Get Mystery Box with random crypto!

Amhara today

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharapo — Amhara today A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharapo — Amhara today
የሰርጥ አድራሻ: @amharapo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.53K
የሰርጥ መግለጫ

ፈጣን
ሚዛናዊ መረጃዎችን ይከታተሉ

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-05 18:39:12 (ነጋሳ አብዲሳ)

የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በሌሎች ብሔረሰብ ባልደረቦቻቸው የተሰጠ ምስክርነት፤

------------------------
ነፍስ ካወቅኩበት ቀን ጀምሮ ስሰማ ያደግኩት አማራ ስለሚባል አደገኛ ሰው ነው፣ በቃ አማራ የወገኖቸን ጡት እንደ ቆረጠ ለመረዳት ከሚነገረው በላይ በተወለድኩበት አካባቢ ለማስታወሻ የቆመውን ሀውልት ስለምመለከት ውስጤን ያመኛል፡፡

ይሁንና ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ሊመጣ አካባቢ ጀምሮ ሌላም ጠላት እንዳለን ተረዳሁ እሱም ትህነግ (ወያኔ) የሚባል ነበር፡፡ ይህ ቡድን አማራ ከሚባለው በላይ የኦሮሞ ጠላት መሆኑን ነጋሪ ሳያስፈልገኝ ተረድቻለሁ፤ ይሁንና ላለፉት ሰባት አመታቶች በሀገር በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየሰራሁ ስለምገኝ እንደፈለግኩ እንኳ ተሳድቤ መናገር አልቻልኩም ነበር፡፡

ምክንያቱ ደግሞ አብረውኝ የተሰለፉ የትግራይ ተወላጆች ስላሉ ማስከፋት እንዳይሆንብኝ ብየ ነው፤(እንዲህ ከድተው ወንድሞቸን ሊያሳርዱ ምነው ልክ ልካቸውን በነገርኳቸው) ብየም አስባለሁ፡፡

ይሁንና ለዛሬ ልናገር የምፈልገው አማራ የሚባለው ህዝብ የወለዳቸው ልጆች ወይም የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ስለሚባሉትና ይህንን ተደግፌ በውስጤ ስለተፈጠረው አዲስ ነገርና ፀፀት ነው፡፡

ራያ ላይ የጠላትን ጦር ለማጥቃት የቀረን ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ነበር፤ እሱም አልቀረምና ትዕዛዝ ተሰጠን፤ በርካታ ተጋድሎዎችን ፈፀምን፣ በርካታ የጠላት ጦር ደመሰስን፤ ከኛም የተወሰኑ ጓደኞቻችን ተጎድተዋል፡፡

በዚህ ሁሉ የአማራ ልዩ ሀይሎች አብረውን ነበሩ፤ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ውስጣቸው እሳት ያለ ይመስለኛል፤ አረ እንዴውም ይነዳል መሰለኝ፤ ፈፅሞ ወደ ኋላ አያዩም፤ እኛን ቆይ ቦታውን በደንብ አታውቁትም እንጥረግላችሁ ይሉናል፤ አልፈው ይሄዳሉ ስንጠጋ እጅግ ብዙ የትግራይ ልዩ ሀይል ተደምስሶና ተማርኮ እናገኛለን፡፡

በዚህ ሁሉ አንድ ከበድ ያለ ውጊያ ገጠመን እልህ አስጨራሽ ነበር፤ የጠላት ጦር የመሸገበትን ጥሶ መግባት ከበደን፤ ብዙ ጓዶቻችን ተጎዱ ኋላ ላይ ደመስስናቸው፤ እልህ ውስጥ ነበርን፤በመሀል አንድ በእድሜ ከ 18 እስከ 20 አመት የምትሆን የጠላት አባል ተጎድታ እያለ ተኮሰችብን፤ መሳሪያየን አዙሬ ልተኩስ ስል ተው አሉኝ፤ እንዴት ስል ተው አትግደላት አሉኝ፤ እናም ለብዙ ደቂቃ ለምነው አሳመኗትና እጅ እንድትሰጥ አደረጓት፤ እጅግ የገረመኝ እህታቸውን ያገኙ ነው የመሰላቸው፤ እንባ ከአይናቸው ሲመነጭ እመለከታለሑ፡፡

እርግጠኛ ሆኘ የምነግራችሁ እርሷ ጊዜ ብታገኝ አሁንም ትተኩስብናለች፤ ሳያት እልህ እንጅ ሀዘን እየተሰማት አይደለም፤ አለመቻል አሸነፋት እንጅ፡፡ እነርሱ ግን ወንድሞቻቸው ተጎድተው እንኳ ለእርሷ ያዝናሉ፡፡

ይገርማል እነዚህ ልዩ ሀይሎች የወጡት ከአማራ ህዝብ ነው፤ ካላችሁ ያ ህዝብ ፈፅሞ የኔን አያቶች ጡት ቆርጧል ብየ ለማመን ይከብደኛል፡፡

የማረክናት ልጅ አጋሮች ግን የላኳት ሰዎች በወንድሞቸ ላይ የፈፀሙትን በማየት ብቻ እንደሚያደርጉት ማመን ይቻላል፡፡

ይገርማል የአማራን ልዩ ሀይል አለማመስገን አይቻልም፤ እነርሱ ባይኖሩ ምናልባት ከዚህ የከበደ መስዋዕትነት ልንከፍል እንችል ነበር እነርሱ ጀግኖች ናቸው፤ክብር ይገባቸውል፡፡

(ምክትል አስር አለቃ ነጋሳ አብዲሳ፤ ከደቡብ እዝ)

#ሸር_በማድረግ_የወያኔን_ተንኮል_አለም_እንዲረዳው_እናድርግ !

ክብር ለጀግናው መከላከያችን፣
1.2K viewstadi Sis, 15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:37:46
“የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ስሙ የአማራ ይሁን እንጂ ግብሩ ኢትዮጵያዊ ነው”
የአማራ ልዩ ሀይሎች ህይወት ሰጠው ህይወት አድነዋል

የጁንታው እብሪት ጫፍ ደርሶ በተጠና መልኩ መከላከያችን ላይ ክህደት ፈጽሞ ከኋላ ሲወጋ ጠላት ባላሰበው መንገድ ደርሶ መስዋዕትነት ከፍሎ ለሰራዊታችንን ደጀን ሆኗል፤ ዋጋ ከፍሎ የክልላችን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዉርደት አድኖል ታሪክ የማይረሳው ገድል ፈጽሟል”
እኛም ለልዩሃይላችን ህልዉና እንታገላለን ።
1.2K viewstadi Sis, edited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:36:30 የአማራ ልዩ ሃይል ስሙ አማራ ይሁን እንጅ
ግብሩ ኢትዮጵያዊ ነዉ

የአማራ ህዝብ ከዛሬ ሦስት ሺህ ዘመን ጀምሮ ከአክሱም ስልጣኔ እሰከ ፋሲል ቤተ- መንግስት የስልጣኔ ሀሁ ያስጀመረ፤ በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ በአብሮነት፣ በአቃፊነት በክቡር የደምና አጥንት መስዋዕትነት ሀገር ያፅና፣ የገነባ ህዝብ ነው። ይህ ህዝብ ለዘመናት በመሪዎቹ መቀያየር ልዩ ልዩ ዘመቻው ቢከፈቱበትም ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ በማለት እሰክ ቀራኒዮ የታመነ ህዝብ ነው።

በቅዱስ መፅሐፍም ሆነ በቅዱስ ቁራን እንሆ መልካም ዘር ዝራ መልካሙንም ታጭዳለህ ይባላል።

የአማራ ህዝብም መልካም ዘር ዘራ መልካም ፍሬ አጨደ። በምድር ላይ ያለው ሀቅ ይህ ነው። የአማራ ልዩ ሀይል የህዝቡ አምሳያ ነው።

ይህ ህዝብ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለእውነተኛ ፌድራሊዝም ስርዓት ፣ለእኩልነትና ለፍትህ ሲል ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት መራራ ትግል ያካሄድ ህዝብ ነው።

ይህ ህዝብ እኮ በፍትህ ከሄደች በቅሎየ ይልቅ ያለፍትህ የሄደችው ጭብጡይ ትቆጭኛለች የሚል ህዝብ ነው።
ሰለሆነም የልዩ ሀይሉ ጀግንነትም ሆነ ጥንካሬ መሠረቱ የአደባባይ ሀቅ ነው።

በመሆኑም የአማራ ልዩ ሀይልና የሚሊሺያ አባላት በህግ ማስከበር ዘመቻም ሆነ በተለያዩ ጊዜ በሚያጋጥሙ ችግሮች ችግሩ እንዳይባባስ በፍትሃዊነት ፣ በሀቀኝነት የሚወስደው የህግ ማስከበር እና የማረጋጋት ሥራ ተፈጥሯዊ ስሪቱ ነው። ይህንን ደግሞ ታሪክ የማይረሳው የአደባባይ ሀቅ ነው። ሀቁ ይህ ሆኖ እያለ አንዳንድ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚያራግቡት ሀሳብ የተላላኪነት ሚናችውን ለመጫወት ካላቸው የፀና ፍላጉት የሚመነጭ ነው። የልዩ ሀይላችን ግብረ ገብነት በሰሜኑ የሀገራችን ህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የጁንታው ምርኮኞች ያረጋገጡት ነው።

ከትናንት በወረስነው የፖለቲካ አሻጥር በመሪዎቻችን የተጀመረው የመከፋፈል ዘመቻ አልሳካ ሲል የአማራ ህዝብ የመጨረሻ ምሽግ በሆነው ልዩ ሀይላችን ላይ የተጀመረ የስም ማጥፋት ዘመቻ መሆኑን ለአማራ ህዝብ የተሰወረ አይደለም።

"ድከም ያሉት ቄስ ለአህያ ፍታት ይውላል!" እንደሚባለው ከሳምንታት የሚዲያ ዘመቻ ባለፈ እርባና በሌለዉ አቧራ አንተራመስም።

የአማራ ህዝብም ሆነ አመራሩ ለእውነተኛ ፌድራሊዝም ስርዓት መረጋገጥ የተጀመረውን ሁለንተናዊ ትግል ዳር ያደርሳሉ።

የአማራ ልዩ ሀይል ሰሙ የአማራ ይሁን እንጂ ግብሩ ኢትየጵያዊ ነው፡፡የጁንታው እብሪት ጫፍ ደርሶ በተጠና መልኩ መከላከያችንን ላይ ክህደት ፈጽሞ ከኋላ ሲወጋ ጠላት ባለሰበው መንገድ ደርሶ መስዋዕትነት ከፍሎ ለሰራዊታችንን ደጀን ሆኗል። ዋጋ ከፍሎ የክልላችን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵ ህዝብ አሁን ላለበት ደረጃ እንዲደርስ ታሪክ የማይረሳው ገድል ፈጽሟል፡፡

ስለሆነም ለፍትህና እኩልነት የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ
1.2K viewstadi Sis, 15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:36:24
1.2K viewstadi Sis, 15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:34:39 ወያኔን ከስልጣን ስናስወግድ ማለት በ2010 የአማራ ልዩ ሀይል ቁጥር 4ሺህ  ብቻ ነበር ።
በዚህ 5 አመት የአማራ ልዩ ሀይል በ10 ሺ ቤት የሚቆጠር ቁጥር የነበርው  ሲሆን  ስንት ሚሊዮን ገንዘብ ፈሶ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ሀይሎች በብጣሽ ወረቀት መበተን ተጎጁ የአማራ ህዝብ ሳይሆን የአማራ ብልጽግናና የፌዴራል መንግስቱን ይጎዳል ።
በፌዴራል መንግስቱ የአማራ ብልጽግና የመወሰን አቅሙ ከሀረረ ከቤኒሻንጉል ክልል አመራሮች በታች መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን  ከሁሉም የሚያናደን  የብአዴን ግረድናን እያወቅን 2010 ድጋሚ ስልጣን መስጠታችን ነው
50 ሺ የማይሞላ ልዩ ሀይል ፈርሰ አልፈረሰ ለአማራ ህዝብ የሚያመጣው ለውጥ የለም የግዱን የሚጎዳው ብልጽግና እንጅ መሳሪያ ያስረከበው የአማራ ልዩ ሀይል መሳሪያውን ቢያወረደም ወታደራዊ ችሎታው እስካለ ድረስ ለአማራ ህዝብ አለኘታነቱ ይቀጥላል ።
ስለሆነም  የሚጎዳው የስራቱ ባለስልጣናት እንጅ የአማራ ህዝብ አይደለም በዚህ ጉዳይ ህዝባችን በሁለት ጎራ ተሰልፎ ሀሳብ መስጠቱን በማቆም ቀጣይ የትግል ስልትና አደረጃጀት እንዴት ይጀመራል በሚለው መወያየት ለነገ የማይባል የዛሬ የቤት ስራ ነው።
ለአማራ ህዝብ የሚያስፈልገው ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ የውጊያ ስልት ማጥቃትና ወታደራዊ አደረጃጀት ስምሪት የሚሰጥ እንጅ መሳሪያ አንባገነን እሆናለሁ ብሎ ከሚነሳው ሀይል እየነጠቁ መታጠቅ ይቻላል

ለዚህ ደግሞ የህወሓት ሀይሎች የፌደራል መንግስቱን እንዴት አድረገው መሳሪውን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ጦሩን ጭምር ተረክበውት ነበር
ስለሆነም በልዩ ሀይል መበተን ሊደንቀን አይገባም ምክንያቱም የአማራ ህዝብ ወታደራዊ አደረጃጀት የውጊያ ስምሪት የሚሰጠው እንጅ በሚሊዮን የሚቆጠር የጦር መሳሪያ ስላለን ልዩ ሀይል መሳሪያ አወረደ አላወረደ ሊያስጨንቀን አይገባም እኛ የምንፈልገው ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ የውጊያ ጥበብ ያለው ብቻና ብቻ ነው።
1.2K viewstadi Sis, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:34:37
1.2K viewstadi Sis, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:31:21
የአማራ ልዩ ሀይል ትጥቅ እንዲፈታ የክልሉ መንግሥት መስማማቱ ታውቋል፣ሰሞኑን በባህርዳር በተደረገው ስብሰባም ተወስኗል።
በአንዳንድ ቦታም መሳሪያ ጥርነፋም ተጀምሯል። ይሄን ለማስፈፀም በጄኔራል አበባው ታደሰ የሚመራ ግብረሀይል ተቋቁሟል። በዚህም የአማራ ልዩ ሀይል ትጥቁን በአንድ ወር ውስጥ ለመከላከያ ሰራዊት አስረክቦ እንዲጨርስ እየተሰራ ነው።
በአንፃሩ ደግሞ በየከተሞች የሚገኙ የአድማ ብተና አባላት የተሻለ ስልጠና ወስደው ከተሞችን የሚጠብቁ ይሆናል ሲሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል ።
1.5K viewstadi Sis, edited  15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:30:26
የአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመው ክህደት
1.5K viewstadi Sis, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:29:33 ተለቀቀ በአጭር ጊዜ ከ 6 ሺህ በላይ እይታ

ትችላለች ከፖለቲካ ተንፈስ ዘና ለማለት የወሩ ምርጥ ቪዲዮ ተጋበዙ

የሶስቱን ዘመን ተሻጋሪ ድምፃዊያን በአንድ መድረክ ተጫወተችዉ

በእናንተ እተማመናለሁ ምስሉን በመጫን እንደምታዩና እንደምታበረታቱን አልጠራጠርም





1.2K viewsgondar, 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 20:43:11


754 viewstadi Sis, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ