2022-11-20 20:44:06
የዛሬው የኳታር አለም ዋንጫ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የተነበበው የቁርዓን አንቀፅ ትርጉም ይህ ነበር..
«እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ከእናንተ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡»
(ቁርኣን 49÷13)
ከዚህ በተጨማሪ ኳታር ጨዋታውን ለመመልከትና ለመጫወት ለመጡ እንግዶቿ ...
በየሆቴሉ ክፍሎቹ ላይ የእስልምናን አስተምህሮ የሚያስተምሩና የሙስሊሞችን እምነት በቀላሉ የሚያብራሩ ሓዲሶች፣ መፃፅፎችና ቁርአናዊ መልእክቶችን ያቀፈ ባርኮድ ተያይዟል።
የአለም ዋንጫ ጨዋታው የሚካሄድባቸው 8 ስታዲየሞች መጠጥ ይዞ መግባት ተከልክሏል።
የመስጅድ ሙኣዚኖች ድምጸ መርዋ በሆኑ አዳዲስ ሙአዚኖች ተተክተዋል።በየስታዲየሞቹ አዛን እንዲሰማ የድምፅ ማጉያዎች ተተክለዋል።
የኳታር የእንግዳ ተቀባይ ሴንተሮች 10 ተንቀሳቃሽ መኪናዎችንና 10 ልዩ ድንኳኖችን በመትከል ወደ እስልምና የሚጣሩ ከ 2000 በላይ አስተማሪዎችን መድበዋል።
የኳታር የአውቃፍ ሚኒስተር በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ኢስላማዊ አውደ ርዕዮችን ለጎብኝዎች አዘጋጅቷል።
በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በስቴዲየም ውስጥ የሶላት መስገጃ ቦታዎች ተሰናድተዋል።
የእስልምናን ውበት የሚያስተዋውቁ የነብዩ (ሰዐወ) ሀዲሶች በየቦታው ተለጥፈዋል።
7.1K viewsedited 17:44