Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ያጋራው አስደንጋጭ መረጃ መንግስት ከቻለ ለንፁሃን ይድረስ አጉትን ከተ | Amhara today

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ያጋራው አስደንጋጭ መረጃ
መንግስት ከቻለ ለንፁሃን ይድረስ

አጉትን ከተማ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉ ነዋሪዎች የኦሮሚያ ልዩ ሃይልን በመፍራት ብቻ፣ ህጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ሁሉ በምሽት እየተሰደዱ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውኛል። መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ዜጎችን ካልታደገ፣ ለሚፈሰው ደምና ለሚደርሰው ስቃይ ሁሉ መንግሥት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው።

ዶ/ር አብይ አህመድ:-

የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር ነው
የብልጽግና ፕሬዝዳንት ነው
የኦሮምያ ብልጽግና ሊ/መንበር ነው
የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ነው
በየትኛውም የስልጣን አቅጣጫ ቢኬድ፣ ዶ/ር አብይ በኦሮምያ የሚካሄደውን የንጹሃ ሞት ጣልቃ ገብቶ የማስቆም ሙሉ መብትና ስልጣን አለው። አሁን እንደ ዜጋ የምጠይቀው ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ብቻ ነው። የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ በላይ ተቀዳሚ ግዴታና ሃላፊነት ደግሞ የለም። ከአቅሙ በላይ ከሆነ ደግሞ ይህንን በአደባባይ መናገር ነው።

እንደ ሃገር ከፍተኛ የመከላከያ አቅም በገነባንበት በዚህ ጊዜ የሚፈጽም የንጹሃን ሞት፣ በየትኛውም አመክንዮ ተቀባይነት የለውም። ይህ የግፍ ሞት እንዲቆም ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በአንድነት ድምጻችን ልናሰማ ይገባል።