጥር፥ ያልነገሰባት ቅናት ከአባቱ ቤት ይበልጥ ስለ ራሱ ኑሮ በላችዉ።

ፈተናዎቻችን ከመሰራታችን ምክንያት ጋር አያይዘን፥ የአባታችንን ቤት የማያስመኙንና የማያስናፍቁን ከሆነ፥ እዉነት እዉነት እላችኋለሁ፥ ለፈተና ፈተና የሆነዉ እኛ ነን።

የሚነደዉን ጧፍ በክብር ለሚጠብቃት እግዚአብሔር፥ ያጨልማት ዘንድ እርሱን ጨለማ አይመለከተዉም፥ የተቀጠቀጠዉን ሸንበቆ ያሰብር ዘንድ፥ በፍቅሩ እርሱ አይደራደርም፤ ነገር ግን "ከክፉ አድነን እንጂ" እንድንል፥ አዳኝነቱን በመስቀል አስመሰከረ፥ እናም ፈተናችንን እርሱ ተቀበለ፥ ስለዚህ እኛ ተፈታኝ ሳንሆን፥ ፈተናዉን ያለፍን ባለዉጤት ነን።

የተከበራችሁ ወዳጆቼ ክርስቶስ ኢየሱስ ካሰበልን በላይ ልናስብ የበቃን አይደለንም፥ እርሱ ደግም አንዴ አስቦልናል!።

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
696 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 18:51:03
“ብቻ ጽና፥ አይዞህ።”
— ኢያሱ 1፥18

የተወደዳችሁ ዉድ ኢትዬጵያዉያን

ዛሬ በቆምንበት የዉድቀት ምዕራፍ ላይ ሆነን፥ የተበታተኑ ነገሮቻችንን ለመሰብሰብ እነሆ በፊቱ እንፍገመገማለን፤ የእኛ ሽንፈት ከእግዚአብሔር ብርታት በላይ የገነነ ሲመስለን፥ ደግሞ ራሳችንን እንታዘብና ለጥቂት ብንፅናናም፥ ደግመን ደጋግመን እንደ ሃገር "አትለፈን!" ብለን፥ ጩኋታችንን ሁሉን በሚችል አምላክ ፊት፥ ማቃችንን እናሳየዋለን፤ ይሄ ማለት ልክ ድፍን እስራኤል በሙሴ ሞት አዝኖና ተክዞ፥ ሲያለቅሱ በነበሩበት ምድረበዳ መካከል፥ ወደፊት የሚቀጥሉበትን ወኔ ባጡና፥ ከፍ ባለ ምሬት ባለቀሱ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ግን ወደ ኢያሱ ድንኳን መጽናናት ይዞ መጣ፤ የእስራኤል እንባ የሚታበሰዉ በሙሴ መኖር ሳይሆን እግዚአብሔር በእስራኤል መኖሩን እንደሆነ ኢያሱ ገባዉ፥ ከሃዘናችን በላይ የእግዚአብሔር ስም በእኛ መጠራቱ ዋጋዉ መፅናናት ነዉ፤ ያለቀሳችሁ ሰዎች ልላችሁ የምችለዉ ነገረረ ቢኖር፦ እግዚአብሔር ዛሬ በድንኳናችሁ ገብቶ፥ ሃዘናችሁን እንዳለፈ ዉሃ እንዲሆን ያዘዋል እያልኳችሁ ነዉ!፤ ስብራትን የሚጠግን የእግዚአብሔር ፀጋ በእናንተ ላይ ይሁን!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
860 views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ