Get Mystery Box with random crypto!

የቃል ጠብታ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yekal_tebta — የቃል ጠብታ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yekal_tebta — የቃል ጠብታ
የሰርጥ አድራሻ: @yekal_tebta
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.29K
የሰርጥ መግለጫ

ከምርጦች የተሰባሰቡ የስነፅሁፍ ማህደሮች
(ግጥም፣ወግ፣ልብወለድ፣ሙዚቃ)
#በድምፅና #በቪዲዮና #በፅሁፍ እዚህ ያገኛሉ።
ይህን ይጫኑ @yekal_tebta
Inbox @Natitg2 0940219376
@Dagi_tecno @akuna444
ፕሮግራማችን
እሁድ_ከክላሲካል ጋር የተቀናበሩ የድምፅ ግጥሞች
ማግሰኞ_የድንቅ ደራሲዎቻችንን ወጎች በድምፅ
ሃሙስ_የሳምንቱ ምርጥ ሙዚቃ ግብዣችን
ቅዳሜ የመፅሃፍ ትረካና ግብዣ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-22 11:25:23 ሁለቱም የግጥም ስራዎቼ ነሃሴ ዓመት ይሞላቸዋል። በዓውደ አመት ማግስት ነሃሴ ላይ አሳዛኝ ክስተትን ሰምተን ነበር። አመት የሞላው ቢሆንም ግን ሃዘን ለአዛኙ ሁሌም አዲስ ነው።
አበባ አየሽ ወይ ልንል ስንል የእንባ እንባ አየሽ ወይ ወደሚል ዜማ በተቀየረበት ጊዜ ነበር።
የደም ዘመን የሚል ርዕስ የሰጠሁት
የደም ዘመን






ደግሞም በሃገር ባህል ወግ ለሃዘን ድባብ ልብስ ይመረጣል። ቀይ እንልበስ ወይስ ጥቁር ወይንስ ነጭ አልኩ።

ሃዘንም የልብስ ጌጥ አለውና።


የሃዘን ልብስ







ሁለቱንም ስራዎች ሊንኩን በመንካት መመልከት ትችላላችሁ።
322 viewsNati. B, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 06:29:25 ቅኑን በቅን አቅኑት አቤል አማረ እና ናትናኤል ብርሃኑ


1.9K viewsNati. B, 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 17:50:14 ቅዳም ስዑር kidam seur by nati berhanu በናቲ ብርሃኑ


611 viewsአሁን Now, 14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 19:28:26
#ሽክረት(በናቲ ብርሃኑ)

ይህ የግጥም መድብል
በቅርብ ቀን በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ይከበራል።

በምርቃ ዝግጅቱ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
637 viewsNati. B, 16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 13:06:18 https://vm.tiktok.com/ZMLaKSaPT/?k=1
690 viewsNati. B, 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 07:24:37 ¶ጥሎሽ
°ተከታታይ ጽሑፍ(ምናባዊ ልቦለድ)°

(ከመኖር ብንሸራተትም
ልብሽ ደግፎኛልና አልወድቅም!)
ክፍል 2


እናቴ ከቤት ስትወጣ ገላዋን ፀሐይ ሲነካት ተሸሽጎ የነበረው ጥላ መሬት ላይ መሳል ጀመረ።

እንደ ጥላ ፈሪና እንደ ጥላ ክፉ አለ?

ጥላ አልወድም። በህይወቴ እንደ ጥላ የሚያስጠላኝ ነገር የለም። ለምንድነው ግን ሁሌም አብሮን ከማይሆን ጋር የምን'ሰፋው? ሁሌም ጉዟችን ወደ ማናገኘው የሚሆነው ለምንድነው? ወደማላገኘው ስጓዝ በእጄ የነበሩት ስንቱ ሻገተ? ለማግኘት ስሄድ ያጣሁት ፊቴ እየተደነቀረ መንገዴን የሚጋርድብኝ ሁኔታ ግራ ይገባኛል። ወደ ማጣት ግስጋሴ ብክነት...

ባለን ነገር ላይ እምነታችን የሳሳ ነው። ስስነት ደግሞ አንድ ቀን ይበጠሳል ወይ ይሰወራል።

በሩን ገርበብ አድርጋ እናቴ ወጣች። ሄደች። ምናለ በሩን በዘጋችው ወይ በከፈተቺው። ገርበብ ማለት ሲያስጠላ። ወደ አንዱ አለመሆን። መሃል ላይ መንገዋለል።

"መሌ አልተነሳህም እንዴ?" ፀሐይ ወጥታ(እናቴ) ፀሐይ ገባች(ርብቃ ገርበብ ያለውን በር ከፍታ)

"ስማ?"

ድምጿን ስሰማ የሆነ የማውቀው ስሜት ነፍሴን ሲያሽኮረምማት ከሰመመኔ ነቃሁ። ይህን ስሜት የት ነው የማውቀው?

"እህ መሌ!"

ካላየሁሽ የሰማሁሽ አይመስልሽማ? በብርድ ልብሴ እንደተጠቀለልኩ መለስኩላት።

"ትኩረትህ እኔ ጋር መሆኑን ለማወቅ እኮ ነው መሌ። መስማትማ ማንም ምንንም ይሰማል። ችግሩ ማድመጥን በመስማት ማሸሹ ላይ ነው። በል ተነስ! ጭራሽ ሻይ ቀድተህ ነው ትተኸው የተኛከው?" ጠረጴዛ ላይ ያለውን ሻይ በጣቶቿ እያነሳች...!

እማ ቀድታው ነው። ቀዘቀዘ እንዴ? ሳላውቀው ትንሽ ሸለብ አደረገኝ መሰለኝ። እስቲ ሞቅ አርጊልኝ።

"አንተን ሃሳብ እንጂ እንቅልፍ አይወስድህም! በል አሁን ተነስ ቤቱን ላስተካክለው!"

ርብቂዬ ትንሽ ብቻ ልተኛ!

ርብቂ አትበለኝ! ስንቴ ልንገርህ? ባንተ ምክንያት ይህን ስም ልጠላው ነው። እስከመቼ ነው ከዚህ ስም የምሸሸው? ንገረኝ እስከመቼ?

አንድ እግሩ በተንጋደደው ወንበር ላይ ልትቀመጥ ስትል አደናቅፏት በእጇ ጠረጴዛውን ስትደገፍ ሻዩ እላይዋ ላይ ፈሰሰ።

"የዚች ስም በተነሳ ቁጥር ሁሌ ችግር እንደተፈጠረ ነው። ባንተ ምክንያት የማላቃትን ሴት ልጥላ?" የረጠበ ቀሚሷን በጣቶቿ አደራርቃ መሬት ላይ ተቀመጠች።

አይኗ ውስጥ ናፍቆትና እልህ፣ ፍቅርና ጥላቻ፣ ከየዋህነት ጋር ተጋምደው ሲርመሰመሱ ሲቀጣጠሉ ህመም ያንገላታው እንባዋ በጉንጮቿ ላይ ኩልል ብሎ ወርዶ ከንፈሯ ውስጥ ተቀበረ። ለእንባዋ ሳታለቅስ እንባዋ ሞተ። እንባዋ ሲሞተ እንባዬ ተወለደ።

ምን ላርግ እሺ! ሁሉ ነገሬ ከትላንት ጋር ተሳስሮብኛል። ሮጬ አላመልጠው ነገር አቅም አጣሁ። ለኔ ከትላንት ውጪ ምን አለኝ? ከናፍቆት ውጪ ምን አለኝ? ረብቂዬ...

ስሟን አትጥራብኝ አልኩህ እኮ!" ከመቅጽፈት ከተቀመጠችበት ተነሳች። ከመሬት ተነስታ መሬት ላይ ቆመች። ከመሬት ወዴት ይሸሻል። "ክፉ ልታደርገኝ ነው እንዴ?"

እሺ ምን ላርግ?

"እኔ ብሌን ነኝ! እንደ ርብቃ ሳይሆን እንደ ብሌን ቅረበኝ!"

አልችልም! ድንገት ይህ ቃል ከአፌ ወጣ። አልችልም። ፊቷን ላለማየት ብርድ ልብሴን ተከናነብኩ። ሽሽት....


አልጨረስኩም ለነገሩ መች ጀመርኩና!


¶መላኩ ነኝ!
@yekal_tebta
@DBU111 Discussion
@Dbu11 Daily news
@dbu_entertain Entertainment on telegram

Subscribe our youtube channel

https://youtube.com/channel/UCAS829K6929J4CVsxrwsyzA
@dbudailyaskbot
830 viewsNati. B, edited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 07:24:37 ¶ጥሎሽ

(ነግቶ ነው መሰል አልነጋ አለኝ!)
ክፍል 1

(በልቦለዱ ውስጥ የገጸ ባህሪ ስምና ባህሪ ቢመሳሰል አጋጣሚ እንጂ ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ይታወቅ። )

ነግቷል። መንጋቱን ያመንኩት አይቼ አይደለም ሰምቼ ነው።ዶሮ ነገረኝ። ወፍ ነገረኝ።

እንደነጋ ቢየገረኝም ግን ምንም የሚታይ ነገር የለም። ሁሉ ነገር የተዳፈነ ጭለማ ነው። ምክንያቱም ተሸፋፍኜ ተኝቻለሁ። ለካ ስለነጋ ብቻ አይነጋምም።

ተኝተው በሚነቁበት በዚህ በዚህ ዘመን ሲቀርብም በዚህ ሰዓት ሰው ነቅቶ ይተኛል?

የኔን ንጋት የሚያውጅልኝ ተፈጥሮ አይደለም። ንጋቴ ልቤ ውስጥ እምነቴ ውስጥ ነው ያለው። ልክ ከአልጋዬ ስወርድ ያኔ ለኔ ይነጋል። ተፈጥሮ ግን ይጨልማል። መነሳት ስለማልፈልግ መነሳት አልችልም። አለመፈለግ መቻልን ይገድለዋል። ስንት ዘመን ላርፍድ። አለማርፈድ አልፈልግም ለምን...

"መሌ!"

እናቴ ናት። ቁርስ ደርሷል ማለት ነው። ከዶሮ እና ከወፎች ባሻገር መንጋቱን የሚያሳውቀኝ የእናቴ ጥሪ ነው። እናቴ ሳትኖር ግን መንጋቱን በምን አውቅ ይሆን? መቼም ንጋቴን እንዳላምን ተስፋዬን የነጠቀ አምላክ እምነቴን ከኔ ያሸሻል ብዬ አላስብም።

"መሌ!"

ዝም አልመለስኩም።

"ልጄ!"

ጭጭ

"አባ!"

እ... ድምጽ አሰማሁ። እንቅልፌን አልጨረስኩም እንደማለት።

"ተነስ አባዬ ቁርስ ደርሷል።"

ትንሽ ልተኛ እንጂ

"ከዚ በላይ እስከ ስንት ሰዓት ልተኛ አሰብክ። አንተ እንደፈለክ ግን በብዙ ስተኛ ፍራሹ ያልቃል። ፍራሹ ከሳሳ እንደ ብርድ ልብስ ለብሰህ መሬት ላይ ትተኛለህ እንጂ ፍራሽ የሚገዛህህ የለም።"

አረ እማዬ! ምንድነው

"አረ አትበለኝ! ይኸው ሻይ አፍልቻለሁ። ዳቦ ደግሞ መሶቡ ዎ
ውስጥ አለ። ከፈለክ ጎረቤት ሄደህ ወጥ አስጨምረህ ቁርስህን ብላ። ካልበላህም ጥሩ ነው ለምሳ ይሆንሃል።"

የማጠጋጋት ህግ መሆኑ ነው?

"ስም መስጠት ላይማ ጎበዝ ነህ። ለማንኛውም እየወጣሁ ነው በሩን ዝጋው። ቶሎ ሳትነሳ ሻዩ ቀዝቅዞብህ ድጋሜ ለማሞቅ ከሰል አያይዛለሁ ብትል ውርድ ከራሴ!"

እንደውም እማዬ ርብቃ መጥታ እሳት አያይዛ ቤቱን ሞቅ ብታደርገው ደስ ይለኝ ነበር።

እንደዛማ የሚያደርገው ወንድ የሆነ ሰው ነው። አንተ ዝም ብለህ ተጋደም በል ሻዩን ቀድቼልሃለሁ። ቤት ጥለህ ደግሞ እንዳትወጣ! ካልሆነም ቤቱን ቆልፈህ ቁልፉን ጎረቤት አስቀምጥልኝ።

ብርድ ልብሴ በትንሹ ገለጥ አድርጌ ሳያት በሩን ገርበብ አድርጋ ወጣች። በበሩ ቀዳዳ የሚገቡ የጸሐይ ጨረር ቤቱን ዲም ላይት የተለክሰበት አስመሰሉት።

እናቴ ከቤት ስትወጣ ገላዋን ፀሐይ ሲነካት ተሸሽጎ የነበረው ጥላ መሬት ላይ መሳል ጀመረ።

እንደ ጥላ ፈሪና እንደ ጥላ ክፉ አለ?


አልጨረስኩም ለነገሩ መች ጀመርኩና!


¶መላኩ ነኝ!


@yekal_tebta
@DBU111 Discussion
@Dbu11 Daily news
@dbu_entertain Entertainment on telegram

Subscribe our youtube channel

https://youtube.com/channel/UCAS829K6929J4CVsxrwsyzA
@dbudailyaskbot
640 viewsNati. B, edited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-09 13:27:09 https://vm.tiktok.com/ZML2rSYye/
681 viewsNati. B, 10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 22:57:37 አንቺ ስትመጪ ግጥም በ ናቲ ብርሃኑ anchi stmeco poem by nati berhanu | dbu daily ent...


725 viewsNati. B, 19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 17:05:48 ጣኦት


Geni
(አዝማሪ_ነኝ_ገጣሚ)


ሰዉ ዘሩን ካክዶ ዘር እያባዘተ፣
የአዳምን እጥን የሄዋንን ሽቶ
ዘንግቶ ከሳተ፣
ጣረሞት መሳዩን ብሔር ከሸተተ፣
ጥኦትን አምልኮ ደም እየገበረ
ከነሳህ ምስጋና፣
እኛ ሚስኪኖቹ የመኖርን
ትርጉም ተርበናልና፣
ሰባብሮልን ይረፍ ቀዳዶልን ይሂድ ሙሴን ላከዉና።


@yekal_tebta
DBU Daily Entertainment
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ አዲስ የመዝናኛ ቻናል። YOUTUBE
https://youtube.com/channel/UCAS829K6929J4CVsxrwsyzA

All in one!

Contact
@at_theTime
@dbu_Entertain
@yegitm_mender
723 viewsNati. B, edited  14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ