2022-07-15 07:44:25
የጁምዓ ሰላት ሸሪዓዊ
ብይኑና ማስረጃዎቹ
➥➥➥➥➥➥➥➥➥➧
➘➘➘ ከዚህ የቀጠለ
የጁምዓ ሰላት አሰጋገድ
➩➩➩➩➩➩➩➩➩➧
የጁምዓ ሰላት ድምፅ ከፍ በመደረግ የሚሰገዱ ሁለት ረከዓዎች እንደሆኑ በነብዩ (ﷺ) ተግባርና በዑለማዎች ስምምነት የተረጋገጠ ነው፡፡ በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል ጁምዓ በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ ሱረቱል ሙናፊቁን
[ሙስሊም 877]
ወይም በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል አዕላ በሁለተኛው ሱረቱል ጋሺያ እንደሚነበብም ነብዩ ﷺ በተግባር አስተምረዋል፡፡
[ሙስሊም 878]
በጁምዓ ዕለት የሚሰሩ ሱና ስራዎች
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▱▬◄◄
⓵ኛ ከፍተኛ ምንዳ ለማግኘት በግዜ ወደ ጁምዓ መስጂድ መሄድ
አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በመጀመሪያው ሰዓት የተጓዘ ግመል እንዳቀረበ ነው፣
በሁለተኛው ሰዓት የተጓዘ ከብት እንዳቀረበ ነው፣
በሶተኛው ሰዓት የተጓዘ ቀንዳማ በግ እንዳቀረበ ነው፣
በአራተኛው ሰዓት የተጓዘ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፤
በአምስተኛው ሰዓት የሄደ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፤
ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጣ መላእክት ኹጥባ ለማድመጥ ይቀመጣሉ››
[ቡኻሪ 881 ሙስሊም 85ዐ]
⓶ኛ ገላን መታጠብ
➔➔➔➔➔➔➔➔
➲ ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹ የጁምዓን ዕለት ገላውን ታጥቦ ….›› በየሳምነት ጁምዓ ገላ መታጠብ ሱና ሲሆን በተለይ የሠውነት ጠረን ባለበት ሰው ይበረታል፡፡ አንዳንድ ዑለማዎች ‹‹ጁምዓን ዕለት መታጠብ እያንዳንዱ አቅመ አዳም የደረሰ ሰው ላይ ግዴታ ነው››
የሚለውን ሀዲስ መሰረት በማድረግ በጁምዓ ገላ ትጥበት ግዴታ (ዋጂብ) ነው ይላሉ፡፡
[ቡኻሪ 879 ሙስሊም 486]
⓷ኛ ከትጥበት ውጭ ያሉ
ሌሎች ፅዳቶችንም ማከናወን
➧
ለምሳሌ፦
➪ ሽቶ መቀባት፣
➩ ጥፍርን መቁረጥ፣
➩ የብብትና የሀፍረተ ገላ አካባቢ ፀጉርን ማፅዳት፣
➪ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።
⓸ኛ ከልብሶቹ ጥሩውን መልበስ
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
ኢብን ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ
‹‹ዑመር ኢብን ኸጣብ መስጂድ በር ላይ ከሰይራዕ የመጣ ካባ ተመልክተው ‹‹ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይህንን ካባ ገዝተው ለጁመዐና እንግዶች ሲመጡ ቢለብሱት?››
አል ቡኻሪ ይህንን ሀዲስ በጁምዓ ዕለት ጥሩን ልብስ መልበስ ሱና ስለ መሆኑ መረጃ አድርገው የተጠቀሙበት ሲሆን አልሃፊዝ ኢብን ሀጀር መረጃ ሊሆን የቻለው ነብዩ (ﷺ) የዑመርን ሀሳብ ባለመቃወም ስለተቀበሉት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
ነብዩም (ﷺ)
‹‹ለስራ ከምትለብሷቸው ሁለት ልብሶች(ሁለት ልብሶች ማለት ከወገብ በታችና ከወገብ በላይ አንድ ጊዜ የሚለብሱትን ማለት ነው) ውጪ ለጁምዓ የሚለበሱ ሁለት ልብሶችን መልካም ነው›› ብለዋል::
[አቡዳውድ 1ዐ78 ኢብን ማጃህ 1ዐ95]
⓹ኛ በነብዩ (ﷺ) ላይ ሰላትና ሰላም ከሌላው ቀን በበለጠ መልኩ ማስፈን ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
➝➝➝➝➝➝➝➝➝➝➧
‹‹ በጁምዓ ዕለት በይበልጥ እኔ ላይ ሰላት አውርዱ››
[አቡዳውድ 1ዐ47 ነሳኢይ 3/91]
⓺ኛ የጁምዓ ሱብሂ ሰላት ላይ በመጀመሪያው ረከዓ ሱረቱ ሰጅዳህ በሁለተኛው ሱረቱል ኢንሳን ማንበብ የነብዩ (ﷺ) ተደጋጋሚ ተግባር ስለነበር ሱና ነው፡፡
በቀኑ ክፍለ ጊዜ ደግሞ ሱረቱል ከህፍን ማንበብ፡፡
[ቡኻሪ 891]
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹በጁምዓ ዕለት ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ዕለተ ቂያማ ከእግሩ እስከ ሰማይ ጫፍ የሚያበራ ብርሐን ይኖረዋል፡፡ እንዲሁም ከዕለቱ ጁምዓ እስከ ቀጣዩ ጁምዓ የሚፈፀም ኃጢአት ይማርለታል››
[ሃኪም 2/368]
⓻ኛ መስጂድ ገብቶ ከመቀመጡ
በፊት ሁለት ረከዓ መስገድ
➾➾➾⁰⁰⁰⁰⁰➾➾➾➾➾⁰➾
ነብዩ (ﷺ) ያዘዙት ተግባር ሲሆን ኢማሙ ኹጥባ ላይ ከሆነ ግን ሰላቱን ቀልጠፍ አድርጎ መስገድ አለበት::
[ቡኻሪ 93ዐ]
⓼ኛ ጁምዓ ዱዓ ይበልጥ ተቀባይነት ያለው ወቅት በመሆኑ ዱዓ ማብዛት
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹በጁምዓ ዕለት አንድ ሰው እየሰገደ ሊገጥመው የሚችል ልዩ ሰዓት አለ፡፡ በዚያ ሰዓት አንድ ሰው አላህን አንድ ነገር ቢጠይቅ ወዲያው ይሰጠዋል፡፡››
[ቡኻሪ 935 ሙስሊም 852]
104 views04:44