Get Mystery Box with random crypto!

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

የሰርጥ አድራሻ: @alainamharic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 69.32K
የሰርጥ መግለጫ

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 283

2022-09-02 16:45:40
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሳምንቱ ጨዋታዎች መርሃ ግብር እንደሚከተለው አቅርበናል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
8.9K viewsedited  13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 15:10:23 ዋትስአፕ በሐምሌ ወር ብቻ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን የህንድ አካውንቶችን አገደ

የፈጣን መልእክት መተግበሪያ ዋትስአፕ፤ በሐምሌ ወር ብቻ 574 የቅሬታ ሪፖርቶችን መቀበሉን አስታውቋል።
https://am.al-ain.com/article/whats-app-bans-2-4-million-accounts-in-india
9.0K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 14:15:36 ጆ ባይደን “ጽንፈኛ” ያሏቸውን ዶናልድ ትራምፕንና ደጋፊዎቻቸውን አስጠነቀቁ

ፕሬዝዳንት ባይደን፤ “ዶናልድ ትራምፕ እና ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ዲሞክራሲ አደጋ ላይ ጥለዋል” ሲሉ ከሰዋል።
ዶናልድ ትራምፕ “ጆ-ባይደን አሜሪካን እያዋረዳት ስለሆነ በ2024 ድጋሚ ለምርጫ ልወዳደር እችላለሁ” ብለው ነበር።
https://am.al-ain.com/article/biden-warns-extremist-trump
9.1K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:45:17 ቮስቶክ 2022” የጦር ልምምድ እየተካሄደ ነው

የሩሲያ መከላመያ ሚኒስቴር የጋራ ወታደራዊ ልምምዱን መከወፈቻ የሚያሳይ ሺዲዮ ይፋ አድርጓል።
በሩሲያ ሩቅ ምስራቅ ፕሪሞስኪ ግዛት በሚካሄደው ልምምድ ላይ የሩሲያ እና የቻይናን ጨምሮ የ14 ሀገራት ወታደሮች እየተሳተፉ ነው።
ከሀገራቱ የተውጣጡ 50 ሺህ ወታደሮች በልምምዱ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ከ5000 በላይ የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሏል።


8.9K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 12:25:59
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ወደ አሜሪካ ሊያቀኑ ነው።

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከሁለት ሳምንት በኋላ አሜሪካንን እንደሚጎበኙ ቢቢሲ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ ወደ አሜሪካ ነጩ ቤተመንግስት አምርተው ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር እንደሚወያዩ ተገልጿል።

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ንግድ፣ ሀይል ዘርፍ እና ሌሎች አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ተገልጿል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ከአንድ ወር በፊት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ራማፎሳ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
8.9K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 11:13:04 ፑቲን ለጎርቫቼቭ ብሄራዊ የቀብር ስነ ስርአት ነፈጉ፤ በቀብራቸውም ላይ አይገኙም

የመጨረሻው የሶቬት መሪ ጎርቫቼቭ ሶቬት ህብረትን ከመፈራረስ ማዳን ያልቻሉ መሪ ናቸው።
https://am.al-ain.com/article/putin-denies-gorbachev-a-state-funeral-and-will-stay-away
9.0K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:53:30 ከ20 ሺህ በላይ በሆኑ ንቦች የተነደፈው አሜሪካዊ ከሳምንት በኋላ ነፍስ ዘራ

የ20 ዓመቱ አሜሪካዊ ኦስቲን ቤላሚ ከአንድ ሳምንት በፊት ከአጎቱ እና እናቱ ጋር ሆኖ የዛፍ ቅርንጫፍ ለመቁረጥ በሚል ነበር ዛፍ ላይ የወጣው።የኦሂዮ ነዋሪ የሆነው ይህ ግለሰብ ዛፉ ላይ ሰፍረው የነበሩት የንቦች መንጋ አንገቱ ላይ ይሰፍራሉ።https://am.al-ain.com/article/a-man-stinged-by-over-20-thousand-bees-revives
9.3K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 04:30:12
ሳዑዲ አረቢያ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ምክክር አካሄደች

የሳዑዲ አረቢያ ንጉሳውያን ምክር ቤት አማካሪ አህመድ ቢን አብዱላዚዝ ካንታን በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው ተነግሯል።

አህመድ አብዱላዚዝ ካንታን በአዲስ በባ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኘት መምከራቸው አል ዐይን ከኤምባሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የሳዑዲ አረቢያ ንጉሳውያን ምክር ቤት አማካሪው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታም በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም በዓለማቀፋዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ታውቋል።

አህመድ ቢን አብዱላዚዝ ካንታን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ቡርቱካን አያኖ ጋር ተገናኝተውም ተወያይተዋል።
https://am.al-ain.com/article/saudi-ethiopian-talks-to-enhance-cooperation-and-discuss-regional-situations
24 views01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 02:31:06
ፖላንድ ጀርመን በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ላደረሰችባት ጉዳት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች

ፖላንድ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአዶልፍ ሂትለር የሚመራው የጀርመን ናዚ ጦር ቀድማ የተያዘች ሀገር ነበረች።

እንዲሁም በእነ አሜሪካ የሚመራው ህብረት የጀርመን ናዚ ጦርን ሲያሸንፍም ፖላንድ በድጋሜ የጦር ሜዳ ሆናም ነበር።

የሁለቱ ቡድን ባካሄዱት የጦርነቱ መጀመርያ እና መቋጫ ላይ ብርቱ ክንድ ያረፈባት ፖላንድ የዓለም ጦርነት ቀስቃሿ ጀርመን በመሆኗ ካሳ ልትከፍለኝ ይገባል ስትል ገልጻለች።

ፖላንድ ጀርመን በቆሰቆሰችው ጦርነት 1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ስለደረሰብኝ ካሳ እንዲከፈላት የሀገሪቱ ግዢ ፓርቲን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
https://am.al-ain.com/article/poland-asks-germany-for-wwii-reparations-of-1-3-trillion
610 views23:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 23:30:10
የሩሲያና የቻይንን 50 ሺህ ወታደሮች የሚሳተፉበት “ቮስቶክ 2022” የጦር ልምምድ እየተካሄደ ነው

በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ግዙፉ ቮስቶክ 2022 የጦር ልምምድ በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል።

ቮስቶክ 2022 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ ከዛሬ ጀምሮ ለ7 ቀናት በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ እና በጃፓን ባህር ላይ የሚካሄድ መሆኑ ተነግሯል።

በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ አዘጋጇ ሩሲያን ጨምሮ ቻይና፣ ቤላሩስ፣ ታጃኪስታን፣ ህንድ እና ሞንጎሊያን ጨምሮ በድምሩ 14 ሀገራት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከሀገራቱ የተውጣጡ 50 ሺህ ወታደሮች በልምምዱ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ከ5000 በላይ የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሏል።
https://am.al-ain.com/article/vostok-2022-military-drills-kick-off-in-moscow
2.5K views20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ