Get Mystery Box with random crypto!

Alif media

የቴሌግራም ቻናል አርማ alif_media_1 — Alif media A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alif_media_1 — Alif media
የሰርጥ አድራሻ: @alif_media_1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.95K
የሰርጥ መግለጫ

አንብብ { አንብቢ }
ስታነብ ታሪክህን ታውቃለህ!
ስታነብ የስኬት ማማ ላይ ትወጣለህ!
ስታነብ ጉድለትህን ታውቃለህ!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-21 08:23:46 Alif media pinned « የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ •════••• •••════• [ክፍል 1] ተራኪ የአንቺን ስም በ Alif tube ተዘጋጅቶ የቀረበ ሙሐመድ የዐብደላህ ልጅ፣ የአብዱል ሙጦሊብ ልጅ፣ የሃሽም ልጅ፣ የመናፍ ልጅ፣ የፈህር (ቁረይሽ) ልጅ፣ የማሊክ ልጅ፣ የነድር ልጅ፣ የኪናነህ ልጅ፣ የዐድናን ልጅ፣ የአላህ ነብይ እስማዒል ልጅ፣ የአላህ ወዳጅ የኢብራሂም…»
05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 08:22:46 የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ
•════••• •••════•

[ክፍል 2]

የነብዩ የዘር ሐረጋቸው፣ አወላለዳቸው እና የልጅነት ዘመን
••┈┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈┈••

አላህ ያደረገላቸው ጥበቃ
•┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈•

ከወጣትነት አጓጉል ድርጊቶችና ጨዋታዎች ሁሉ አላህ ጠብቋቸዋል። ስለ ራሳቸው እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡-

“በመሐይምነት ዘመን ወጣቶች ይፈጽሟቸው የነበሩ ድርጊቶችን ለመፈጸም ያሰብኩት ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር። በነዚህም ጊዜያት አላህ ያሰብኩትን እንዳላደርግ አቀበኝ። ከዚያ በኋላ በመልእክተኛነት እስኪልከኝ ድረስ ተመሳሳይ ድርጊት አስቤ አላውቅም። ይኸውም አንድ ቀን ሌሊት በመካ ከፍታማ ቦታዎች ላይ ፍየል አብሮኝ ይጠብቅ ለነበረ ልጅ፡- ‘ፍየሌን ጠብቅልኝ። ልክ እንደወጣቶች መካ ውስጥ ስጫወት ልደር’ አልኩት። ‘ይሁን’ አለኝ። ወደ መካ ወረድኩ። እዚያ እንደደረስኩ ከአንድ ቤት ውስጥ ዘፈን ሰማሁ። ምንድን ነው? በማለት ስጠይቅ፣ የሰርግ ዘፈን እንደሆነ ተነገረኝ። ቁጭ ብዬ ማድመጥ ስጀምር አላህ ጆሮዬን ደፈነው። ጥልቅ እንቅልፍም ወሰደኝ። ከእንቅልፍ ያነቃኝ የረፋዱ ጸሐይ ግለት ነበር። ወደ ባልንጀራየም ተመለስኩ። ስለ አዳሩ ጠየቀኝ። የሆነውን ነገርኩት። በሌላ ሌሊትም ተመሳሳይ ሙከራ አደረግኩ። ልክ የመጀመሪያው ሌሊት ዓይነት ሁኔታ አጋጠመኝ። ከዚያ በኋላ ያን ዓይነት ሐሳብ አስቤ አላውቅም።”

በአላህ ብቻ መመካት
•┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈•

የፍጡራን ፈርጥ ለየት ያለ የሕይወት ጅማሬ፣ አላህ ቀልባቸው ከርሱ ውጭ በሌላ አካል እንዳይንጠለጠል እንደፈለገ ያመለክታል። በአባት፣ በእናት፣ በአያት ወይም በአጎት፣ በገንዘብ፣ በስልጣን ወይም በሌላ ነገር እንዳይመኩ የፈለገ ይመስላል። ይህ ስሜት ለሙስሊም ባጠቃላይ እና ለዳዒ በተለይ ለስብእናው ስሪት እጅግ አስፈላጊ ነው። ከሚንከባከባቸው ክንድ ወይም ድሎት ከሚለግሳቸው ሰው ገንዘብ አርቆ አላህ ብቻ ሊጠብቃቸው እና ሊንከባከበው በመሻት ይህን አደረገ። ይህ ሲሆን፣ “አባቴ” በማለት ፋንታ “አምላኬ” ይላል። ነፍሳቸውም ወደ ገንዘብ ወይም ክብር፣ ወደ አያት ቅድመ አያቶች ንግስናና ስልጣን ወደማስመለስ ስሜት አትዘነበልም። ሰዎችም የዱንያ (ምድሯዊ) ክብር ከነብይነት የተቀደሰ ደረጃ ጋር አይቀላቀልባቸውም።

ይህም በመሆኑ መልእክተኛው ነብይ ነኝ ያሉት ዓለማዊ ክብርና ጥቅም ለማግኘት ወይም በዘመናችን አገላለጽ “በሐይማኖት ለመነገድ” ነው የሚባሉ ክሶች ሁሉ የሚቆሙበት መሠረት አጡ። ዓለማዊያንና አምላክ የለሾች በቅን የዳዕዋ ሰዎች ላይ ይህን ክስ በየዘመናቱ ሲሰነዘሩት ይደመጣል።

ጠቃሚ ትምህርቶች
•┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈•
ገና በለጋ እድሚያቸው እንጀራ ፍለጋ ያሳዩት ትጋት ሦስት ጠቃሚ ትምህርቶችን አካቷል።

1. አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያላበሳቸውን ውብ ባህሪና ረቂቅ ስሜት ያሳያል። አጎታቸው የተሟላ እንክብካቤ ያደርጉላቸው ነበር። ልክ እንደ አባት ያዝኑላቸውም ነበር። ይህም ሆኖ ግን መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ሰርተው ማደር እንደሚችሉ ሲሰማቸው ወደ ስራ ተሰማሩ። የአጎታቸውን የገንዘብ ቀዳዳዎች ያቅማቸውን ያህል ለመሸፈን ጥረት አደረጉ። ከስራቸው የሚያገኙት ገቢ ምንም ያህል አነስተኛ ቢሆንም እንኳ ኩሩ ስብእናቸው፣ ያቅሙን ያህል ከመጣር የማይሰስተው ባህሪያቸው ወደ ስራ መራቸው። የአጎታቸው ውለታ ለመመለስና የተግባር ምስጋና ለማድረስ ይህን አደረጉ።

ስለዚህ አንተም ልክ እንደርሳቸው ጥንቁቅና ኩሩ ሁን። “ራስህን ባንገትህ ተሸከም።”

2. አላህ ለባሪያው በምድር ላይ የሚወድለትን የሕይወት ዓይነት የሚያብራራ አጋጣሚ ነው። ይኸውም አላህ ቢፈልግ ኖሮ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ገና ከሕይወታቸው መጀመሪያ ጀምሮ ኑሯቸውን ድሎታማ በማድረግ እንጀራ ፍለጋ ከመኳተን መታደግ ይችል ነበር። ግና ለሰው ልጅ መልካሙ ገንዘብ ለሕብረተሰቡ በሚሰጠው አገልግሎት ወይም በጥረቱ የሚያገኘው መሆኑን፣ ሳይሰራ እና ሳይለፋ፣ ለሚኖርበት ማሕበረሰብ ቅንጣት በጎ ነገር ሳያደርግ፣ ስራ ፈትቶና እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ የሚያገኘው ገንዘብ ደግሞ መጥፎ መሆኑን በጥበቡ ሊያስተምረን ስለከጀለ ነው።

በመሆኑም ልክ እንደ ተወዳጁ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) ሐላል ስራዎችን ብቻ ሰርተህ ገንዘብ ለማግኘት ጉጉና ትጉ ሁን።

3. ዳዒ የኑሮ መሠረቱ ዳዕዋ ሲሆን፣ ወይም በሰዎች ስጦታና ምጽዋት ላይ ሲመሠረት ዳእዋው ክብደትና ግምት ያጣል።


يَا قَوْمِ لَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى الَّذِي فَطَرَنِي أَفَلَا تَعْقِلُونَ
“ሕዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይ ምንዳን አልጠይቃችሁም። ምንዳዬ በዚህ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም። አታውቁምን?” ( ሁድ 11፤51)

መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) የሰዎች ውለታ በአንገታቸው ዙሪያ ተጠምጥሞ ሐቅን ይሉኝታ ሳይዛቸው በድፍረት እንዳይናገሩ የሚያደርጋቸው አንድም አጋጣሚ በነብይነት ከመላካቸው በፊትም ሆነ በኋላ በሕይወታቸው ውስጥ እንዲኖር አላህ አልፈቀደም። ስለዚህም ለራስህ እና ለዳዕዋው ክብር ቀናኢ ሁን። ለምትሰጠው የዳዕዋ አገልግሎት ከሰዎች ምንዳም ሆነ ምስጋና አትሻ። የእስልምና ዳእዋ ልክ እንደ አንበሳ ኩሩና ቁጥብ፣ እንደ ዳመና ውሃ ንጹህ መሆኑን እወቅ።

ፍጹም ሰዋዊ ስብእና
•┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈•
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ማንኛውም ሰው ሰዋዊ ባህሪን የተላበሱ፣ ሰዋዊ ስሜቶችና ፍላጎቶች ያሏቸው መሆኑ ጥርጥር የለውም። በማንኛውም ወጣት ላይ የሚስተዋሉ ተፈጥሯዊ ዝንባሌዎች ነበሩባቸውም። ይህም እውነት ከሌሎች ሰዎች የተለዩ እንዳልሆኑ ያመለከታል። ልክ እንደ ሌሎች ወጣቶች በጨዋታ የሚያሳልፉት ጊዜ ቢኖራቸው ይፈልጋሉ። ይህ ተፈጥሯዊ ስሜት መጥፎ አይደለም። ይሁንና አላህ ይህን ተከትሎ ከሚመጣና ከበጎ ስነ-ምግባሮች ተምሳሌ፣ የዘልዓለማዊው አምላካዊ ሸሪዓ መምህር ከመሆናቸው ጋር ከማይጣጣሙ አጓጉል አጋጣሚዎች ጠበቃቸው።

የምን አንብቦ ዝም ለአላህ ብላችሁ share
---------ይ
------------ቀ
---------------ጥ
---------------------ላ
--------------------------ል

@Alif_media_1


ክፍል 3 ይቀቀጥላል
595 views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 11:58:09
Part 17

ለሴቶች ሒጃቡስጥ ካለሽ

https://t.me/Alif_media_1
634 viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 07:45:12
Part 16

ለፈገግታ ያህል በተለይ ለሴቶች

https://t.me/Alif_media_1
592 viewsedited  04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 06:07:23
ቅመሜ

ሃፊዘል ቁርአን ማሻ አላህ
740 views03:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 09:57:34 የምትፈልጉ አለላችሁ

ቴሌግራም

@Nagaa_wollo
729 viewsedited  06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 07:10:56
708 views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 14:07:46 ዛሬ ማታ 3 : 00 ላይ የ ጥያቄና መልስ ውድድር በዩቲዩብ ቻናላችን ይጠብቁን ።

ሽልማቱ

1 ኛ ለወጣ የአላህን ቃል የያዘ 30 ጁዝ ቁርአን ሲሆን

2 ኛ ለወጣ የድምፅ ጥቅል ሲሆን

መወዳደር ለምትፈልጉ በሙሉ ማታ 3 : 00 ላይ በዩቲዩብ ቻናላችን ይጠብቁን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን ።



https://youtube.com/channel/UCm45bo74RJ-a5C2b19svo6Q
108 views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:32:28
ዛሬ ማታ በዩቲዩብ ቻናላችን ለሚለቀቀው ጥያቄና መልስ ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ ?? ውድድሩ ትልቅ ሽልማት አለው ።
Anonymous Poll
81%
100 %
0%
50 %
0%
25 %
19%
0 %
21 voters129 views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:16:17

114 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ