Get Mystery Box with random crypto!

Amhara today

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharapo — Amhara today A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharapo — Amhara today
የሰርጥ አድራሻ: @amharapo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.53K
የሰርጥ መግለጫ

ፈጣን
ሚዛናዊ መረጃዎችን ይከታተሉ

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2023-02-08 18:58:25 የተጋለጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ማስቀየሻ ሊያመጡ ነው!

የተወገዘው ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክት መሆኑ ተጋልጧል። በዚህ የተጋለጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ "ማብራሪያ" ብለው መጥተው ሲኖዶሱ ላይ ዝተዋል። ባለስልጣናትን "ጣልቃ እንዳትገቡ" ብለው በይፋ የተወገዘውን እያገዙ ቤተ ክርስቲያን ሰብሮ እንዲገባ እያገዙት ነው። ለተወገዘው ቡድን ዲያቆንና ቄስ መስለው እንዲሰሩ እየተደረጉ ያሉት "መልካም ወጣት" በሚል ፕሮጀክት የሰለጠኑ ናቸው።

በፕሮጀክቱ የተካተቱት ግለሰቦች ማንነት በየቀኑ እየተጋለጠ ነው። ህዝብ ቁጣውን አሳይቷል። ይህ ሁሉ ያስደነገጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ነው የተደረገብኝ" ብለው ሊመጡ ነው ተብሏል። መፈንቅለ ሲኖዶስ አድርገው ሲከሽፍ መፈንቅለ መንግስት ተደረገብኝ ማለቱን አዋጭ አድርገው ወስደውታል።

ጫካ ሆኖ ሲመክር የከረመ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደገፉት የተወገዘው ቡድን ነው። ቤተ ክርስቲያን ሰብሮ የገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያግዙት ቡድን ነው። የዚህ ቡድን አላማና ፕሮጀክታቸው ይፋ ሲወጣ "ከአፈርኩ አይመልሰኝ" ብለው በሌላ ቲያትር ሊመጡ ነው። አጠፋው ብለው ይቅርታ እንዳይጠይቁ ውርደት መሰላቸው። ፕሮጀክቱን እንዳያስቆሙ ቀብድ ተቀብለውበታል። "ምንም አያመጣም" እንዳይሉ የህዝብ ቁጣ አስደንጋጭ ነው።

ምን አልባት በቅርቡ ጊዜያዊ አዋጅ አውጀው የኦርቶዶክስ አማኞች ወደ ቤተ ክርስትያን እንዳይሄዱ አድርገው ለተወገዘው ቡድን ሊያስረክቡም ይፈልጉ ይሆናል። የባሰ ነው የሚያመጣባቸው እንጅ!
3.0K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:49:34 በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ7 ሺ 800 በላይ ሆኗል

በደቡብ ምስራቅ ቱርክ በጋዚያንቴፕ ከሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በተከሰተዉ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በቱርክ ብቻ ከ5 ሺ 894 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በሰኞው አሰቃቂ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በከፋ ጉዳት በደረሰባቸው 10 ግዛቶች ዉስጥ ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።

በ10 ከተሞች ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሀገሪቱ ከ1939 ዓ.ም ወዲህ ባጋጠሟት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጎድተዋል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በመሬት መንቀጥቀጡ ወደተመቱ አካባቢዎች የፍለጋ እና የነፍስ አድን ቡድን የሚሰሩ ባለሙያዎች ወዲያውኑ መላኩን ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ መረጃ ለማሰባሰብ ከተጎዱት የስምንት ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጽህፈት ቤታቸው መግለጫ አስታውቋል።ፕሬዝዳንቱ አክለዉ አሜሪካ፣ እንግሊዝን እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ እርዳታ ላደረጉ 70 ሀገራት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኳታር 10 ሺ  ተንቀሳቃሽ ቤቶችን በቱርክ እና ሶሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ120 የነፍስ አድን ሰራተኞችን ጋር ልካለች፡፡ከ11 ዓመታት በላይ በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ክፉኛ በተጎዳችው ሶሪያ፣ ከ1 ሺ 932  በላይ ሰዎች መሞታቸውንና 3 ሺ 500የሚያህሉ ሰዎች መቁሰላቸውን የሶርያ የመንግስትና ወዶ ገቡ የነጭ ቆብ የረድኤት ተቋም አስታዉቋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሶርያ ሐማ፣ አሌፖ እና ላታኪያ ግዛቶች በርካታ ሕንፃዎችን አውድሟል።የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋዚያንቴፕ ከተማ አቅራቢያ 17 ነጥብ 9 ኪ.ሜ ያለው ጥልቀትና  በሬክተር  ስኬል 7 ነጥብ 8 የተለካ አደጋ መድረሱን ይፈ አድርጓል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተሰማው በዋና ከተማዋ አንካራ እና በሌሎች የቱርክ ከተሞች እንዲሁም በሰፊው የሀገሪቱ ክልል መሆኑን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።በአደጋው በርካታ ሕንፃዎች የፈረሱ ሲሆን በዲያርባኪር ከተማ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ ወድሟል።

አንድ እማኝ  እንደተናገሩት እኔ ያረፈኩበት ቤት ለ45 ሰከንድ ያህል መንቀጥቀጡን ተናግረዋል። የቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች አደጋው በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 4 የተለካ እንደሆነ ገምተዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ሁለተኛ መንቀጥቀጥ አካባቢውን እንደመታ ተናግረዋል።ቱርክ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከሚደርስባቸው ዞኖች ውስጥ አንዷ ነች። እ.ኤ.አ. በ 1999 በቱርክ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ17 ሺ  በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
2.9K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 22:53:12 ፍራት አያዋጣም አትደናገሩ
የሚሰማን አምላክ አለ ከመንበሩ
ተብሎ ይሰበካል ጎንደር በየደብሩ !!

ጎንደር ተቆጣች
የአርባአራቱ ታቦታት ሀገር የሃይማኖት መፍለቂያዋ ጎንደር
ባለማተቧ ጎንደር ሚዛኗ ጎንደር ተቆጥታለች

በአፄ ፋሲል ዙርያ እንደጎርፍ በተመመዉ የህዝብ መዕበል
በቅድስት ቤተክርስቲያን ቀልድ የለም ብላለች !!


ምስሉን ሊንኩን ተጭነው ቪዲዮዉን ይመልከቱት




1.6K views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 22:51:32
አሳዛኝ ዜና

የሻሸመኔ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቄስ ሀረገወይን በላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ በሀዋሳ ህክምና ሲደረግላቸው ቢቆይም ዛሬ አርፈዋል፡፡

የሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል  ተወዳጅ አገልጋይ ቀሲስ ሐረገወይን በላይ በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል።

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት  ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ በንፁሀን ዜጎቹ ላይ ሞት ባወጀው የጸጥታ ኃይል ደጋፊነት በጸጥታ ኃይሎች በአጣና ጭንቅላታቸውን እጅና እግራቸውን ተቀጥቅጠው  በሀዋሳ ሕክምና ሲደረግላቸው የነበረው የሻሸመኔ ምእመናን እጅግ የሚወዷቸው የቅዱስ ሚካኤል ደብር አገልጋይ ቀሲስ ሐረገወይን በላይ በሰማዕትነት ከምሽቱ 3 ሰዓት ማረፋቸውን   ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ክልል ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ እንዲሁም የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለ EOTC TV በኃዘን  ገልጸዋል።

በሌላ አሳዛኝ ዜና

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት ፊት አውራሪነት በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጦ በሀዋሳ ሕክምና ሲደረግለት የነበረው አያሌው ተረፈ በሰማዕትነት ማረፉን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ገለፁ!!
1.5K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 22:50:22
"ከፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች ጋር አገኘኋቸው።"

".... 'አንተ ጥሩ ሰው ነህ እባክህ ሽማግሌ ሁንና አስታርቀን' ብለው ደውለውልኝ ልምጣና በአካል እንነጋገር ብያቸው አዲስ ከበባ ወሰን አካባቢ ቀጥረውኝ ወዳሉበት ስፍራ ሂጄ ነበር። ከእሳቸው ጋር ወደ 6 የሚሆኑ የፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች አብረዋቸው ነበር። ደህንነቶችም ' አንተ ነፍጠኛ አይደለህ ለምን መጣህ? በማለት አፋጠጡኝ እኔ ግን በዘር፣ በቋንቋና በብሄር ሳይሆን በእጄ በያዝሁት መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ እንደማምን ነገርኳቸው። ከብዙ ወከባ በኋላ ተመልሼ ሄድኩ።

በማግስቱ ለጳጳሱ ደወልኩና ሌላ ስፍራ እንገናኝና እንወያይ ስላቸው 'ተው አይሆንም ደግሞ ከጴንጤ ጋር ታዬ ተብዬ ሌላ ችግር ልፍጠር' አሉኝ። እውነት ለመናገር ሁሉም አፈንጋጮች ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ የሚመሩትን ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቤታቸው መመለስ ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ልክ ወጥመድ ውስጥ እንደገባች አይጥ መውጫ አጥተዋል።....

"ይሁን እንጂ የብልጽግና መንግስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ያወቃት አይመስለኝም። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መከራ በመጣባት ጊዜ ሁሉ ይበልጥ የምትፀና፣ በሯ በተንኳኳ ቁጥር አጥብቃ የምትቆልፍ ረቂቅ ቤተክርስትያን መሆኗን መረዳት ነበረበት። አሁን በኦርቶዶክስ ላይ እየሆነ ያለውን ሁሉ ሁላችንም አጥብቀን የምናወግዘው ከመሆኑም ባሻገር ከቤተክርስትያኒቷ ጎን በመቆም አብሮነታችንን መግለጽ እንፈልጋለን።"

ፓስተር ቢንያም
1.5K views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:36:22 ከባድ መልዕክት

ከአክሱም የተላከ

አረፉ የሶስት ሽህ ዘመን ታሪክ አታጉድፉ

ምስሉን ተጭነው ይመልከቱት




671 viewsedited  15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 10:32:11
3,830 ሰዎች ሞተዋል

በቱርክ እና ሶሪያ በደረሰው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ 3,830 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።የቱርክ የድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኤጀንሲ እንደገለፀው በቱርክ ቢያንስ 5,606 ህንፃዎች ፈርሰዋል።በሰሜን ሶሪያም በተመሳሳይ ከ1000 በላይ ሰዎች ሞተዋል።በቱርክ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን ሀገሪቱን የጦርነት ቀጠና አስመስሏል።
1.8K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 19:06:18 ሰበር ዜና !


ሙስሊሞች
መንግስት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጀመረውን ጭፍን ጥላቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳሰቡ


በቪዲዮ የደረሰንን መረጃ ከቀስቱ ስር ተጭነው ይመልከቱት






1.9K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 16:56:03 መረጃ

ጥቁር ልብስ ለብሰው አገልግሎት ለማግኘት ወደ መንግስት ተቋማት የሄዱ ዜጎች እንዲመለሱ እየተደረገ እንደሆነ ዛሬ ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

"ከበላይ በመጣ ትእዛዝ" በማለት እንደ ገቢዎች፣ መንገድ ትራንስፖርት፣ ፍርድ ቤት... ወዘተ ያሉ ተቋማት በዚህ መልኩ ሰዎችን እየመለሱ እንደሆነ ታውቋል።

በተጨማሪም፣ በዛሬው ሱባዔ ላይ ካራቆሬ ባለው የአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ በመልበስ የሄዱ በሙሉ ለእስር እንደተዳረጉ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

#elias meseret
2.3K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 16:21:09
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ ታሰሩ!

ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፉት የመንግሥት አካላት ሥራ አስኪያጁን ቁልፍ አስረክበው እንዲወጡ ቢነግሯቸውም አልቀበልም በማለታቸው ዛሬ ጠዋት ታሥረዋል።በሌላ በኩል በሀገረ ስብከቱ ያሉ 13 ወጣቶችም በዛሬው ዕለት መታሠራቸው ተገልጿል።

ምንጭ:- EOTC
2.3K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ