Get Mystery Box with random crypto!

አረብኛን ይማሩ 🕌 مدرسة اللغة العربية 🕌

የቴሌግራም ቻናል አርማ arebiclangugeschool — አረብኛን ይማሩ 🕌 مدرسة اللغة العربية 🕌
የቴሌግራም ቻናል አርማ arebiclangugeschool — አረብኛን ይማሩ 🕌 مدرسة اللغة العربية 🕌
የሰርጥ አድራሻ: @arebiclangugeschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 600
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል በአረብኛ ቋንቋ ላይ መሰረታዊ ዕውቀት እንዲኖርዎ ይረዳዎታል-
- የቃላት ዝርዝሮችን (Vocabulary)
- ቀላል ሐረጎችን (Simple phrases)
- ከስህተት ሊጠብቅዎ የሚችሉ በጣም አስፈላጊ ህጎችን
- ጥያቄ እና መልስ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-13 01:12:33
ከአብሬትዩ ሳኒ ወአዝ የተወሰደ
❀❀❀❀❀❀❀ ❀❀❀❀❀❀❀ ❀❀❀❀❀❀❀

ጫት የኸረ በኸረ ቢፍቴ ዘበር አነበረ... ቃዋ የኸረ በኸረ አነበረ... በኸለፍ ዘበር ተቀነሰም... የኢባዳ ጠቃሚ ቃር አመነዎም ታነ አዘዎዪም... አታት ግዝየ ይበሁሪ፣አታት ግዝየ ይረህዊ... የበኮሪ ግዝየ በቀሪም ቃር ተብቃቆቱ... እማት እማት እንዝርም ቦኔም ታነ ማይና ቢቾቺ ወሄ ቃሩ... አታት ሲንም ተቃዊምታ ሜና ቢቾቺ ዱኣ ቢያሟሪ ወሄ ቃሩ...

ያሙዌን ዱኣ ጫት ኤኔ ይቺ ዌ? ያሙዌን ዱአ ቃዋ ኤኔ ይቺ ዌ? ቢፍት ዘበር ጫትም ኤባር ዱአ ይጨቁሺባ... ቃዋም ኤባር ዱአ ይጨቁሺባ... ማይና ያሙወሪባ...

#በአማሪኛ

ጫት የሆነ እንደሆነ በፊት ዘመን አልነበረም... ቡናም የሆነ እንደሆነ አልነበረም... በኸለፍ ዘመን ተጀምረ... ለኢባዳ ጠቃሚ ነገር እንደሆነ አድርገው አዩት... አንዳንዴ ይገኛል ፣ አንዳንዴ አይገኝም:: ያልትገኘ ግዜ በትንሹም መብቃቃት ነው... አንድ አንድ ቅጠልም ተቅሞ ኢባዳ ቢሰራ ጥሩ ነው... አንድ አንድ ሲኒ ቡና ተጠጥቶ ስራ ቢሰራ ጥሩ ነው::

የሚሰራ ስራ(ዒባዳ) ጫት ስለሌለ ይተዋል እንዴ? የሚደረግ ዱዓ ቡና ስለሌለ ይተዋል እንዴ? በፊት ዘመን ጫትም ሳይኖር ዱዓ ይለመን ነበር... ያለ ቡናም ዱዓ ይለመን ነበር... ስራ(ዒባዳ) ይሰራ ነበር::
Hasen injamo
283 views22:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 11:50:22 عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال كل عام وأنتم بخير

Mäý ž mäģïc òf Êįď břĩñğ łöťś òf ĥåppïņêś & fïłľ űŗ ĺïfę ŵĩťĥ ď/ț čőľŏůř ĥv bĺëşŝėď imméņšë ĵöý Ëĩď ťõ ų & ũŕ bęłøvėď fąmĭł¥ ëĩď műbąŕěķ
302 views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:13:10 የመጅሊሱ ዕጣ-ፋንታ ከ2ቱ 1ዱ ነው ሚሆነው

በትላንቱ የቤተ-መንግስት ስምምነት መሰረት ከ300 እስከ 400 የሚደርሱ የሱፊያና የወሃቢያ ዑለሞች ከየገጠሩ እና ካያሉበት ተጠርተው መጥተው የመጅሊስን ረቂቅ ደንብ ከሀገራችን የእስልምና ታሪክ አንፃር ይመረምራሉ፡፡ (ዶ/ር ዐብይ እንደውም ትላንት ቁጥራቸውን 400 ዑለሞች ነበር ያለው) ረቂቅ- ደንቡን መርምረው ምን ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ማወቅ በጣም ቀላል ነው፡፡ ከ95 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ቀደምት የዓለም ዑለሞች፣ ሙስሊሞችና ግዙፍ የሙስሊም ኢምፓየሮች በሙሉ ዐቂዳቸው አሽዓሪያ/ማቱሪዲያ መሆኑ ማንም የማይክደው ሐቅ ነው፡፡ በዘመናችን የሚገኙ የዓለም ዑለሞች ከ95 ከመቶ በላይ የሚሆኑት ተመሳሳይ ዐቂዳ ሚከተሉ ናቸው፡፡ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ የሐበሻ ዑለሞችም በሙሉ እና መጅሊሱን የመሰረቱት ዑለሞች ጭምር ይህንኑ ዐቂዳ እንደሚከተሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ዛሬ በየገጠሩና በየሐሪማው ያሉትም ዑለሞች ይህንኑ ዐቂዳ እንደሚከተሉ ለሁላችንም ግልፅ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የወሃቢያ ዑለሞች ይህን ዕውነታን መቀበል ከፈለጉ የመጅሊስ የዐቂዳ መስመር አሽዓሪያ/ማቱሪዲያ መሆን እንደሚገባው ከሱፊያ ዑለሞች ጋር በጋራ እንደሚያፀድቁ ጥርጥር የለውም፡፡

በመሆኑም የመጅሊሱ የመጨረሻ ዕጣ-ፈንታ ከሚከተሉት ከሁለቱ አንዱ ነው ሊሆን ሚችለው፡፡ ከዚያ ውጪ አይሆንም፡፡ በሁለቱም ኬዝ ግን መጅሊሱ በሱፊዮች እጅ ውስጥ ነው ሚሆነው፡

. የመጀመሪያው ሊሆን የሚችለው ዑለሞቹ ህገ-መጅሊሱን በሚያፀድቁበት በአሽዓሪያ/ማቱሪዲያ ላይ ተንተርሰው የአሽዓሪያ/ማቱሪዲያ ዐቂዳን የሚያስቀጥሉ ሙፍቲን የመሰሉ የሱፊያ ዑለሞች ዳግም የመጅሊሱ አመራሮች ተደርገው ይመረጡና ወሃቢዮች ደግሞ ይህን ተስማምተው ከተቀብሉ ከስሩ ታቅፈው ይቀጥላሉ፡፡

. ወይም ምናልባት ዑለሞቹ ስምምነት ላይ መድረስ ባይችሉ ዶ/ር ዐብይ ትላንት ቃል በገባው መሰረት የመጅሊሱ ቁልፍ ከሚያዚያ 23/2011 በፊት የነበረው የቀድሞው የመጅሊስ ፕሬዝደንት ለነበሩት ለሸኽ ሙሐመድ አሚን ጀማል ይሰጥና አሁንም መጅሊሱ በሱፊዮች እጅ ይቀጥላል፡፡

ዶ/ር አብይ ትላንት በተናገረው መሰረት ይህን አልቀበልም ያለ አካል ዞር ማለት አለበት እንጂ አሁንም በመጅሊስ ዙሪያ ዳግም ረብሻ እቀሰቅሳለሁ ካለ ግን መጨረሻው ዘብጥያ ይሆናል፡፡ አሁን ውስጣዞቹም ይህን ሁከት ይሞክሩታል ብዬ ጨርሶ አላስብም፡፡ በፊት እንኳ ቢታሰሩም ምንም አልነበረም ችስታ ነበሩ፡፡ አሁን ግን በእስሩ ሸቅለውበት ከብረውበታል፡፡ ይህን እያጣጣሙ ይኖራሉ እንጂ ሌላ ነገር ውስጥ ይገባሉ ብዬ አልጠብቅም፡፡ ምናልባት ሸይጧን አሳስቷቸው አመፅ ለመቀስቀስ ቢሞክሩ ያው ቅሊንጦ ሄደን እንዘይራቸዋለን፡፡ ግን እመኑኝ ፈፅሞ አያደርጉትም፡፡ ጎመን በጤና ብለው ሽቀላቸውን ነው ሚያሯሩጡት፡፡

እንደዚሁም ውስጣዞቹ የ #ቤርጎውን_መጅሊስ እንደ አዲስ መቀጠልም አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ዶ/ር ዐብይ ስለባነነባቸው .. ‹‹አሁን ሁሉም ነገር ቀድሞ ወደነበረበት ይመለስ›› .. ብሎ በሲስተም የ #ቤርጎውን_መጅሊሳቸውን አፍርሶታል፡፡ ዳግም ወደ #ቤርጎው_መጅሊስ እንዳይመለሱ አድርጎ አስቀድሞ ነው አሪፍ ምት የመታቸው፡፡ የፈረሰውን የ #ቤርጎ_መጅሊስ መልሰን እንደ አዲስ እንመስርት ቢሉ አሁንም አመፅ መቀስቀስ ስለሚሆን ዶ/ር ዐብይ ትላንት ባስጠነቀቀው መሰረት ዕጣ-ፋንታቸው ዘብጥያ መውረድ ይሆናል፡፡

ምናልባት .. ‹‹በሐበሻ ዑለሞች ዐቂዳ ላይ ከተመሰረተው መጅሊስ ጋር ወሃቢዮቹ ካልተስማሙ የራሳቸውን ሌላ መጅሊስ ማቋቋም አይችሉም እንዴ? ይህን ለማድረግ የሃይማኖት ነፃነትስ የላቸውም እንዴ?›› .. ካላችሁኝ፤ መልሴ .. ‹‹ማቋቋም ይችላሉ፡፡ ነፃነትም አላቸው፡፡›› .. የሚል ነው፡፡ ነገር ግን የእኛ መጅሊስ አሁን እየተደራጀበት ባለው .. ‹‹አህሉ-ሱና ወል-ጀማዓ›› .. በሚል ስም መጅሊስን ማቋቋም አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ሁለት ተመሳሳይ ሃይማኖት በአዋጅ ሊቋቋም አይችልምና፡፡ ሌላ ስም ሰጥተው ግን ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡ ‹የሰለፊያ መጅሊስ› ወይም ‹የወሃቢያ መጅሊስ› ብለው ማቋቋም ይችላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ሁለት የተለያዩ መጅሊሶች ይፈጠራሉ፡፡ አንደኛው .. ‹‹የአህለ-ሱና ወል-ጀማዓ›› መጅሊስ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ‹‹የሰለፊያ›› ወይም ‹‹የወሃቢያ›› መጅሊስ ይሆናል፡፡

ይህ ክፍፍል የመጣው እንግዲህ .. ‹‹አንድ ነን›› .. ብለው ሚፎግሩን ወሃቢዮች የኢትዮጵያ እና የዓለም መሻኢኾች የዐቂዳ መስመር የሆነውን ዐቂዳ አንቀበልም በማለታቸው ነው፡፡ መጅሊስን የመሰረቱት ዑለሞች ሳይቀሩ የሚከተሉትን ይህን ዐቂዳ ተቀብለው ወይም ከስሩ ታቅፈው ቢጓዙ ክፍፍሉ አይከሰትም ነበር፡፡ ዑለሞቻችን ደግሞ ከዛሬ 30 ዓመት ወዲህ ወደ ሀገራችን ለገባ መጤ ዐቂዳ ብለው ለ1ሺ ዓመታት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ዓለም አቀፍ ዓቂዳን የሚተዉበት ምክንያት አይኖርም፡፡ መጤው ቡድን የምር አንድነትን ቢፈልግ ኖሮ በሀገራችን የነበረውን እና አሁንም ያለውን ዐቂዳ ተቀብሎ መቀጠል ይችል ነበር፡፡ ‹‹ይህን አልቀበልም›› .. ሲል .. ‹‹አንድ ነን›› .. ብሎ ሲዋሽ የነበረው ቅጥፈቱ በሁሉም ዘንድ ተጋልጧል፡፡ ምክንያቱም አንድ ብንሆን ኖሮ በነበረው ላይ ተስማምቶ ይቀጥል ነበር፡፡ በዐቂዳ/በእምነት ስለምንለያይ እኮ ነው ለዐቂዳው ብሎ መጅሊስን እስከመገንጠል የሄደው፡፡

ለማነኛውም የመጅሊስ ዕጣ-ፈንታ ከላይ ከገለፅኳቸው 2 ነጥቦች ውጪ ሊሆን አይችልም፡፡ በሁለቱም ሁኔታ መጅሊሱ ‹‹አህሉ-ሱና ወል-ጀማዓ›› በሆኑት ዑለሞቻችን እጅ ውስጥ ነው ሚሆነው፡፡

ኸላስ!!
314 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 02:03:54
ከሚንበር ቲቪ መልስ እንጠብቃለን
493 views23:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 00:56:13 አንድ ሰው ከጎደኛው ዘንድ ይሄድና ይሄ ጎራዴ ከፋርስ የመጣ እና ስል ነው ምንም አይነት ነገር መቁረጥ ይችላል ይለዋል ጎደኛውም ይገርምና ሁሉን መቁረጥ ይችላል እስቲ እንሞክረው ይባባሉና ይሄን ድንጋይ ለሁለት ከከፈለው እውነትም ይሄ ጠንካራ ነው በል ምታው ይለዋል?
ሰውዬውም በሰይፉ ደንጋዩን መታው ነገር ግን ድንጋዩ ሳይሆን ሰይፉ ነበር ለሁለት የተከፈለው።

*እና ወዳጆቼ ምንም የተሳልክ ስል ብትሆን ምንም ጠንካራ ብትመስል የረሱልን እና የዑለሞችን መንገድ ለማጥፋት ብትሞክር አንተ ትጠፋለህ እንጂ መንገዳችን ኢላ የውሚል ቂያማ አይጠፋም።
*በእና አፄ ዩሀንስ በሌሎቹም ሲገደል የኖረው ሱፍያው እንጂ ከ30 አመት በፊት የመጣው ወሮ በላ አይደለም ሰይድ ጦልሀ ጃእፋር ሀሰን እንጃሞ እኮ ወሀብይ ሚባል ነገር እንኮን አያውቁም ታድያ ራስህን በቀጥተኛ መንገድ ላይ አድርገህ ስታወራ አታፍርም።
*አንዱ ኡስታዝ ዛሬ ተነስቶ Fb ምን ለጠፋ ሱፍይ ማለት ሰውን ያማያማ ቂም የማይዝ ነው። (ያሲን ነው ሚባል የአረብ ብር እኳ ታሰክራለች) አንተ የበታች እንድትሆን የነብዩን የዑለሞቹን መስመር ሲፈርስ ዝም ብለህ ቤትህ እንድትቀመጥ ነው ሚፈልጉት። ይሄ ግን አይሆንም በደም በስቃይ ዋጋ ተከፍሎበት የመጣው ዲን በኛ ዘመን እንዲፈርስ አንፈቅድም!!!!

@abduftsemier
@abduftsemier
369 views21:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 01:54:33 ከዛሬ 290 አመት ጀምሮ ሀገራችን ላይ ደግሞ ከዛሬ 30 አመት ጀምሮ የመጣ የሙሐመድ ኢብን ዐብዱልወሃብ አስተሳሰብ ተከታይ ቡድን ነው።
---
[17]. አዲሱ የመጅሊስ አመራር አብዛኛው አባላቱ የተፈራረሙበት የሽግግር ጊዜ መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጀ ቢሆንም ይኸው ጊዜያዊ መተዳደሪያ ደንብ ብዙ ችግሮች ያሉበት እና እርስ በእርሱ የሚቃረን ሠነድ ነው ለማለት ይቻላል።
---
[18]. የቦርድ አመራሩ ከዑለማ ስራ አስፈጻሚ ጋር ሽኩቻ ውስጥ ገብቶ የነበረ ሲሆን መንስኤውም፤ ቦርዱ በሱፍያው ወገን ለሰለፊ ወገን የሚያደላ ተደርጎ መታሰቡ እና በድርጊቱም ይህንኑ ማረጋገጡ ነው።
---
[19]. ይህ የሆነበት ምክንያትም፤ ቦርዱ በጉዳዮች ዉሳኔ ላይ በገለልተኝነት ከሱፊ ሰለፊ ወጥቶ ሙያዊ አስተዋጽኦ ብቻ መስጠት ሲጠበቅበት ራሱን የጠቅላላ ጉባኤ አካል አድርጎ በመቁጠር ከዑለማ አባላት ጋር እኩል ስልጣን አለኝ የሚል የአክቲቪዝም ስራ ውስጥ በመግባቱ ነው። ሌላው ሁላችንም የኡማው አማና ተሸክመናል በሚል እሳቤ ጉዳዮችን ወደ ጠቅላላ ጉባዔ የመውሰድ እና ከሰለፊው ቡድን ጋር ተባብሮ የዑለማ ሠነዱን እና ደንቡን የድምጽ ብልጫ ስርዓትን ተግብሮ ለማጽደቅ መሞከሩ ነበር። ይህንንም የዛሬ ዓመት ኢሌሌ ሆቴል ተግብሮታል።
---
ይቀጥላል…
---
462 views22:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 01:54:33 የመጅሊስ ሒደት ላይ አጭር ማብራሪያ
✦•✦•✦
ክፍል አንድ
---
[1]. ከተለያዩ ወገኖች የተውጣጡ 9 አባላት ያሉት "የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ" ኮሚቴ በጠ/ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ተቋቋመ። ይህ ኮሚቴ 3ት አባላቱ የአህሉ ሱንናውን መስመር ወክለው ሲሆን 3ቱ ደግሞ ከወሃቢያ/ሰለፊ መስመር ነበሩ። የተቀሩት 3 አባላት ደግሞ "ገለልተኛ" ምሁራን ነበሩ።
---
[2]. መጀመሪያ ላይ የኮሚቴው ሚና መጅሊሱን በአዲስ መልክ ለማደራጀት የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ማዘጋጀት የነበረ ቢሆንም በሂደት ግን ነባሩን መጅሊስ አመራር ስልጣን አንዲያስረክብ የማግባባት ስራና ጊዜያዊ መጅሊስ አመራር የማዋቀር ስራን ሰርቷል።
---
[3]. ኮሚቴው "የኢትዮጵያ ዐሊሞች የአንድነት እና የትብብር ሠነድ" እና "የመጅሊስ መተዳደሪያ ደንብ" የሚባሉ ሁለት ረቂቅ ሰነዶችን አዘጋጀ። መተዳደሪያ ደንቡን በተመለከተ 9ኙም ኮሚቴ አባላት (ሙፍቲን ጨምሮ) መስማማታቸውን በፊርማቸው ያረጋገጡት ቢሆንም በአማርኛ እና አረብኛ የተዘጋጀው 31 አንቀጾች ያሉት "የዑለሞች የአንድነት እና የትብብር ሠነድ" የሚባለውን ግን ከ9ኙ ኮሚቴ ውስጥ ሙፍቲን ጨምሮ ሶስት ግለሰቦች ብቻ ተስማምተው የፈረሙበት ሲሆን በተቃራኒው አንድም የወሃቢያ/ሰለፊ ተወካይ ሠነዱ ላይ አልፈረሙም። በመሆኑም በሸራተን ጉባዔ የተነበበው ይህ አዘጋጆቹ እንኳን ያልተስማሙበት ሠነድ ነው።
---
[4]. በዑለሞች መካከል በዐቂዳ መስመሮች፤ በመውሊድ እና ተሰውፍ ዙሪያ ዑለማ ሰነዱ ላይ እንዴት መግባት እንዳለባቸው በተፈጠረ አለመግባባት ከሚከተሉት አማራጮች ይበልጥ ገላጭ የሆኑትን ማስቀመጥ ይቻል ዘንድ መነሻ እንዲሆን በሚል ሶስት አማራጭ አንቀፆችን ያቀረበ ሲሆን የዘርፉ ዑለሞች አንዲወስኑበት የተተወ ነበር።
---
[5]. "አንድነት" በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረው ወሃቢያ/ሰለፊ ቡድን ይህንኑ ፍላጎቱን በዑለሞች መግባቢያ ሠነድ ላይ እንዲያረጋግጥ ሲጠየቅ፤ የሚያለያዩን ጉዳዮች ተራ እና ጥቃቅን ጉዳዮች በመሆናቸው በዑለማ ሰነዱ መጠቀስ የለባቸውም እያለ ሲያጣጣል ሌላኛው ወገን ደግሞ ለኔ ወሳኝ ናቸው ሰነዱ በኡለሞች መካከል የሚፈረም እስከሆነ ድረስ በዚህ ጉዳይ ሳንስማማ እና ሳንፈራረም "አንድ ነን" ብለን መንቀሳቀስ የውሸት ነው፤ ጉዳዮቹ ላንተ ተራ ከሆኑ ተቀበልና በፊርማህ አረጋግጥ የሚል ጥያቄ አንስቷል።
---
[6]. በሌላ በኩል 9ኙ ኮሚቴ ያዘጋጀው መተዳደሪያ ደንብም ቢሆን የአህሉ ሰንናው ወገን ያሉ በርከት ያሉ ምሁራን እና ዑለሞች ትችት እና ተቋውሞ ያጋጠመው በመሆኑ፤ መጅሊሱን በአዲስ እና ሁሉንም ያሳተፈ እንዲሆን የተወጠነው ሀሳብ እንቅፋት ገጠመው።
---
[7]. የመተዳደሪያ ደንቡ ዋነኛ ችግሮች ተብለው በወቅቱ የተጠቀሱት፤
---
➥ መጅሊሱን ከእምነቱ በተጸጻሪነት እና የቀደምት ስርዓትን ፈለግ በመከተል በብሄር ለማዋቀር መሞከሩ፤
---
➥ የእምነት ተቋም ሆኖ እያለ የኃይማኖቱን መሪዎች ተራው ህዝብ እንዲመርጥ የሚፈቅድ በመሆኑ፤ የእምነት ተቋሙ የበላይ መሪ ዑለማ ብቻ መሆን ሲገባው ዑለማን እና ምሁራን መካከል ያለውን የስልጣን ኃላፊነት ስህተት መሆኑ ግልጽ አለማድረጉ ወይም አሰራር መዘርጋቱ፤
---
➥ ተቋሙ ዋና ግቡ በዋነኛነት የምእመኑን መንፈሳዊ ሕይወት ማጠናከር እና ማሳደግ ሆኖ ሳለ፤ ለዚህ ግብ መሳክት አስፈላጊ የሆኑ ተጓዳኝ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶቹን በሚወጣበት መልኩ ማደራጀት አስፈላጊነቱ የማያጠያይቅ ቢሆንም፤ የተዘጋጀው ሰነድ ግን መንፈሳዊ ሚናውን የሚያኮስስ እና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎት ላይ አላስፈላጊ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ፤
---
➥ የመንግስት አስፈጻሚ መስሪያ ቤት የሚመስል መዋቅር መከተሉ፤
---
➥ ላለፉት 1400 አመታት የዘለቀውን የሀገራችንን ሙስሊሞች እና እስልምና ትውፊቶች እና ባህል የሚያኮስስ እና ከነጭራሹም አውቅና የሚነፍግ አደረጃጀት መሆኑ፤
---
[8]. በሌላ በኩል ከመጀመሪያውኑ የአንድነት ውጥኑ የይስሙላ ነው፤ እውነተኛ አንድነት እንዲመጣ ከተፈለገ በአንድ ተቋም መሰባሰብ ብቻ አንድነት አያመጣም፤ ከዚህ ይልቅ አሉ የሚባሉት ልዩነቶች ከኃይማኖቱ የመነጩ ሳይሆን በጊዜ ሂደት ከእውቀት እና ግንዛቤ ማነስ፤ እና ሌሎችም ውጫዊ ምክንያቶች የተፈጠሩ በመሆናቸው፤ የአትዮጵያ ሙስሊም ይሁን የዓለም ሙስሊም ላለፉት 1400 አመታት በአንድ ዓይነት ኃይማኖታዊ አስተሳሰብ የመጣ በመሆኑ፤ አሉ በሚባሉ ልዩነቶችን ዙሪያ በቅድሚያ የሀይማኖቱ ምሁራን ተሰባስበው ውይይት እና ምክክር እንናድርግበትና ይህንኑ ይቀመጥ የሚል መጠይቅም ነበር።
---
[9]. ከዚህ ጋር በተያያዘ፤ መጀመሪያ ላይ ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ 4 ለ 4 የዐሊሞች ውይይት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም አንደኛው ወገን ውይይቱ ከፍ ባለ ታዳሚያን እና በዛ ያሉ ምሁራንን አካቶ እንዲደረግ ቢጠይቅም ሌላኛው የወሃቢያ ወገን በውይይቱ ለመቀጠል ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሂደቱ በአጭር ተቋጨ።
---
[10]. በወቅቱ የተፈጠረውን የፖለቲካ አለመረጋጋት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም አንደኛው ቡድን ህዝብ ወደ ማነሳሳት እንቅስቃሴ በመጀመሩ መንግስት ጣልቃ በመግባት ሚያዝያ 23 ቀን 2011 የሸራተን ጉባዔ አንዲዘጋጅ ተደረገ።
---
[11]. በዚሁ መሰረት በወቅቱ የነበሩት ነባሩ መጅሊስ አመራር አባላት ስልጣናቸውን በፍቃደኝነት እንዲለቁ መንግስት በማግባባቱ እና ጫና በማድረጉ የቀድሞው አመራር አባላት ስልጣናቸውን በ9ኙ ኮሚቴ ለተመረጡ 26 ዑለሞች እና 7 የስራ አመራር ቦርድ አባላት አስረከቡ።
---
[12]. 26 አባላት ዑለማ ም/ቤት እና መጅሊሱ የሚመራው 11 አባላት ባሉት ዑለማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲሆን የስራ አመራር ቦርዱ ደግሞ በ7 አባላት የተወከለ ነበር።
---
[13]. ሸራተን ጉባዔ በአጠቃላይ ፖለቲካዊ የነበረ ሲሆን የጉባዔውም አጀንዳ ሠነድ ማጽደቅ ሳይሆን የአንድነት ጉዞ ጅማሪውን ማብሰሪያ እና ጊዜያዊ መጅሊስ ስራ አስፈጻሚ ማስተዋወቂያ ነበር። ነገር ግን፤ ሸራተኑ ስብሰባ ላይ 9ኙ ያልተስማማበት ረቂቅ ኡለማ ሠነዱ በግርድፉ ተነቧል።
---
[14]. በሸራተኑ ጉባዔ ላይ የመጅሊሱ አመራር የተቀየረ ቢሆንም ስለ ነባሩ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባዔው እጣ ፈንታ ምንም የተባለ ነገር አልነበረም። የዚህ ነባሩ መጅሊስ ጠቅላላ ጉባዔው እጣ ፈንታ በህግ አግባብ እንዴት ነው የሚለው ወደፊት የሚታይ ጉዳይ ነው።
---
[15]. አዲሱ አመራር ዋነኛ ተግባሩ ሁለቱን ሠነዶች (ማለትም የዑለማ መግባቢያ ሠነዱን እና የመተዳደሪያ ደንቡን) በባለድርሻ አካላት ውይይት ማዳበርና (በሌላ አካል) ማስጸደቅ ሆኖ በተጓዳኝም የመጅሊሱን የዕለት ተዕለት ተግባር እና ሌሎች ስራዎችን በጊዜያዊነት አንዲያከናውን ነበር። በመሆኑም በሸራተን የተቋቋመው ኮሚቴ ወይም ጉባዔ 26 አባላት ያሉት የዑለማ ም/ቤት እና ተጠሪነቱ ለዚሁ ም/ቤት የሆነ 7 አባላት ያሉት ስራ አመራር ቦርድ ነበር እንጂ 33 አባላት ያሉት ጉባዔ አልነበረም።
---
[16]. የ26ቱ ኡለማ አባላት 13ቱ ራሱን ወሃቢያ/ሰለፊ ብሎ ከሚጠራው ቡድን የተወከለ ሲሆን 13ቱ ደግሞ ዋና ሰብሳቢውን የመጅሊሱን ፕሬዝዳንት ሙፍቲን ጨምሮ ከነባሩ ሱኒ እስልምና የተወከሉ ነበሩ፡፡ ነባሩ/ሱኒ እስልምና ማለት የዛሬ 1400 በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጣውንና ከጥንት አመታት ጀምሮ በሀገራችንም ይሁን በአለም ላይ ሲተገበር የነበረውና በኃይማኖታዊ ቴክኒክ ቋንቋ አህሉ-ሱንናህ ወልጀመዓ መስመር የሚባለው እስልምና ሲሆን ራሱን ሰለፊያ ብሎ የሚጠራው ወሀቢያ ቡድን ደግሞ አለም ላይ
417 views22:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 00:38:48
377 viewsedited  21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 01:15:14
ሸህ ዐዲል ከሸሀቸው ጋር
469 viewsedited  22:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 07:18:33
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
ኡስታዝ ፈድሉ ወደ አኺራ ሄደዋል
622 views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ