2022-12-23 20:30:56
"ዉለታ እንደዋዛ" በሚል መሪ ቃል በሰሜኑ ግጭት የተጎዱ ሃሪማዎችን መልሶ ለማቋቋም እና ለማደራጀት ፕሮጀክት ተወጥኗል ።
ታህሳስ 14 - 2015 : በቢላሉል ሀበሽ ኢስላማዊ ማዕከል የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት የእስልምና እምነትን
መሰረታዊ አስተምህሮ ከትውልድ ወደ ትዉልድ በማስተላለፍ ሂደት ዉስጥ ዘመን የማይሽረውን መስዋእትነት ከፍለው ባቆዩ እና በሚያቆዩ ሃሪማዎች ፤ ዛውያዎች እንዲሁም መሰል ተቋማት ሊይ
ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራዉና በ አስራ አንድ (11) የቦርድ አባላት የሚመራ ደረጅት መሆኑን በመግለጫችን አንስተናል ።
ሲወርዱ ሲዋረዱ የመጡ ... በቃችሁ ሊባሉ ከሚገቡ ዋነኛ ከ ማዕከላቱ ክፍተቶችና የዚህ ፕሮጀክት አበርክቶዎች ከሚሆኑ መሰረታዊ ተግርባራት ዉስጥም የ ደረሶች ፤ የመሻኢኾችን የምግብ አቅርቦት
ችግር መቅረፍ ፤ የመብራት የዉሃና ሌሎች የመሰረት ልማት እጥረቶችን ማሟላት ፤ የኪታብ (የመጽሃፍት) አቅርቦቶችን በማሻሻል ማእከላቱን የሚመጥኑ ቤተ-መጽሃፍትን ማደራጀት ፤ የሰርአተ ትምህርት ክለሳ ማድረግ እና የ አቅም ማጎልበት ስራዎችን መስራት እንዲሁም በማዕከላቱ የሚገኙ የመረጃ አያያዝ ስርአቶችን ማዘመን በ ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት የተያዙ ዋነኛ ተግባራት መሆናቸዉም በእለቱ ከተነሱ ነጥቦች መካከል ናቸዉ ።
በዚህም መሰረት 50 የተመረጡ ሃሪማዎች የሶላር ተጠቃሚ ይሆናሉ ፤ ላይብረሪዎች በተደራጀ መልኩ ይገነቡላቸዋል ፤ ምግብና አልባሳት ለማዕከላቱ እና በዙሪያቸው ላሉ የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ
እንዲሆኑ ይደረጋል ተብሏል ። ተቋማቱን በ ቋሚነት የሚደግፉ ወቅፎች ( ስጦታዎች ) እና የገቢ ማስገኛ ስራዎች ይጀመራሉ ፤ 50 ለሚሆኑ ሼኾች የ ላፕቶፕና የ ሶፍት ኮፒ መጽሃፍት ድጋፍ ይደረጋል ።
እነዚህ ድጋፎች በመደረጋቸው ሳቢያም በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ከ ሃሪማና ዛውያዎች ወጥተው የነበሩ ተማሪዎች ቁጥር መሻሻል ከማሳየቱ ባሻገር ፤ የ ማዕከላቱ የትምህርት አሰጣጥ ጥራት መልካም መሆን ሃሪማና ዛውያዎች ተመራጭ የ ኢስላማዊ እውቀት ተቋማት እንዲሆኑ ያደርጋል ።
በመጨረሻም ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት ይህን ሀሳብ ለሚደግፉ ሁሉ በሩ ክፍት መሆኑን በ ታላቅ ደስታ ይገልፃል ።
በሚከተሉት የድርጅቱ አካውንቶች ድጋፍ ስላደረጉ እናመሰግናለን።
ዘምዘም ባንክ
0015172010301
አጭር ኮድ
151720
ሂጅራ ባንክ
1000013130001
አጭር ኮድ
1313
ንግድ ባንክ
1000517781178
አጭር ኮድ
4224
#ውለታ_እንደዋዛ!
እናመሰግናለን !!
6.7K views17:30