Get Mystery Box with random crypto!

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

የሰርጥ አድራሻ: @alainamharic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 69.32K
የሰርጥ መግለጫ

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 282

2022-09-03 06:45:00
ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጡ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተሻለ “የዘር ፖሊሲ” ያስፈልጋቸዋል- ኢጋድ

ለከፍተኛ የምግብ እጥረት በተጋለጡት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ያለውን ችግር ለማቃለል የተሻለ “የዘር ፖሊሲ” እንደሚያስፈልግ የኢጋድ ሪጅናል ሲድ ዳያሎግ ፎረም ጠቆመ፡፡

ፎረሙ ይህን ያመላከተው የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች እንዲሁም የተላያዩ ባለድርሻ አካላት ባሳተፈውና ላላፉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ ከአል-ዐይን አማርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢጋድ የእርሻና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ሞህይልዲን ኢልቶሃሚ አፍሪካ ቀንድ ከተለመዱ ዘሮች በዘለለ የተሻሻሉ የዘር አማራጮች ለመጠቀም የሚያችላቸው የዘር ፖሊሲ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/igad-said-horn-of-afric-needs-a-better-seed-policy
5.7K views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 04:30:59
ጆ ባይደን ዶናልድ ትራምፕንና ደጋፊዎቻቸውን አስጠነቀቁ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ደጋፊዎቻቸውን በጽንፈኝት ወነጀሉ።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፊላዴልፊያ ባደረጉት ንግግር "ጽንፈኛ የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ ዴሞክራሲን አደጋ ላይ ጥለዋል" ያሉ ሲሆን፣ በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ ያሉ "ጨለምተኛ" ሀይሎችን ለመከላከል ሁሉም አሜሪካውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
https://am.al-ain.com/article/biden-warns-extremist-trump
5.7K views01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 02:30:34
ቻይና፤ እየተባባሰ ለመጣው ውጥረት “የታይዋን ገዥ ፓርቲ ተጠያቂ ነው” አለች

በቅርቡ የሰው አልባ አውሮፕላን በታይዋን መመታቱን ተከትሎ የታይዋን-ቻይና ውጥረት መባባሱ ቻይና ገለጸች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ ማንነቱ ያልታወቀው ሰው አልባ አውሮፕላን መመታቱን ተከትሎ ታይዋን ውጥረቱን እየተባባሰ መምጣቱ ለዚህም ታይዋን ኃላፊነቱን ትወስዳለች ሲል ተደምጠዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን፤ “ማንነቱ ያልታወቀ ሲቪል ሰው አልባ ሰው አልባ አውሮፕላኑን በጥይት መመታቱን ተከትሎ የታይዋን ገዥ ፓርቲ ውጥረቱን ለማጉላት እየሞከረ ነው”ም ብለዋል።
https://am.al-ain.com/article/china-taiwan-s-ruling-party-is-responsible-for-the-worsening-tension
5.9K views23:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 23:31:06
ከ20 ሺህ በላይ በሆኑ ንቦች የተነደፈው አሜሪካዊ ከሳምንት በኋላ ነፍስ ዘራ

የ20 ዓመቱ አሜሪካዊ ኦስቲን ቤላሚ ከአንድ ሳምንት በፊት ከአጎቱ እና እናቱ ጋር ሆኖ የዛፍ ቅርንጫፍ ለመቁረጥ በሚል ነበር ዛፍ ላይ የወጣው።

የኦሂዮ ነዋሪ የሆነው ይህ ግለሰብ ዛፉ ላይ ሰፍረው የነበሩት የንቦች መንጋ አንገቱ ላይ ይሰፍራሉ።
የአደጋው ወጣት ለአንድ ሳምንት ያህል ራሱን ስቶ ሆስፒታል ከቆየ በኋላ ወደ ራሱ ተመልሷል ተብሏል።

አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ከአስር ጊዜ በላይ ንቦች ከተነደፈ የምስመለስ፣ ተቅማጥ እና የመረበሽ ስሜት ሊሰማው እንደሚችል ጥናቶች ያስረዳሉ።
https://am.al-ain.com/article/a-man-stinged-by-over-20-thousand-bees-revives
6.4K views20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 21:44:33 የቡድን ሰባት ሀገራት በሩሲያ ነዳጅ ላይ የመሸጫ ጣሪያ አወጡ

አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን ጣልያን እና ካናዳ ስብስብ የሆነው የቡድን ሰባት ሀገራት የፋይናንስ ሚንስትሮች በሩሲያ ነዳጅ ላይ የዋጋ ተመን አውጥተዋል።
https://am.al-ain.com/article/g7-countries-set-price-for-russian-oil
7.4K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 21:22:06 የአሜሪካ ባለስልጣናት ነቪዲያ የቴክኖሎጂ ኩብንያ ለቻይና የኤ. አይ ቺፖችን ሽያጭ እንዲያቆም አዘዙ

የቺፕ ዲዛይነር የሆነው ኒቪዲያ ኮርፕ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንት ቺፖችን ለቻይና መሸጥ እንዲያቆም መታዘዙን አስታውቋል።
ኩባያው ካሳለፍነው ረቡዕ ጀምሮ የአሜሪካ ባለስልጣናት ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስራ የሚውሉ ሁለት ዋና የኮምፒዩተር ቺፖችን ወደ ቻይና መላክ እንዲያቆም ነግሮታል።
በዚህም የቻይና ኩባንያዎች እንደ ምስል መለያ ያሉ የላቀ ስራዎች ለመስራት ይቸገራሉ ተብሏል። ኒቪዲያ በቻይና ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚጎዳበትም ተነግሯል።
https://www.youtube.com/shorts/htR9NSMpebk
7.6K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:50:33 ሩሲያ፤ የአውሮፓ ህብረት ለሩሲያውያን የቪዛ ማመቻቸትን የማቆም ውሳኔ “የማይረባ” ነው ስትል አወገዘች

ሩሲያ፤ ይህ ሁኔታ ለአውሮፓውያንም የበለጠ አስቸጋሪ እንደሚያደርግም አስጠንቅቃለች።
https://am.al-ain.com/article/kremlin-denounces-absurd-eu-decision-to-suspend-visa-facilitation
7.9K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 19:13:25 ኢጋድ፤ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጡ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተሻለ “የዘር ፖሊሲ” ያስፈልጋቸዋል አለ

ዶ/ር ሞህይልዲን ኢልቶሃሚ፤ በቀጠና ደረጃ “ድንበር ተሻጋሪ የሰብል ዘር ግብይት” እንዲኖር እንሰራለን ብለዋል። የአፍሪካ ቀንድ “የተሻሻለና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ዘር ያስፈልገዋል”ም ተብሏል።
https://am.al-ain.com/article/igad-said-horn-of-afric-needs-a-better-seed-policy
8.5K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 18:25:05 የ2022 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ አሸናፊ ኢትዮጵያዊያን “ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድላችን እየጠበበ ነው” አሉ

የአሜሪካና ኢትዮጵያ ወቅታዊ ግንኙነት የድቪ እድለኞችን እየጎዳ መሆኑ እድለኞቹ ተናግረዋል። በድቪ 2022 ፕሮግራም ሶስት ሺህ ገደማ ኢትዮጵያዊያን እድለኛ ሆነው ተመርጠው ነበር።
https://am.al-ain.com/article/ethiopian-us-dv-lottery-2022-winners-complain
9.1K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 17:39:24 ቻይና፤ እየተባባሰ ለመጣው ውጥረት “የታይዋን ገዥ ፓርቲ ተጠያቂ ነው” አለች



በቅርቡ የሰው አልባ አውሮፕላን በታይዋን መመታቱን ተከትሎ የታይዋን-ቻይና ውጥረት መባባሱ በመገለጽ ላይ ነው።https://am.al-ain.com/article/china-taiwan-s-ruling-party-is-responsible-for-the-worsening-tension
8.7K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ