2022-12-04 15:24:39
ኢንዶኔዥያ ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ወሲብን በወንጀል የሚያስቀጣ ህግ ልታጸድቅ ነው!!
ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖርም ጭምር የሚያግድ ነው የተባለው አዲሱ ህግ በታህሳስ 15 ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም የኢንዶኔዥያ የፍትህ ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር ኤድዋርድ ኦማር ሻሪፍ ሂሪዬይ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
"ከኢንዶኔዥያ እሴቶች ጋር የሚስማማ የወንጀል ህግ በማግኘታችን ኩራት ይሰማናል"ም ብለዋል ሚኒስተሩ።
በረቂቁ ውስጥ የተሳተፉት የህግ አውጭ የሆኑት ባምባንግ ዉሪያንቶ አዲሱ ህግ በቅርቡ እንደሚጸድቅ ተናግረው፤ ህጉ በኢንዶኔዥያ ዜጎች እና የውጭ ዜጎች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን እንደመሆኑ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በሆነችው ሀገር ገጽታ ላይ የራሱ የሆነ ተጽእኖ ሊፈጥር እንደሚችል ያላቸውን ስጋት አስቀምጠዋል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም የህግ ማሻሻያው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትን ወይም የመንግስት ተቋማትን መሳደብ እና ከኢንዶኔዥያ መንግስት ርዕዮተ ዓለም ጋር የሚቃረኑ ሃሳቦችን መግለጽ ይከለክላል።
ፕሬዝዳንቱን መሳደብ፣ ሶስት አመታት ሊያሳስር እንደሚችልም በህጉ ተደንግጓል ሲል ዐል አይን ነው የዘገበው።
4.0K views12:24